TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቿን ከነገ ጀምሮ በተቀናጀ መንገድ የመመለስ ሥራ እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግሥት ልዑክ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና የጂዳ ቆንስላ ጀነራል ሰራተኞች እና የኮሙኒቲ አስተባባሪዎች ጋር በመወያየት በተመላሾች መለየት እና መመለስ ላይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በመሆኑም ሪያድ እና ጂዳ አካባቢ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ወደ ሀገር ቤት የመመለሱ ስራ ነገ አርብ ሚያዚያ 04 ቀን 2016ዓ.ም እንደሚጀመር አቅጣጫ ተቀምጦ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተነግሯል።

70 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከሳውዲ አረቢ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እቅድ አለ።

@TikvahethMagazine
#መቐለ

በትግራይ ክልል፣ መቐለ ዓይደር ኮምፕሬሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል የላፕራቶሪ ማሽኖች ላይ ወድመት ደርሷል።

ከሰሞኑን አንድ በጭንቅላቱ ላይ ካርቶን ያደረገ ማንነቱ የማይታይ ግለሰብ በሆስፒታሉ የህክምና ቁሶች ላይ ጉዳት ሲያደርስ የሚያሳይ የCCTV ቅጂ ተሰራጭቷል።

ግለሰቡ ለምን እንዲህ ያለውን ተግባር እንደፈጸመ የሚታወቅ ነገር የለም።

ሆስፒታሉ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል በሰጠው ቃል ፥ በትክክል ድርጊቱ የተፈፀመው ዓይደር ውስጥ እንደሆነ አረጋግጧል።

ድርጊቱ የተፈፀመው በራሱ ሰራተኛ እንደሆነ አመልክቷል።

ድርጊቱ የተፈፀመው ቅዳሜ መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያላቸው በርካታ የህክምና መሳርያዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

የጉበት፣
የኩላሊት እጥበት፣
የሰውነት ሆርሞን መለኪያ
የካንሰር አመላካቾች እንዲሁም በተለያዩ እንደ የልብ ህመም ያሉ ድንገተኛ ሁኔታዎች መመርመሪያዎች፣ የሆርሞኖች፣ የሰውነት ስብን መለኪያ መሳሪያዎች ከተጎዱት የሆስፒታሉ መገልገያዎች መካከል ናቸው።

ጉዳት ከደረሰባቸው የህክምና መሳሪያዎች አንዱ ለተለያዩ ምርመራዎች የሚውለው " ኮባስ 6000 " የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን፣ በትግራይ ያለው ብቸኛው እና ትልቁ የሆስፒታሉ መሳሪያ ነው።

አሁን ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል።

መሳሪያው ቀደም ብሎ በ20 ሚሊዮን ብር የተገዛ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ዋጋው 30 ሚሊዮን ብር እንደደረሰ ሆስፒታሉ ገልጿል።

የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባልም ጉዳዩ ዓይደር ኮምፕሬሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል ድረስ በመጓዝ ጉዳዩ ሲከታተለው ነበር።

ከሆስፒታሉና ስለ ጉዳዩ እውቀትና ቅርበት ካላቸው ወገኖች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ማንነቱ ያልታወቀው ግለሰብ በስለት በመጠቀም ሲቆርጠው የሚታየው (ከላይ ቪድዮ አለ) ከ30 ሚሊዮን ብር ዋጋ እንዳለው የተነገረለት የላቦራቶሪ ማሽን የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ ክፍል ነው።

በመቐለ ከተማ የዓይደር ክፍለ ከተማ ፓሊስ በዓይደር ኮምፕሬሄንሲቭ ሪፈረሰል ሆስፒታል የላብራቶሪ ማሽኖች ወድመት በተያያዘ ቪድዮው ላይ ያለው ግለሰብ ጨምሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሏል። 

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ”…
#Update

“ ልጄን ለመልቀቅ ቀነ ገደብ አልሰጡም ” - የታጋች ጌድዮን እናት

ሊቢያ ውስጥ የታገተው የሀዋሳ ከተማው ወጣት ጌድዮን ሳሙኤል እናት በሰጡን ቃል ፣ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው #እየገረፉት ቪድዮ ላኩልኝ። ‘ 1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለነው ቪዲዮ እንልክልሻለን ’ አሉኝ ” ማለታቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

አሁንስ ታጋቹ ተለቀቀ ? በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለታጋቹ እናት ጥያቄ አቅርቧል።

እሳቸውም ፥ “  ‘#እንለቀዋለን’ ብለዋል። በፊት በየጊዜው ማግኘት እንችል ነበር አሁን ላይ ግን ማገናኘት ከልክለዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ግን በቅርብ ጊዜ ያየሁት ለውጥ ግንባሩ ላይ #ተፈንክቷል። ለመልቀቅ ቀነ ገደብ አልሰጡም ” ብለዋል።

ቅድሚያ 800 ሺሕ ብር ለአጋቾቹ እንዳስገቡ፣ ቀሪውን ታጋቹ ሊለቀቅ ቀናቶች ሲቀሩት ለመላክ ከአጋቾቹ ጋር መነጋገራቸውን አክለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ታጋቹን የሚለቁት የበርካታ ታጋቾች ቤተሰቦችም የተጠየቁትን ገንዘብ አሟልተው ሲልኩ 20፣ 20 ታጋቾችን በማሳፈር እንደሆነ፣ ቢያንስ የ20 ታጋች ቤተሰቦች የተጠየቁትን ገንዘብ ካላኩ መኪና ስለማይሞላ፣ የከፈሉትም ያልከፈሉትን መጠበቅ ግድ እንደሚላቸው እንደገለጹላቸው አስረድተዋል።

የወጣት ጌድኦን እናት ባስተላለፉት መልዕክትም፣ “ ልጆቻችን የሚሰደዱበት ምክንያት አላቸው። ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው መጥተው ወላጅ ጋር ነው የሚቀመጡት። እኛ ደግሞ ሲቸግረን ሲያዩ አይችሉም። ይህንን መንግሥት በትኩረት መስራት አለበት ” ብለዋል።

“ ወጣቱ አሁንም ከሀገር #እየተሰደደ ነው። እስቲ ወላድ ምን እንሁን ? እነዚህ ልጆች ለአገራቸው አይጠቅሙም ? ” ሲሉ ጠይቀው፣ “ ቢያንስ እንኳ መንግሥት ተበድሮም ቢሆን የሆነ ፋብሪካ ከፍቶ ወጣቱን ቢያሰራ እኮ ወጣቱ አይሰደድም ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

መኢአድ፤ ኢሕአፓ፤ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፣ እናት ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ  ፥ በሰላማዊ የፖለቲካ አመራሮችና አባላት ላይ እስራትና ወከባ እየደረሰ እንደሆነ ገልጿል።

ፓርቲዎች ይህ እስራትና ወከባ " ለፖለቲካ ትግሉም ሆነ ለአገር በአጠቃላይ በቀደሙ ጊዜያትም ያመጣው በጎ ነገር የለም " ሲሉ አስገንዘበዋል።

" ዛሬም ቢሆን ከዚህ የተለየ ውጤት የማያመጣም " ሲሉ አክለዋል።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው እየተወሰደ ነው ያሉት እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም የጠየቁ ሲሆን " የታሰሩ አመራሮችም የሃሰት ማስረጃ ማቀነባበር ሳያስፈልግ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀን እንጠይቃለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
" ስፖርተኞች ያረፉበት ሆቴል እየተከተሉ አልጋ በመያዝ ስርቆት ሲፈጸሙ ነበር " - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ

የሲዳማ ክልል ጸጥታ ኃይል " ስፈልጋቸው የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ይዛለሁ " አለ።

በቁጥጥር ስር የዋለቱ ተጠርጣሪዎች ስፖርተኞች ያረፉበት ሆቴል እየተከተሉ #አልጋ_በመያዝ ስርቆት ሲፈጹም የነበሩ እንደሆነ የጸጥታ ኃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ካሁን በፊት በተመሳሳይ አይነት መንገድ ስርቆት ፈጽመዉ ሀዋሳ ከተማን በመልቀቃቸዉ ሳይያዙ ቢቆዩም ከሰሞኑ ከተማውን ሲረግጡ ጀምሮ በተደረገ ክትትል መያዛቸዉን የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ " ከገንዘብ አንስቶ ስማርት ስልኮች ከባጃጅ እስከ መኪኖች ድረስ ተደራጅተዉ የሚዘርፉና ከሀገር ውጭ ዶላር ተመድቦላቸው የዘረፋ ተግባር የሚፈጽሙ መሆናቸውን " የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ሀሚድ አህመድ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ ፤ በከተማው የተተከሉ ካሜራዎችና የተሰማሩ የጸጥታ አካላት ሲከታተሏቸዉ ቆይተዉ እንደተለመደው ስፖርተኞች ያረፉበት ሆቴል በማረፍ የዘረፋ ተግባራቸውን ለመፈፀም ሲሞክሩ እጅ ከፈንጅ መያዛቸዉን አስረድተዋል።

ግለሰቦቹ እንዲህ ያለዉን ተግባር ለመፈጸም እንዲችሉ ከሁለት መቶ በላይ ማስር ቁልፎችን እንዲሁም ሲያዙ ህገወጥ የውጭ ሀገር ገንዘቦች እና በርካታ ስልኮች እንዲሁም የባንክ ቼኮች መያዛቸዉን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ጉዳያቸው በህግ ተይዞ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን ወደፊት የወንጀል ምርመራው እና የፍርድ ሂደቱንም ሆነ የተጠርጣሪዎችን ሰንሰለት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
" የስምምነት ሃሳቡ ተቀባይነት ካገኘ #ኢትዮጵያ የተረጋጋ እና ተገማች የባህር ሀብት ተደራሽነት ይሰጣታል " - ኮሪር ሲንግኦኢ

ኬንያ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ቀጠናዊ የባህር ላይ ስምምነት ሃሳብ ማቅረቧን ሮይተርስ ዘግቧል።

ኬንያ የስምምነት ሃሳቡን ያቀረበችው ፤ ከጅቡቲ እና ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት ኢጋድ ጋር በመመካከር ነው።

ይህ ስምምነት ወደብ የሌላቸው ሀገራት በንግድ እንዴት ወደብ መጠቀም እንደሚችሉ የሚገዛ መሆኑን የኬንያ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሃፊ ኮሪር ሲንግኦኢ ተናግረዋል።

ኢጋድ የባህር ሃብትን ለመጋራት የሚያስችል ስምምነት መፍጠር እንደሚችልም ገልጸዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ትላንት ከኬንያ አቻቸው ዊሊያም ሩቶ ጋር በኬንያ ዋና ከተማ ለውዝግቡ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ላይ መወያየታቸው ተሰምቷል።

በውይይቱ መጨረሻም " ቀጠናው የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ ከሁሉም አካላት ጋር መገናኘታችንን እንቀጥላለን " ሲሉ ሲንግኦይ ተናግረዋል።

የናይሮቢ መፍትሄ ተቀባይነት ካገኘ ኢትዮጵያ የተረጋጋ እና ተገማች የባህር ሀብት ተደራሽነን ስለሚሰጥ የንግድ ስራዋን ያለምንም እንቅፋት እንድትፈጽም እንደሚያደርግ እና የሶማሊያን የግዛት አንድነት እንደሚያከብርም አክለዋል።

ኮሪር ሲንግኦኢ ፥ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ሃሳቡን እያጤኑበት ነው ያሉ ሲሆን " መሪዎቻቸው ሂደቱን ወደፊት ለማራመድ ተገናኝተው እንዲመክሩበት ተጠይቀዋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የሮይተርስ / ዶቼ ቨለ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ከፖሊስ አባላት ጋር ቶክስ በመክፈታቸው የተነገረላቸው የፋኖ መሪዎችና አባላት መገደላቸውን ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ፤
- ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣
- አቤኔዜር ጋሻው አባተ
- ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት " ፋኖ " ቡድን አባላት በከተማው " የሽበር ጥቃት ለመፈፀም እየተንቃሰቀሱ " መሆኑን የፀጥታ አካላት ባደረጉ ክትትል እንደደረሱባቸው ገልጿል።

ዛሬ " ሚሊኒየም አዳራሽ " አካባቢ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ " እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም ተኩስ መክፈታቸውን " አመልክቷል።

በዚም ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት አቤነዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጡ መሃል  መገደሉን ገልጿል።

ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በነበረው የተኩስ ልውውጥ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ቆስለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የፈኖ አባለቱ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበርም በማለታቸው  እንደገደሏቸው አመልክቷል።

አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ ከፖሊስ አባላት ጋር ቶክስ በመክፈታቸው የተነገረላቸው የፋኖ መሪዎችና አባላት መገደላቸውን ፖሊስ ገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ፤ - ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ - አቤኔዜር ጋሻው አባተ - ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት " ፋኖ " ቡድን አባላት በከተማው " የሽበር ጥቃት ለመፈፀም እየተንቃሰቀሱ " መሆኑን የፀጥታ አካላት ባደረጉ ክትትል…
“ በፀጥታ ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር የለም ” - አዲስ አበባ ፓሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ በፋኖና በፓሊስ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አንድ ሲቪልና ሁለት ታጣቂዎች ሲገደሉ፣ በሁለት የፓሊስ አባላት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የ“ፋኖ” አመራርና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሚሊኒየም አዳራሽ አጠገብ ከፀጥታ አካላት ተኩስ እንደከፈቱ፣ በ “ፋኖ” በኩል ሁለት ታጣቂዎች ሲገደሉ አንድ በቁጥጥር ስር እንደዋለ፣ በመንግሥት በኩል ሁለት የፓሊስ አባላት ላይ ጉዳት እንደደረሰ፣ በንጹሐን በኩል ደግሞ አንድ አሽከርካራ እንደተገደለ፣ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡት ቃል፣ “ የተገደሉት የ “ፋኖ” ቡድን አመራርና አባላት ናቸው። አመራሩ ናሁሰናይ አንዳርጌ ነው። ሌላው አቤኔዘር ጋሻው የተባለው ነው፣ እዛው ቦታው ላይ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሂወቱ አልፏል። ሀብታሙ አንዳርጌ ግን ምንም አልሆነም በቁጥጥር ስር ውሏል ” ብለዋል።

የ “ፋኖ” አመራርና አባላት የነበራቸውን እንቅስቃሴ ሲያስረዱም ኮማንደሩ፣ “ በከተማው ውስጥ ነው የሚንቀሳቀሱት የነበረው። በከተማው ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ጥፋቶች ለማጥፋት ነው እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበረው ” ነው ያሉት።

አክለውም፣ “ እነርሱን ለመያዝ በተደረገው ሂደት ቦሌ ወረዳ 3 ሳጅን አራርሳ ተሾመና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ የሚባሉ ሁለት የፓሊስ አባላት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ከእነርሱ (“ፋኖ”) በተተኮሰ ጥይት ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ እሱም ብቻ አይደለም አንድ አሽከርካሪ እንዲጭናቸው ሲያስገድዱት ‘አልተባበርም’ ስላለ መኪና ውስጥ በጥይት መትተውት ሞቷል። የአንድ ግለሰብ ተሽከርካሪ መስታውት በጥይት መትተውታል። ሙሉ ለሙሉ ጉዳት ደርሶበታል። ሰውየው ግን ምንም የሆነው ነገር የለም ” ነው ያሉት።

“ ማኀበረሰቡ ከፓሊስና ከፀጥታ አካላት የሚተላለፉ መረጃዎችን በቁም ነገር ማዳመጥ፣ አካባቢውን ማዬት መቻል አለበት። በሰላምና በፀጥታ ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር የለም። እነዚህ ሰዎች መካከላችን አሉ። ይሄ አንዱ ማሳያ ነው። ቦሌ መሀል ከተማው ላይ እንግዲህ እየኖሩ ነው የነበረው ” ብለዋል ኮማንደር ማርቆስ።

“ እነዚህ ሰዎች መንፈስ አይደሉም። በተሽከርካሪያቸው ሲወጡ ሲገቡ ይታያሉ። ግን ፓሊስ በራሱ ነው ሲከታተተል የነበረው ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፤ አሁንም ማህበረሰቡ አካባቢውን መጠበቅ አለበት ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ባህር ማዶ ከሚኖር ወዳጅ ዘመድ በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሃዋላ በኩል እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ሲቀበሉ 20% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፤ የዕድል ጨዋታ በመጫወት የአየር ሰዓት ይሸለማሉ!

ለተጨማሪ መረጃ ማስፈንጠሪያውን bit.ly/3ArwoEO ይጫኑ

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
የኤርትራ መንግሥት 46 እስረኞችን ለቀቀ።

በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ #ኤርትራ ተወስደው በኤርትራ መንግሥት ታስረው ከነበሩ የትግራይ ተወላጆች ውስጥ 46ቱ በዛሬው ዕለት ተለቀው ሽራሮ ከተማ ገብተዋል።

የሽራሮ ከንቲባ አቶ ሙሉ ብርሃነ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድርገጽ በሰጡት ቃል ፥ እስረኞቹ በኤርትራ የጋሽ ባርካ ዞን መቀመጫ በሆነችው የባረንቱ ከተማ ታስረው የቆዩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ዛሬ ጠዋት በ”አይሱዙ” ተሽከርካሪ ተጭነው ሽራሮ እንደገቡ ተናግረዋል።

በእስር ላይ የቆዩት የትግራይ ተወላጆች “ ምህረት ተደርጎላቸው ” የተለቀቁ ሲሆን ይህም በኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት እና በኤርትራ ሰራዊት መካከል ሲካሄድ በቆየ ንግግር መሆኑን ከንቲባው ገልጸዋል።

እስረኞቹ ተለቅቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው፤ በጦርነቱ ጊዜ “ ከባድ የሆነ ወንጀል ያልፈጸሙ ናቸው ” በሚል ምክንያት ነው።

በኤርትራ እስር ላይ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች መካከል አሁንም ያልተፈቱ አሉ።

የዛሬው እርምጃ የቀሩትም እንደሚለቀቁ “ ተስፋ ሰጪ ነው ” ሲሉ የሽራሮ ከተማ ከንቲባ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@tikvahethiopia