TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ ስፍራ ምን ተፈጠረ ? በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል የራያ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በትጥቅ የተደገፈ ግጭት እንደነበረ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል። የካቲት 6 / 2016 ዓ.ም የተቀሰቀሰው መጠነኛ ነው የተባለው ግጭት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥረት ሊቆም እንደቻለ ነው የተነገረው። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ…
" ችግሩ በሰላማዊ መንገድ የፌደራል መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲፈታ ፍላጎታችን ነው " - አቶ ኃይሉ አበራ

ከሰሞኑን #በአማራ እና #በትግራይ ክልሎች መካከል ተቀሰቀሰ የተባለውን ለአጭር ጊዜ የቆየ የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ በአማራ ክልል በኩል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ በአሁን ሰዓት በአማራ ክልል ስር እየተዳደረ ያለው የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ኃይሉ አበራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ኃይሉ አበራ ምን አሉ ?

- በባላ አቅጣጫ ማሮ በሚባል ቦታ ከእኛ ሚሊሻ ጋ ገጠሙ። ተመትተው ተመልሰዋል አሁን ላይ ቦታውን ለቀዋል።

- ወደ ሁለት ቀበሌዎች ወረራ ለማድርግ ሙከራ አድርገው ነበር። በመጀመሪያ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ ነበር እየተላለፈ የከረመው፣ አሁን ግን እሳቢያቸው የነበረው በወረራ ቦታውን ይዘው ‘እንደራደራለን’ አይነት፣ በተፈናቃይ ስም ግጭት መፍጠር ነው።

* የጉዳት መጠንን በተመለከተ ፦ " እኛ ጋር የደረሰ ጉዳት የለም። እነሱ ግን ሊያጠቃ የመጣ ምንጊዜም ተመትቶ ነው የሚሄደው። የተወሰኑት ተመተው ሂደዋል። " ብለዋል።

- አላማጣን፣ ኮረምን ለመውረር እንዲሁ በጡሩባ እና በጩኽት የሚለቅ ህዝብ መስሏቸው ነበር። ሕዝቡ ማዕበል ሆኖ ነው የወጣው ከዚህ በኋላ የሰላሙን ጥሪ የማይቀበሉት እና ሰላሙን የማይፈልጉት ከሆነ አሁን እኛ ህዝባዊ አድርገነዋል።

* የመፍትሄ ሀሳብን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ፦ " ችግሩ በሰላማዊ መንገድ የፌደራል መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲፈታ ፍላጎታችን ነው። 'አይ የለም ህዝቡ ወደ ሚፈልገው መሆን አይችልም፣ እኔ ብቻ ነኝ የምወስንልህ' የሚል እሳቤ የሚቀሳቀስ ከሆነ እሱ የሚቻል አይደለም። ፋሽኑም ግዜውም አልፎበታል። አሁን ላይ ወደ ኋላ የሚመልስ ኃይል የለም። Already ሁሉም ተደራጅቷአል። " ብለዋል።

- የትግራይ ፖለቲከኞችም ሀይ ሀይ የሚሉትን ዲያስፖራ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል። ' አይ የለም የትግራይ ሉዐላዊ ግዛት ' እያሉ በወረራ የያዙትን ቦታ 'በኃይል እናስመልሳለን' የሚሉ ከሆነ ግን ከዚህ በኋላ የሚኖረው ሕዝባዊ ነው። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው። በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ነው ሊፈጠር የሚችለው። ይህንን እንዲያስቡበት ነው የምናስገነዝበው።

- እኛ የማንንም መብት አንጋፋም የትኛውንም ሰው በማንነቱ ምክንያት የምናደርስበት ጉዳት የለም። ሊወርና ሊገድል ኃይል ከመጣ ግን ህዝብን መቆጣጠር አይቻልም። ስለዚህ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ከመሆናቸው በፊት ቆም ብለው ቢያስቡ ይሻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ/ም
አላማጣ

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia