TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

የክፍያ መንገዶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በሚያስተዳድራቸውን የአዲስ አበባ - አዳማ፣ የድሬዳዋ - ዳዋሌ እና የሞጆ - ባቱ የክፍያ መንገድ ከታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የታሪፍ ጭማሪ አድርጓል፡፡

ኢንተርፕራይዙ ባለፉት 9 ዓመታት ለ2 ጊዜ ያህል ብቻ ነው የታሪፍ ጭማሪ / ማሻሻያ የተገበረው።

የመጀመሪያው በመጋቢት 2011 ዓ.ም በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ላይ የተተገበረ ነው።

በኮቪድ ወረርሽኝ እና ሃገራዊ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ለ4 አመታት የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ ሳይደረግ ቆይቶ በህዳር 2015 ዓ.ም. የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ መተግበሩን አመልክቷል።

የአሁኑ የታሪፍ ጭማሪ ለምን ተደረገ ?

1ኛ. የስራ ማስኬጃና መደበኛ ጥገና ወጪዎች የዋጋ ግሽበትን በመቋቋም ተቋማዊ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ፤

2ኛ. ለወቅታዊ ጥገና (Periodic Maintenance) መጠባበቂያ ፈንድ ዓመታዊ ተቀማጭን በማረጋገጥ የክፍያ መንገዶችን የአገልግሎት ደረጃ ለማስጠበቅ፤

3ኛ. ምክንያታዊ ትርፍ በማስመዝገብ የመንግስት የትርፍ ድርሻ አስተዋጽዖን ለመወጣት የሚያበቃ የፋይናንስ አቋምን ለማረጋገጥ ዓመታዊ የክፍያ መንገዶች የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ተመን መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብሏል።

የአዲስ-አዳማ እና የሞጆ-ባቱ የፍጥነት መንገዶች የአገልግሎት ደረጃቸው በፍጥነት መንገድ ደረጃ ያሉ እና ተመጋጋቢ የክፍያ መንገዶች በመሆናቸው በአንድ ዓይነት የታሪፍ ተመን የሚተዳደሩ ሲሆን በዚህም ለአዲስ-አዳማ እና የሞጆ-ባቱ የፍጥነት መንገዶች በተመሳሳይ 31% የታሪፍ ዕድገት እንዲኖረው ተደርጓል።

ለድሬደዋ - ዳዋሌ የክፍያ መንገድ ደግሞ 42% የታሪፍ ዕድገት እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

በድሬዳዋ - ደዋሌ የክፍያ መንገድ " ባለሶስት እግር " ተሸከርካሪ ይከፍሉ የነበረው ታሪፍ ብር 10 ተቋማዊ ማህበራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አንጻር ታይቶ ማህበረሰቡ ለተጋነነ ትራንስፖርት ወጪ ጫና እንዳይዳረግ በሚል የአገልግሎት ክፍያ ታሪፉ በልዩ ሁኔታ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።

(የተደረገው የታሪፍ ጭማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
በዘመናችን እንቅስቃሴዎች ሁሉ በጎግል መተግበሪያዎች ተደግፈው ድካም እና ወጪ ተቆጥቧል !

ጉዞዎን በጎግል ማፕ የሚደግፉ፣ በዩትዩብ ደስታን የሚፈጥሩ፣ የፍላጎትዎን የሚያገኙባቸው የጎግል መተግበሪያዎች የተጫነባቸውን ዘመናዊና ኦሪጂናል ስማርት ስልኮች በተመጣጣኝ ዋጋ በአገልግሎት መስጫ ማእከሎቻችን ሲገዙ ለ1 ዓመት በየወሩ የሚታደስ 2 ጊ.ባ ነጻ የዩትዩብ ጥቅል እንዲሁም እስከ 100 ጊ.ባ ዳታ እና 1000 ደቂቃ የድምጽ ወርሃዊ ጥቅሎች በስጦታ ያገኛሉ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
ቀኑ እስከ ታኅሣሥ 21 ተራዝሟል                    

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ከሜታ ጋር በመተባበር ፈጠራ በተሞላበት መንገድ የሰላም መልዕክት አዘጋጅተው በማጋራት በርካታ ምላሽ ያገኙ የፌስቡክና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎችን ለመሸለም ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ሆኖም ይህ ውድድር እስከ ታኅሣሥ 21 ድረስ ተራዝሟል። አሸናፊዎች ከ50 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ ይሸለማሉ፡፡

በዚህ ውድድር ለመሳተፍ #Peace4Ethiopia #ሰላምለኢትዮጵያእና #CARDEthiopia ሃሽታጎችን ይጠቀሙ
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA " ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ ? " - አቶ ወንድሙ ኢብሳ " መከላከያ ወንድሞቹን መግደል የለበትም፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም " - አቶ ታዬ ደንደአ ሰላም ሚኒስቴር ረቡዕ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም አዳማ ከተማ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ የተጋበዙት ጠበቃና የሕግ አማካሪ አቶ ወንድሙ ኢብሳ፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎችም ጋዜጠኞች ፦ °…
" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለማባረር ዘግይተዋል " - ጠበቃና የህግ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ

ከቀናት በፊት አዳማ በነበረ መድረክ " ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር እራሱ #ሰላም_ነው_ወይ ? ሰላም ሚኒስቴር ሰላም መስበክ ሲገባው በመ/ቤቱ ሆነው በስውር አማፂያንን የሚደግፉ ሰዎች አያለሁ " ሲሉ በወቅቱ የሚኒስትር ዴኤታ ለነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ጥያቄ ያቀረቡት ጠበቃና የሕግ አማካሪው አቶ ወንድሙ ኢብሳ የአቶ ታዬን ከስልጣን መነሳትና በፌስቡክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተናግረው ስለፃፉት ፅሁፍ እንዲሁም አቶ በሕግ የሚያስጠይቃቸው ጉዳይ ይኖር እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ጠበቃና የሕግ አማካሪው አቶ ወንድሙ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

- ከዚህ በፊት አቶ ታዬ ደንደአ በሚዲያዎች ላይ የሚሰጡት አስተያየት ላይ ተቃውሞ ስላለኝ የዛሬ አመትም " አቶ ታዬ የሰላም ሚኒስቴር እራሱ ሰላም ነው ወይ ? " ብዬ ጠይቄያቸው ነበር። ባለፈውም እንዲሁ ጠይቄያቸዋለሁ።

- በሰላም ሚኒስቴር ውስጥ ሆነው ሰላምን ሲሰብኩ አልነበረም።

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለማባረር ዘግይተዋል። (አንስተዋቸዋል ሳይሆን አባረዋቸዋል ነው የምለው)

- አቶ ታዬ ከስልጣን ከተባረሩ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እጅግ በጣም ወራዳ በሆነ ቃላት መናገራቸው ቦዶነታቸውን የሚያሳይ ነው።

- ምን ጊዜም ልዩነት ይፈጠራል ፤ በለማና በዐቢይ መሃከል ልዩነት ተፈጥሯል ተከባብረው ነው የተለያዩት አልተሰዳደቡም ፤ ጉዱም ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ወይም ከብልፅግና ጋር ልዩነት ፈጥሯል አልተሰዳደቡም ፤ ሌላው ቀርቶ የኦነጉ ዳውድ ኢብሳ ' ትጥቅ ፈቺ ትጥቅ አስፈቺ ማነው ? ' ከማለት ባለፈ ኢትዮጵያዊ ባህል ያልሆነ ስድብ አልተሳደቡም።

- አቶ ታዬ ባለፉት አምስት ዓመታት የብልፅግናን መዝሙር ሲዘምሩ ፣ ስለብፅግና ሲቀሰቅሱ ፣ ብልፅግና ትክክል እንደሆነ ሲሰብኩ ነበር ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያወድሱ ቆይተዋል ይሄን አቋማቸውን እጥፍ አድርገው  " የሚፅፉትን የሚናገሩትን እውነት ነው ብዬ ተሸወድኩኝ " ማለታቸው አቋም የሌላቸው መሆኑን ነው ያሳየኝ።

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ሳያባርሯቸው በፊት አስቀድመው ስልጣን በገዛ ፍቃዳቸው ቢለቁ ኖሮ አንድ ነገር ነው። አቶ ለማ በጨዋ ደንብ  ' ከብልፅግና ጋር #አልስማማ አልሰራም ' ብለው እንደሄዱት አላደረጉም።

- የአቶ ታዬ ጉዳይ ሰሞኑን ይወራል በቃ ያልፋል።

- በሕግም ይጠየቃሉ፣ ከባድ ማኖ ነው የነኩት።

- እራሳቸው መንግሥት ውስጥ ሆነው " ይሄ መንግሥት ሰላም አይፈልግም ፀረሰላም ነው ፣ ድርድሩ እንዳይሳካ ያደረገው የኔ መንግሥት ነው " ማለታቸውም ያስጠይቃቸዋል።

- እስከ ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን እስኪያባርሯቸው ድረስ ምንም ሳይሉ ነው የቆዩት። ልክ ከስልጣን ሲባረሩ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ' ጨካኝ  ፣ በደም የሚነግድ ' ሆኑ፤ በዚህም ይጠየቃሉ።

- ወይ ለይቶላቸው እንደነ ክቡር ለማ፣ እንደነ ክቡር ገዱ ተቃውሟቸውን በጨዋ በሰለጠነ መንገድ ገልፀው አርፈው አልተቀመጡ። ከእሳቸው ይልቅ ጫካ ያሉት ሰዎች አቋም አላቸው ፤ ለይቶላቸው አቋማቸውን ገልጸው ግልፅ የሆነ ትግል እያደረጉ ናቸው።

- አቶ ታዬ ከብልፅግና " ስልጣን አልፈልግም " ብለው ስልጣን አለቀቁም። ከስልጣን እስኪባረሩ ድረስ ነው የቆየቱ። አቶ ለማ እኮ መከላከያ ሚኒስትርን ነው ለቀው የሄዱት።

- አቶ ታዬን መሳይ ሌሎችም ብልፅግና ውስጥ አሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም አይታሰብም አሉ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፦ - የትግራይ ግዛቶችን በወረራ የያዙ ኃይሎች ሳይወጡ፤ - ተፈናቃዮች ወደ ቀደመው ቄያቸው ሳይመለሱ ሪፈረንደም የሚባል ነገር #አይታሰብም ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሚስተር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ…
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ የፈፀመው ወንጀል በሽግግር ፍትህ የሚዳኝ አይደለም " አሉ።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የፓለቲካና ኢኮኖሚ አማካሪ ጆን ሮቢንሰን ትላንት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳና የፓለቲካና ኢኮኖሚ አማካሪ ጆን ሮቢንሰን በዋነኝነት በሽግግር ፍትህ ጉዳይ ፣ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ውጪ በክልሉ የሚገኙ ኃይሎች ስለመውጣት መሰረት በማድረግ መወያየታቸው ተሰምቷል።

አቶ ጌታቸው ፤ " በተለይ ወራሪው የኤርትራ መንግስት በትግራይ የፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው " ያሉ ሲሆን ይህ ወንጀል በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ፍትህ መዳኘት አለበት ብለዋል።

በኢትዮጵያ እንዲተገበር የሚጠበቀው የሽግግር ፍትህ ትግራይን የዘነጋ እንዳይሆንም ያሳሰቡት አቶ ጌታቸው ፤ " ትግራይ በአሁኑ ሰአት በፌደራል መንግስት ተወካይ የሌላት ፣ የትግራይ ህዝብ ድምፅ የሚሆን አካል በሌለበት የተመሰረተው የሽግግር ፍትህ ክልሉ ያገለለ እንዳይሆን ሊሰራበት ይገባል " ብለዋል።

ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ስለመመለስና የትግራይ ክልልን ግዛታዊ አንድነት ስለ ማስጠበቅ አስመልክተው ማብራርያ የሰጡት ፕረዚደንቱ ፤ " ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ባልተመለሱበት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የፌደራል መንግስት የገለፀው የሪፈረንደም ጉዳይ በፍፁም አይሆንም " ሲሉ ተናግረዋል።

" በክልሉ ምዕራባዊ ዞን ሙሉ በሙሉ  ፣ እንዲሁም በተወሰኑ የምስራቅ ፣የሰሜናዊ ምዕራብና ደቡባዊ ዞን አከባቢዎች የሚገኙ ወራሪ ሃይሎች በማእከላይ መንግስቱ ትእዛዝ እንዲወጡ ፤ በአከባቢዎቹ ያለው አስተዳደር ፈርሶ በጊዚያዊ አስተዳደሩ መዋቅር መተካት አለበት " ብለዋል አቶ ጌታቸው ረዳ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ ከአሜሪካው ዲፕሎማት ጆን ሮቢንሰን በነበራቸው ቆይታ አገራዊ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች በማንሳት የተወያዩ ሲሆን አሜሪካ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ አወንታዊ አስተወፅኦ እንደሚኖራት ዲፕሎማቱ መግለፃቸውን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ፅህፈት ጠቅሶ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ዘግቧል።
                    
@tikvahethiopia            
ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎቹ በመኪና አደጋ ተነጠቀ።

ትናንት በቀብሪደሀር ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ሁለት የቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ተማሪዎች ፋርዶሳ መሀመድ እና ቢሻሮ አህመድ የሶሲዮሎጂ ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንደነበሩ ተገልጿል።

የተማሪዎቹ ህልፈት የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ ልብ የሰበረና አስደንጋጭ ክስተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተቋሙ ለሟች ተማሪዎች ቤተሰቦች፣ ለጓደኞቻቸው እና ለአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via @tikvahuniversity
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ በክልሉ ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ #መጋለጡን አሳወቀ።

እስከ አሁን 25 ህፃናት የሚገኙባቸው 400 ሰዎች በራብ ምክንያት ሞተዋልም ብሏል። 

በክልሉ ያጋጠመው የድርቅ አደጋ ለመከላከል ያለመ 22 አባላት ያሉት ከተለያዩ የህብረተሰብ ልፍሎች የተውጣጣ " አፋጣኝ ምላሽ ለትግራይ " የተሰኘ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተሰምቷል።

የ " አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ " ግብረ ሃይል ሰብሳቢ የሆኑት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሲሆኑ  ዛሬ ለጋዜጠኞች መገለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ በአሁኑ ሰአት ለረሃብ አደጋ የተጋለጠው ከ2 ሚሊዮን ትግራዋይ ህይወት ለመታደግ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ የክልሉ ተወላጅና ወዳጅ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

የ " አፈጣኝ ምላሽ ለትግራይ " ግብረ ሃይል ድጋፍ የሚያግዙ ግለሰቦችና ደርጅቶች የሚገለገሉባቸው ሶስት የባንክ የሂሳብ ቁጥሮች የከፈተ ሲሆን ቁጥሮቹ ፦

* አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 👉00112180095-49

* ወጋገን ባንክ 👉 1001077411101

* የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ 👉 1000592420809 መሆናቸውን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                    
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace #GoE #OLA

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA መካከል ከዚህ ቀደም ታንዛኒያ ላይ ሁለት ጊዜ የሰላም ድርድር ተደርጎ ያለ ስምምነት / ወጤት መበተኑ ይታወሳል።

አሁንም ሌላ #ሶስተኛ_ዙር የሰላም ውይይት/ድርድር ሊኖር የሚችልበት ዕድል መኖሩን የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?

- የመጀመሪያው ንግግር በጣም ጥሩ ርቀት ሄዶ ነበር ፤ በዚህም ብዙ መካሰስ ቀርቶ ለሚቀጥለው ዙር ለመነጋገር እናመቻች በሚል ነው የተጠናቀቀው።

- ሁለተኛው የሰላም ድርድር መጀመሪያ ላይ ከሁለቱም ወገን አግባቢዎች ሄደው ከሳምንት በላይ ፈጅተዋል። አዝማሚያው ጥሩ ነበር።  መጨረሻ የማያግባቡ ነጥቦች መጡ። በዚህም ትንሽ የተሻለ ኃይል ያለው ሰው ይምጣ ተብሎ ከመንግሥትም ከነሱም ሄዷል። በዚህም ጊዜ ጥሩ ሂደት ነበር።

- በህገ-መንግስት ጥላ ስር "የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ አንድነት መቀበል ላይ ፤ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት በምርጫ የመጣ Legitimacy ያለው መሆኑ ላይ መግባባት ተደርሶ ነበር። ወደ ዝርዝር ሲመጣ ግን እነዚህን መግባባቶች የሚሸረሽር ነገር ነው የመጣው።

- ስምምነቱ በመጨረሻ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ደረጃ / ወደ ሰነድ ደረጃ ሲደርስ ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ተነስትዋል።

ምንድናቸው ?

* አንደኛው --- ' #ስልጣን_አካፍሉኝ ' ነው እያንዳንዱን ጠብመንጃ የያዘ፣ ጫካ የገባ ሁሉ ስልጣን ለማግኘት ከሆነ የሚደራደረው ይሄ ለሀገር ሰላም አይሰጥም።

ጫካ እየገቡ ፣ ግጭት የፈጠሩ ፣ ህዝቡን እያበሳሰቡ ከዛ እንነጋገር እያሉ " እሺ " ሲባል ስልጣን አካፍሉኝ የሚባል ነገር ካለ መቼም ስርዓት አይመጣም። ሀገር ሰላም አይሆንም።

ምሳሌ ብንወድስ ፦ ከአማራ፣  ከቤንሻንጉል ጉምዝም ከሌላውም የታጣቁ ኃይሎች ስልጣን አካፍሉኝ ካሉ ስንት የታጠቀ ኃይል ስልጣን ሲካፈል ይኖራል ? ይሄ ኢትዮጵያን ይጎዳል።

እንዲህ አይነት ጥያቄ ነው ይዘው የቀረቡት (OLAን ማለታቸው ነው)።

መንግሥት ስልጣን ላካልፍ ቢልም ፍፁም አይችልም ፤ መብትም የለውም። #ማሳተፍ ግን ይችላል። ሸኔን ጭምር ማሳተፍ ይችላል።

ዋናው መሰረታዊ ልዩነት ይሄ ነው። ስልጣን አካፍሉኝ ስሉም እራሳቸው ፕሮፖዛል አስቀምጠው ፤ እዚህ ላይ ስልጣን ስጡኝ የሚል ነበር።

* ሁለተኛው --- ወደ ' DDR ' አልገባም ነው።

በሰላም ለመታገል ፣ ፓርቲ አቋቁሞ ለመታገል ፣ ወደ ህዝብ ምርጫ ለመቅረብ የገጠር ትጥቅ ትግል ትቶ በሰላም ወደ ህዝብ መመለስ ነው። ለዚህ ደግሞ ትጥቅ መፍታት አለባቸው።

DDR / Disarm, Demobilized , Reintegrate መሆን አለባቸው። ይሄ ዓለም የሚሰራበት ነው። ማንኛውም ግጭት የተፈታውም በዚህ ነው። ይሄን ለመቀበል የመቸገር ነገር ተከስቷል።

ትጥቅ ሳይፈታ ፦
° እንዴት እንደራደራለን?
° እንዴት Demobilize ይሆናሉ?
° እንዴት ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ?

መንግስት በግልፅ DDR ፕሮግራም ውስጥ መግባት አለብን ብሏል። በአንድ ሀገር በፍፁም ሁለት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም። ትጥቅ የመያዝ መብት ያለው መንግስት ብቻ ነው።

ይሄንን #መቀበል_ነበረባቸው። በዓለም ላይ ይሄን ሳይቀበሉ ስምምነት የለም። ድርድር ብሎ ነገር የለም።

ንግግሩ ጥሩ ሄዱ ከላይ ባሉት ሁለት ምክንያት ነው መጨረሻ ላይ የቆመው።

- ሶስተኛ ዕድል ይኖራል ? እኔ የሚኖር ይመስለኛል።

- ሁለቱን #ያልተስማማንባቸው_ነጥቦችን በተሳሳተ መንገድ እንዲወስዱ በማድረግ ሌሎች ኃይሎች እጅ አላቸው። OLA ላይ ታዝሎ የሚሄዱ ኃይሎች አሉ። ከሀገር ውስጥም ከሀገ ውጭም አሉ። ባዕዳንም ዜጎችም እነዚህ ኃይሎች OLA በሰከነ መንገድ አይቶ ስምምነቱን እንዳይቀበል አድርገውታል። OLA ሌላ መስማት አልነበረባቸውም፤ ችግር ውስጥ ያሉት እራሳቸው ስለሆኑ እራሳቸው መወሰን ነበረባቸው።

(ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እነዚ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልተናገሩም)

- ሌላው ኃይል ጣልቃ ስለገባ በዓለም experience ታይቶ የማይታወቅ ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ መንግሥትን አስቸግረዋል (OLA ማለታቸው ነው)።

- ሶስተኛ ዕድል ሊኖር ይችላል። ሰከን ብለው አስበው አደራዳሪዎች ጭምር የሚያምኑበት የመጨረሻው ወረቀት / ዶክመንት / የቀበል ደረጃ ከደረሱ ሶስተኛ ውይይት ሊኖር ይችላል።

- ምናልባት ሶስተኛ ውይይት እንደሁለተኛው ውይይት ሰፊ ላይሆን ይችላል እስካሁን የተደከመበት ሰነድን መቀበል ላይ ከተደረሰ ሶስተኛው ውይይት ሊኖር ይችላል፤ ሶስተኛው ውይይት የመጨረሻም ይሆናልም ብዬ ገምታለሁ ወደሰላም ለመምጣት ወይም እስከመጨረሻው ሁለተኛ ላለመነጋገር የመጨረሻ ሊሆን ይችላል።

🕊 የኢጋድ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሳምንታት በፊት ያለ ስምምነት የተጠናቀቀውን 2ኛው ዙር የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድርን በተመለከተ ሰጥተው በነበረው መግለጫ ሌላ አዲስ ዙር ውይይት ይጀመራል ብለው #ተስፋ እንደሚያደርጉ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

ጥራትን ከሚገርም ዋጋ ጋር ይዞ የመጣውን አዲሱን Kimem Itel Pro እናስተዋዉቅዎ! በአቅራቢያችን ወደ የሚገኝ የሳፋሪኮም ሱቅ ጎራ ብለን የግላችን እናድርገዉ።

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
ዓመታትን የፈጀው መንገድ . . .

" የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ " - የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

ግንባታው ከተጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረው የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት አሁን ወደ መጠናቀቁ መድረሱ ተነግሯል።

ይህ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በደቡብ የአዲስ አበባ ክፍል እየገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው መንገድ ፤ ከደቡብና ከምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለመግባትና ለመውጣት፣ ለረጅም ዓመታት ብቸኛው የወጪና ገቢ መተላለፊያ መስመር ሆኖ ሲያገለግል ነበር።

መንገዱን ያለውን የትራፊክ  እንቅስቃሴ በአግባቡ ማስተናገድ እንዲችል በሚል ግንባታ ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን እንደሚለው ፤ ከመንገድ ፕሮጄክቱ አጠቃላይ ግንባታ ሂደት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተፈፅሞ በከፊል አገልግሎት መስጠት ችሏል።

ነገር ግን፦
- #ከፋይናንስ
- #ከወሰን_ማስከበር ጋር በተያያዘ በገጠሙ ችግሮች ምክንያት ቀሪው የግንባታ ሥራ በተፈለገው ልክ ሳይፈፀም መቆየቱን አመልክቷል።

ለችግሮቹ በተሰጠ መፍትሄ የፕሮጀክቱ ግንባታ ቀጥሎ አሁን ላይ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ መሸጋገሩን አሳውቋል።

መ/ቤቱ በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ ክረምት በጭቃ፣ በጋውን በአቧራ ሲፈተን እንደነበር ገልጿል።

በዚህ መንገድ ምክንያት የትራፊክ እንቅስቃሴው እንደ ኤሊ ጉዞ እያዘገመ ይጓዝ እንደነበረም ገልጾ አሁን ግን ወደመጠናቀቁ መድረሱን አሳውቋል።

አሁን ላይ ቀደም ሲል ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ በቆየው የመንገዱ የቀኝ ክፍል ተደራቢ አስፋልት የማንጠፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን የእግረኛ እና የፔዳል ሳይክል መተላለፊያ መስመርና ቀሪ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው ብሏል።

ቃሊቲ ማሰልጠኛ የቀለበት መንገድ መሸጋገሪያ ላይ እየተሰራ የሚገኘውን የመንገድ ማገጣጠሚያ ግንባታ ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃሉ ብሏል።

አሸከርካሪዎች በግንባታው ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ ችግሮች እንዳይገጥማቸው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል።

@tikvahethiopia