TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " የህዝቡን ኑሮ አይታችሁታል ? ይሄ ማህበረሰብ ከኮሪደር ልማቱ ይልቅ የዕለት ጉርሱን ሸፍኖ የሚበላበት ነገር አያስፈልገውም ? " - ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ የኮሪደር ስራው ላይ የሚነሱት ጥያቄዎች ምንድናቸው ? የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ ይቀይራል የተባለው የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል። አሁን ላይ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ስራ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ ነው።…
#AddisAbaba

ለምን የልማት ተነሺዎችን እዛው ቦታቸው ላይ ቤት ሰርቶ ማስገባት አልተቻለም ?

በአዲስ አበባ ከሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ ነዋሪዎች ረጅም ዓመታት ከኖሩባቸው ሰፈሮች እንዲነሱ እየተደረገ ነው።

አስተያየት ሰጪዎች ፤  " ይሄ ነገር ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመሃል ለማስወጣት ፤ የማህበራዊ ትስስሩንም ለመበጣጠስና ፤ ነባሩን ነዋሪ ለመበታተን ፤ የልማት ተነሺ ቦታዎችንም ለሚፈልጉት ባለሃብት ለመስጠት ነው ፤ እውነት ልማት ከሆነ ለምን ባሉበት በኖሩበት ቦታ የጋራ መኖሪያ ቤት አይሰራላቸው ? " ሲሉ ይጠይቃሉ።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች በተገኙበት ከዚሁ ከኮሪደር ልማት ጋር የተያያዘ የውይይት መድረክ ላይ ፤ " ለምን የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ከተገነባ በኃላ ከለማ በኃላ በነበሩበት ቦታ መኖር አይችሉም ? ልክ እንደ አዋሬ ለምን አልተደረገም ? እዛው እንዲኖሩ ለምን ማድረግ አልተቻለም ? " የሚል ጥያቄ ተስቷል።

እንዲሁም ረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ነዋሪዎች ፦
- ከእድራቸው
- ከእቁባቸው
- ከሰንበቴያቸው ፤ በእስልምናም በኩል ያሉት የማህበረሰቡ መገናኛዎች እንዲበተኑ እየተደረጉ ነው የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" እዛው አካባቢ ላይ ብታለሙ አይሻልም ወይ ? እውነት ነው ይሻላል እንላለን። በነበሩበት አካባቢ ቢሆን የበለጠ ቅድሚያ የሰጠዋል።

አዋሬ እንደዛ ነው የለማው። አዋሬ ብቻ ሳይሆን 70 ደረጃ የገነባናቸው ቤቶች እዛው ሰፈራቸው ነው። በተመሳሳይ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ የበጎነት መንደር ብለን የሰራነው እዛው ነው። ለሚኩራም ሎውኮስት ሀውስ የተሰሩት እዛው ነው፣ ጉለሌ፣  አየር ጤና ሁሉንም መዘርዘር ይቻላል።

ሰፋፊ አካባቢዎችን ስናነሳ አንደኛ የሚገነባበት ቦታ የለም ፤ ካልተነሱ በስተቀር። ሁለተኛ በጥናታችን ሲገነባ የመስረተ ልማቱ የፍሳሽ፣ የጎርፍ መውረጃው የከተማ ልማት የመሬት አጠቃቀሙ የመኖሪያ ቤት መሆን የሌለበት አካባቢ አለ። ተዘግቶ የተገነባበት አለ ጥናቱ በዝርዝር ያስረዳል።

ስለዚህ ሰፋ ወዳለ ቦታ ይሄንን ማህበረሰብ መውሰድ ያስፈልጋል። ቤት ብቻ አይደለም ያየነው። በአካባቢያቸው የሚያስገልጉ ሌሎች መሰረተ ልማቶች አብረው መኖር አለባቸው።

ሌሎች ሀገሮችን እኮ እናውቃለን መኖሪያ ቤቶች መሃል ዋናው ከተማ ላይ ናቸው እንዴ ? ንጹህ አየር ወዳለበት ከተማ ውስጥ ነው ከከተማ አልወጣም። እዚህ ነው የተሻለ ቦታ የተሻለ ሰፋ ያለ ለልጆችም የሚሆን ፤ ብዙ ሰው ሊይዝልን የሚችል ቦታ ላይ ገንብተን አዲስ ቤት መሰረተ ልማት የተሟላለት ቤት አስገብተናል።

ጥያቄ የምታነሱ ወገኖቻችን ኑ አብረን እንሂድና ገላን ጉራን፣ አቃቂን እንመልከት ፣ አቃቂ የቁጠባ ቤቶች ግቢ እንሂድ አብረን ፣ አራብሳ ግቢም የልማት ተነሺዎች የገቡበት አካባቢን እንይ።

አንዳንድ ቦታዎች የተጠቆሙ (የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸው) ካሉ እንደግብዓት እንወስዳለን ህዝባችን እንዲንገላታ አንፈልግም ፤ ህዝባችን እንዲንገላታ ምንም አይነት ፍላጎት የለንም።

ግን እሱም ቢሆን ይኖሩበት ከነበረው ጋር አይወዳደርም።

ከማህበራዊ ትስስራቸው ተበታተኑ የሚለው ፍጹም ውሸት ነው። አልተበታተኑም። የአንድ አካባቢ ሰዎችን አንድ አካባቢ ነው ዕጣ ያስወጣነው። ዕጣውን ለሁሉም ከየአካባቢው ለሚነሱት በጋራ አይደለም ያደረግነው ቀጠናቸውን እንኳን ጠብቀንላቸዋል።

እቁብ፣ እድር፣ ማህበር አላቸው፣ ትስስር አላቸው። ' አይ የቁጠባ ቤት ላይ አንገባም ኮንዶሚኒየም ነው ' ሲሉ የተወሰኑ ሰዎች ኮንዶሚኒየም ሲመርጡ ወደ ሌላ ሄደው ሊሆን ይችላል። ይሄ ለተባለው ግን በቂ ማሳያ አይሆንም።

ባለቤቱ መርጦ ' ይሄ ይሻለኛል በዛው ንብረት ይዛለሁ የጋራ መኖሪያ ቤት ማግኘት ማለት ባለቤት መሆን ነው በቁጠባ እየከፈልኩ ከምኖር ባለቤትነትን እመርጣለሁ ' ካለ ለምንድነው ? ከማህበራዊ ትስስርህ ተነጥለህ ፤ እዚህ እቁብ፣ እድር አለ እዚህ ሰፈር ካልሆነ አትገባም አንለውም። እንደዛ የተባለ ካለ ይዛችሁ ኑ " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaAddisAbabaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba #ኮንዶሚኒየም

🔵 " ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " - አቶ አበበ አካሉ

" የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ


ከአዲስ አበባ የኮሪደር ስራ ጋር በተያየዘ በርካቶች በልማት ተነሺነት ከኖሩበት አካባቢ ተነስተው ወደ ተለያዩ ጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲገቡ እየተደረገ ነው።

ምንም እንኳን ተነሺዎቹ መግባታቸው ላይ ቅሬታ ባይፈጥርም ከ97 አንስቶ ሲቆጥቡ የኖሩ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ መቅረታቸው እና አሁን ላይ አስተዳደሩ ቤት የተሰጠ መሆኑ ቅሬታ አሳድሯል።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በተካሄደ የኮሪደር ስራውን በሚመለከት የውይይት መድረክ ላይ ይኸው ቅሬታና ጥያቄ ተነስቷል።

ጥያቄውን ካነሱት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

" ሲቆጥቡ የኖሩ ሰዎች ጉዳይ ምን ደረሰ ? አሁን ማህበረሰቡ ምን ያማል ከተማ አስተዳደሩን ' እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው የልማት ተናሺዎችን እያሰፈረ ያለው ' የሚል ሮሮ አለ።

ለዚህ ምንድነው ምላሻችሁ ?

ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " ሲሉ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" የኮንዶሚኒየም ቤት እስኪ ከየት አምጥታችሁ ነው በዚህ ደረጃ ያላችሁ ኃላፊዎች ' በቆጡት ገንዘብ ነው የሚሰራው ' የምትሉት።

እነ ንግድ ባንክ ናቸው ብሩን የሚያቀርቡት እስቲ እንነጋገር ትንሽ ወደ መረጃው ጠጋ ብላችሁ ብናወራ ምናለበት።

ኮንዶሚኒየም በብድር ነው የሚሰራው። የከተማ አስተዳደሩ በጀቱን አስይዞ ነው የሚበደረው።

ለምንድነው የሚቆጥቡት ? ከተባለ ዕጣ የደረሳቸው ዕለት የሚከፍሉትን እንዳያጡ ነው። እንጂ ቤቱን መገንቢያ አይደለም። ልክ ቤቱ ሲገነባ ብሩን ይከፍሉታል።

ሁለተኛ እንዴት ነው እኛ ብቻችንን የምንጠየቅበት ? ቤት ባልተዘጋጀበት በሚሊዮኖች መዝግቦ ቆጥቡ ብሎ ኃላፊነት ወስዶ የሰራ አካል እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

ቤት ሳያዘጋጅ ዜጎችን ልክ እንደ ማታለያ በሚሊየን መዝግቦ የበተነ እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

የኮንዶሚኒየም ቤት አጠቃላይ አንድ ቦታ እጅብ ብሎ ስለተሰራ ብዙ ይመስላችኋል እንጂ እስካሁን እስካጠናቀቅነው ያለው 300,000 ነው። የተመዘገበው በሚሊዮን ነው። በየጊዜው ተስፋ ቆርጦ፣ ተጣርቶ ተጣርቶ እኛ የደረስንበት 600,000 ነው። አክተቭ ይቆጥብ የነበረው። ግን ቤት ማግኘት እንዳለባቸው እናምናለን። ቤት ማግኘት አለባቸው።

ካለቁት ኮንዶሚኒየሞች ብራቸው ተዘርፎ፣ ቀድሞ ተከፍሎ ያልተሰራ 80 ህንጻ ብር ተከፍሎበት ጥለው ሄደዋል። በብዙ ውጣውረድ ነው 139,000 ቤቶችን የጨረስነው። የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ብቻ።

አሁንም ቢሆን ግን የከተማችን ነዋሪዎች ቤት ማግኘት አለባቸው። ለዚህም በኮንዶሚኒየም ብቻ አይደለም እንደ ቀድሞ በሚፈለገው ደረጃ ብድር ማግኘት አልቻልንም ከባንክ። ኮንዶሚኒየም መጥፎ ስለሆነ አላቆምነውም።

ከተማ አስተዳደሩ ዕዳ እየከፈለ ነው። ንግድ ባንክ የሚያበድረው የባለሃብትን ገንዘብ ነው አይደል ? 56 ቢሊዮን የኮንዶሚኒየም ዕዳ ነው የተረከብነው ዋስትና የሚሰጠው ከተማ አስተዳደሩ ስለሆነ ክፈሉ ተባልን ተገደድን በለውጥ ዘመኑ 30 ቢሊዮን ከፍለናል የኮንዶሚኒየም ዕዳ።

ይህ ሁሉ ዕዳ አንደኛ በከፍተኛ ሰብሲዲ ስለሚሰራ ነው ፤ ሌላው ያልተሰሩ ቤቶች የተከፈለባቸው አሉ። ሳይከፍሉ ሲሸጡ በተለያየ መንገድ ሲተላለፉ የነበሩ ቤት ውስጥ ያገኘናቸው ሰዎች ከግለሰብ የገዙ ናቸው፤ ሊገደዱ አይችሉም የኮንዶሚኒየም ክፈሉ ተብለው። አጣርተን እኮ በሚዲያ ነግረናችኋል ፤ ያጋጠመንን።

አሁን በግልና በመንግሥት አጋርነት ወደ 100,000 ቤቶች አስጀምረናል። የቁጠባ ቤቶችንም እየሰራን እያከራየን ነው። በሪስልቴትም በግል የሚሰሩትን እንደ ከተማው ፕሮጀክት ጠጋ ብለን እያገዝን ቶሎ እንዲጨርሱ እያደረግን ነው።

እስካሁን የቆጠቡትን አሁን በግልና መንግሥት ትብብር ከምንሰራው  ውስጥ ቅድሚያ ሊያገኙ የሚችሉበትን አግባብ እየተከተልን ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተደራጅተው በማህበር እንዲሰሩ ...እስካሁን ለተደራጁት መሬት አስረክበናል።

መነገጃ አታድርጉት፤ ከእውነታው ውጭ መነጋጃ ማድረጉ አይጠቅምም።

የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል። ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድሚያ 97 አክቲቭ ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል።

እነሱ ከወጣላቸው በኃላ ዲአክቲቬት ያደረገውን አካውን አክቲቬት ያደረገ ካለ እሱ ስለቆጠበ ቤት ስለሚፈልግ ለሚቀጥለው ጊዜ ሊታይ ይገባል ፤ እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ የለበትም " ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
#AddisAbaba #Education

“ በሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት ላይ እጥረት በመታየቱ ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው ” - አ/አ ትምህርት ቢሮ

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት መፅሐፍ ማሳተም ላይ እንደ አገር በተለያዩ ትምህርት ቢሮዎች ክፍተቶች እንዳሉ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት በ2017 የትምህርት ዘመን መፅሐፍትን አሳትሞ ለተማሪዎች ማዳረስ ተቻለ ? ሲል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥያቄ አቅርቧል።

የቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሰጡት ቃል፣ “ በተወሰኑ ትምህርቶች ላይ፤ ሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት  እጥረት በመታየቱ ምክንያት ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው። ሪዘርቭም እያደረግን እንገኛለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

የመፅሐፍት እጥረቱ በምን ደረጃ ነው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረባቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “ ይህንን ሬሽዎ በተለይ ከግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ላይ ያለ ችግር ነው ” ብለዋል።

“ እነርሱም መፅሐፉን ወስዶ ለማሰራጨት ፍላጎት ማጣት፣ ይሄ ደግሞ የራሳቸው መፅሐጽት አትመው ለመሸጥ ከሚመነጭ ነገር ስለሆነ እሱ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየወሰድን ትምህርት ቤቶች ወስደው ለተማሪዎቻቸው ተደራሽ እንዲያደርጉ አድርገናል ” ነው ያሉት።

“ ከሁለተኛ ደረጃና ቅድመ አንደኛ ደረጃ በስተቀር ለሁሉም አንድ ለአንድ ተዳርሷል ” ሲሉም ተናግረዋል።

“ ለሁለተኛ ደረጃም ትምህርት ሚኒስቴር አሳትሞ ሰሞኑን ባስገባው መሠረት ለሁሉም ተማሪዎች ማዳረስ ተችሏል" ያሉት ኃላፊው፣ " ባለፉት ሁለት ዓመታት በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተማሪዎቻችን ጋር ተደራሽ ለማድረግ ተሞክሯል” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ከተማሪዎች ምገባ ጋር በተያያዘ መጋቢ እናቶች ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ የሚከፈላቸው ገንዘብ አነስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ።

ይህንኑ በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ የጠየቅናቸው ዘላለም (ዶ/ር)፣ “ በተማሪ 22 ብር የነበረው በዚህ ዓመት ወደ 32 ብር አሳድጎላቸዋል። ስለዚህ ያ ጥያቄ ተመልሷል ማለት ነው ” ብለዋል።

“ በቀን 800 ሺሕ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ይመገባሉ ” ሲሉ ተናግረዋል።

በተያያዘም በትምህርት ቤት አካባቢዎች ያሉ ሱስን የሚያበረታቱ ቤቶች እንዳሉ፣ ይህም ተማሪዎችን ከዓላማቸው የሚያደናቅፍ ከመሆኑ አንጻር በቂ ትኩረት ተሰጥቷል? ሲልም ቲክቫህ ጥያቄ አቅርቧል።

ዘላለም (ዶ/ር) በምላሻቸው፣ “ትክክል ነው። የተማሪዎችን ሀሳብ፣ ልቦና የሚሰርቁ ጉዳዮች በትምህርት ቤት አካባቢዎች እንዳይኖሩ ባለፉት ዓመታት ጠንካራ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።

“ ከ3000 በላይ የሚደርሱ የተለያዩ መማር ማስተማር ሂደቱን ሊያውኩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ እርጃ ተወስዷል ” ብለው፣ “ አሁንም እንደዛ አይነት ፍላጎቶች በትምህርት ቤቶች ብቅ ብቅ እንዳይሉ መልሶ ጠንካራ እርምጃና ክትትል ያስፈልጋል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በርካታ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ እንዲሸጡ ቀረቡ።

አዲስ አበባ ውስጥ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ለሊዝ ጨረታ መቅረቡ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት ለሊዝ ጨረታ እንደቀረበ አሳውቋል።

የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉ ነው የተሰማው።

ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታ የቀረቡ መሬቶች መኖራቸው ተነግሯል።

ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ 4ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ነው።

143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት / ቦታ ለሊዝ ጨረታ ሲቀርብ በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ቢሮው መግለፁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

🔴 ለአንድ የጨረታ ሰነድ የሚከፈለው የማይመለስ ብር 2,300 ብር ነው ተብሏል።

🔴 የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 08/2017ዓ.ም እስከ ጥቀምት 21/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በ (
2merkato.com link :- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) ላይ ነው መግዛት የሚቻለው።

🔴 ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ እንዳለባቸው ተገልጿል።

🔴 አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ተብሏል።

የጨረታ ቁጥር እና የቦታዎቹን ኮድ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች በዚህ ማግኘት ይቻላል :
https://www.aalb.gov.et/blogs/detail/72

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በድጋሚ ቢሮ ሂደን ጠየቅናቸው ግን የተስፋ ቃል ከመስጠት ውጪ መሬት ላይ ምንም ተጨባጭ ነገር አይሰሩም  " - ቤት ገዢዎች ከ600 በላይ የሚሆኑ የአያት ግሪን ኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች፣ በውላቸው መሠረት ድርጅቱ የመብራት፣ የውሃ፣ የታንከር መሠረተ ልማቶችን ባለሟማላቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው ከገዙት ቤታቸው መግባት እንዳልቻሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡…
#AddisAbaba

“ ከቆጣሪ ጋ የመገጣጠም ሥራው ግፋ ቢል ከዚህ በኋላ አንድ ወር ቢፈጅ ነው ” - ኖህ ሪልስቴት

ኖህ ሪልስቴት ሰሚነት አካባቢ “ ኤርፓርት ድራይቭ ” በተሰኘ ሳይቱ የገነባቸውን ሱቆችና ቤቶች ዛሬ ለገዢዎቹ ማስረከቡን ገልጿል።

የድርጅቱ የሕግ ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ደስታ፣ “ ዛሬ ሰሚት አካባቢ በሚገኘው 'ኤርፓርት ድራይቭ' የተሰኘ ሳይት ቤቶችን ስላጠናቀቅን የምረቃት ሥነ ስርዓት አካሂደናል ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ሱቅን ጨምሮ ወደ 750 ቤቶች እንዳስረከቡ ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባደረጉት ንግግር፣ “ በዛሬው እለት እያስመረቅናቸው ያሉ 750 ቤቶቾና 43 ሱቆች ከተማችንን የሚመጥኑ ሆነው ለምተዋል ” ብለዋል።

እስከዛሬ ባስረክባችኋቸው ቤቶች የመሠረተ ልማት ቅሬታ ይነሳል (ለምሳሌ አያት ግሪን ሰይት ተጠቃሽ ነው) በአሁኑ ሳይትስ ተመሳሳይ ቅሬታ እንዳይኖር መሠረተ ልማቱ ተሟልቷል ? ሲል ቲክቫህ ለአቶ ዮሴፍ ጥያቄ አቅርቧል።

ምን አሉ ?

ከአያት ግሪን ፓርክ ልምድ ወስደናል። ሁሉም ፕሮጀክቶቻችን ላይ መዘግዬት የተፈጠረው ከኮቪድ ጀምሮ ባለው ችግር ነው። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ያለውን ነገር እንዴት እንፍታ ? በሚል ግሪን ፓርኩ ላይ ልምድ ወስደናል።
 
ከወሰድነው ልምድ አንጻር ለዚህኛው ፕሬጀክት አስፈላጊው ጀነሬተር ገብቷል ፤  ትራንስፎርመር ገብቷል። የመብራት ፓሎችም ተተክለዋል። ከህንጻዎቹ ጋር የማገናኘት ሥራ ብቻ ነው የሚቀረን።

ውሃን በተመለከተ ፤ ቦታው ላይ የከርሰ ምድር ውሃ ቆፍረን ለነዋሪው አዘጋጅተናል። ስለዚህ የውሃ ችግር አይኖርም። 

መብራትን በተመለከተም ከመንግስት የፓወር ችግር የለም። በኛ በኩል የሚያስፈልገውን ትራንስፎርመር፣ ጀነሬተር፣ ሌሎቹን ኢንፍራስትራክቸሮች በሙሉ አዘጋጅተናል። ስለዚህ እሱን የማገናኘት ሥራ እንሰራለን ”
ብለዋል።

በአጠቃላይ በገዢዎች የሚነሱ የመሠረተ ልማት ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ኖህ ምን እየሰራ ነው ? ዛሬ ያስረከባችኋቸው ቤቶች መሠረተ ልማቶች መቼ ይጠናቀቃሉ ? የሚጠናቀቁበትን ጊዜስ ከገዥዎቹ ጋር ተነጋግራችኋል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ማብራሪያቸው ምንድን ነው?

ትልቅ እንቅፋት የነበረው የትራንስፎርመር ችግር ነው። ከመንግስት (ከኤሌፓ) ነው የሚገዛ የነበረው። ከዚያ ብቻ በሚገዛበት ጊዜ ወረፋ እንጠብቅ ነበር። አሁን ግን ተፈቅዶልናል ከገበያ እንድንገዛ። ያ እንቅፋት የለም።

ውሃን በተመለከተ ፤ የከተማውን የውሃ እጥረት ስለምናውቅ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው በከርሰ ምድር ላይ ነው። ውሃም ቶሎ የሚገኝበትን መንገድ እንሰራለን።

ህንጻዎቹ ያልቃሉ ከዛ የመሠረተ ልማት ጥያቄ አለ። ይሄ ጥያቄ የኛ ብቻ አይደለም። ዋናው ሆኖ እያለ በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይም የውሃ እጥረት አለ። ለመቅረፍ እየሰራን ነው


መሠረተ ልማቱ በምን ያክል ጊዜ ውስጥ ያልቃል ? ሁሉም እቃ ቀርቧል። የቀረው ነገር መብራት በሚሰራው ኮንትራክተር መገጣጠም ነው። ከቆጣሪ ጋ የመገጣጠም ሥራው ግፋ ቢል ከዚህ በኋላ አንድ ወር ቢፈጅ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

የአያት ግሪን ፓርክ የገዢዎች የመሠረተ ልማት ከምን እንደደረሰ ጠይቀናቸው በሰጡን ቃል አቶ ዮሴፍ ፤ “ ተመሳሳይ እምጃዎችን ወስደን የመብራት አገልግሎቱ አሁን በዬቤቱ ቆጣሪ የማስገባት ሥራ ተጀምሯል” ነው ያሉት።

“ ስለዚህ እዛም ያለውን ችግር አቃለናል። ውሃን በተመለከተ ለውሃ የሚያስፉፍገው የታንከር ማስቀመጫ ቦታ ችግር ነበረብን እሱን ፈትተን ውሃውን ግቢ ውስጥ አስቀምጠን ወደ ፊት እየተራመድን ነው ያለነው ” ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን 545 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላልፈ ጨረታ አውጥቶ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ቤቶቹን " በተለያዩ ሳይቶች ያስገነባኋቸው ናቸው " ብሏል።

የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 1000 ብር ነው በ6 የመሻጫ ጣቢያዎች እየሸጠ ያለው።

የመኖሪያ ቤቶቹ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ግራር (235 ቤቶች) እና አየር ጤና (110 ቤቶች) እንዲሁም በጉለሌ ክ/ከተማ እንጦጦ (200 ቤቶች) እንደሚገኙ ተሰምቷል።

የአንድ ካሬ ሜትር የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 80,000 (ሰማንያ ሺህ ብር) እንደሆነም ከጨረታ ሰነዱ መመልከት ተችሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአቢሲንያ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች የATM ካርድ በቆማችሁበት በሰከንዶች ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

የአቢሲንያ ባንክ ፌስቡክ ፔጅን ሊንኩን በመጠቀም ይቀላቀሉ፡ https://www.facebook.com/BoAeth

#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ