TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://t.iss.one/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#ETHIOPIA #Eurobond

ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም።

ገንዘብ ሚኒስቴር የክፍያ መጠኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል እንደሚቻል ገልጿል።

ክፍያውን ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች በፍትሃዊነት እኩል ለማስተናገድ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #Eurobond ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም። ገንዘብ ሚኒስቴር የክፍያ መጠኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል እንደሚቻል ገልጿል። ክፍያውን ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች በፍትሃዊነት እኩል ለማስተናገድ ነው ብሏል። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #Eurobond

ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ በወቅቱ ያልከፈለችው ለምንድነው ?

ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም።

የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ የቀረበው ከ9 ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም ነበር።

ኢትዮጵያ ይህንን ቦንድ ሸጣ ከገዢዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘች ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው በ10 ዓመት ውስጥ ነው።

እስከዚያው ድረስ መንግሥት በዓመት ሁለት / 2 ጊዜ የሚፈጸም የ6.625 በመቶ ዓመታዊ ወለድ ለቦንዱ ገዢዎች ይከፍላል።

ኢትዮጵያ ባለፈው ሰኞ ዕለት 33 ሚሊዮን ዶላር ወለድ መክፈል የነበረባት ቢሆንም ክፍያውን ሳትፈጽም ቀናት አልፈዋል።

" የክፍያ መጡኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል ይቻላል ፤ ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች እኩል ለማስተናገድ ነው " - ገንዘብ ሚኒስቴር

የብድር ቦንዱን አስመልክቶ ትላንትና ከቦንድ ገዢዎች ጋር የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በነበሩበት ውይይት ተደርጎ ነበር።

ይህን በተመለከተ ገንዘብ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ኢትዮጵያ #የታኅሣሥ_ወርን ወለድ ያላስተላለፈችው ክፍያውን ለማዘግየት ወስና ነው። ይህም ለገዢዎቹ ተገልጿል።

- ኢትዮጵያ #ወለዱን_ለመክፈል የሚያስችል ገንዘብ አላት።

- ክፍያውን የማዘግየት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ሁሉንም የውጪ አበዳሪዎች በፍትሐዊነት ለማስተናገድ ሲባል ነው።

- አበዳሪዎች #በፍትሐዊነት ለመመልከት አለመቻል በዕዳ ሽግሽግ ላይ ከሌሎች የውጭ አበዳሪዎች ጋር የሚደረገውን ውይይት አደጋ ላይ ይጥለዋል። ወለዱ ቢከፍል መስተገጓጎል ሊያጋጥም ይችላል።

- በቅርቡ ከኦፊሴላዊ አበዳሪዎች ጋር የብድር ክፍያ ሽግሽግን በተመለከተ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- #የቦንድ_ገዢዎችን ጨምሮ ሌሎች አበዳሪዎችም ተመሳሳይ አይነት የብድር ክፍያ ማስተካከያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ከሁሉም አበዳሪዎች ጋር በሚኖር ግንኙነት ላይ #ወጥነት እና #እኩልነትን ለማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የብድር እፎይታ ....

* ኢትዮጵያ ላለባት ብድር #የብድር_እፎይታ ለማግኘት በ " ቡድን 20 " የጋራ ማዕቀፍ በኩል የዕዳ ሽግሽግ ለማድረግ ውይይት ስታካሂድ ቆይታ ነበር።

* ባለፈው ኅዳር ወር በቻይናና በፈረንሳይ በሚመራው የፓሪስ ክለብ አማካኝነት የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

* በዚህ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ለአበዳሪዎቿ መክፈል የሚጠበቅባትን ብድር እና ወለድ 2 ዓመት ገደማ አትከፍልም።

* ይህ የዕዳ ክፍያ ሽግሽግ በየዓመቱ የሚከፈለውን 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዕዳ በጊዜያዊነት የሚያስቀር ነው።

ኢትዮጵያ የዚህን አይነቱን ስምምነት የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንዱን ከገዙ የግል ባለሀብቶች ጋርም ለመፈጸም ትፈልጋለች።

የዋናው ብድር የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምና በየዓመቱ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔው ከ6.625 በመቶ ወደ 5.5 በመቶ ዝቅ ማድረግ ሀሳብ አላት።

መንግሥት የብድር አከፋፈሉ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የፈለገው ከሌሎች አገራት ጋር በሚያደርገው የብድር ሽግሽግ ላይ አበዳሪዎችን በተመሳሳይ መልኩ ማስተናገድን በተመለከተ ስጋት እንዳይነሳ በማሰብ መሆኑን አሳውቋል።

መንግሥት የብድር አከፋፈል ማስተካከያው ላይ ከቦንዱ ገዢዎች ጋር በተቻለ ፍጥነት ስምምነት ላይ መድረስ ጠንካራ ፍላጎት አለው።

የቦንዱ ገዢዎች ጋር ያለው ስሜት ምንድነው ?

° ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለዱን በቀኑ እንደማትከፍል ማስታወቋ በቦንዱ ገዢዎች ዘንድ በመልካም አልተወሰደም።

° የቦንዱ ገዢዎች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ አላስፈላጊ እና አሳዛኝ አድርጎ እንደሚመለከተው ገልጿል።

° የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔውን የማያጥፍም ከሆነ ከፍ ያለ ዳፋ ይኖረዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፈው #ሰኞ መክፈል የነበረባትን ወለድ ለቦንድ ገዢዎች ለማስተላለፍ የ14 ቀናት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቷታል።

በእነዚህ በተሰጡ ቀናት ውስጥ ወለዱን የማትከፍል ከሆነ ውልን አለማክበር (#technical_default) እንደሚገጥማት የዘርፉ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

" ፊች " የተሰኘው የአገራትን ብድር የመክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣ አሜሪካ ተቋም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ዕዳ የመክፈል ደረጃ ከነበረበት " ሲሲ " (CC) ደረጃ ወደ " ሲ " (C) ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል።

ተቋሙ ለዚህ ደረጃ ምደባ የጠቀሰው አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያ የቦንዱን ወለድ በቀኑ አለመክፈሏል ነው ያለ ሲሆን በ14 ቀናት ውስጥ ክፍያው ካልተፈጸመ ይህንን ደረጃ በድጋሚ ዝቅ እንደሚያደርገው ገልጿል።

Credit - BBC AMAHRIC / REUTERS

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ኮንስታብል ማክቤል ሮባ የተባለ የፖሊስ አባል ለስራ በታጠቀው ታጣፊ ክላሽ በተኮሰው ጥይት ነው የዶ/ር እስራኤል ጥላሁን ህይወት ያለፈው " - ፖሊስ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የተባለ የጤና ባለሞያ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ #ተገድሏል

ግድያው የተፈፀመው #በፖሊስ_አባል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

ፖሊስ ስለጉዳዩ ምን አለ ?

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰሞኑን " ቦሌ አትላስ " አካባቢ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን በተባለ ግለሰብ ላይ ተፈፅሟል ከተባለው የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ ምርመራ መዝገቡን ዋቢ አድርጎ እንዳስረዳው በቀን 28/3/2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11:20 ሰአት ላይ ነው ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን ወንጀሉ የተፈጸመበት።

ወንጀሉ የተፈፀመው ወረዳ 4 ልዩ ስሙ " አዲስ ህይወት ሆስፒታል " አካባቢ ነው ብሏል።

ዶክተር እስራኤል ያሽከረክራት የነበረችው ተሽከርካሪ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 36734 አ.አ ሲሆን፤ በወቅቱ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 28177 የሆነ #ቪትስ ተሽከርካሪ የያዘ ግለሰብ የመኪና " መስታወት - ስፖኪዮ ገጭቶ አመለጠኝ " በሚል ከፍተኛ ድምጽ እያሰማ ከኋላ ይከተለው ነበር፡፡

ወደ 11፡20 አካባቢም " ፋሲካ የመኪና መሸጫ " የሚባል ቦታ ሲደርስ፤ በአካባቢው ያሉ ኑሯቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎች " ያዘው ያዘው " የሚል ድምጽ በማሰማት ከፍተኛ ግርግርና ወከባ ሲፈጥሩ፤ በዚያን ሰአት #ኮንስታብል_ማክቤል_ሮባ የተባለ የፖሊስ አባል፤ ለስራ በታጠቀው ታጣፊ ክላሽ " የመኪናውን ጎማውን መትቼ ለማስቆም " በሚል በተኮሰው ጥይት የዶ/ር እስራኤል ህይወት ሊያልፍ ችሏል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስረድቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ አንዳንድ ግዜ ወዲያውኑ መረጃ የማይሰጠው #ከምርመራ_ሂደቱ ጋር በተያያዘ የሚበላሹ ነገሮች ስለሚኖሩ ነው ያለ ሲሆን ቀጣይ የምርመራ መዝገቡ እየታየ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትርታ ኤፍ ኤም 97.6 ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን ያሳውቃል።

* በጉዳዩ ላይ ከሟች ቤተሰቦች / ከቅርብ ጓደኞች መረጃ የሚገኝ ከሆነ ተከታትለን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የ32 ዓመቷ ወጣት በፖሊስ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ፖሊስ የድርጊቱ ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ይገኛል ብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ተመታ ህይወቷ አልፏል። በፖሊስ አባል ጥቃት የደረሰባት ኢየሩሳሌም አስራት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ጥቃቱ ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ…
#AddisAbaba

#ሕዳር

* ባለፈው ሕዳር 13/2016 በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት እየሩሳሌም አስራት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ማለፉ መነገሩ አይዘነጋም። ይህች ወጣት በፖሊስ አባል ጥቃት ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና እና ሕክምና ክትትል ሲደረግላት የነበረ ቢሆንም ህይወቷ ሊተርፍ ግን አልቻለም።

* አሁን ደግሞ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የተባለ የጤና ባለሞያ የፖሊስ አባል ነው በተባለ ግለሰብ ሕዳር 28 ቀን 2016 በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን እንዳጣ ተሰምቷል። ይህ ወጣት የጤና ባለሞያ " ስፖኪዮ ገጭቶ አመለጠ " በሚል አንድ የፖሊስ አባል " ጎማውን መትቼ ለማስቆም " ነው ብሎ በታጠቀው መሳሪያ ዶክተሩ ላይ በመተኮስ #ግድያ እንደፈፀመ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

በዶ/ር እስራኤል ጥላሁን ግድያ ዙሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን አሉ ? #ትርታኤፍኤም

" እጅግ በጣም የሚያሳዝንና ሁላችንንም አንገት ያስደፋ ወንጀል ነው የተፈጠረው።

በ28/03/2016 ለሊት 11 ሰዓት ለቅዳሜ አጥቢያ ቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ስፍራው አዲስ ሕይወት የሚባል አካባቢ የተፈፀመ ወንጀል ነው።

ምርመራ መዝገቡ እንደሚነግረን ሟች ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3 36734 አአ ሃሉክስ ፒካፕ እያሽከረከሩ ነበር።

ከኃላ ደግሞ ሌላ ስፖኪዮውን ገጭቶ አመለጠብኝ የሚል ከፍተኛ ክላክስ እያሳማ በፍጥነት የሚያሽከረክር የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 B28177 የሆነ ተሽከርካሪ ከኃላ እየተከታተለ ነበር።

የወንጀል መከላከል ስራ እንዲሰሩ የተመደቡ ሁለት የፖሊስ አባላት አሉ ፤ ለአንደኛው ፖሊስ ይነግረዋል። ይሄ ፖሊስ እንደሰጠው ቃል ' ምናልባት ወንጀል ፈፅሞ ሊሆን ይችላል በሚል ጎማውን መትቼ አቆመዋለሁ ' በሚል ጥይት ይተኩሳል።

ጥይቷ በጀርባ በኩል የተሽከርካሪውን አካል ቀዳ ገብታ የዶክተሩ ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። እጅግ በጣም አሳዛኝ ድርጊት ተፈፅሟል።

ወዲያው ተጠርጣሪ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ ምርመራ እየተጣራ ነው። ከእሱ ጋር ተመድቦ የነበረውን ጨምሮ ስፖኪዮ ተገጨብኝ ያለውን በከፍተኛ ፍጥነት ሲከታተል የነበረውን አሸከርካሪ በቁጥጥር ስር እንዲወል ተደርጎ ምርመራ እየተጣራ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያ ' የተሽከርካሪዬን ስፖኪዮ ገጭተህብኛል በሚል ከገቢና ወርዶ አንዳንዱ ፖሊስ ነው ከተገጨው መኪና ወጥቶ በቀጥታ በሽጉጥ የመታው ይላል አንዳንዱ ዳግሞ ባለስልጣን ነው ይላል ' የተለያዩ የሀሰት መረጃዎች ናቸው እየተናፈሱ ያሉት፤ ህብረተሰቡ ለሀሰት መረጃ ጆሮውን መስጠት አይገባውም። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ውሳኔው ገፍቶ የሚመጣ ከሆነ  ጎዳና ላይ ለመውጣት እንገደድ ይሆናል። " - ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ አሁን እየኖሩበት ያለበትን የመንግሥት ቤት ለቀው እንዲወጡ እንደተነገራቸው ከቢቢሲ አማርኛው  አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ተናግረዋል። ምን አሉ ? - የባለቤታቸው መታሰር መላው ቤተሰባቸው…
" የበቀል ፖለቲካ አገርን ይጎዳል " - አቶ ጃዋር መሀመድ

ፖለቲከኛው አቶ ጃዋር መሀመድ የአቶ ታዬ ደንደአ ቤተሰቦች የሚከራዩትን መኖሪያ ቤት የሚፈልጉበት መንገድ ሳይመቻችና ጊዜ እንኳን ሳይሰጣቸው ከሚኖሩበት ቤት እንዲወጡ መደረጉ ፍፁም ተገቢ አይደለም ሲሉ ኮነኑ።

አቶ ጃዋር መሀመድ " በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በጣም መጥፎው ነገር ሰዎች /ቡድኖች ሲጣሉ ቤተሰቦቻቸው የሚጎዱት ነገር ነው " ብለዋል።

" እኛ ትግል / ፖለቲካ ህይወትን ስራ አድርገን የመረጥን ሰዎች ወደዛ ህይወት የገባነው ሊመጣ የሚችለውን የግል መስዋዕትነት እያወቅን ነው። ነገር ግን እናቶቻችን፣ አባቶቻችን፣ አያቶቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና ልጆቻችን በዚህ ውሳኔ / የህይወት መንገድ ምንም አይነት ድርሻ የላቸውም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ለሚፈጠረው ጥፋት / በደል ተጠያቂ መሆን የለባቸውም " ያሉት አቶ ጃዋር መሀመድ ፤ " ምንም ቢሆን ታዬ ዳንዳአ ምርጠው ለገቡበት የፖለቲካ መስመር እና ስልት ቤተሰቡን መጉዳት ተገቢ አይደለም። " ሲሉ ኮንነዋል።

" የመኖሪያ ቤት ክራይ የሚፈልጉበትን መንገድ ሳይመቻችና ጊዜ እንኳን ሳይሰጧቸው ከመኖሪያ ቤታቸው ማስወጣት ኃጢአት ነው " ሲሉም አክለዋል።

" እንዲህ አይነት ድርጊት በፖለቲካ ልሂቃን መካከል ያለውን ቁርሾ ያባብሳል " ያሉት አቶ ጃዋር መሀመድ " ነገ ጊዜው አልፎ ሲቀየር እርስ በርስ ጠባሳውን ለመፈወስ አስቸጋሪ ያደርገዋል። የበቀል ፖለቲካ አገርን ይጎዳል " ብለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ እየኖሩበት ከነበረው የመንግስት የኪራይ ቤት ትላንት ጥዋት በፀጥታ ኃይል እንዲወጡ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ከቤቱ እንዲወጡ የተደረጉት የ3 ቀን ገደብ ተቀምጦላቸው ሲሆን ተማሪ ልጆቻቸውን እንዲሁም ሌላ አብረዋቸው የሚኖሩ የቤተሰብ አባልን ይዘው በቤተሰቦቻቸው ቤት በጊዜያዊነት ተጠግተው መቀመጣቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia M-PESA

ሳፋሪኮም በድጋሚ በሽልማቶች ሊያንበሸብሻቹ በተረክ በM-PESA ተመልሷል! እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ እና እንሸለም!

የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
ቀኑ እስከ ታኅሣሥ 21 ተራዝሟል                    

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ከሜታ ጋር በመተባበር ፈጠራ በተሞላበት መንገድ የሰላም መልዕክት አዘጋጅተው በማጋራት በርካታ ምላሽ ያገኙ የፌስቡክና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎችን ለመሸለም ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ሆኖም ይህ ውድድር እስከ ታኅሣሥ 21 ድረስ ተራዝሟል። አሸናፊዎች ከ50 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ ይሸለማሉ፡፡

በዚህ ውድድር ለመሳተፍ #Peace4Ethiopia #ሰላምለኢትዮጵያእና #CARDEthiopia ሃሽታጎችን ይጠቀሙ
#ሀገራዊምክክር #ሀገራዊመግባባት

በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግር ለሥራው እንቅፋት እንደሆኑበት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የኮሚሽኑ አንጀዳ ቀረፃ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተመስገን አብዲሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦

- የጸጥታ ችግር በአንዳንድ ቦታዎች በተለይ በአማራ ክልል አሁን፣ በኦሮሚያ ክልል ቀድሞና አሁንም አንዳንድ ቦታዎች መኖሩ እንደ አንድ እንቅፋት የሚታይ ነው።

- ኮቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ተሳታፊዎችን ከቦታ ቦታ ማምጣት በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው የጸጥታ ችግር ባለበት።

- የጸጥታ ችግር ባለበት አገራዊ ምክክር እንቅፋት ያጋጥመዋል። ስለዚህ ቅድሚያ እንግዲህ እነዚህ የጸጥታ ችግሮችን እንዴት እንፈታለን ? እንዴት መፈታት አለባቸው ? የሚሉትን ጭምር ቁጭ ብለን እየተወያዬን ኮሚሽኑ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም እያስቀመጠ በዚያ ልክ እየሄደ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኮሚሽኑ ላይ ስለሚነሳው በተለይም የገለልተኝነት ጥያቄና ሌሎች ቅሬታዎች ለኮሚሽን የቅሬታ አያያዝ አስተባባሪና የኦሮሚያ ክልል ተሳታፊ ልየታ ቡድን መሪ አቶ ብዙነህ አሰፋ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ምላሻቸውም ፦

* ' ኮሚሽኑ ነፃ አካል አይደለም፣ የመንግሥት ጥገኛ ነው ' የሚል አስተሳሰብ በተወሰኑ አካላት ዘንድ እንዳለ እንገነዘባለን። ያነን የሚያራምዱት በብዛት የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ናቸው።

* 'ለዚህ ሀሳብ መነሻ የሆናቸው ነገር ' ኮሚሽኑ ሲመሠረት በበቂ አልተሳተፍንም እኛ ' ከሚል የሚመነጭ ይመስለኛል። ይሄ ቅሬታ የተወሰኑ እውነታዎች ሊኖሩት ይችላሉ። በአብዛኛው ግን በጥላቻ እና ጥርጣሬ ላይ የተመሠረተ ነው።

* እውነት ነው። ኮሚሽኑ ሲቋቋም ሰፊ ሚና የተጫወተው መንግሥት ነው ግን የኮሚሽን መሪዎች የተመረጡበት ሂደት ደግሞ ከሞላ ጎደል ህዝባዊ እና ገለልተኛ ነው የነበረው።

* የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሲቋቋም በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀሳብ ልዩነት ማደራደር የተቋቋመ ተቋም አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ እና በህዝብ፣ በህዝብ እና በመንግሥት፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሀገርን ደህንነት ስጋት ላይ ሊጥሉ የሚችሉ መሠረታዊ ልዩነቶች መንስኤ መለየትና ልዩነቶቹን ለመፈታት ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግበት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የተቋቋመ ኮሚሽን ነው።

ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-16

@tikvahethiopia
" #ዓይደርን_ከመዘጋት_እንታደግ ! "

በትግራይ፤ መቐለ ከተማ የሚገኘው ዓይደር ስፔሻላይዝደድ ሆስፒታል ከወድቀትና ከመዘጋት ለማዳን ያለመ ጥሪ ቀረበ። 

በእጅግ አሳሳቢ ሁኔታ የሚገኘው የዓይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአጭር ጊዜ ለማዳን ካልተቻለ #በወራት ውስጥ አገልግሎት መስጠት ሊያቆም ይችላል።

ስለሆነም ያለበት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ በጥልቀት በመረዳት እንዲድን ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ሲል የመቐለ ዩኒቨርስቲ አልሙናይ ጉዳዮች ፅህፈት ቤትና የቀድሞ ተመራቂዎች ማህበር ጥሪ አቅርቧል።

ሆስፒታሉ ያለበት የባለሞያ ፣ የመሳሪያና የመድሃኒት አጥረት ለመቅረፍ ያለመ ወርክሾፕና የገቢ ማሰባሰብያ ቴሌቶን በያዝነው የታህሳስ ወር የመጨረሻው ሳምንት ይካሄዳል።

ትግራይ መቐለ ማእከሉ በማድረግ ለመላው ትግራይ የዓፋርና የአማራ አዋሳኝ አከባቢዎች የተሟላ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረው የዓይደር  ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጦርነቱ ምክንያት እጅጉ መጉዳቱንና አገልግሎት ለመስጠት በሚያስቸግር ሁኔታ እንደሚገኝ ታህሳስ 6/2016 ዓ.ም በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልፀዋል ።

ጋዜጣዊ መግለጫው ያዘጋጁት የመቐለ ዩኒቨርስቲ አለሙናይ የጤና ኮሌጅ ሳይንስ የቀድሞ ምሩቃንና ሃኪሞች እንዳሉት ፦
- ሆስፒታሉ ጦርነቱ ተከትሎ በርካታ የህክምና ማሽኖቹ ተበላሽቷል
- ከፍተኛ የበጀት እጥረት አጋጥሞታል
- ልሎችም ችግሮች ተደራርበው አገልግሎት እስከማቋረጥ የሚደርስ አደጋ ተደቅኖበታል ብለዋል። 

ሆስፒታሉ አሁናዊ ሁኔታው ሲታይ እጅግ አስደንጋጭ ነው ያሉት የቀድሞ ምሩቃን በሆስፒታሉ ባለው ሁለንተናዊ እጥረትና ውድቀት በየቀኑ የሚያጋጥም የመሟች ታካሚ ቁጥር በእጅጉ ጨምረዋል ብለዋል።

* የስቲ ስካንና የኤምአርአይ አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና መሳሪዎች ከጥቅም ውጭ ሆኗል
* የልብ ህክምና ማእከል አገልግሎት መስጠት ካቆመ ወራት መቆጠራቸው በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልፀዋል።   

ቀደም ሲል ከመላ ትግራይ ፣ ዓፋርና አማራ ክልሎች ለሚመጡ ከ10 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ታካሚዎች አገልግሎት የመስጠት አቅም የነበረው ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከመላ አገር አልፎ ከደቡብ ሱዳንና ሶማልያ ጎረቤት አገራት ለመጡ ተማሪዎችም የመማር ማስተማር አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ተገልፀዋል። 

አሁን ሆስፒታሉን ከውድቀትና መዘጋት ለማዳን " ዓይደር ሆስፒታልን ከውድቀት እንታደግ "  በሚል ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም በሚካሄደው ወርክሾፕና የገቢ ማሰባሰብያ ቴሌቶን ሆስፒታሉ ከውድቀትና ከመዘጋት የሚታደግ ውጤት ይጠበቃል ተብሏል።

መረጃውን የላከው ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                       
@tikvahethiopia            
#ETHIOPIA🇪🇹 #UAE🇦🇪

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) አየር ኃይል አባላት በጋራ ሆነው " ጥቁር አንበሳ " የተሰኘ የአየር ላይ ወታደራዊ ትርዒት አቀረቡ።

ትርዒቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ነው።

በስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው የአየር ትርዒቱ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢማራት በፖለቲካው እና በውትድርናው መስክ ያላቸውን መልካም ግንኙነት፣ ወዳጅነትና ትብብር ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከተመሰረተ 88ኛ አመቱን የያዘ ሲሆን ካለፈው ህዳር 20 ጀምሮ የምስረታ በዓሉ እየተከበረ ነው።

Photo Credit - #PMOfficeEthiopia

@tikvahethiopia