TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የዜጎችድምጽ

" የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለይ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ (ዶላር እና ሌሎች ምንዛሬዎች መውጣት መውረድ) ገበያውን እንደሚያናጋው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

በተለይም ሁኔታው በዝቅተኛ ማህበረሰብ ክፍል / ዝቅተኛ የወር ገቢ ያለው ዜጋ ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ እንደሚሆን ለማንም ግልጽ ነው።

ነገር ግን የአንዳንድ ነጋዴዎች ተግባር ብዙዎችን ያበሳጨ ፣ ያስቆጣ ሆኗል።

' የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ተደርጓል ' ከመባሉ ከወራት በፊት ያስገቡትን ምርት ፣ ቁሳቁስ በተለይ የምግብ ግብዓት ላይ ጭማሪ ለማድረግ ሲጥሩ ተስተውሏል።

እነዚህ ነጋዴዎች እዚሁ ከማህበረሰቡ ጋር አብረው የማይኖሩ ይመስል ያለ አንዳች ምክንያት በዚህ ልክ ራሳቸውን ክፉኛ ወደው ወገናቸውን ለመጉዳት የሚሄዱበት ርቀት አሳፋሪም ጭምር ነው።

አንዳንዶቹ ምርት ደብቀው " የለም " ማለትም ጀምረዋል።

ለመሆኑ ማሻሻያ ሳይደረግ በፊት ያስገቡት እና መጋዘን ውስጥ ያስቀመጡትን ምርት፣ ቁሳቁስ ላይ " ዶላር ጨምሯል " በማለት  ፦
° በምን አግባብ ነው ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉት ?
° ለምንስ ነው ከገዛ ወገናቸው ምርት የሚደብቁት ?
° እነሱስ የሚኖሩት ከህብረተሰቡ ጋር አይደለም ?
° አብረው ደስታንና ሀዘንን ችግርን የሚጋሩት ከዚሁ ህዝብ ጋር አይደለም ? ፤
° ነገ አንድ ነገር ቢሆኑ የሚደርስላቸው ይኸው ዛሬ ዋጋ እየጨመሩ የሚያሰቃዩት ህዝብ አይደል ?

ህዝቡ ከዛሬ ነገ ምን ይጠብቀኛል ፤ ኑሮው እንዴት ልገፋው ነው ብሎ በተጨነቀበት በዚህ ወቅት መሰረታዊ አቅርቦትን መደበቅ እና ዋጋ መጨመር ምን አይነት የጭካኔ ተግባር ነው ? ምን አይነት ስግብግብነትስ ነው ?

ይህ የነጋዴዎች ተግባር ጭንቀት ላይ ጭንቀት የሚጨምር እጅግ የሚያስተዛዝብ ነው። እንዲህ ያለ ወቅት መረዳዳት እና መተዛዘን ሲገባ ትርፍ ለመሰብሰብ መሮጥ አሳፋሪ ነው።

ከምንም በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ነዋሪ ጫናው እንደሚበረታበት እየታወቀ ፣ እንደሚያሰቃየው እየታወቀ መቶ አመት ለማይኖር ህይወት በወገን ላይ እንዲህ መጨከን ተገቢ አይደለም።

ከላይ የሚወርደውን ሁሉ በማይችል ጫንቃው የሚሸከመው በዝቅተኛ ገቢ የሚኖረው የሀገሬው ህዝብ ነው። "

(በናውስ የሐሳብ መድረክ)

የሐሳብ መድረኩን ይቀላቀሉ :
https://t.iss.one/NousEthiopia/36

Via
@nousethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ° " በርካታ መሰረታዊ ሸቀጥ የያዙ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ጣቢያዎች ተንቀሳቅሰዋል " - መንግሥት ° " የዋጋ ጭማሪ ቁጥጥር የአንድ ሰሞን ወሬና ወከና ሆኖ በዛው ጨምሮ እንዳይቀር ተከታተሉልን ፤ከዚህ ቀደም በዘይት የሆነውን አይተናል። ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም " - የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ (ከአ/አ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደረገ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ መሰረታዊ በሚባሉ…
🔈 #የዜጎችድምጽ

የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ ፦

" እኔ ደመወዜ አንድም ጊዜ ሳይጨምር ይኸው ዘይት ጨምሮ ጨምሮ በሺህ ቤት ገብቷል። እንዴት መኖር እንዳለብኝ አልገባኝም።

ደመወዘኔን ምኑን ከምኑ እንደማደረገው ጠፍቶብኛል።

የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር የሚጨምረው ዋጋ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ወሬና ወከባ ይሆንና ዋጋው በዛው ጨምሮ ጣራ ነክቶ ይቀራል ፤ ይህ ከዚህ በፊት በዘይት አይተነዋል።

ነጋዴው አያዝንልን፣ የመንግስትም ሰዎች ተገቢና ዘላቂ ቁጥጥር አያደርጉልን ፣ የሚመጣው ሁሉ ግን እኛ ላይ ያርፋል።

እንደ ከዚህ ቀደሙ ' ዋጋ ጨመረ. ' ተብሎ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ግርግር ሆኖ በዛው ዋጋ ሁሉ ተሰቅሎ እንዳይቀር መደረግ ያለበት ሁሉ ይደረግ ፤ ኑሮው በጣም ከብዶናል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምፅ “ ግድያና እገታ የሚፈጸመው መሀል ከተማ ላይ ነው፡፡ ለዛውም ፖሊስ ጣቢያ ባለበት አጠገብ፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቷል፡፡ ፖሊስና ሚሊሻ ወደ ህዝቡ ነው የተኮሰው ” - ነዋሪዎች በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በተለይ ከሦስት ወራት ወዲህ " በታጠቁ አካላት አማካኝነት ግድያ፣ እገታና ዝርፍያ " በመበራከቱ ሰቆቃ ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡…
🔈 #የዜጎችድምጽ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ አመታት ወዲህ እጅግ እየተስፋፋና እየተባባሰ የመጣው የእገታ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ሰዎች ይታገታሉ ፤ ገንዘብ ይጠየቃል ፤ አንዳንዴማ ጭራሽ የገንዘብ ዝውውር በባንክ ይፈጸማል።

አጋቾች ዘገያችሁ በማለትም ታጋቾችን ይገድላሉ።

ህጻን፣ አዛውንት፣ ወጣት፣ ሴት ፣ ሀብታም ፣ ገንዘብ የሌለው የሚቀር የለም ይታገታል።

ድርጊቱ በተለይ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ላይ በስፋት የሚስተዋል ሲሆን ትግራይ ውስጥ ጦርነቱ ከቆመ ወዲህ እገታ ሲፈጸምና ሰው ሲገደልም ተሰምቷል።

አማራ ክልል ከዚህ ቀደምም እገታ ይፈጸም የነበረ ሲሆን ህዝቡ " የመፍትሄ ያለህ !! "እያለ ሲጮህ ነው የኖረው ባለፉት ዓመታ ግን በክልሉ ካለው የጸጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ እገታ እጅግ ተባብሷል።

ሰው ይታገታል ፤ ድሃው ቤተሰብ ብር አምጣ ይባላል ብር መላክ ሳይችል ሲቀር ታጋች ተገድሎ ይጣላል ፤ አዘገያችሁ እየተባለም መግደል ተጀምሯል።

አሽከርካሪዎች ተዘዋውረው ስራ መስራት ፈተና ሆኖባቸዋል። ወጥቶ መግባት ብርቅ ሆኗል። በዚህ የተማረረው ዜጋ አካባቢውን ጥሎ ለመውጣት እየተገደደ ነው። ያውም ያለው። የሌለው አማራጭ ስላጣ እዛው በሰቀቀን ይኖራል።

አሁን አሁን ግን እገታ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን ማሸበር የተያያዘ ስራ ይመስላል። ብር ተሰጥቶ እንኳን ታጋች ተገድሎ ይጣላል። ህዝቡንና ህብረተሰቡን ተስፋ የማስቆረጥ ፤ በስነልቦና የመጉዳት ነገር !

ኦሮሚያም በተመሳሳይ ዓመታት አልፈዋል።

እጅግ በሚያስገርምና ጥያቄንም በሚፈጥር ሁኔታ አንድ ቦታ ላይ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ እገታ ይፈጸማል።

ተማሪ ፣ ሰላማዊ መንገደኛ ሳይቀር ታፍኖ ተወስዶ ቤተሰብ ብር ይጠየቃል። ሰው ይገደላል።

አንዳንድ ቦታዎች ጭራሽ መንገድ ሄዶ መመልስ ብርቅ ነው። ሰው አቅም የለው በአየር ትራንስፖርት እንዳይጠቀም ህይወቱን አስይዞ ለኑሮው ለስራው ሲል ይጓዛል።

ለመሆኑ አንድ ቦታ ላይ ተደጋግሞ እገታ ሲፈጸም ዘላቂ እርምጃ የማይወስደው ለምንድነው ? ፣ ሌላው ይቅር ችግሩን መፍታት ከተፈለገ የደህንነት ካሜራዎችን እንኳን እየተጠቀሙ ፣ የስልክ መስመሮችን እያጠኑ መፍትሄ መስጠት ለምን አልተቻለም ? ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነው።

አንድ መስመር ላይ ዓመታት ሙሉ ሰው እየታገተ ገንዘብ ሲጠየቅ ችግሩን በዘላቂነት እንዲፈታ አለማድረግ ትልቅ ጥያቄ ነው የሚያስነሳው።

ትግራይ ላይ ከጦርነት ማግስት ሰዎችን አግቶ ብዙ ሚሊዮን ብር መጠየቅ የተለመደ ሆኗል። በዚህ ዓመት በርካቶች ታግተው ገንዘብ ተጠይቆባቸዋል።

ከእገታ በኃላ የተገደለም አለ።

በእርግጥ የሰላም መጥፋት ለእንዲህ ያለው ስርዓት አልበኝነት በር እንደሚከፍት የታወቀ ቢሆንም ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ ሁሉንም አቅም አሟጦ በመጠቀም ለምን አልተሰራም ?

ብዙዎች በእገታና ግድያ ተግባራት መሯቸዋል።

ከዓመታት በፊት በዚህ በሰፋ ልክ ያልተለመደ አሁን ግን ልክ ፋሽን እየሆነ የመጣን ተግባር ከምንጩ ለምን ማድረቅ እንዳልተቻለ የብዙዎች ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የዜጎችድምጽ

" ስራ መስራት ... ቤተሰብ ማስተዳደር አልተቻለም ! " - አሽከርካሪዎች

በክልል ከተሞች የሚታየው ቤንዚን የማግኘት ፈተና አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ስራ ሰርቶ መግባትና ቤተሰብ ማስተዳደር ፈተና ከሆነባቸው ቢቆይም አሁን ላይ ሁኔታው ይበልጥ እየከበዳቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

" ቤንዚን እንደልብ ማግኘት ከቆም በርካታ ወራት አልፈዋል " የሚሉት መልዕክታቸውን የላኩ ዜጎች " ልጆቻችንን ለማስተዳደር፣ እኛም በልተን ለማደር ስንል አንድ ሊትር  ቤንዚን ከ120 ብር በላይ ስንገዛ ከርመናል አሁን ጭራሽ ቤንዚን ጨመሯል ተብሎ እሱም ጠፍቷል ፤ ሲገኝ ደግሞ ብሩ ጨምሯል " ብለዋል።

ባሉበት አካባቢ ማደያዎች ቢኖሩም ቤንዚን እንዲሁ መቅዳት ቅንጦት ከሆነ መቆየቱን ተናግረዋል።

" 1 ቀን መስራት 1 ቀን ደግሞ ሰልፍ ተሰልፎ መዋል ነው ፤ እንዲህ እየሆንን እንዴት ነው ይህንን ከዕለት ወደ ዕለት እየናረ ያለውን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መቋቋም የምንችለው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" ልጆቻችንን የምናሳድገው ፤ ከሰው እንዳያንሱ ጥሩ ትምህርት እንዲማሩ የምንለፋው መስእዋትነት የምንከፍለው በዚሁ ባለችን ስራ ነው ይሄን ለመስራት ፈተና ከሆነ ምን ተስፋ ይኖረናል ? እንደው ግራ ተጋብተናል " ብለዋል።

የሞተር አሽከርካሪዎችም የስራና የተለያዩ የግል ጉዳዮች ለሚፈጽሙበት የሞተር ሳይክል እንኳን የሚሆን ቤንዚን ለማግኘት በብዙ ይሰቃያሉ።

ቤንዚን በሰልፍ በሚኖርበት ወቅት ከጥበቃ እስከ ቀጂ ድረስ በመመሳጠር ሰው በፀሀይ ተንገላቶ ተሰልፎ እያለ ካለሰልፍ የሚያስቀዱት ብዙ ነው ፤ ከዚህ ሲያልፍም ለህገወጥ ሽያጭ የሚያውሉ ሰዎችን ደጋግመው እንዲቀዱ በማድረግ የችግሩ አካል ሲሆኑም ይታያል።

በክልል ከተሞች ቤንዚን እንደልብ አይገኝም ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ማግኘቱ ቅጦት ወደመሆን ተሸጋግሯል።

በየከተማው እንደ አሸን የፈሉት ማደያዎች ሲጠየቁ " ቤንዚን የለም ፤ ካለም አገልግሎት የምንሰጠው በፈረቃ ነው "  የሚል መልስ ነው የሚመልሱት።

ከጥዋት 2:30 በፊት አይከፈይም ፤ ከምሽት 12:00 በኃላ ደግሞ የቤንዚን ሽያጭ ጥርቅም ተደርጎ ይዘጋል።

ማደያዎች 24 ሰዓት መስራት ቢጠበቅባቸውም ፤ እንኳን 24 ሰዓት ሊሰሩ ቀኑን እንኳን " ቤንዚን የለም " የሚል ምንም ምክንያቱ የማይገለጽ ምላሽ በመስጠት ነው የሚውሉት።

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን በህገወጥ መልኩ ቤንዚን በየቦታው በውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ልክ እንደ ህጋዊ ነገር ከእጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ ሲቸበቸብ ይታያል። ያውም በየቦታው በየስርቻው።

በአንዳንድ ቦታዎች ማደያዎች በጥቅም ለተሳሰሯቸው አካላት በምሽት በህገወጥ መንገድ ቤንዚን በበርሜል እንደሚሸጡ ይነገራል።

ማደያ ሲጠየቅ " የለም " የሚባለው ቤንዚን በጥቁር ገበያ በህገወጥ መንገድ በየመንደሩ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ ነው የሚሸጠው።

ከዋናዎቹ አካላት በአቅርቦት ጉዳይ ላይ ምንም ችግር እንደሌለ በተደጋጋሚ ይነሳል ፤ ነገር ግን ክልል ከተሞች ላይ ቤንዚን ማግኘት ፈተና እንደሆነ ይኸው አመታት አልፏል። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ መዘዙ ብዙ ሊሆንም ይችላል።

° እንዴት ይሄን ሁሉ ጊዜ ዜጋው ሲቸገር ዝም ተብሎ ታየ ?
° እንዴት ይሄን ሁሉ ጊዜ መፍትሄ አይገኝም ?
° በክልል ከተሞች ያለው ህገወጥ የቤንዚን ሽያጭና ስርጭት ሰንሰለት የሚቆረጠው መቼ ነው ?
° በሀገር ደረጃ የሚገባ መጠን ላይ ችግር ከሌለ ለሚታየው ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂ ማን ነው ?  የሚሉ ጥያቄዎች መልስ ይሻሉ።

ከክልል ከተሞች ውጭ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ቤንዚን አንዳንድ ወቅቶች ላይ ካልሆነ በስተቀር በከተማው ባሉ ማደያዎች በቀንም በማታም ይገኛል።

የክልሎቹ ግን ልዩ ነው ማደያ ውስጥ የለም ፤ በየስርቻው በችርቻሮ እንደጉድ ይቸበቸባል።

በአሁን ሰዓት በማደያዎች የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 91 ብር ከ14 ሳንቲም ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የዜጎችድምጽ

ችግሩ ቢነገር ቢነገር መፍትሄ ያልተገኘለት በክልሎች ያለው የቤንዚን ጉዳይ !

በክልል ከተሞች ነዳጅ በተለይም ቤንዚን ማግኘት ፈተና እንደሆነ ቀጥሏል።

በርካታ በትራንስፖርት ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ባለው ችግር ምክንያት ሰርቶ መግባት ቤተሰብ ማስተዳደር ከባድ ሆኖባቸዋል።

ከክልል ከተሞች አንዷ የሲዳማ መዲናዋ ሀዋሳ ናት።

በዚህች ከተማ ነዳጅ እንደልብ ማግኘት ከቆመ ዓመታት አልፈዋል።

ያለው ችግር በተደጋጋሚ ቢነገርም በክልል መዲናይቱ ምንም የተቀየረ ነገር የለም። አሁንም ችግሩ እንደቀጠለ ነው። እንደልብ ነዳጅ ማግኘት አይቻልም።

አሽከርካሪዎች " ነዳጅ ማግኘት ከፍተኛ መከራ ሆኖብናል " ሲሉ ድምጻቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።

" ብላክ በኃይላድ እየተሞላ እንደሸቀጥ ዕቃ በየሱቁ አንድ ሊትር  ከ160 እስከ 180 ከዛም በላይ እየተሸጠ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በከተማው በርካታ ማደያዎች ቢኖሩም ነዳጅ ማግኘት ስቃይ ነው።

ነዳጅ በፕሮግራም ማሸጥ ከተጀመረም በርካታ ወራት አልፈዋል።

ምንም እንኳን በየማደያው ቤንዚን የለም ይባል እንጂ ባጥቁር ገቢያ ነጋዴዎች በከፍተኛ ብር እንደጉድ ይቸበቸባል።

ቤንዚን ከከተማ እስከ ገጠር ድረስ ከጥቁር ገበያው ጠፍቶ አያውቅም።

ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉት የሥራ ኃላፊዎች " ችግሩ ይቀረፋል እየሰራን ነው " እያሉ ተደጋጋሚ ቃል ከመስጠት ውጪ ያመጡት መሬት ላይ የሚታይ ለውጥ እንደሌለ ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ባለው ሁኔታ ምክንያት " ሰርቶ መኖር በጣም ችግር ሆኖብናል " ብለዋል።

ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ክልሎችም ብንመለከት የቤንዚን ችግር እንደዚሁ ነው።

በየማደያው የለም የሚባለው ቤንዚን ከጥቁር ከገበያ እንደልብ ሲገኝ ይታያል።

ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች " ቤንዚን በየሱቁ ፤ በየመንደሩ እንደጉድ ይቸበቸሻል ነዳጅ ማደያ ሲኬድ የለም ነው መልሳቸው " ብለዋል።

" ህዝብ እየተሰቃየ ነው። በተለይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች መከራቸውን እያዩ ነው። ችግሩ በርካታ ጊዜ ቢያልፈውም ለምን ማስተካከል እንዳልተቻለ ሊገባን አልቻለም " ሲሉ አክለዋል።

ከነዳጅ ማደያዎች ሌሊት በሲኖትራክ ሳይቀር ነዳጅ ተጭኖ እንደሚወጣ ፤ በዚህ የጥቁር ገበያና የነዳጅ ሽያጭ ሰንሰለት እጃቸው የረዘመ በመዋቅር ውስጥ ያሉ አካላት ሊኖሩ እንደሚችላ ጠቁመዋል።

በየመዋቅሩ ተጠቃሚ ሰዎች ባይኖሩ እንዴት ይሄን ያህል ጊዜ ችግሩ ይቀጥላል ? ሲሉም ጠይቀዋል።

ለአብነት ወላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ ቤንዚን ማግኘት አይታሰብም።

በጥቁር ገበያ እስከ 200 ብር ድረስ ይቸበቸድረስ

ከዚህ ባለፈ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከነዋሪዎች እንደሰማው አንዳንድ ከከተማ የወጡ ማደያዎች ሳይቀሩ ነዳጅ በድብቅ ይሸጣሉ።

አንድ ሊትር ቤንዚን 92 ብር መሸጥ ሲገባው ከጀርባ በትውውቅ እስከ 220 ብር ድረስ ለመሸጥ የሚደራደሩ አሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የመፍትሄ እርምጃ ሲወሰድ እና ማስተካከያ ሲደረግ አይታይም።

በአጠቃላይ በክልል ከተሞች በቤንዚን ምክንያት ስራ መስራት ፈተና እንደሆነ ነው። ከከተማ ወጥቶ ለመስራትም እየተቻለ አይደለም።

የዚህ ሁሉ ችግር መጨረሻ የሚወርደው ህዝብ ላይ ነው። " ነዳጅ የለም ተወዷል " በሚል በትራንስፖርት ተገልጋዩ ዜጋ ላይ የሚጨመረው ዋጋ ከፍተኛ ነው ፤ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ይሄ ተጨምሮ የሚያሳድረው ተፅእኖ እንዲሁ በቃላት የሚገለጽ አይደለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM