TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AmharaPolice

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን " በተለያዩ ወንጀሎች ጠርጥሬ ስፈልገው የነበረው ዘመነ ካሴን በቁጥጥር ስር አውያለሁ " ሲል ዛሬ አሳውቋል።

የአማራ ፖሊስ ዘመንን በባህር ዳር ቀበሌ 3 በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደብቆ በህብረተሰቡ ጥቆማ እንደያዘው ገልጿል።

" በወቅቱ ከ500 ሺህ ብር በላይ በኢግዚቢት የተያያዘ ሲሆን ቀሪ የምርመራና የፍተሻ ሂደቶች እየተከወኑ ነው " ሲል የአማራ ፖሊስ አመልክቷል።

የአማራ ፖሊስ ምርመራው የሚካሄደው #በክልሉ ፖሊስ መሆኑንም አሳውቋል።

ዘመነ ካሴ በቀድሞ የአርበኞች ግንቦት 7 ውስጥ በአባልነትና በአመራር ውስጥ የነበረ እና ረጅም ጊዜ በኤርትራ በርሀ ውስጥ በመሆን ኢህአዴግ መራሹን አገግዛ ሲታገል ያሳለፈ ፤ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎም ውጭ ያሉ የታጠቁ አካላት ትጥቃቸው አውርደው ወደ ሀገር ሲገቡ ወደ ሀገር የገባ ሲሆን ወደ ሀገር ከገባ በኃላ በፋኖ አደረጃጀት እንቅስቃሴ ውስጥ በፊት መስመር ላይ ከሚታወቁት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው።

በአማራ ክልል በጎጃም አካባቢ የሚንቀሳቀውና እራሱን " የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ " በማለት የሚጠራው ቡድን ሰብሳቢ እንደሆነም ዘመነ ካሴ ከዚህ ቀደም ለአንድ የውጭ ሚዲያ ተናግሮ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል " - ብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በ" ጅግጅጋ ኤርፖርት " ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ብልፅግና ፓርቲ አሳውቋል። " ጉዳዩ #በህግ_አግባብ ተይዞ እየተጣራ…
#Update

" በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች " - የሶማሌ ክልል መንግስት

የሶማሌ ክልል መንግስት ጅግጅጋ " ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት " የተከሰተውን ድርጊትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በዛሬው እለት ከቀኑ 9:00 ላይ በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ በጥበቃ ላይ የነበረ " የፌደራል ፖሊስ " አባል በከፈተው ተኩስ የ1 ሰው ህይወት ማለፉንና በ4 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግስት አሳውቋል።

" አባሉ በከፈተው ተኩስ የክልሉ ም/ቤት አባልና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወ/ት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂም #ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች 4 ዜጎች በህክምና ተቋማት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል " ሲል ክልሉ አመልክቷል።

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ #በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከድረጊቱ በኋላ በኤርፖርት የተፈጠረውን ክስተት ወዳያኑ በቁጥጥር ስር በመዋሉ ኤርፖርቱ ወደ መደበኛው ስራ ተመልሷል ሲል ክልሉ በመግለጫው አሳውቋል።

በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ #የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ እንደምትግኘ የገለፀው የሶማሌ ክልል መንግስት " ጉዳዩ ተመርምሮ ወደፊት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል " ብሏል።

@tikvahethiopia