TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓለምአቀፍ : የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺክህ ሃሲና ስልጣን ለቀው ሀገር ጥለው ወጡ። በባንግላዴሽ ምን ተፈጠረ ? ➡️ ተማሪዎችና ሌላውም ዜጋ የመንግስትን የስራ ቦታ ኮታ ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ተቃውሞ የጀመሩት ከሳምንታት በፊት ነው። ይህ የኮታ ተቃውሞ ምንድነው ? እኤአ በ1971 ባንግላዴሽ ለነጻነቷ ከፓኪስታን ጋር ጦርነት አካሂዳ ነበር። በዚህም " 30% የመንግሥት ስራ ለነዚሁ ተዋጊዎች…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Bangladesh : ለ15 ዓመታት ያህል ባንግላዴሽን የመሩት ሺህክ ሀሲና የተነሳባቸውን ጠንካራ ተቃውሞ ተከትሎ ሀገር ጥለው  ጠፍተዋል።

የተቆጡ ተቃዋሚዎችም ወደ ሚኖሩበት ቤተመንግስት በኃይል ሰብረው በመግባት ወረው በመኖሪያ ቤታቸው እንዳሻቸው እየፈነጩበት ነው።

ግማሹ አልጋ ላይ ፣ ግማሹ በየክፍሉ እየዞረ እቃቸውን ይፈትሻል፣ ግማሹ ይጨፍራል።

ከመንግሥት የስራ ኮታ ስርዓት ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የጀመሩት እና ሌሎችም ዜጎች የተቀላቀሉበት ተቃውሞ ለሳምንታት ቆይቷል፤ በርካቶች ሞተዋል። በመጨረሻ ግን ሀሲናን ሀገር ለቀው እንዲጠፉ አስገድዷቸዋል።

የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከስልጣን ወርደው መሄዳቸውን አሳውቋል።

በሚመሰረት ጊዜያዊ መንግሥት ሀገሪቱ ትመራለችም ብሏል። ህዝቡም በሰራዊቱ ላይ እምነቱን እንዲጥል ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል። የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል…
#Ethiopia

የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ " ለማኅበራዊ ድጋፍ " የሚውል ነው ብለዋል።

ተጨማሪ በጀቱ የፌደራል መንግሥቱን ሰኔ ወር ላይ ያጸደቀውን የ2017 ዓ.ም. በጀት 1.5 ትሪሊዮን ብር ገደማ ያደርሰዋል።

የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀትም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ትሪሊዮን እንዲሻገር ያደርገዋል።

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ምን አሉ ?

የህህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከአንድ ወር በፊት አንድ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ማጸዕደቁን ያታወሳል።

አሁን 551 ቢሊዮን አካባቢ የሚሆን ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤቱ ይቀርባል።

በተጨማሪ በጀት መልክ ለፓርላማ ከሚቀርበው ግማሽ ትሪሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን የሚሆነው ፦
° ለማኅበራዊ ድጋፍ፣
° ለሴፍቲኔት፣
° ለሠራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣
° ለመድኃኒት ድጎማ፣
° ለዘይት ድጎማ፣
° ለነዳጅ ድጎማ የሚውል ነው።

ከወጪው በተጨማሪ የገቢ በጀትንም ለሕ/ተወ ምክር ቤት አቅርበን እናሳውጃለን።

563 ቢሊዮን የነበረው የፌደራል መንግሥት ገቢ ተከልሶ 851 ቢሊዮን ይሆናል። ይሄ የሚሆነው ግን አንድም የታክስ መጠን ሳይጨምረ ነው።

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ፦

" ይሄንን ስናደርግ ተጨማሪ ታክስ በመጣል ወይም የታክስ ምጣኔ በመጨመር አይደለም መጨመር ያሰብነው። ኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን distortion ዝንፈት በማስተካከል ነው።

ታክስ ሳይከፍል ይከብር የነበረ ባለሃብት አሁን ቶሎ ወደ መስመር መግባት አለበት። ይሄንን የሚፈቅድ ነገር አይኖርም። ጠንካራ የሆነ enforcement ሥራ ይሠራል። "

#Ethiopia #FBC #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ይህ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ የተከሰተ የመሬት መንሸራተት ነው። ትላንት ቀን 10:30 በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ 1 ሰው ሲሞት ፣ 1 ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። 8 የአከባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በተከሰተው ናዳ አደጋ ህይወቷ ያለፈው የ11 ዓመት ሴት ልጅ ናት። አብራት የነበረችው ወላጅ እናቷ ደግሞ ከአደጋው…
#Alert🚨

" እስካሁን የ11 ሰዎች አክስሬን ተገኝቷል " - የካዎ ኮይሻ ወረዳ

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር አሳውቋል።

ከቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ 1 ሰው ህይወቱ ማለፉ እና 1 ሰው ከባድ ጉዳት እንደረሰበት ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከወረዳው ኮሚኒኬሽን ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ " የከንቲባዋ ታናሽ ወንድም እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ " በማለት ከ4 ግለሰቦች ላይ ከ970 ሺ ብር ያታለለን ተጠርጣሪ መያዙን አሳወቀ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው ግለሰብ ታደለ ጌታነህ ይባላል፡፡

በስሙ ግን " ታደለ አቤቤ " እንደሚባል ሐሰተኛ መታወቂያ አዘጋጅቷል።

ይኸው ግለሰብ የግል ተበዳይ አቶ ልዑል ኪሮስን የከንቲባዋ ወንድም እንደሆነ እና መንግስት ለቤት መስሪያ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ስለሰጠው ለሊዝ የሚክፍለው 800 ሺ ብር እንዲያበድሩት ይጠይቃል።

የግል ተበዳይም የተባሉትን በማመን 600 ሺ ብሩን አስናቀ ጌታነህ ቀሪውን 200 ሺ ብር ደግሞ በላይ ጣሰው በተባሉት ግብራበሮቹ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ በነገራቸው መሰረት ብሩን ገቢ ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ አቶ ፈለቀ ሃይሉ የተባሉ ግለሰብን በመቅረብ ቤት ለመገንባት 4 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገውና 500ሺ ብር ብድር እንዲሰጡት ጠይቆ 105 ሺ ብር መቀበሉን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።

በተመሳሳይ አዳማ ላይ የተዋወቀቃቸውን አቶ ለገሰ ሲሳይ የተባሉ ግለሰብን ደግሞ " የከንቲባዋ ወንድም ስለሆነኩ በቀላሉ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሬት አሰጥሃለሁኝ " ብሎ 10 ሺ ብር ወስዷል።

እንዲሁም ለቤተሰባቸው ' #ፓስፖርት ' ለማውጣት ኢሚግሬሽን ላይ ያገኛቸውን አቶ ፈለቀ ዝናቡ የተባሉ ግለሰብን " የከንቲባዋ ወንድም ነኝ በተጨማሪም እኔም ዳኛ ነኝ ምናልባት ያለ አግባብ የሚያጉላሉህ ካሉ አሳውቀኝ ሰብስቤ አሳስራቸዋለሁኝ " የሚል የማታለያ ቃል በመናገር ጉዳያቸው በፍጥነት እንዲያልቅል 80 ሺህ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ 10 ሺህ ብር አታሎ ወስዷል።

ፖሊስ ግለሰቡ ከከንቲባ አዳነች ጋር ምንም አይነት ዝምድና የሌለውና በድለላ ስራ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቡን ጨምሮ በዚህ ወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ሦስት ተጠርጣዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
🔈#የሰራተኞችድምጽ

" ቢብስብን ነው ወደ ህዝብ ፊትና ሚዲያ የመጣነው " - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን

በሚሰሩበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ስርዓት መማረራቸውን የገለጹ የአካዳሚክ ጉዳይ አካላት፣ መምህራንና ሌሎችም ችግሮች ካልተፈቱ ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አሳስቡ።

ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በኦዲት ግኝት እንዲሁም በሌሎችም ችግሮች በስፋት ስሙ መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም።

" ከፍተኛ የሆነና እስካሁን ያልተፈታ ቅሬታ አለን " ያሉት የተቋሙ ሰራተኞች ሰሞኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ምን አሉ ? ምንድነው እንዲህ አማሮ ወደ ህዝብ ያስወጣቸው ጉዳይ ?

➡️ ተቋሙ ይኸው ከ10 ዓመት በላይ ቢሆነም ዛሬም እጅግ ብዙ ነገሮቹና ክፍተቶች አሉበት።

➡️ ተቋሙን ከውድቀት መታደግ ያስፈልጋል።

➡️ ዘንድሮ ጥቅምት ላይ ከላይ አመራሮች አንስቶ ሪፎርም ተደርጎ ነበር። ፋይናንስ ላይ ሪፎርም አልተደረገም።

➡️ ምንም እንኳን በሪፎርሙ ብዙ ለመስራት ቢሞከርም ትልቅ ችግር የነበረው የፋይናንስ ስርዓቱ በዛው ነው የቀጠለው።

➡️የፋይናንስ ስርዓቱ በዛው በመቀጠሉ ከክፍያም ሆነ ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ትልቅ ችግር ነው ያለው።

➡️ የፋይናንስ ችግሩ ለመምህራን ፈተና ሆኗል። ይህ ሁኔታ በተማሪዎች ትምህርት ላይም የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ ነው።

➡️ አካዳሚክ ስታፎች ምንም አይነት የአቅም ማጎልበቻ የሚያገኙበት እድል የላቸውም። በሪሰርች፣ በሶፍትዌር ስልጠና ፣ በመማር ማስተማርም ...ይሁን በሌላ ምንም እየተሰጠ አይደለም። ለዚህ ጉዳዮች እቅድ ወጥቶ ፋይናንስ ላይ ይደውቃል።

➡️ ከመምህራን ክፍያ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር ነው ያለው።

➡️ በጫና ውስጥ ሆነው የሚሰሩ ሰራተኞች በአግባቡ ከፍያ አያገኙም።

➡️ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ ተጋብዘው የሚያስተምሩ መምህራን ለክፍያ ስቃይ ነው። መጀመሪያ ተጋብዞ የመጣ " ድጋሚ ወደዚህ አንመጣም ነው " የሚሉን።

➡️ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ተጋባዦች ስለሚቸገሩ አንዳንዴ ኮርሶች ወደ ሌላ ጊዜ ይዞራሉ ይህ ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጫና ያሳድራል።

➡️ ብዙ ላብራቶሪ ግቢው ስለሌለው ተማሪዎች የግድ መማር ስላለባቸው ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ይላካሉ በዚህ ወቅት ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መጓተት አለ። በመምህራን ክፍያም ላይ ችግር አለ። በዚህ ምክንያት ብዙ ትምህርቶች የላብራቶሪ የሚፈልጉ ትምህርቶች ድሮፕ ይደረጋሉ።

➡️ ኢተርንሺፕ የሚወጡ ተማሪዎች ክፍያም ችግር ነው። ተማሪዎች በዚህ በጣም ነው የሚጎዱት።

➡️ ተማሪዎችን ጠብቀው አጅበው የሚወስዱ የሴክዩሪቲ ሰዎችም ክፍያ ቶሎ አይፈጸምም ይጓተታል።

➡️ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የሚመጡ መምህራን የሚያዙበት መንገድም ጥሩ አይደለም። ህግና ደንብ ተከትሎ ባለመስራት  ምክንያት ይጎዳሉ። እጅግ በጣም የክፍያ መጉላላት አለ።

➡️ የመንግሥት ተቋም መሆኑ እስኪያስጠረጥር ድረስ ነው የፋይናንስ ችግር ያለው።

➡️ በአግባቡ ስራ ስለማይሰራ የበጀት ችግር አለ። መከፈል ያለበት አይከፈልም።

➡️ ተቋሙ ችግር በበዛባት ቁጥር ውጤታማ ተማሪ ፍራት አይችልም። ይህም ባለፉት የመውጫ ፈተናዎች ታይቷል። በዘንድሮው አመት ከአምናው ያነሰ (29%) ተማሪዎችን ነው በመውጫ ፈተና ያሳለፈው።

.... ሌሎችንም አሉ ያሏቸውን ችግሮች በዝርዝር አሳውቀዋል።


የአካዳሚክ ጉዳይ ሰራተኞች፣  መምህራንና ሌሎች ከዚህ ቀደም ሪፎርም ሲደረግ የፋይናንስ ዘርፉ ማታለፉን አመልክተው ባለው ችግር የሚቀጥል ከሆነ ስራ ለመስራት እንደሚቸገሩ አሳስበዋል።

" ካልሆነ የአካዳሚክ ጉዳዩን እነሱ የፋይናንስ ሰዎች ይስሩት አናስረክባቸዋለን " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

ጉዱዩን በመለከተ ከሰሞኑን የፋይናንስ ስርዓቱ እንዲቀየር ፒቲሽን ፈርመው በ72 ሰዓት መልስ እንዲሰጣቸው እንዳስገቡ  ነገር ግን ምንም ምላሽ ሳይገኝ ሰዓቱ ማለቁን ጠቁመዋል።

" ያለው ችግር በውስጥ እንዲፈታ ጥረናል " ያሉት ሰራተኞቹ " ቢብስን ነው ወደ ህዝብና ሚዲያ የቀረብነው " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴፍ ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ አይተው ማስተካከያ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በዚህ አይነት የትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚያልፉ ተማሪዎችን ነገ መውቀስ ስላማይቻል ዛሬ ያሉ ችግሮች ይፈቱ ብለዋል።

(መምህራኑና ሰራተኞቹ በፋይናንስ ሴክተር አሉ ያሏቸውን ችግሮች ዘርዝረው ፈርመው ያስገቡት ፒቲሽን ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተቋሙን ጉዳይ እስከመጨረሻ ይከታተላል። የተቋሙን አመራሮችና ኃላፊዎችንም ያነጋግራል።

#GambellaUniversity

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" 50,000 ብር ተቀጥተዋል " - የአ/አ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፤ በከተማው በተሰራው የኮሪደር ልማት ለተሽከርካሪ ባልተፈቀደ የእግረኛ መንገድ ላይ " ሆን ብለው በቸልተኝነት " የደንብ መተላለፍ ፈጽመዋል ያለውን ግለሰብ በ50,000 ብር መቀጮ መቅጣቱን አሳውቋል።

ቅጣቱ የተላለፈባቸው በሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 C 03643 አ.አ የተመዘገበ የቤት መኪና ሲያሽከረክሩ የነበሩ ግለሰብ ናቸው።

" ግለሰቡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቀደም ሲል የቀይ ሽብር ሠማዕታት ወይም ሠላም ፓርክ በተሠራ የልማት ኮርደር ላይ ለተሽከርካሪ ባልተፈቀደ የእግረኞች መንገድ  ሆን ብለው በቸልተኝነት በማጥፋት አምልጠው ተሰውረው ነበር " ብሏል ባለልስጣኑ።

ለግዜው ቢሠወሩም ግን በአዲስ አበባ  ትራፊክ ፖሊስ አባላት ክትትል ከነ ተሽከርካሪያቸው በዛሬው ዕለት መያዛቸውን ፤ ባጠፉት ጥፋት መሰረት 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ ብር መቀጣታቸውን አሳውቋል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
🔈#የተማሪዎችድምጽ

° “ ሳንመረቅ አመታት ተቆጠሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው መቼ እንደሚጠራን ያሳውቀን ” - ተመራቂ ተማሪዎች

° “ መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ ” - መቐለ ዩኒቨርሲቲ


ትግራይ ውስጥ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ጭምር የመመረቂያ ጊዜያቸው የተራዘመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመመረቅና ድግሪ ለመያዝ አመታትን እንደጠበቁ ፣ አሁንም ዩኒቨርሲቲው እንዳልጠራቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ምን አሉ ?

- ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ስለጉዳዩ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቀን ነበር። የመውጫ ፈተና እንደምንፈተን እና ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ላይ እንደምንመረቅ ነበር ስኬጁል የወጣው።

- የመውጫ ፈተናውን ብንወስድም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን ለቀን ወጥተናል። ከዚያ ነሐሴ 2016 ዓ/ም ትጠራላችሁ ተባልን፡፡ አሁን የክረምት ተማሪዎችም ተጠርተዋል፡፡ እስካሁን የኛ ግን ምንም ነገር የለም። ዝም ጭጭ ብለዋል።

- የፌደራል መንግስትም በጦርነነቱ ጊዜ የነበሩ ተማሪዎች በዓመት 3 ሴሚስተር ማካካሻ ጊዜ ፈቅዶልን ነበር፡፡ ያኔ የተፈቀደልንን ማካካሻ በአግባቡ ያስተናግዱን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ፤ “ ተማሪዎቹ እያነሱት ያለው ቅሬታ ትክክል ነው ” ብሏል።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ተከስተ ብርሃን (ዶ/ር) ምን አሉ ?

በተለያዩ ምክንያቶች በተለይ ትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች አሉን።

ክረምቱን እንዲማሩ ነበር በዩኒቨርሲቲው ማኔጀመንት የወሰነው። ነገር ግን በአገር ደረጃ በተሰጠው ዳይሬክሽን መሠረት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲፈተኑ መደበኛ ተማሪዎቹ ማስወጣት የግድ ነበር።

በኮረና እና በነበረውም ጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ የክረምት ተማሪዎች ነበሩ። እነርሱንም ተቀበልን፡፡ ለመምህራን የሚሰጥ ስልጠና አለ፡፡ እነርሱንም ተቀብለን እያሰለጠንን ነው።

በእነዚህ ምክንያቶች መደበኛ ተማሪዎቻችንን መጥራት አልቻልንም።

አሁን እንደ አቅጣጫ የያዝነው መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ጠርተን ማካካሽ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ባለፉት ዓመታት ሊመረቁ ለነበሩ ተማሪዎች ብቻ ካላንደር አዘጋጅተን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ነው።

መስከረም ስንት ቀን ይጠራሉ ? ቁርጥ ያለውስ ቀን መቼ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ተከሰተ (ዶ/ር)፣ " የክረምት ተማሪዎቹ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ/ም እንዲያጠናቅቁ ብለናል፡፡ ስለዚህ ካላንደሩ ገና አልጸደቀም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

#TIkvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
ዓለም ወደለየለት ቀውስ ውስጥ ትገባ ይሆን ? የፍልስጤም እና እስራኤል ጦርነት መቆሚያ ማጣቱን ተከትሎ በየጊዜው አዳዲስ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ፤ መካከለኛው ምስራቅ እየታመሰ ነው። ምንም ሰላማዊ መፍትሄ በመጥፋቱ አሁንም በጦርነቱ ሰዎች እያለቁ ነው። " ፍልስጤምን አትንኳት " የሚሉና ሃማስን የሚደግፉ ኃይሎችም እስራኤልን በሮኬት / ሚሳኤል መደብደብ አላቋረጡም። ከሰሞኑን ግን በኢራን ቴህራን ውስጥ…
" ኢራን ዛሬ ምሽት ጥቃት እንደምትሰነዝር ሰምቻለሁ " - ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ  ፥ " ኢራን ዛሬ ምሽት በእስራኤል ላይ ጥቃት እንደምታደርስ ሰምቻለሁ " ብለዋል።

" ዛሬ ምሽት ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል ሰምቻለሁ፤ ጥቃት ይደርስባቸዋል [እስራኤል] ይህን እነግራችኋለሁ " ሲሉ አዲን ሮስ ከተሰኘ ዩትዩበር ጋር በነበራቸው ቆይታ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ትራምፕ " እኔኮ ፕሬዝዳንት ብሆን ኖሮ ማንም ስለዚያ ቃል (ጥቃት) እንኳን አይነገርም ነበር ፣ ምክንያቱም ይህ 100% አይከሰትም ነበር " ብለዋል።

በመካከለኛ ምስራቅ ያለው ውጥረቱ እጅግ የተባባሰ ሲሆን ምንም እንኳን ሰዓቱና ቀኑ ባይነገረም የኢራን ጥቃት አይቀርም ተብሏል።

የተለያዩ ሀገራት ኢራንን " እባክሽ ሁኔታውን አረጋጊው " ብለው ቢማጸኗትም " እስራኤልን ሳልቀጣት አርፌ አልቀመጥም " ብላለች።

በእስራኤል እና በአሜሪካ በኩልም ፥ የኢራን ጥቃት ትፈጽማለች ተብሎ ዝግጅት ማድረጋቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 የፓሪስ ኦሎምፒክ የ5,000 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር ተጀምሯል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦ 🇪🇹 በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 🇪🇹 በአትሌት መዲና ኢሳ 🇪🇹 በአትሌት እጅጋየሁ ተወክላለች። መልካም ዕድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ! More - @tikvahethsport
ኬንያዎቹ ወርቁንም ብሩንም ጠራርገው ወስደውታል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን 3ኛ ሆና በመውጣት ነሃስ ወስዳለች።

የሀገራችን ልጆች እጅጋየሁ ታዬ 6ኛ ፣ መዲና ኢሳ 7ኛ ፣ ጉዳፍ ፀጋይ 9ኛ ሆነው አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ስሟ በገነነበት ርቀት ከሜዳሊያ ውጭ ሆናለች።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በፓሪስ ኦሎምፒክ የሴቶች 800 ሜትር ፍጻሜ ውድድር ጀምሯል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦
🇪🇹 በአትሌት ወርቅነሽ መሰለ 
🇪🇹 በአትሌት ፅጌ ድጉማ ተወክላለች።

በዚህ እንኳን አስደስቱን ፤ ተስፋን ስጡን !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኬንያዎቹ ወርቁንም ብሩንም ጠራርገው ወስደውታል። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፋን ሀሰን 3ኛ ሆና በመውጣት ነሃስ ወስዳለች። የሀገራችን ልጆች እጅጋየሁ ታዬ 6ኛ ፣ መዲና ኢሳ 7ኛ ፣ ጉዳፍ ፀጋይ 9ኛ ሆነው አጠናቀዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ስሟ በገነነበት ርቀት ከሜዳሊያ ውጭ ሆናለች። @tikvahethiopia
ፌዝ ኪፕዬጎን ውጤቷ ተሰረዘ ፤ ሲፋን ሃሰን ሁለተኛ ሆነች።

ከደቂቃዎች በፊት በ5000ሜትር ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው ፌዝ ኪፕዬጎን ውጤቷ መሰረዙ ተገልፆል።

ኪፕዬጎን በውድድሩ ከጉዳፍ ፀጋይ ጋር በነበራቸው አካላዊ ንክኪ (መደነቃቀፍ) ምክንያት ውጤቷ ሊሰረዝ ችሏል።

ይህንንም ተከትሎ ሲፋን ሀሰን ሁለተኛ ፤ ጣልያናዊቷ ባቶሶሌቲ ሶስተኛ ሆነዋል።

Via @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
ብር ለኢትዮጵያ የ800ሜትር ሴቶች ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ አትሌት ፅጌ ድጉማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። @tikvahethiopia
#TsigeDuguma

ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በ800 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ለሀገሯ ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው ፅጌ ዱጉማ ከውድድሩ በኃላ " JESUS IS LORD ! " የሚል ጽሁፍ አሳይታለች።

ፅጌ ስሟ ተጽፎ ደረቷ ላይ ከተለጠፈበት ወረቀት የጀርባ ክፍል ላይ ነው ይህን መልዕክት ፅፋ ገብታ ያስተላለፈችው።

የዘንድሮ የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነስርዓት በክርስቲያኖች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethsport