TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GlobalBankEthiopia

ማንችስተር ሲቲ ወይስ አርሰናል

በመገመት የሚያሸልም ጥያቄ በኢንስታግራም ገጻችን (https://bit.ly/3NiRHOn ) ብቻ ግምትዎን ይስጡ!

በፕሪሚየር ሊጉ በጉጉት ከሚጠበቁት ጨዋታዎች መካከል አንዱ የፊታችን እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በማንችስተር ሲቲ እና በአርሰናል መካከል ይካሄዳል፡፡ ጨዋታውን በትክክል ለሚገምቱ 3 የኢንስታግራም (https://bit.ly/3NiRHOn) ተከታዮቻችን ለእያንዳንዳቸው የ300 ብር የካርድ ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡

1. የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የኢንስታግራም ገጽን https://bit.ly/3NiRHOn ገፅ መከተልዎን አይዘንጉ!
2. ትክክለኛ መላሾች ከ 3 በላይ ከሆኑ አሸናፊዎቹን የምንለየው በዕጣ ይሆናል፡፡

መልካም ዕድል!!
ግሎባል ባንክ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትክክለኛ ፍትህ እንሻለን " - የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ ቤተሰቦች

ላለፉት 5 ወራት በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞዉ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር  ጸጋዬ ቱኬ ቤተሰቦች ፥ " በፍትህ እጦት እየተንገላታ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።

የቀድሞው ከተንቲባ ወንድም እንደሆኑ የገለጹት አቶ አስፋዉ ቱኬ ፤ " ወንድሜ በፍትህ እጦት እየተንገላታ ነው " ያሉ ሲሆን  " በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ምን ያክል ህዝባዊ አመራር እንደነበርና ከሙስና የጸዳ ሰው እንደሆነ ሙሉ የሲዳማም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቃል " ብለዋል።

" በዚህ ንጽህናዉ ስለሚተማመንም ነበር ከሀገር ከወጣ በኋላ ወደሀገር ተመልሶ ለእስር የተዳረገው " ሲሉ አክለዋል።

አቶ አስፋው ፥ " ላለፉት አምስት (5) ወራት ፍትህ ተስተጓጉሎበትና የህክምና አገልግሎት አጥቶ ከፍርድ ቤት ፍርድ ቤት እየተመላለሰ ነው " ያሉ ሲሆን " አሁን ላይ የቀረበበት ክስም እሱ ከሀገር በወጣበት ወቅት በተወሰደዉ የመንግስት ቤት ውስጥ በነበሩና ጠፉ በተባሉ  ተራ የምንጣፍና የመጋረጃና መሰል የቤት እቃዎች ተጠያቂ መሆኑ እሱን በእስር ለማቆየት ብቻ የታሰበ ይመስላል "  ብለዋል።

" ከመምህርነት አንስቶ ሀዋሳ ከተማን በከንቲባነት ባገለገለበት ወቅት ያሳያቸዉ ቀና የህዝብ ፍቅር የልማት ወጤቶችና የመልካም አስተዳደር ፍሬዎች እንዲሁም በከተሞች መድረክ ያሳየዉ ከፍተኛ ውጤት በሲዳማም ሆነ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የሚያስመሰግኑትና የሚያሸልሙት እንጅ የሚያሳስሩት አልነበሩም " ብለዋል።

አቶ አስፋው ቱኬ ፥ ወንድማቸው በጤና ችግር እየተሰቃዩ እንደሆነ በመግለጽ ቤተሰቡ ትክክለኛ ፍትህ እንደሚሻ ፤ የሚመለከተው አካል ሁሉ ይሄን ተማጽኗቸው እንዲሠማ ጥሪ አቅርበዋል።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ጸጋዬ ቱኬ ፥ በስልጣን ጊዜያቸው በሙስና ወንጀል እንዲሁም በከተማው ውስጥ ብልሹ አሰራር እንዲንሰራፋ አድርገዋል በሚል ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገው መታሰራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በየጊዜው እየተፈፀሙ ያሉት #ጎራን_የሚለዩ ግድያዎች ፣ ጥቃቶች አሁን ካለው የከፋ ነገር ይዘው እንደይመጡ ፦
➡️ ሳይረፍድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው
➡️ ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ
➡️ ለተበዳይ ወገኖችም ፍትህ መስጠት እንደሚገባ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች አሳስበዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ የክልሉ ነዋሪ ፥ " በየጊዜው እየተፈፀሙ ያሉት ግድያዎች የከፋ መዘዝ ይዘው ሊመጡ የሚችሉ ናቸው ስለዚህ ጠንካራ መፍትሄ ይፈልጋል " ብለዋል።

ከግድያ ባለፈም የሚፈፀሙ የወንጀል ተግባራት ደህንነትን የሚነሱ ናቸው ሲሉ አክለዋል።

ነገ እርስ በእርስ ሰዎች እንዳይጠፋፉ አሁን ያለው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደረስ መድረግ አለበት ብለዋል።

ሌላኛው ቃላቸው የሰጡ ነዋሪ ፥ በዚህ ወር ብቻ ሰዎች በተለያዩ ስፍራዎች ተገድለዋል ብለዋል።

በጋምቤላ አንድ የትራፊክ አባል " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ሰዎች በጥይት ከተመታ በኃላ ችግሮች እየተባባሱ ሄደው በፍራቻ ምክንያት በከተማው እንቅስቃሴ እስከመስተጓጎል ደርሶ እንደነበር ገልጸዋል።

በአቦቦ ወረዳ ደግሞ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ቢያስን 3 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀድምም እዚሁ ወረዳ ግድያ ተፈፅሞ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከቀናት በፊት ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ባለው መስመር ህዝብ ጭኖ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 5 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳም ግጭቶች እንደነበሩ ጠቁመዋል።

" እየተፈፀሙት ላሉ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች  ተጠያቂነት ሲረጋገጥ እያየን አይደለም " ብለው ችግሩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ሌላው መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የክልሉ ነዋሪ ፥ " በቀን 18/7/2016 ከተርፋም ወደ ጋምቤላ መስመእ የህዝብ ማመላለሻ መኪናን ታጣቂዎች መትተውት እስካሁን የሰው ህይወት አልፏል ፣ የተጎዱም ሆስፒታል ገብተዋል " ብለዋል።

እኚሁ ነዋሪ ጥቃቱ የተፈፀመ ከተርፋም ወደ አቦል ሲቃረብ ቢያንስ 7 ኪ/ሜ እንደሆነ አስረድተዋል።

አቦል የምትባለው ወረዳ ላይ ዝርፊያና ግድያ በተደጋጋሚ እንደሚፈፀም ጠቁመዋል።

ነዋሪው ፥ ባለፈው ሳምንት አንድ  የትራፊክ ፖሊስ መሀል አደባባይ ላይ በባጃጅ በመጡ ሰዎች በጥይት ከተመታ በኃላ ነገሮች መባባሳቸውን ጠቁመዋል።

ሌላው በክልሉ ያለው ችግር የሚያጠፉ ሰዎች በህግ አለመጠየቃቸው ነው ያሉት ነዋሪው " የህግ የበላይነት የሚባለው ነገር ጠፍቶል " ሲሉ ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ አስረድተዋል።

ነዋሪዎቹ ጋምቤላ ክልል ያለው ሁኔታ ቸል የሚባል ስላልሆነ የፌዴራሉም መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥበት አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፥ ጋምቤላ ክልል እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር  ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት ነው የፌዴራል እና የክልል ፀጥታ አመራሮች ውይይት የተካሄደው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሸነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ፥ አንዳንድ ግለሰቦች ጎራ እየለዩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ ማፈናቀልና የተለያዩ ጉዳቶችን እያደረሱ እንዳሉ መገምገሙን ተናግረዋል።

ችግር ፈጣሪዎችም በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።

የፌደራል ፖሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ አካላት የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ ወደ #ኦፕሬሽን_ገብተው ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ ይገኛሉ ብለዋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ፤ ፒያሳ የሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት (ተርሚናል) መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ ፥ " ህብረተሰቡ ደህንነቱ ተጠብቆ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኝበትን የከተማ አውቶብስ #ተርሚናል አስጀምረናል " ብሏል።

ቀድሞ በፒያሳ እና አከባቢው ሲሰጡ የነበሩ አስር የከተማ አውቶብስ መስመሮች ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ገብተው በአንድ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ ተጠቁሟል።

ህብረተሰቡ በሙዚየሙ በ " ምስራቅ ጀግኖች በር "  በመግባት ወደ ፦
- አየር ጤና፣
- ካራ ቆሬ፣
- ቦሌ ቡልቡላ፣
- ሳሪስ፣
- ኮልፌ ቀራኒዮ፣
- አጃምባ፣
- ጀሞ 3፣
- ሃና ማርያም፣
- ቱሉዲምቱ
- ዩኒሳ የሚሄዱ የብዙሃን ትራንስፖርት (አውቶብስ) ማግኘት እንደሚችል የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ጠቁሟል።

@tikvahethiopia
#መቐለ

በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ፥ ዘስላሴ ቀበሌ ቀጠና 14 በሚገኘ " እየሩሳሌም " በተባለ ሆቴል እፍሬም ፍትዊ ገ/ክርስቶስ የተባሉ ግለሰብ በመኝታ ክፍል ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን የክ/ከተማው ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ መጋቢት 20/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ነው በያዙት የመኝታ ክፍል ውስጥ ሞተው የተገኙት።

የአሟሟታቸው ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችል የአስክሬን ምርምራ በዓይደር ሆስፒታል በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የሟች ቤተሰቦች እስከ መጋቢት 22 /2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ ወደ ፖሊስ ሪፓርት ካላደረጉ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ከአስከሬን ምርመራ በኃላ የቀብር ስነ-ሰርአት ለመፈፀም እንደሚገደድ ፖሊስ አመልክቷል። (104.4 የመቐለ ኤፍኤም ሬድዮ)

#TikvahFamilyMekelle
        
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ገንዘቡን እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ስም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል። ባንኩ ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት በህገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቦ ነበር። በዚህ መሰረት 9281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን…
#CBE

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ #የራሳቸውን_ያልሆነውን ገንዘብ ከባንኩ ወስደው ሙሉ በሙሉ ያልመለሱ (በከፊል የመለሱ) 5166 ግለሰቦች የሚቀረውን ብር እንዲመልሱ የሰጠው የመጨረሻ ቀነ ገደብ ዛሬ ቅዳሜ 11:00 ላይ ያበቃል።

ባንኩ ፤ ገንዘቡን #የማይመልሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ፦
- ሙሉ ስማቸው
- ፎቷቸው
- በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመግለፅ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት እንዲሁም ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አሳስቦ ነበር።

ባንኩ ከቀናት በፊት ፤ ገንዘብ ወስደው ጭራሽ ያልመለሱ 565 ደንበኞቹንና በከፊል መልሰው የሚቀር ገንዘብ ያልመለሱ 5166 ደንበኞቹን ስም ዝርዝር ይፋ ማድረጉ ይወሳል።

በሌላ በኩል ፤ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወሰዱትን እና ወደ ግል ባንኮች ያዘዋወሩትን ገንዘብ በዲጂታል መንገድ ወደ ንግድ ባንክ ቢመልሱም ገንዘብ ካልመለሱት ጋር ስማቸው መውጣቱን በመግለፅ ንግድ ባንክ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ንግድ ባንክ ዓርብ በመጋቢት 6 / 2016 ለሊት በ25,761 ደንበኞች ከ801 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ እንደተወሰደበት ከዛ ውስጥ 622 ሚሊዮን ያህሉን ማስመለሱን ከ4 ቀን በፊት መግለጹ ይወቃል።

@tikvahethiopia
የተረክ በM-PESA የመጨረሻው 6ኛ ዙር እድለኞች ሽልማቶቻቸውን ተረክበዋል ፤ መኪናዋን የምዕራብ አርሲ አሳሳ ደንበኛችን ፣ የጅግጅጋው ነጋዴ ፣ባጃጇን ከዲላ ፣ከሐረር አራተኛ ፣ከእንጅባራ ወስደዋታል!

ስለነበረን የተረክ በM-PESA ወራት ወሳኞቻችንን ከልብ እናመሰግናለን ፤ በዚህ አናበቃም እንቀጥላለን ፤ በአብሮነት ወደፊት!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom
#TerekBeMPESA #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ? ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው…
#ትግራይ #አማራ

" እኔ #ከሪፈረንደም ውጭ መፍትሄ ያለ አይመስለኝም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትግራይ እና አማራ በኩል ላለው ችግር " ዘላቂው መፍትሄ ህዝባዊ ሪፈረንደም " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅለይ ሚኒስትሩ ፥ ከዚህ ቀደምም በትግራይ እና አማራ ላለው ችግር ዘላቂ መፍትሄ " ህዝቡ ህዝበ ውሳኔ ሲያደርግ " እንደሆነ በተደጋጋሚ እንደተናገሩት ጠቁመዋል።

" የሆነን ሰዎች እዛ ተቀምጠው ፣ እዛ ተቀምጠው ሲናገሩ አይደለም። ህዝቡን መልሰን ህጋዊ በሆነ መንገድ ዓለም እያየው ሪፈረንደም አድርገው ወደሚፈልጉት ቢጠቃለሉ ከዚያ በኃላ ለጥያቄ አይመችም " ብለዋል።

" አሁን ላይ ግን ሪፈረንደም የሚባል ነገር አይፈልገም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " እራሱ ነዋሪው ሳይሆን ሌላ ሰው ነው መወሰን የሚፈልገው እዚህ እየመጣ ጥያቄ ያቀርባል ' አልተፈታም ' እያለ እኔ ደግሞ አቅጣጫ አስቀምጫለሁ እንዲፈታ " ሲሉ ተናግረዋል።

እሳቸው ያስቀመጡት አቅጣጫ በመጀመሪያ የተፈናቀውለው ህዝብ እንዲመለስ ከዛ ህዝቡ እንዲወስን (ሪፈረንደም እንዲያደርግ) መሆኑን ተናግረዋል።

" ሪፈረንደም ከተደረገ በኃላ ህዝቡ የወሰነውን እናክብርለት ፤ እኔ እዚህ ሆኜ መወሰን አልችልም " ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ " በትግራይ በኩል ስናነጋግር ያለው ናሬሽን እና በአማራ በኩል ስናነጋግር ያለው ናሬሽን በጣም የተራራቀ ነው ምንም የተቀራረበ አይደለም ለማቀራረብ የሚቻለው ህዝቡ እራሱ ሲወስን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ (ሪፈረንደም) ውጭ ለጊዜው ሌላ #መፍትሄ ያለ እንደማይመስላቸውም ገልጸዋል።

" ህዝቡ እንዲወስን ከተደረገ የተረጋጋ አካባቢ ይፈጠራል " ብለዋል።

" እያባላን ያለው የቦታ ችግር አይደለም እኛን የሚያባላን እንደ ንብ ቀፎ ውስጣችን የሚጮኸው ጩኸት ነው እንጂ ሀገሩማ በቂ ነው ቢሰራበት ቦታዎቹ ክፍት ናቸው መንገድ የላቸው ፣ ቤት የላቸው ክፍት ናቸው ' አልገባሁም ገባሁ ' እንጨቃጨካለን እንጂ የቦታ ችግር የለም ቦታው ላይ የሚስራት ችግር ነው የሚያጨቃጭቀን " ብለዋል።

@tikvahethiopia