TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ። ፓርቲው በግድያው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። " በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና…
#Update #MNO

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአቶ በቴ ኡርጌሳን ግድያ በፅኑ #እንደሚያወግዝ ገለጸ።

በወንጀሉ ዙሪያ ተገቢው ምርመራ እንደሚደረግና ውጤቱ ለህዝብ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ የኦነግ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ በመቂ ከተማ #ባልታወቁ_ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን ገልጿል።

" ይህ በማንኛውም መንገድ በየትኛው አካል ይፈፀም ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ያለው የክልሉ መንግሥት ግድያውንም " በፅኑ አወግዛለሁኝ " ሲል አሳውቋል።

" ምንም እንኳን መንግሥት ከአቶ በቴ ኡርጌሳ ጋር የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረውም ከግድያው ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር የለም " ሲል ገልጿል።

ምርመራ ባልተደረገበት ሁኔታና ወንጀል ፈጻሚው ገና ባልታወቀበት ሁኔታ  ክስተቱን ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ የሚጠቀሙ ኃይሎች መኖራቸውን በማመልከት አጥብቆ አውግዟቸዋል።

" ከመንግስት ጋር የአቋም ልዩነት ስላላቸውና የፖለቲካ አቋማቸው ስለሚለይ ብቻ ግድያው በመንግሥት አካል እንደተፈፀመ ተደርጎ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፥ " የፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን ለግድያው ተጠያቂ በማድረግ ይህንን ሁኔታ ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው " ሲል ወቅሷል።

መንግሥት በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ባወጣው መግለጫ ቃል ገብቷል።

የፀጥታ ኃይሎች የግድያውን ፈፃሚ በህግ አግባብ መርምረውና አጣርተው እስካላሳወቁ ድረስ " ይህ አካል ነው ኃላፊነት የሚወስደው " ብሎ መናገር እንደማይቻል ጠቁሟል።

ማህበረሰቡ ገና ውጤቱ ሳይታወቅ እየተካሄዱ ካሉት " እከሌ ነው የገደለው " ከሚሉ ፕሮፖጋንዳዎች ራሱን መጠበቅ አለበትም ብሏል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" እስሮች እንዳሉ መረጃዎች እየደረሱን ነው " - ኢሰመኮ

" ምናልባት ወንጀል ፈጽመው ሊሆን ይችላል " - የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምክንያቱ በትክክል ባልታወቀ ጉዳይ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት አማካኝነት አፈሳና እስር እየተከናወነ መሆኑ እየተነገረ ነው።

ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰዎች እየታፈሱ ወደ ፖሊስ ጣቢዎች እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን እንዲሁም የታሰሩትን ለመልቀቀ የገንዘብ ድርድር የሚያደርጉ የፀጥታ አካላት እንዳሉ እና በገንዘብ ተደራድረው የተፈቱ ስለመኖራቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ተነግሯል።

ስልክ አስከፍተው የሚበረብሩ እና ውስጡ ባሉት የተለያዩ ይዘቶች " እናተ ተልዕኮ አላችሁ " በሚል የሚታሰሩ እንዳሉም ተገልጿል።

የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትም ለእስር እየተዳረጉ ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም እየተፈጸመነ ነው የተባለውን የአፈሳና እስር ጉዳይ ሰምቶ እንደሆን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን የጠየቀ ሲሆን ፣ አንድ የኮሚሽኑ አካል በሰጡት ቃል ፤ " በከተማው እስሮች እንዳሉ መረጃዎች እየደረሱን ነው " ብለዋል።

አክለውም " ሰዎቹ የታሰሩበትን ጉዳይ ለማጣራት አዲስ አበባ ላይ ከሚሰራው የእኛ ቲም ጋር እየተነጋገርን ነው። አሁን ላይ የተረጋገጠ መረጃ የለም። በተለመደው ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች ሲኖሩ ክትትል ነው የምናደርገው ፣ አሁንም እሱን ነው የምናደርገው " የሚል ቃል ሰጥተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንንም ጠይቋል።

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " ምናልባት ወንጀል ሰርተው ሊሆን ይችላል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" የታሳሪ ቤተሰቦች በርካቶች ሰዎች ታሰሩባቸው በተባሉ ጣቢያዎች፣ ገብተው የሥራ ኃላፊዎችን ያነጋግሯቸው። የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ የሚሰጡ ይሆናልም " ብለዋል።

ኮማንደር ማርቆስ፣ " ምናልባት ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ ወደ ኮሚሽኑም (አዲስ አበባ ፓሊስ) መምጣት ይችላሉ። " ሲሉ ጠቁመዋል።

አክለውም ፣ " ምንድን ነው ? የሚለውን ነገር ቼክ ማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ ቢሯችን ሁሌም በማንኛውም ሰዓት ክፍት ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

(ጉዳዩን በተመለከተ ከፓሊስም ሆነ ከኢሰመኮ የሚሰጥ ተጨማሪ ምላሽ ካለ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahethiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#አውሮፓ

የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን #የስደተኞች እና #የጥገኝነት ደንቦችን የሚያጠናክር ትልቅ ማሻሻያ አጽድቋል።

የአውሮፓ ህብረት የጥገኝነትና ፍልሰት ስምምነት ከ2015 ጀምሮ ሲመከርበት የቆየ ሲሆን በ2 ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

አዲሱ ሕግ ምን ይዟል ?

➡️ የጥገኝነት ሂደት ጥያቄ #ያፋጥናል ፤ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ #ያስገድዳል

➡️ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎችን ኃላፊነት እንዲጋሩ ያደርጋል።

➡️ የአውሮፓ ህብረት 27 አባል አገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከጣሊያን፣ ግሪክ እና ስፔን ካሉ " #የድንበር " አገራት እንዲወስዱ ወይም በምትኩ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያደርጋል።

➡️ ዝቅተኛ ተቀባይነት የማግኘት እድል ያላቸው የጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አውሮፓ ህብረት ግዛት ሳያስገቡ ጉዳያቸው በፍጥነት መታየት አለበት ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄዎች ቢበዛ በ12 ሳምንታት ውስጥ እንዲያልቁ ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ #በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው  ይላል።

➡️ ስደተኞች ከመግባታቸው በፊት ባሉ በ7 ቀናት ውስጥ ጠንከር ያለ የማጣራት ሂደት ይደረግላቸዋል። የጤና እና የደህንነት ፍተሻዎችን ይጨምራል።

➡️ ከ6 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ማናቸውም ስደተኞች የባዮሜትሪክ መረጃ ይሰበሰባል። ስደተኞች ቁጥር በአጋጣሚ ካሻቀበም ምላሽ የሚሰጥበት አሠራር ተዘርግቷል።

ምንም እንኳን አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አገራት የተወሰኑ የስምምነቱን ክፍሎችን ቢቃወሙም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በሚደረግ ድምጽ አሰጣጥ የአብዛኛውን ይሁኝታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው አመት 380 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የአውሮፓ ህብረትን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ አቋርጠዋል። ይህም እ.አ.አ ከ 2016 ወዲህ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

ስለ ሕጉ ምን ተባለ ?

#ጀርመን፦ የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ “ ታሪካዊና አስፈላጊ እርምጃ ” ብለውታል።

#የአውሮፓ_ፓርላማ፦ የፓርላማው ፕሬዝዳንት ሮቤታ ሜሶላ “ በአብሮነት እና በኃላፊነት መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቋል ሁሉንም ነገር በአንድ ጀምበር ባይፈታም ግን 10 ግዙፍ እርምጃ የተጓዘ ነው " ብለዋል።

#ሀንጋሪ ፦ ምንም አይነት የስደት ስምምነት ቢደረስ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን አልወስድም ብላለች።

#ፖላንድ ፦ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መውሰድ አልያም ለድንበር አገራት ገንዘብ መክፈል የሚለውን ሃሳብ " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

#ስሎቫንያ፦ “ ልንሰራበት የምንችለው ስምምነት ነው ” ስትል ደግፋለች።

#ቤልጂየም፦ “ ፍፁም አይደለም (ሕጉን) ግን እንደግፈዋልን ” ስትል አሳውቃለች።

#ፈረንሳይ ፦ ፕ/ት ኢማኑኤል ማክሮን ድጋፍ ሰጥተዋል። የፈረንሣዩ ቀኝ አክራሪ ናሽናል ራሊ አባል ጆርዳን ባርዴላ ስምምነቱ “ #አስፈሪ ” ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

#አምነስቲ_ኢንተርናሽናል ፦ ስምምነቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ “ከፍተኛ ስቃይ” የሚመራ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚነሳው አንዱ ተቃውሞ ዝቅተኛ ተቀባይነት የሚኖራቸው #ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው በድንበር #መግቢያዎች ላይ ወይም #በማቆያ_ስፍራዎች እንዲስተናገዱ በማድረግ ፍትሃዊ ዕድል የማግኘት ተስፋቸውን ያመነምነዋል የሚል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#ወጋገን_ባንክ

አጓጊው ቀን ደረሰ ‼️

ወጋገን ባንክ ባዘጋጀው የጥያቄና መልስ ውድድር ጠቀም ባሉ አጓጊ ሽልማቶች ሊያንበሸብሽዎ ነው!

ታዲያ ምን ይጠብቃሉ!! አሁኑኑ ከስር የተቀመጡትን የወጋገን ባንክ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል እና የፌስቡክ ገፅ ሊንኮች ተጭነው በመቀላቀል እና ጥያቄዎችን አስቀድመው በመመለስ አጓጊ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ!

👉ቴሌግራም https://t.iss.one/WegagenBanksc

👉ፌስቡክ https://m.facebook.com/bankwegagen/

ልብ ይበሉ ይፋዊ የባንካችንን ገፆች በመቀላቀል እና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ በመጋበዝ ለወራት በሚቆየው የጥያቄ እና መልስ ውድድር በመሳተፍ አሸናፊ ሲሆኑ አጓጊ እና ጠቀም ያሉ ሽልማቶችን ከባንካችን ይረከባሉ ‼️
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል💥

👉 እነዚን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ልዩ ቻናል 240 እንዲሁም ልዩ2 ቻናል 239 ይመልከቱ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#EthiopianPremierLeague #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfService #DStvEthiopia
#Hawassa

➡️ " እህታችንን የጠለፋት ግለሰብ ወደ ፓሊስ እንዳንሄድ በእህታችን ህይወት እያስፈራራን ነው " - የተጠላፊዋ ውድነሽ ማቲዎስ ቤተሰቦች በእንባ የታጀበ መልእከት

➡️ " ቆየት ብዬ ዝርዝር መረጃ ሰጣችኃለሁ " - ፖሊስ

ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ ነው። ስሟ ውድነሽ ማቲዮስ ይባላል።

በቀን 28/07/2016 ቅዳሜ ምሽት ከቤት " ሰው ይጠራሻል " ተብላ እንደወጣች አልተመለሰችም።

ቤተሰቦቿ ከፖሊስ ጋር ሆነዉ ትገኛለች ብለው ያሰቡበትን ሁሉ ሲያስሱ ቢቆዩም ሊያገኟት አልቻሉም።

በመጨረሻ ያለችበትን ሁኔታ ገልጾ " ተረጋጉ " የሚል መልእክት ያስተላለፈ የስልክ ጥሪ ደረሳቸው። በዚህን ወቅት ነው መጠለፏን ያወቁት።

የተጠላፊዋ ወንድም ዘላለም ማቲዮስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ስልክ ደውሎ #ከማስፈራሪያ ጋጋታ ጋር የመጠለፏን ዜና ጠላፊው ራሱ አሰማን " ብለዋል።

" ይህ አያሌው ጌታሁን የተሰኘ ግለሰብ ሀዋሳ በሚገኘዉ መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ተከራይታ በምትኖረዉ እህቱ በኩል የአብረን እንሁን የሚል የፍቅር ጥያቄ ሲያቀርብ እንደነበር እናውቃለን " ሲሉ የታጋቿ ወንድም ገልጸዋል።

" ጥያቄዉ ' ፍቅረኛ አለኝ ' በሚል ምክኒያት አወንታዊ ምላሽ አለማግኘቱን ተከትሎም  ከእሷ ባለፈ የፍቅር ጓደኛዋን ሁሉ ሲያስፈራራ ቆይቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ ሙከራዉን ጨምሮ ብዙ መንገዶች ቢሞክርም አልሳካ እንዳለዉ ሲረዳ በመጨረሻም ከእህቱ ጋር ተጋግዞ ጠለፋዉን ፈጽሟል " ሲሉ አስረድተዋል።

" አሁን ላይ ወደፖሊስ በመሄድ ሁኔታዉን አሳዉቀን ክስ ለመመስረት እንቅስቃሴ ጀምረናል " የሚለዉ የታጋቿ ወንድም " ከአጋቹ ባለፈ ተባባሪ ለነበረችው እህቱም  ላይ መጥሪያ አዉጥተናል " ብሏል።

" አሁን ላይ ወላጆቻችን በታላቅ ለቅሶና ሀዘን ውስጥ ናቸዉ የሚመለከተዉ አካል ህግ አስከብሮና ጥፋተኛዉን በመያዝ ልጃችንን ያስመልስልን " ሲል ተማጽኗል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዡን ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን አነጋግሯል።

አዛዡ ጉዳዩን በጥብቅ እየተከታተሉት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ቆየት ብለው እንደሚያሳዉቁን ቃል ገብተዋል።

በቀጣይ የኢንስፔክተሩን ዝርዝር ሀሳብ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተካተቱበት መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

መረጃውን አዘጋጅዮ የላከው የሀዋሳው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘትና እውነቱን ማወቅ ነው " - የአቶ በቴ ኡርጌሳ ቤተሰብ

የአቶ በቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።

ስርዓተ ቀብራቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ ዘመዶቻቸው በርካታ ሰዎች ፣ ወዳጆቻቸው በተገኙበት ዛሬ በመቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው የተፈፀመው።

አንድ ቀላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡ የቤተሰብ አባል ፤ " ያው እንደ በቴ ከዚህ በላይ ብጠበቅም ብዙ ሰው ከሩቅም ከቅርብም መጥተው ስርዓተ ቀብራቸው ላይ ተገኝተው ቤተሰብም ቀብሩን ፈጽመው በሰላም ወደ ቤት ተመልሰዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

በትውልድ ከተማቸው መቂ ስርዓተ ቀብራቸው የተፈጸመው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ማክሰኞ ሌሊት ተገድለው ትናንት ማለዳውን አስከሬናቸው ከመቂ ወደ ባቱ መውጫ መንገድ ላይ ተጥሎ መገኘቱ ይታወቃል።

የቤተሰቡ አባል ፤ " የበቴ አስክሬን ትናንት ጠዋት በአከባቢው ማህበረሰብ እና ቤተሰቦቻቸው ከመንገድ ተነስቶ ወደ ቤት ከተወሰደ በኋላ፤ ዛሬ ጠዋት ወደ አከባቢው ሆስፒታል በመውሰድ የአስከሬን ምርመራ ተደርጎለት ነበር፡፡ " ብለዋል።

" ቤተሰብ እንደ ትልቅ ነገር ያየው አንዴ የሞተውን ልጃቸውን ወስደው በስርዓቱ ቀብሩን መፈጸም ነው፡፡ ዛሬ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ አስከሬኑ እንዲመረመር የሆነው #በህግ_አዋቂዎች ምክር ነበር፡፡ ፖሊስ አስከሬኑን ወደ ምርመራ ባይወስድም ትናንት ጠዋት መረጃዎችን አሰባስቦ ሄዷል " ሲሉ ገልጸዋል።

እኚህ የቤተሰብ አባል በአቶ ቤተ አስከሬን የተለያዩ የሰውነት አካል ላይ በርካታ ያሉት ቦታ ላይ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የሚያመላክት ብዙ ቁስሎች በአይናቸው መመልከታቸውን አስረድተዋል፡፡

" የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘት እና እውነቱን ማወቅ ነው " ብለዋል።

" ቤተሰብ የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ በፍርድ ሂደት ፍትህ ቢገኝ ቤተሰቡንም የአከባቢውንም ማህበረሰብ የሚያረካ ጉዳይ ነው " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

በግፍ ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ተጥሎ የተገኘው የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳ ባለትዳርና የ4 ልጆች አባት ነበሩ።

@tikvahethiopia