TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ምን እየጠበቅን ነው ? ሊሞት የምንፈልገው የህዝብ ቁጥር ገና አልሞተም ማለት ነው ? " - ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቡፅዕ አቡነ ኤርምያስ " ችግራችንን በውይይት እንፍታው " ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቀረቡ። ይህን ጥሪ ያቀረቡት ዛሬ ተከብሮ በዋለው የግሸን ደብረ ከርቤ በዓል ላይ ተገኝተው ለምዕመናን ባሰሙት ንግግር ነው። ብፁዕነታቸው…
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ " ታፍነዋል " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ጽ/ቤት አስታወቀ።
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ከመስከረም 18- 22 ቀን 2016 ዓ.ም በግሸን ደብረ ከርቤ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ተልዕኮ አጠናቀው በሰላም ወደ መንበረ ጵጵስናቸው ተመልሰዋል ተብሏል።
መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም በወልድያ ከተማ ሀገረ ስብከታቸው የሚገነባውን G+8 ሁለገብ ሕንጻ ቦታ ዝግጅት በአካላዊ የመስክ ጉብኝት በቦታው ተገኝተው አባታዊ ቡራኬ ማካሄዳቸውም ተገልጿል።
ትናንት እና ዛሬም የተለመደ አባታዊ አገልግሎታቸውን በመንበረ ጵጵስናቸው እያከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል።
ከብፁዕነታቸው ጋር በተያያዘ " ታፍነዋል " እየተባለ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች እየተላለፈ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ጽ/ቤት አሳውቋል።
@tikvahethiopia

#ኢሬቻ
የኢሬቻ በዓል ምንድነው ? ለምንስ ይከበራል ?
የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር መቆየቱን የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።
የማህበረሰቡ መሪዎችም ኢሬቻ " የምስጋና በዓል " እንደሆነ ይገልጻሉ።
የኦሮሞ ሕዝብ ምድር እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪው ዋቃ ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን እንደሚያከብሩ ያስረዳሉ።
የኦሮሞ ሕዝብ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው።
የኦሮሞ ታሪክ ምሁሩ ዲሪቢ ደምሴ፤ " ኢሬቻ ማለት ዋቃ (ፈጣሪ) የፈጠረውን ማመስገን ማለት ነው " ይላሉ።
ማኅበራዊ ደረጃ እና የእድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብር ቆይቷል።
ኢሬቻ የዘመን መለወጫ በዓልም ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በማለፉ በኢሬቻ ቀን ምስጋናውን ለፈጣሪ ያቀርባል።
በክረምት ወራት ተራርቆ ሳይገናኝ የቆየ ዘመድ አዝማድ መስከረም ላይ ይገናኛል።
ሕዝቡም ክረምቱን በፈጣሪ ፍቃድ የሞላው ውሃ ጎድሎ ከዘመድ አዝማድ አገናኝን ብሎ ምስጋና ያቀርባል።
የአንትሮፖሎጂ ባለሙያው ገመቹ መገርሳ (ዶ/ር)፤ " ክረምት ለሊት ነው። ለሊት ደግሞ ጨለማ ነው። ጨለማ ለአውሬ እንጂ ለሰው ልጅ አይሆንም። ጨለማው ሲነጋ ደግሞ ብርሃን ነው፤ ብርሃን ሲሆን ሃሳብ የለም ደስታ እንጂ። 'መስከረም በረ'ባ ማለት ይህ ነው " በማለት የኦሮሞ ሕዝብ ከክረምት መገባደድ በኋላ የኢሬቻ በዓልን የሚያከብርበትን ምክንያት ያስረዳሉ።
ዲሪቢ ደምሴ የኢሬቻ በዓልን ለማክበረ የሚወጣ ታዳሚ እንደ ሳር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይዞ እንደሆነ ይገልጻሉ።
" ፈጠሪያችን ሆይ አንተ ያጸደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመስግንሃለን' በማለት እርጥብ ነገር ተይዞ ይወጣል" ሲሉ የታሪክ ምሁሩ ይናገራሉ።
ዲሪቢ በኢሬቻ በዓል ላይ የኦሮሞ ሕዝብ ለመላው የሰው ልጅ ሰላምና ደኅንነት ፈጣሪውን ዋቃን ይለምናል፤ ያመሰግናል ሲሉ ገልጸዋል።
የአንትሮፖጂ ምሁሩ አለማየሁ (ዶ/ር) ፤ " የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ትቶ በነጻ ልቦና ፈጣሪ ንጹህ ወዳደረገው የውሃ አካል ይሄዳል። ኢሬቻ ቀልብ የሚነጻበት ቦታ ነው " ሲሉ ነው የሚያስረዱት።
____
በኢሬቻ ላይ የሚቀርበው ፀሎት እና ልመና ምንድነው ?
(ከአፍሪካ ፍልስፍና መምህሩ ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ (ዶ/ር) መጣጥፍ ላይ የተወሰደ) ፦
" ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን አሜን አሜን)
ሀዬ! የእውነትና የሰላም አምላክ!
ሀዬ! ጥቁሩና ሆደ ሰፊው ቻይ አምላክ!
በሰላም ያሳደርከን በሰላም አውለን!
ከስህተትና ከክፉ ነገሮች ጠብቀን!
ለምድራችን ሰላም ስጥ!
ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ!
ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን!
ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ!
ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን አሜን አሜን! "
____
" ከመጥፎ አየር ጠብቀን!
ንፁሕ ዝናብ አዘንብልን!
ያለአንተ ዝናብ የእናት ጡት ወተት አይሰጥምና!
ያለአንተ ዝናብ የላም ጡት ወተት አይሰጥምና!
ያለአንተ ዝናብ መልካው ውኃ አይሰጥምና!
ያለአንተ ዝናብ ምድሩ ቡቃያ አይሰጥምና!
ከእርግማን ሁሉ አርቀን!
እውነትን ትቶ ከሚዋሽ አርቀን!
ከረሃብ ሰውረን!
ከበሽታ ሰውረን!
ከጦርነት ሰውረን!
ልጄ እያሉ አልቅሶ ከመቅበር ሰውረን!
ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! "
የ2016 ዓ/ም የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ከንጋት ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያሰባሰበው ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ / ሪፖርተር ነው።
ተጨማሪ ቲክቫህ አፋን ኦሮሞ ፦ https://t.iss.one/+UTMftkYHBuOGaQ23

#ትግራይ " 1,329 የሚደርሱ ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን አረጋግጠናል " - መቐለ ዩኒቨርሲቲ እና የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት በትግራይ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ግጭት ካበቃበት ካለፈው የጥቅምት ወር አንስቶ ‘ቁጥራቸው 1,329 የሚደርሱ ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን አረጋግጠናል’ ሲሉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች አስታወቁ። የአካባቢ የጤና ባለስልጣናት እና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ባካሄዱት…
#ትግራይ
" የጥናት ውጤቱ አስደንጋጭ ነው " - የትግራይ ክልል ጤና ምርመር ኢንስቲትዩት
የትግራይ ክልል ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አካሄድኩት ባለው ጥናት በ9 ወረዳዎች እና በ53 መጠለያዎች ባሉ ተፈናቃይ ወገኖች ብቻ በርካቶች በረሃብ እየሞቱ እንደሆነ ገልጿል።
ምንም እንኳን በክልሉ ከጦርነት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ሁኔታ በረሃብ የሰው ህይወት እየጠፋ እንደሆነ ቢታወቅም የጥናቱ ውጤት እጅግ አስደንጋጭ እንደሆነበት ኢንስቲትዩቱ አመልክቷል።
እንደ ጥናቱ ውጤት ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በረሃብ እየሞተ ያለው ሰው ቁጥር ከ60 በመቶ በላይ መሆኑ ተገልጿል።
በ9 ወረዳዎች በተደረገው ጥናት ከ1300 በላይ ወገኖች መሞታቸው ተገልጿል።
በረሃብ እየሞቱ ካሉት ውስጥ ከገዛ ቄያቸው ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችም ይገኙበታል ብሏል።
እንደ ሪፖርቱ አሁን ላይ ከ60 % በላይ ህብረተሰብ በመካከለኛ እና የከፋ ረሃብ ላይ እንደሚገኝ ያመለክታል።
የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሃየሎም ካህሳይ የጥናቱን ውጤት በተመለከተ በሰጡት ቃል ፤ " ረሃብ እንዳለ ሰው እየሞተ እንዳለ እናውቃለን፤ እንጠብቃለን በዚህ ደረጃ ሰው እያለቀ መሆኑን አልተገነዘብንም ነበር " ብለዋል።
" የጥናቱ ውጤት ለኛ አስደንጋጭ ነው " ያሉት ዶ/ር ሃየሎም " ምናልባት ሁሉን ነገር አቁመን ይህን ሁኔታ ማስቆም እንዳለብን ነው የተረዳነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ጥናታችን በ9 ወረዳዎች እና በ53 መጠለያ ጣቢያዎች ብቻ ነው ፤ ጥናቱ የተካሄደው ደግሞ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ ባሉት 9 ወራት ነው።
በዚህም በ9 ወረዳዎች 2,694 ሰዎች እንደሞቱ ነው ዳታ ያገኘነው ቤት ለቤት ዞረን። የዓለም ጤና ድርጅትን የመለያ መንገድ ተጠቅመን 1329 በረሃ እንደሞቱ ነው ያረጋገጥነው። ይህ ደግሞ 68.3 በመቶውን ይይዛል።
ይሄ እንግዴ በ9 ወር ውስጥ በ9 ወረዳዎች ብቻ ነው፤ ሳይንሱም ስለሚደግፈው ያን ፕሮጀክት ስናድረገው ወደ 76 ወረዳዎች አጠቃላይ ሞት 16,342 ነው የሚጠበቀው ከነዚህ ውስጥ በረሃብ የሞቱ ተብለው የተሰሉ 7,949 ነው ይሄ በጣም አስደንጋጭ ቁጥር ነው " ብለዋል።
በጥናቱ የህብረተሰቡ የምግብ ሁኔታ ምን ይመስላል ? የሚለውን የዳሰሰ ሲሆን 60 በመቶ አካባቢ መካከለኛ ወይም ከፍተኛ የምግብ ችግር እንዳለበት አሳይቷል።
የትግራይ ክልል ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት በረሃብ እያለቀ ያለውን ህዝብ ለመታደግ መንግሥት እና የሚመለከቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲወስዱ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲቀርብ፣ ተፈናቃዮችም ወደቄያቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ ጠይቋል።

Photo
" በዓሉ #በሰላም ተጠናቋል " - ግብረ ኃይሉ
የ2016 የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ #በሰላም መከበሩን የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።
ግብረ ኃይሉ ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል ያለድ የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ #መጠናቀቁን ገልጿል።
የነገው የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓለም በተመሳሳይ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እና ለፀጥታ ኃይሉ እገዛውን እንዲያጠናክር ተጠይቋል።

#ዓለምአቀፍ
ሃማስ እስራኤል ላይ ድንገተኛ የተባለ ጥቃት መክፈቱ ተሰማ።
የፍልስጤሙ ሃማስ በዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለ ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።
ሃማስ ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል 5000 ሮኬቶችን ያስወነጨፈ ሲሆን የሰው ህይወት መጥፋቱም ተነግሯል።
እየሩሳሌምን ጨምሮ በደቡባዊ እና መካከለኛው እስራኤል የማስጠንቀቂያ ድምፅ እየተሰማ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጸጥታ ባለስልጣናትን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል ተብሏል።
የሃማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ መሐመድ ዴይፍ በሃማስ ሚዲያ ቀርበው " የአልአቅሳ ማዕበል ኦፕሬሽን " በሚል ወታደራዊ ዘመቻ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
" በየቦታው ያሉ ፍልስጤማውያን እንዲዋጉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዲፍ " በቃ ልንል ወስነናል " ያሉ ሲሆን ሁሉም ፍልስጤማውያን እስራኤልን እንዲጋፈጡ አሳስበዋል።
" ይህ በምድር ላይ የመጨረሻውን ወረራ ለማስወገድ ታላቅ ጦርነት የሚካሄድበት ቀን ነው " ብለው እስካሁን 5,000 ሮኬቶች ተወንጭፈዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ሃማስ ኦፕሬሽኑ በአል-አቅሳ እየተካሄደ ላለው ትንኮሳ እና በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ በፍልስጤም እስረኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ምላሽ ለመስጠት ነው ብሏል።
በደቡባዊ እስራኤል በሲዴሮት ከተማ የታጠቁ ተዋጊዎች በአላፊ አግዳሚ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የፍልስጤም ዩኒፎርም የለበሱ ተዋጊዎች በድንበር ከተማ ውስጥ ግጭት ሲፈጥሩ እንዲሁም የሚነድ የእስራኤል ታንክ ታይቷል።
" ሃማስ ለድርጊቱ እጅግ ከባድ ዋጋ ይከፍላል " - እስራኤል
የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ የሚኖሩ እስራኤላውያንን በቤታቸው እንዲቆዩ አሳስቧል።
ሃማስ "ለድርጊቶቹ እጅግ ከባድ ዋጋ " እንደሚከፍል ዝቷል።
ጦሩ ሃማስ ላይ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተነግሯል።
" ከዚህ ጥቃት ጀርባ ያለው ሃማስ፣ ለቀጣይ ውጤት እና ክስተቶች ሁሉ ሃላፊነቱን ይወስዳል። " ያለው የእስራኤል ጦር ' ሰራዊቱ ለጦርነት ዝግጁ " እንዲሆን አውጇል።
አሜሪካ ሁኔታውን ብቻ ቅርበት እየተከታተለች እንደሆነ አሳውቃለች።
@tikvahethiopia