TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሲአን‼️

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ለሲዳማ መብት መከበር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስታወቀ።

በውጭ የሚኖሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የንቅናቄው አባላት ሀዋሳ ከተማ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበሉ ላይ የሲዓን ሊቀመንበር ዶክተር #ሚሊዮን_ቱማቶ እንደተናገሩት ንቅናቄው ዘመን ተሸጋሪ ጭቆና፣የፍትህ እጦትና የአስተዳደር በደሎች የወለዱት ነው።

ከ1970 ጀምሮ የሲዳማ ህዝብ መብት እንዲከበር ንቅናቄው ረጅምና አድካሚ ትግል ማድረጉንም ገልጸዋል።

የተፈጠረውን እድል ገቢራዊ እንዳናደርግ የሚጥሩና የህዝቦችን ጥቅም በመቃወም አንድነትን የሚፈታተኑ የፖሊቲካ ሃይሎችን መታገል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ትላንት የገባውን የልኡካን ቡድን የመሩት ዶክተር በዛብህ በራሳ በበኩላቸው ንቅናቄው በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ  ሰላማዊ ትግል በማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

ከጄኔቫ የመጡት አቶ ደጀኔ ወልደአማኑኤል በፌዴራልና በክልል መንግስት እንዲሁም በአባሎቻቸውና በደጋፊዎቻቸው የደረገላቸው አቀባበል እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

በፖሊቲካው ዓለም ያለውን ልዩነት በማስወገድ ለሲዳማ የሚታገል አንድ አውራ ፓርቲ እንደሚገነቡና የግለሰብና የቡድን መብቶችን ህዝቡ እንዲረዳ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የክልሉን ርዕስ መስተዳዳር ወክለው የተቀበሏቸው የርዕሰ-መስተዳደሩ አማካሪ አቶ አኒሳ መልኮ እንኳን ወደ ምድራችሁ በደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል፡፡

በሀገሪቱ የመጣውን የፖለቲካ ለውጥ ተከትሎ በውጭ ሀገር ሆነው ለዜጎች ነፃነት፣ ክብርና እኩልነት ሲታገሉ የነበሩ ፓርቲዎች ከበርካታ ዓመታት በኋላ እየተመለሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

“የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በሀገሪቱ የታየውን ለውጥ በመጠቀም ራሱን እንዲያጠናክርና ለሲዳማ አንድነት በመስራት ኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ በጋራ እንሰራለን” ብለዋል፡፡

ከአውስትራሊያ፣ ከስዊዘርላንድና አሜሪካን የመጡት የንቅናቄው አመራሮች ትላንት ሃዋሳ ሲገቡ ደጋፊዎቻቸው፣ አባሎቻቸው፣ የዞንና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia