TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" አስደናቂ ድል ተቀዳጅቻለሁ " - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ " አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ " አሉ። የሪፐብሊካኑ ዕጩ ትራምፕ ድላቸውን ለደጋፊዎቻቸው የተናገሩት በፍሎሪዳ በተካሄደ መድረክ ነው። ትራምፕ ይህ የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን እንደሚሆን ተናግረዋል። " ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል " ብለዋል። በድንበሮች ያሉ ጉዳዮችን እልባት እንደሚሰጡ ቃል…
#USA

ስደተኞች በትራምፕ የስልጣን ዘመን ምን ይገጥማቸው ይሆን ?

ከዚህ ቀደም በምርጫ ዘመቻ ወቅት ዶላንድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በስደተኞች ጉዳይ ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቃል ገብተው ነበር።

ትራምፕ " በአስቸኳይ የስደተኞችን ወረራ አስቆማለሁ፣ ማንኛውም አይነት የህገወጥ ስደተኞችን በረራ እንዲቆም እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ አደርጋለሁ " ነበር ያሉት።

ከዚህ ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ የተባለ ዲፖርቴሽን (ከሀገር የማስወጣት) ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

" ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ያሏቸው ዶክመንት አልባ ህገወጥ ስደተኞችን ነው።

በስድተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ከዚህ ቀደምም የሚታወቀው ትራምፕ አሁንም ፕሬዜዳንት ሲሆኑ እንደሚያጠናክሩት ነው በዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ቃል የገቡት።

ትራምፕ ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ህገወጥ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው ነው የሚባለው።

ይሄን ሁሉ የሰው ቁጥር ግን እንዴት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደሚያደርጉ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ በተጨማሪም በዘመቻቸው ወቅት ፥ ለ4 አመት በስልጣን ሲቆዩ ህገወጥ ስደትን ከማስቆም ባለፈ በህጋዊ ስደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ ፥ " ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ ፣ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ፤ ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ ነበር የተናገሩት።

ስደተኞችን " #የሀገራችንን_ደም_እየበከሉ_ነው " በማለት ተናግረውም ብዙዎችን አስቆጥተው ነበር።

በስደተኞች ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት መሆናቸው እርግጥ ሆኗል።

#TikvahEthiopia
#USA #deport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው " ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ' ትዕዛዝ ' እንዲሰጡ ያስችላቸዋል " ብለዋል።

ይህም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት / በገፍ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ (ማስ ዲፖርቴሽን) እንደሆነ ጠቁመዋል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ይህ ሰነድ አልባዎችን በብዛት ከአሜሪካ የማስወጣቱ /ማስ ዲፖርቴሽን/ ተግባር የትራምፕ የመጀመሪያው ቀን ስራ ይሆናል ብለዋል።

ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በሚመለከት " ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ሲሉ ቃል ገብተው ነበር።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው።

#TikvahEthiopia
#USA #massdeportation

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው " -የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ከክፍያ ጋር በተያያዘ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ዘግተው ስለወጡና ስራ ስላቆሙ ጤና ባለሞያዎች በተመለከተ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል። " እኔ እንደ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ ይከፈላቸው ብዬ እየጠየኩ ነው በዕለቱም ይህንን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር…
#Update

" ጥያቄያችን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " - ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሙያዎች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መግለጻችን ይታወሳል።

የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ማለትም 12/02/17 እስከ 18/02/17 ድረስ ስራ ሳይገቡ ቆይተው ማክሰኞ በ19/02/2017 ዓ.ም ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር የወረዳው ባለሥልጣናት በተገኙበት በተደረገ ውይይት ሽማግሌዎች ከወረዳው ሃላፊዎች ጋር ለማደራደር በመስማማታቸው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።

ይሁን እንጂ ከስብሰባው ማብቃት በኋላ " አድማውን አስተባብራቹሃል " በሚል 14 የሚሆኑ ባለሞያዎች ለእስር ተዳርገዋል።

በተለያየ ቀናት ለእስር የተዳረጉት እነዚህ ባለሞያዎች ከ 2 እስከ 6 ቀናት ለሚሆን ጊዜ ታስረው በዋስ ከእስር ተፈተው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለእስር ከተዳረጉት ባለሞያዎች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሯል።

ባለሙያዎቹ  " ጥያቄያችን ፓለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " ብለውናል።

" የጠየቅነው የሰራንበትን ክፍያ ሆኖ ሳለ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ' ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳ አድርጋቹሃል፣ ሰዎችን ወደ ሥራ እንዳይጋቡ አስፈራርታቹሃል ' የሚል ክስ ተነቦልናል " ነው ያሉት።

በተጨማሪም ባለሞያዎች ወደ ሆስፒታል ሲመለሱ ከአሁን በኋላ ተመሳሳይ የሆነ የስራ ማቆም አድማ ውስጥ ቢገቡ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርሙ ተደርጓል ብከዋክ።

ሰራተኞቹ ከተመለሱ በኋላ BPR የተሰኘ በየስምንት ሰዓቱ በሺፍት የሚቀያየሩበት አሰራር እንዲዘረጋ መደረጉን ተናግረዋል።

በአዲሱ አሰራር መሰረት ጠዋት 12 ሰዓት ወደ ስራ የገባ ሰራተኛ 8 ሰዓት ከስራ የሚወጣ ሲሆን 8 ሰዓት የገባው ምሽት 4 ሰዓት ከስራ ይወጣል።

ይሁን እንጂ ይህ አሰራር " ሆስፒታሉ ለሰራተኞች ሰርቪስ የሌለው በመሆኑ እና በምሽት ሺፍት ከስራ ስንወጣ እና ስንገባ ለጅብ እየተጋለጥን ነው " በሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

" ይህ አይነቱ አሰራር የተዘረጋው የወረዳው አስተዳደር ለመቀጣጫ እንዲሆን በሚል ነው " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማስቀረት የተደረገ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ጉዳዩ በዋናነት የሚመለከታቸውን የአንጋጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የሆስፒታሉ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ማርቆስ ማሞን ቅሬታውን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ለማናገር ተደጋጋሚ የሆነ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ አቶ ተሰማ አበራ አዲሱ  አሰራር ለአደጋ አጋልጦናል የሚለውን የሆስፒታሉን ባለሞያዎች ቅሬታ አይቀበሉም።

" የትርፍ ሰዓት ስራ ሲሰሩ ያልነበረ ጅብ ዛሬ ከየት መጣ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ አይነቱ አሰራር ያልነበረና አዲስ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ብለዋል።

አክለውም " ይህን ጭቅጭቅ የሚያመጣው ወረዳው የመክፈል አቅም የሌለው በመሆኑ ነው በቀጣይም መጋጨት የለብንም " በማለት አሰራሩ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለሞያዎቹ የሰሩበት ገንዘባቸው ሳይከፈላቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል መቼ ክፍያቸው ይፈጸማል ስንል በድጋሚ ላነሳንላቸው ጥያቄም "አሁንም እየተነጋገርን ነው ከወረዳ መንግሥት ጋር የገንዘብ ክፍተት ስላጋጠመ እንጂ መከፈል እንዳለበት ተግባብተናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደመወዝ : የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም.  ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዛሬ አሳውቋል። ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደው በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ መተላለፉም ተገልጿል። (ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይፋዊ የደመወዝ…
#ደመወዝ

" በእኛ መስሪያ ቤት በኩል የተስተካከለው የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል " - መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ፥ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያን በተመለከተ ባሰራጩት ፅሁፍ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የተጨማሪ ክፍያ በጀቱን ለሚመለከታቸው ተቋማት ፈቅዷል። በእኛ መስሪያ ቤትም በኩል የተስተካከለውን የጥቅምት ወር ደመወዝ ተከፍሏል " ብለዋል።

" ሌሎችም እንደዚሁ የከፈሉ አሉ። የቀሩት ደግሞ የማጥራት ሥራ እየሰሩ ሊሆን ይችላል። " ሲሉ ገልጸዋል።

" እነዚያም ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ የተስተካከለው የጥቅምት ወር ክፍያ ታሳቢ በማድረግ የሚከፍሉ ይሆናል " ሲሉ አስረድተዋል።

" የተፈቀደው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ክፍያ ዘግይቷል፥ ቀርቷል የሚሉ ሃሳቦች እየተራመዱ ነው " ያሉት ኮሚሽነሩ " በሲቪል ሰርቪስ በኩል የሚለቀቁ መረጃዎች ኦፊሴላዊና የሚተገበሩ መሆኑን መተማመን ጥሩ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከሠራተኞች ደመወዝ ስኬል ጋር በተገናኘ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሳሳች ወሬዎችን እንዳታምኗቸው መልዕክት አስተላልፌ ነበር " ሲሉም አክለዋል።

ከሰሞኑን ከሠራተኞች ደመወዝ ጋር በተገናኘ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎችን ተዘዋውረዋል።

ከነዚህም አንዱ ጭማሪው እንዳልተከፈለ የሚገልጽ ነው።

ነገር ግን በአንዳንድ መ/ቤቶች ጭማሪው መከፈሉ ታውቋል። ጭማሪው ያልተከፈለባቸውም መ/ቤቶችም ግን አሉ ፤ እነዚህ ናቸው ' እያጣሩ ናቸው " የተባሉት።

" ተጨምሯል የተባለው ገንዘብ ያን ያህል አይደለም " - ሠራተኞች

" የደመወዝ ጭማሪ ይደረጋል " የሚለውን መረጃ የሰሙ ሠራተኞች ከፍተኛ ጭማሪ ጠብቀው እንደነበር ነገር ግን እጃቸው ላይ የደረሰው እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ሠራተኛ ፥ " ምንኑን ከምኑን ልናደርገው ይሄ ብቻ እንደተጨመረ አልገባኝም " ብለዋል።

ጭማሪው አነስተኛ እንደሆነ የገለጹ አንዲት ሠራተኛ በበኩላቸው " ከሚጨመረው ብር በላይ ወሬው በዝቶ ይበልጥ ኑሮውን እንዳያስወድደው " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

" አይደለም ደመወዝ ተጨመረ ተብሎ ሳይባል እንኳን ነጋዴው ሁሉን ነገር አምጥቶ የሚጭነው እኛው ድሃው ዜጎች ላይ ነው አሁን ተጨምሯል የተባለው ገንዘብ ከኑሮው ውድነቱ አንጻር ያን ያህል አይደለም፤ ጭራሽ ነጋዴዎቹ ዋጋ ጨምረው አሁንም አልገፋ ያለውን ኑሮን እንዳያከብዱብን " ብለዋል።

ያነጋገርናቸው ሌሎችም ሠራተኞች " ደመወዝ ተጨመረ " የተባለው አነስተኛ እንደሆነ፣ የቁጥጥር ስራ እንዲሰራ ፣ ሌሎች የሠራተኞችን ህይወት የሚያቀሉ መፍትሄዎች እንዲፈለጉ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia