TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጸሎተ_ሐሙስ

የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።

ዛሬ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክሃይማኖት መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።

በስነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ቆሞሳት ፣ ካህናትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit - TMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማኅብረቅዱሳን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሁለቱም አገልጋዮች የመኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል…
የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ " #ለጥያቄ_ይፈለጋሉ " በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

ቀደም ብሎ ፥ የሰንበት ት/ ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ከቤታቸው በጸጥታ ኃይል መወሰዳቸውና ቤታቸው ላክ ፍተሻ መደረጉን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዝገቡ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ጸሎተ_ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብሯል።

በአዲስ አበባ ፒያሳ ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ካህናት፣ ደናግላንና ምዕመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴና የቅባ ቅዱስ ቡራኬ ተካሂዷል።

Photo Credit - FBC & Emdiber Catholic Secretariat

@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር

በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ!

የዘመናዊነት ተምሳሌት!


አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282

👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture

👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ " - ቀሲስ በላይ መኮንን የቀሲስ በላይ መኮንን ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ስለ ዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር። በዚህም ወቅት ፥ ደንበኛቸው ቀሲስ በላይ መኮንን በሐሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የተገኙት " ሰዎች አታልለዋቸው " እንደሆነ ለፍ/ቤት መናገራቸውን ገልጸዋል።…
እነ ቀሲስ በላይ ክስ እስኪመሰረትባቸው በእስር ይቆያሉ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በነ ቀሲስ በላይ መኮንንና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት ፈቅዷል።

በሀሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ከ6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩትና በቁጥጥር ስር የዋሉት ቀሲስ በላይ መኮንንና 2 በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

በዚህም ፍርድ ቤት ለዐቃቤ ሕግ 15 ቀናት የክስ መመስረቻ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪዎች ክሱ እስኪመሰረት ድረስ ባሉበት ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዟል።

@tikvahethiopia
" በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር።

በዚህም ፤ " የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም " ብለዋል።

" የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን " ያሉት አቶ ጌታቸው " ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል " ሲሉም አስገንዝበዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን "  - አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከዋልታ ቴሌቪዥን ቆይታ አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም በሲስተም ችግር ምክንያት በተፈጠረው እክል ተዘርፎ የተወሰደውን ባንኩ ገንዘብ  እያስመለሰ መሆኑንና ከ801 ሚሊዮን ብር የቀረው 25 ሚሊዮን ብር መሆኑን ገልጸዋል።

በዕለቱ 30 የባንኩ ሰራተኞች በግብይት ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ አሁን ላይ ከስራ ታግደው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፥ ባንኩ በምን የሕግ አግባብ ነው ሰዎች ነጻ ሆኖ የመገመት መብታቸው ተጥሶ ፎቷቸው የተሰራጨው ? የሰዎችን ምስል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት አሰራጨ በሚል ተጠይቀዋል።

አቶ አቤ ፤ " እኛ ዛሬም ድረስ ወንጀለኛ ናቸው የሚል ቃል አልወጣንም። ይሄን ገንዘባችንን ወስደዋል መልሱ ነው ያልነው መውሰዳቸውን 101% እናውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ዛሬ ያለንበት ሁኔታ እና መጀመሪያ ላይ የነበረው ይለያያል። እሁድ የነበረው ታሪክ ' ባንኩ ማን ብር እንደወሰደበት አያውቅም ' የሚል ነው በተለይ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲቀለድ ነበር እኛ ግን ' እናውቃለን መልሱ ስንል ' ነበር ምላሹ ' አያውቅም ' የሚል ነበር በኃላ 1 ሳምንት ሰጠን በተደጋጋሚ አስጠነቀቅም እንዲመልሱ ከዛ ስም እና ፎቷቸው እዲወጣ ወደማድረጉ ገባን " ብለዋል።

" ምስል አታሰራጭ የሚል በህገ-መንግስቱ አልተገለጸም። ሲቀጥል 15 ሺህ ሰው በኮንቬንሽናል ህግ ሊፈታ የሚችል ችግር አይደለም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " naming and shaming የሚል ህግ አለ ገንዘብ የወሰደውን ሰው ስሙን አውጥቶ ያያችሁት ንገሩትና ይመልስ ነው ያልነው " ብለዋል።

" ነጻ ሆኖ የመገመት መብቴ ተነክቷል " የሚል ካለ ይክሰሱንና ካሳ ይጠይቁ ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ አቤ " ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

" ያደረግነው ነገር በተወሰነ ደረጃ ወቀሳ ሊቀርብበት የሚችል ነገር ነው። ለችግሩ መፍትሄ ግን ያደረግነው ብቻ ነበር። ነገሩ ከህግም ከፖሊስም አቅም በላይ ነው ይሄን ሁሉ ሰው ማሰር አይችሉም፤ ፍርድ ቤት ይሄን ሁሉ ሊዳኝ አይችልም። የህግ ጥያቄ ቢነሳም ትክክለኛው መፍትሄ ያደረግነው ብቻ ነበር እሱንም አማራጭ ስላልነበረን ነው ያደረግነው ያን ማድረጋችን ህዝቡ እንዲያውቀው ሆኖ የወሰደው ሁሉ ተሰልፎ መጥቶ መለሰ " ብለዋል።

" ገንዘቡ የህዝብ ነው እያስመለስን የቀረው ከ801 ሚሊዮን ብር 25 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ፤ የማሰባሰቡ ስራ 96.8 በመቶ ደርሷል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ምንም እንኳን ልጆች ቢያጠፉም ወላጆች መጥተው አርመዋልና የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ጨዋ ነው ፤ አሁንም አዋቂ አለ ፣ የሚያስትምር አለ፣ ሽማግሌ አለ፣ ጨዋ ወላጅ አለ ማለት እፈልጋለሁ " ሲሉ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር #ታንዛኒያ ለሳምንታት በዘለቀ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት 155 ሰዎች ሲሞቱ ፤ 236 ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ ጠ/ሚ ቃሲም ማጅዋሊ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት በጎረቤት #ኬንያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ በትንሹ 35 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። 40,000 ሰዎች  ደግሞ ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ ሆነዋል።…
#Kenya

በጎረቤት ኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል።

ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በደረሰው አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 188 መድረሱን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር አሳውቋል።

እስካሁን ያልተገኙ በርካታ ሰዎች መኖራቸውም ተገልጿል።

በኬንያና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች በተከታታይ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የብዙ ሰዎች ህይወት እየጠፋ ሲሆን የከፍታ ቦታዎች መናድም ነዋሪዎችን ካለመጠጊያ አስቀርቷል፡፡

መንገዶችን ድልድዮችን እና ሌላም የመሰረተ ልማት አውታሮችን ውድሟል። #VOA

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሲከናወን ቆይቷል።

ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከ28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መራዘሙ ተነግሯል።

ተጫራቾች ፦
- የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣
- ሲፒኦ፣
- የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣
- ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ
- ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉ እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ተብሏል።

ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ  እንደሚከፈት ተገልጿል።

የጨረታው ዝርዝር👇
https://t.iss.one/tikvahethiopia/87112

@tikvahethiopia