TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት።

አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው።

ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል።

" ጊዜያዊ አስታዳደሩ በተቋቋመበት ህግ እና አሰራር መሰረት ወደ ስራ ገብቻለሁ አሁን ላይ በፅ/ቤት ስራ ርክክብ እያደረኩ ነው " ብለዋል።

ዛሬ ደግሞ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ዓዲግራት ከተማ በተካሄደ የም/ቤት ጉባኤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩትን ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ረዳኢ ሹመቱን አረጋግጠዋል።

" TPLF ተወዳድሮ በተመረጠበት ትግራይ እስካሁን ያለው የTPLF ም/ቤት አባላት ናቸው ፤ እኔም እንደ TPLF አንድ አካል ተወካይ ሆኜ ነው የቀረብኩት " ሲሉ ሹመቱ በም/ቤት እንደፀደቀላቸው ተናግረዋል።

አቶ ዓለም ስለ ረዳኢ ሹመት የማውቀው የለም ብለዋል።

" በምክር ቤት ስለተደረገው ሹመት በማህበራዊ መገናኛ ነው ያየሁት በይፋ በመንግሥት መዋቅር አልሰማሁም " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ረዳዒ ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ሹመት ምንም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።

" ሹመት እንደተሰጠው ሰምቻለሁ ያው ትግራይም ኢትዮጵያም ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አካሄዳችን የአንድ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አስተዳደር የራሱ ምክር ቤት አለው ምክር ቤቱ ነው ከንቲባም ፣ የወረዳ አስታዳዳሪም ፣ ካቢኔም የሚያፀድቀው በዚህ ም/ቤት ያላለፈው ከንቲባ ወይም አስተዳዳሪ የመሆን እድል የለውም " ብለዋል።

" እንደ ድርጅት ከምክር ቤት ውጭ ከመጣ ተቀባይነት አለው ብዬ አላምንም እንደ ህወሓት አቋማችን ይሄው ነው " ያሉት ረዳኢ ከምክር ቤት ውጭ ማንም ሰው ደብዳቤ እየፃፈ የሚሾመው ተቀባይነት የለም ሲሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሰጠውን ሹመት አጣጥለዋል።

ትላንት በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ የወረዳና የከተማ ም/ ቤቶች አብላጫው መቀመጫ በህወሓት በመያዙ ከባለፈው ጉባኤ በኃላ የአመራር ማስተካከያ እያደረግን ነው ብለው ነበር።

የጊዛያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመመራው ቡድን ጊዜያዊ አስታዳደሩን ስራ አላሰራ እንዳለና የወረዳና የከተሞች ም/ቤቶችን በመጠቀም በመንግሥት የተመደቡ አስተዳዳሪዎች እንዲነሱ እያደረገ መሆኑን ይህም መፈንቅለ መንግሥት እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ቪኦኤ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
ጠብታ አምቡላንስ በድንገተኛ አደጋ ያሉ ጉዳቶችን ለመቀነስ እንዲሁም በዘርፉ የነበረውን የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ በነፃ የትምህርት ዕድል በኢመርጀንሲ ሜዲካል ሰርቪስ ደረጃ 4 እያሰለጠነ ይገኛል።

በዚህም ሁለት ባቾችን ያስመረቀ ሲሆን የ3ኛ ዙር ሰልጣኞችን በቅርብ ቀናት ውስጥ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

አሁንም ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በድንገተኛ በኢመርጀንሲ ሜዲካል ሰርቪስ ደረጃ 4 ሰልጣኞችን በመቀበል ለ20 ወራት ያለምንም ክፍያ ለማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

🕒 የመመዝገቢያ ጊዜ እስከ ታህሳስ 5/2017 ይቆያል።

የምዝገባ ቦታ ፡ ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ
አድራሻ ፡ የካ ክፍል ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 207 (22 አካባቢ ጆቫኒ ሆቴል ጀርባ ገባ ብሎ

ያለው ውስን ቦታ በመሆኑ ቅድሚያ መመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ
ለበለጠ መረጃ  0943302400/ 0923514151 /0912419354/ 0910855115 ላይ ይደውሉ!

https://www.tebitaambulance.com
ሕይወት ለማዳን 8035 ይደውሉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሕብረት ባንክ ቤተሰብ ይሁኑ!

ሕብረት ባንክ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና ወቅታዊ መረጃዎች በቀላሉ ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!

ቴሌግራም: https://t.iss.one/HibretBanket
ፌስቡክ:   https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን: https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ኢንስታግራም፡  https://www.instagram.com/hibretbank/
ዩቲዩብ:   https://www.youtube.com/@hibretbanket

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#Hibretbank #getconnected #digitalcommunity #subscribe
#ሹመት : የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማይናማር🚨 🔴 “ ልጆቻችን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት። መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርልን ” - የወላጆች ኮሚቴ 🔵 “ ከአገራቱ ጋር የስራ ሥምሪት ስምምነት ባለመኖሩ፣ ሰዎቹም ያቀኑት በህገ ወጥ መንገድ በመሆኑ ያሉበት ቦታና ቁጥራቸውን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ አዋቅረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልጆቻቸው ካሉበት አስከፊ ሁኔታ…
#Myanmar (Burma) #ማይናማር

" በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር " - ሽኩር  (የአይን ምስክር)

" ስሜ ሽኩር ይባላል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለምን ባመሰቃቃላ ግዜ እኔ ሥራ ካጡ ሰዎች አንዱ ነበርኩ።

በአገራችን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጉዳዩን የበለጠ አባብሶት የነበረ ቢሆንም ለመኖር ሲባል ለ 7ወር የህል በመምህርነት አገልግያለሁ። ነገር ግን ገቢዬ ፍላጎቴን ለማሟላት በቂ አልነበረም።

አንድ ቀን በታይላንድ ውስጥ የውሂብ ማስገቢያ ኦፕሬተር ለመሆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የስራ ማስታወቂያ አየሁ።

በጣም ማራኪ መስሎ ታየኝ። በወር 1,000 ዶላር ቃል ገቡልኝ።

ማረፊያ ቦታ እና በቀን 8 ግዜ የምግብ ሰዓት እንደለው    ተነገረኝ።

ቤተሰቤን እና ራሴን ከድህነት ለማላቀቅ እና የተሻለ ህይወት ለመኖር ወደ ታይላንድ መሄድ  እንዳለብኝ አሰብኩ።

በማስታወቂያው ላይ ያለውን ቁጥር አግኝቼ የመፃፍ ችሎታዬን እና የእንግሊዝኛ ችሎታዬን በቪዲዮ ገመገሙ። 

ከዛም ታይላድ ከሄድኩ በኃላ ተወዳደርኩ እና ፈተናውን አልፌ በመቀጠሬ ኩራት ተሰማኝ።

🛬 ስራው ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ ነበር 🛬

በታይላንድ ውስጥ ያለው ስራ ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ፤ ለቤተሰቤ እና ለጓደኞቼ የተሻለ ህይወት ይሰጥልኝ ይሆን ብዬም ነበር።

ነገር ግን ያሰብኩት ነገር ቅዠት ሆኖ ተገኘ።

ባንኮክ አየር ማረፊያ ስደርስ አንድ ሰው ወደ መድረሻው በር ወሰደኝና ሹፌሩን እንድጠብቅ ነገረኝ።

ሹፌሩ እኔንና ሌላ ሠራተኛ ጨምሮ እዞን ሄደ።

እዞን የሄደው ማይ-ሶት ወደምትባል የታይላንድ ትንሽ ከተማ (ማይናማር  ጋር ትዋሰናለች) ወደዛ ነው።

ያኔ ጨለማ ስለነበር ምን እየሆነ እንዳለ ሙሉ በሙሉ አላውቅም ነበር። 

ጥቂት ሰዎች ወደ እኛ መጡ፣ እና በጀልባ እንድንገባ አስገደዱን። ሳንፈልግ ወደ ማይናማር ወሰዱን። ማይናማር  ወዳለው ግቢ ስንደርስ ደነገጥኩ፣ ፈራሁ ፤ አቅመ ቢስ ሆንኩኝ።

🏦 አሰሪዎቻችን ህይወታችንን ተቆጣጠሩት 🏦

ግቢው ሰፊና በህንጻዎች የተሞላ ነበር።

እያንዳንዱ ሕንፃ አራት ፎቆች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ወለል 16 ክፍሎች አሉት። እያንዳንዱ ክፍል አራት ተደራቢ አልጋዎች አሉት።

በግቢው ውስጥ አሠሪዎቻችን ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት።

በሳምንት ሰባት ቀን እስከ 16 ሰአት እንድንሰራ አድርገውናል።

በሥራ ላይ እያለ እንቅልፍ ከተሰማን ወይም እግሮቻችንን ትይዩ ካላደረግን እንቀጣለን።

በግቢዎቹ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ። 

በጣም ብዙ ኢትዮጵያዊያን ፣ ህንዶች፣ ፊሊፒኖዎች፣ ፓኪስታናውያን፣ ቻይናውያን፣ ኢንዶኔዥያውያን፣ ሩሲያውያን፣ ዩክሬናውያን፣ ታይላንድ፣ ጃፓናውያን፣ አፍሪካውያን ከኡጋንዳ እና ኬንያ እና የአካባቢው  ማይናማር ሰዎች ጭምር ይገኙበታል።

👨‍💻 ስራው ማጭበርበር ነበር 👨‍💻 

በግቢው ውስጥ የነበረው ስራ አሰቃቂ ነበር።
 
ዋናው ሥራው በCrypto-currency ማጭበርበሮች በዓለም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ገንዘብ መስረቅ ነበር።

አሰሪዎቻችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የውሸት መገለጫዎችን (ፌክ ፕሮፋይል የሴት / የወንድ) እንድንፈጥር አስገድደውናል።

የተዘጋጀውን ስክሪፕት ተከትዬ፣ ከአሜሪካ ፣ ከጃፓን እንዲሁም ከታይዋን የውጭ ዜጎች እንዲወዱኝ አድርጌአለሁ።

አመኔታቸዉን ካገኘሁ በኋላ ብዙ ገንዘብ ማግኘት እንዲችሉ የCrypto-currency መድረክን አስተዋውቄያለሁ። 

ግን ሁሉም ውሸት ነበር።

እስከ ዛሬ ድረስ የተገደድኩበትን ሥራ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞቼ ጋር ለመካፈል አፍራለሁ።

ሰዎችን በማጭበርበር ተጸየፍኩኝ ነገር ግን ምንም ምርጫ አልነበረኝም ፤ ለህይወቴ እፈራ ስለነበር ነው።

🪖 ቦታው በታጠቁ ሰዎች ነው የሚጠበቀው 🪖

ከዚያ ቦታ ለማምለጥ ምንም መንገድ አልነበረም። 10 ጫማ ከፍታ ያላቸው ግድግዳዎች በላዩ ላይ ሽቦዎች ነበሯቸው።

ቦታው በታጠቁ ሰዎች ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለት ነበር። 

ከግቢው ለማምለጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ የሞት ምኞት ነው።

ሰዎችን ማጭበርበር አለመቻል ማለት አካላዊ ጉዳት ወይም ሞትንም ያስከትላል።

አንድ ጓደኛችን ለቅጣት ወደ ‘ ውሃ እስር ቤት ’ ተላከ። ተደብድቦ ወደ ቢሮው ተመለሰ ከዛ በኃላ ማውራትም ሆነ መሄድ አልቻለም።

ሞባይል ስልኮቻችንን፣ ፓስፖርቶቻችንን እና ሁሉንም የግል ማህደሮች የባንክ ካርዶችን ጨምሮ ነው የተወሰደው።

የሚሉንን ያህል ብንሰራም ቃል የገቡትን ገንዘብ በፍጹም አይከፍሉም።

💰 3000 ዶላር ከፈልን 💰

ወደ ቤት ሀገሬ ለመምጣት በጣም ፈለኩኝ።

ነገር ግን አጋቾቼ ለመልቀቅ 5,000 ዶላር መክፈል እንዳለብኝ ነገሩኝ።

የሌለኝ እና ማድረግ የማልችለው ገንዘብ ስለሆነ   ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን ከአለቃው ጋር በድጋሚ ለመደራደር ሞከርን። 

3000 ዶላር ከፈልኩኝ፣ በመጨረሻም ለቀቁኝ።

ማይናማር ወደ ባንኮክ መሻገር በጣም አስፈሪ ነበር ነገር ግን የአለህ ፊቃድ ሁኖ ከዛ እስር ቤት ወጣሁ።

ከዚያ መከራ በመትረፌ እፎይታ ተሰማኝ።

በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ለዚህ እድል እና እንዲወጣ ለረዱኝ ሰዎች የዘላለም አመስጋኝ እሆናለሁ።

ወደፊት እየሄድኩ፣ አዲስ ጅምር እፈልጋለሁ። አሁን ቤተሰቤን ለማስተዳደር ጥሩ ሥራ እየፈለግኩ ነው።

💻 በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የውሸት ማስታወቂያ አያለሁ 💻

አሁንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የውሸት የስራ ማስታወቂያዎችን እያየሁ ነው። ይህን ሳይ በግቢው ውስጥ የታሰሩትን ሰራተኞች አስባለሁ። 

የሀገራት መንግስታት እንዲሁም ሌሎች ኤጀንሲዎች ሰዎችን ከህገወጥ ዝውውር እና ከግዳጅ የጉልበት ስራ ለመጠበቅ ስለዚህ ጉዳይ የበለጠ ግንዛቤ እንደሚገነቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

ይህ መቆም አለበት !

ህብረተሰባችን ከህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ህገ ወጥ ጉዞ ራሱንና ልጆቹን መጠበቅ አለበት። "

(ሽኩር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዩጋንዳ በሀከሮች 17 ሚሊዮን ዶላር ተዘረፈች።

ዩጋንዳ በማዕከላዊ ባንኳ ላይ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት 62 ቢሊዮን ሽልንግ ወይም 17 ሚሊዮን ዶላር ተዘርፋለች፡፡

ቢው ቪዥን ጋዜጣ እንደዘገበው ምዝበራው የተፈጸመው ሀከሮች (ጠላፊዎች) የባንኩን አይቲ ክፍል ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው፡፡

ምዝበራው ባሳለፍነው ማክሰኞ ነው እንደተፈጸመ የተነገረው።

ምዝበራው በደቡብ እስያ የሚገኙ ጠላፊዎች የተፈጸመ እንደሆነ ገንዘቡ በመጨረሻ ወደ ጃፓን እንደተላከ ባንኩ አስታውቋል፡፡

ባንኩ ከተመዘበረው ገንዘብ ውስጥ ግማሹን አስመልሻለሁ ብሏል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ መንግስታቸው በሚስተዳድረው ባንክ ላይ የተፈጸመው ምዝበራ እንዲመረመር አዘዋል።

ዴይሊ ሞኒተር ባወጣው ዘገባ ይህ ምዝበራ የተፈጸመው በባንኩ የውስጥ ሰራተኞች እርዳታ አማካኝነት ሳይሆን አይቀርም።

የፕሬዝዳንቱን ጥዕዛዝ ተከትሎ ፖሊስ ሁኔታውን እየመረመረ ነው ተብሏል። በቅርቡ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ዩጋንዳ በተደጋጋሚ መሰል የበይነ መረብ / ሳይበር ጥቆቶችን ስታስተናግድ የአሁኑ የመጀሪያዋ አይደለም።

በተለይም በቴሌኮም ኩባንያዎች እና የገንዘብ አተላላፊ ተቋማቶቿ ላይ በተደጋጋሚ ዝርፊያ ተፈጽሟል፡፡

በባንኮች ላይም መሰል ምዝበራዎች የሚፈጸሙ ቢሆንም ባንኮች ከደንበኞቻቸው ሊደርስ የሚችልን ጉዳት በመፍራት ምን ያህል ገንዘብ እንደተሰረቁ ከመናገር ይቆጠባሉ፡፡

ይህን መረጃ አል አይን ኒውስ ቢው ቪዥን ጋዜጣና ዴይሊ ሞኒተርን ዋቢ በማድረግ ነው ያጋራው።

@tikvahethiopia
#ጭማሪ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

አሁን አገልግሎት እየተሰጠበት ያለው 10 ብር ሲሆን ወደ 20 ብር ጭማሪ እንደተደረገ ታውቋል።

የታሪፍ ጭማሪው ከታኅሣስ 1/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
 
@tikvahethiopia
የጥሪ ማሳመሪያ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ተረከቡ!!
እንኳን ደስ አላችሁ 🎉

አሁንም ለጥሪ ማሳመሪያ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎችን በመግዛት ከ645 ለሚደርስዎት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ሽልማቶችን ይውሰዱ!

📺 ስማርት ቴሌቪዥኖች
💻 ላፕቶፖች
📱 5ጂ ስማርት ስልኮችና ሳምሰንግ ታብሌቶች
🎁 እንዲሁም በርካታ የሞባይል ጥቅሎችን በሽልማት ያግኙ!

ለመመዝገብ 822 ወይም *822# ይደውሉ አልያም https://www.crbt.et ይጎብኙ!

🗓 እስከ ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም ብቻ!


#CRBT
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia