TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FireAlert - አዲስ አበባ ለቡ ጀርባ ትራኮን 75 የሚባለው አካባቢ በሚገኝ አንድ እየተሰራ ባለ የትራኮን ሪል ስቴት ህንፃ የእሳት አደጋ መነሳቱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።

በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ምንም እንኳን የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች በስፍራው ቢገኙም እሳቱ እስካሁን እንዳልቆመ አስረድተዋል።

ቪድዮ - Al3X (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
" በዓመት 44,000 በላይ የሚሆኑ የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ " - ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ

በኢትዮጵያ የካንሠር በሽታ #የከፋ_ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ ማኅበረሰቡ ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ አሳስቧል።

የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " በእኛ አገር ሕሙማን ራሳቸውን ስለሚደብቁና ታክሞ መዳን አይቻልም ስለሚባል በሽታው በጣም እየከፋ ነው " ብለዋል።

ማኅበረሰቡ ወደ ሕክምና ተቋም በወቅቱ በመምጣት ከሕመሙ መዳን እንደሚችል ሊያውቅና ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም ተጠይቋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ " በአሜሪካን አገር ግን ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ታክመው ድነው ሕይወታቸውን እየመሩ ነው " በማለት ከበሽታው መዳን እንደሚቻል አስረድተዋል።

አክለውም፣ " በኢትዮጵያ ሕሙማን ወደ ሕክምና ተቋም አለመምጣታቸውና ታክሞ መዳን እይቻልም የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ በመኖሩ ወደ 75 በመቶ የሚሆኑት ሕሙማን ሕይወታቸው ያልፋል " ነው ያሉት።

የድርጅቱ ሜዲካል ዳይሬክተር ናትናኤል አለማየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ባለፉት ዓመታት ውስጥ የካንሠር ሕሙማን ወደ ሕክምና የመምጣት ቁጥራቸው የመጨመር ሁኔታ ይታያል " ብለዋል።

አክለውም፣ " በየዓመቱ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሠር በሽታ ይያዛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 44,000 በላይ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ " ነው ያሉት።

"ከካንሠር ሕመም መዳን ይቻላል ተገቢዉን ምርመራ እና ህክምና በተገቢዉ ጊዜ በማድረግ መዳን ይቻላል" ያሉት ናትናኤል (ዶ/ር)፣ የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸው የሚያልፍበትን ምክንያት ሲያስረዱ፣ " ሕሙማን ወደ ሕክምና ማዕከል የሚመጡት የሕመም ደረጃቸው ከፍ ካለ፣ ሥር ከሰደደ፣ መዳን የሚቻልበት ደረጃ ካለፈ በኋላ ነው " ብለዋል።

በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ያለበት ምክንያት ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ናትናኤል (ዶ/ር)፦
- ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ መስፋፋት፣ በቂ ያልሆነ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤ መቀየር
- የሲጋራ፣ ሽሻ አጫሾች መበራከት የአልኮል መጠቀም
- ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ
-ከተለያዩ ኢንᎊክሽኖች ጋር የሚያያዙ የካንሰር አይነቶች መበራከት
- በወቅቱ ሕክምና ሳያገኙ የኖሩ ሰዎች አሁን አሁን ወደ ሕክምና እየመጡ በመሆኑና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።

ወደ ሕክምና የሚመጡት 70 በመቶ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን የህመሙ ደረጃ ከፍ ካለ እና ስር ከሰደደ መሆኑን ተናግረዋል። ለህሙማን ሁለንተናዊ የሆነ እንክብካቤ እና ድጋፍ ሁሉም ካለዉ ቀንሶ እንዲያደርግ፣ ማህበረሰቡም በካንሰር ላለመያዝ አጋላጮቹን መከላከል እና ቅድመ ምርመራ ላይ እንዲያተኩር አሳስበዋል።

ድርጅቱ የ20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዛሬው ዕለት በማሪዮት ሆቴል ያከበረ ሲሆን፣ ድርጅቱ እስካሁን ከ3,000 ሺሕ በላይ የካንሠር ሕሙማን እንዳከመ፣ በአሁኑ ወቅት ከ150 በላይ ሕክምና የሚጠባበቁ እንዳሉ ተነግሯል።

መረጃው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

አዲስ አበባ ፤ ከለቡ ሙዚቃ ቤት ጀርባ / ሃጫሉ ጎዳና " ትራኮን ሪል እስቴት " #እያስገነባው ባለዉ አፓርታማ ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ እስካሁን በሰው ላይ ጉዳት አለማድረሱን እና እሳቱ ወደሌሎች ቦታዎች ተዛምቶ የከፋ ጉዳት እንዳይደረስ ማድረግ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

እንደ ኮሚሽኑ መረጃ እሳቱ የተነሳው 5ኛ እና 6ኛ ፎቅ ላይ ነው።

እሳት አደጋው በምን ሳቢያ እንደተነሳ የተባለ ነገር የለም።

ከደቂቃዎች በፊት መልዕክት የላኩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የአካባቢው ቤተሰባች እሳቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መጥፋቱን በቪድዮ አስደግፈው አሳውቀዋል።

#Update በአደጋው 2 የእሳት አደጋ ሰራተኞች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንደኛዉ ሰራተኛ እሳቱን በማጥፋት ሂደት ከህንጻዉ ላይ ወድቆ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁን ሰዓት በአለርት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

የእሳት አደጋው በንብረት ላይ ከባድ ጉዳትም አድርሷል።

ቪድዮ 1. የእሳት አደጋው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከጠፋ በኃላ የተቀረፀ።

ቪድዮ 2. የእሳት አደጋው ተባብሶ በነበረበት ወቅት ከመንገድ ላይ የተቀረፀ።

Credit - Al3X / Ali (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

የአቢሲንያ ባንክን የተለያዩ አገልግሎቶች አጠቃቀም እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ከዚህ ጋር የተያያዘውን ሊንክ በመጠቀም ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.iss.one/BoAEth
#TPLF

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አካል የሆነው ፓለቲካዊ ውይይት በአስቸኳይ በተጠናከረ መልኩ እንዲጀመር ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት ጠየቀ።

ድርጅቱ ለአንድ ሳምንት ያህል ዝግ ስብሰባ ሲያካሄድ ቆይቶ ትላንት ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል።

ህወሓት መስከረም 14 /2016 ዓ.ም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ ፥ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ህዝቡ ከጥይት ድምፅ ርቆ ተነፃፃሪ ሰላም ማስገኘቱንና ስምምነቱ ተከትሎ  የቴሌ ፣ የባንክ ፣ የመብራት ፣ የአውሮፕላን እና በተወሰነ መልኩ የየብስ የትራንስፓርትና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች መጀመር መቻላቸው በማስታወስ የሰላምን ውድ ዋጋ አወድሷል።

የሰላም ሂደቱ በፅኑ መሰረት እንዲቀመጥ እንዲደለድልና በሙሉነት እንዲተገበር በማድረግ የህዝብ ስቃይ እንዲቀረፍ በማስቻል በኩል አሁንም ብዙ ይቀራል ያለው መግለጫው ፤ የህዝብ ስቃይ ሙሉ በሙሉ ማስቆም የሚያስችል ፦
-  የተቀናጀ ፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል እንዲካሄድ
- ነፃ ያልወጣው ህዝብ በአስቸኳይ ነፃ እንዲወጣ የሚያስችል ስራ እንዲሰራ
- ተፈናቅሎ በየማረፍያ ማእከላት የሚገኝ ህዝብ ወደ ቄየው ተመልሶ መደበኛ ኑሮው እንዲመራ እንዲደረግ
- ተጠያቂነት ተረጋግጦ የተበደለ እንዲካስ የሚያደርግ ትግል እንዲካሄድና ፓለቲካዊ ውይይት ተቋማዊ ሆኖ በአስቸኳይ እንዲጀመር በተደራጀ መልኩ እንዲመራ ወስኛለሁ ብሏል ህወሓት በመግለጫው። 

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውጤት የሆነው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በሁለንተናዊ መንገድ እንደሚደግፍና እንደሚያጠናክር ያረጋገጠው የህወሓት መግለጫ ፤ የፌደራል መንግስት ትግራይ የደረሰባት ውድመት የሚመጥን በጀት እንዲመደብ ፣ የክልሉ ፀጋዎች የሚያጎለብት የህዝቡን ችግር የሚቀርፍ የማገገም እና የመልሶ ግንባታ ስራ ሳይውል ሳያድር እንዲጀመር በፅኑ ለመታገል ወስኛለሁ ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በማንነታቸው ብቻ በእስር የሚገኙ ትግራዎት እንዲፈቱና የተበደሉ ፍትህ እንዲያገኙና እንዲካሱ ለማስቻል ከበፊቱ የጠነከረ ፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ መወሰኑን ገልጿል።

የህወሓት መግለጫ ለትግል አጋሮቹ ባስተላለፈው ባለ 7 ነጥብ ጥሪ ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ' ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ' በአገራቸው እና በአከባቢያቸው ሰላም እንዲሰፍን ያላቸው ከፍተኛ ጉጉትና ፍላጎት በመግለፅ ከሁሉም ህዝቦች በሰላምና በአብሮነት ለመስራት ዝግጁ መሆናችን ደጋግመን እናረጋግጣለን " ሲል መግለፁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

More - @tikvahethiopiatigrigna
                         
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መውሊድ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነገ ረቡዕ የሚከበረውን የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) 1498ኛ ዓመት የልደትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ምክር ቤቱ በዚህ መግለጫው ፤ " እኛ ሙስሊሞች ይህን ታላቅ በዓል ሲያከብር አላህ (ሱ.ወ.) ለመልእክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) መርጦ ያላበሳቸውን መልካም ስነ-ምግባራት በመላበስና ለሌሎችም አርኣያ በመሆን፣ ሱናቸውን (ፈለጋቸውን) ሕያው በማድረግ መርኅ ሊሆን ይገባል " ብሏል።

" ከምንም ነገር በላይ ከታላቁ ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ) አስተምህሮና ከሕይወት ፈለጋቸው አኳያ ራሳችንን ከመፈተሽ ባሻገር ፦
- የተቸገሩትን በመርዳት፣
- የታመሙትን በመጎብኘት፣
- ቅስማቸው የተሰበረ የኅብረተሰብ ክፍሎችን አለንላችሁ በማለትና በመደገፍ፣
- የሕግ ታራሚዎችን በመጠየቅ፤
- በመሃከላችን የተፈጠሩ ልዩነቶች እና አለመግባባቶችን ለአላህ ብለን በመተው፣ ዐውፍ በመባባል፣ ፍቅራችንንና እንድነታችንን በማደስና ብሎም ከመልእክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) በወረስነው ባህርይ መሠረት ከእምነቱ ውጭ ላሉ ወገኖች ጭምር ረሱላችን (ሶ.ዐ.ወ) ለዑመታቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ ርኅራኄ እና እዝነትን በመግለጽ ጭምር ሊኾን ይግገባል " ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም ዕለቱን ልዩ ልዩ የግልና የቡድን ዒባዳዎችን በመፈፀም፣ ለሰው ልጆች በአጠቃላይ፣ በተለይም ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟ እንዲሟላ፣ አስተማማኝ ደኅንነት እንዲሰፍንባት፣ የተሟላ ፀጋ ይለግሳት ዘንድ ፈጣሪያችንን አላህ (ሱ.ወ.) በመማጸን እስላማዊ አደብን በጠበቀ መልኩ እንድናሳልፈው አደራ ለማለት እንወዳለን ብሏል ምክር ቤቱ።

እነዚህን ማድረግ በሚገባበት በዚህ ጊዜ ፣ በተቃራኒው ሌሎች ሰዎችን በማንጓጠጥ፣ በመወረፍና በመዝለፍ ላይ መዘውተር፣ የነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ.) አስተምህሮ በሚቃረን ተግባር ላይ መሰለፍ ስለሚኾን፣ ከዚህ ዓይነቱ ባህርይ እጅግ መጠንቀቅና መራቅ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ይነበብ

ኢትዮጵያ ውስጥ የካንሠር በሽታ #የከፋ_ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ ማኅበረሰቡ ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ አሳስቧል።

የካንሠር ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ያለው ለምንድነው ?

የድርጅቱ ሜዲካል ዳይሬክተር ናትናኤል አለማየሁ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ የዓመቱ ወደ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሠር በሽታ ይያዛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 44,000 በላይ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ።

በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ያለበት ምክንያት ፦

- ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ መስፋፋት፣

- በቂ ያልሆነ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤ መቀየር

- የሲጋራ ፣ ሽሻ አጫሾች መበራከት ፣ የአልኮል መጠቀም

- ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ፣

- ከተለያዩ #ኢንᎊክሽኖች ጋር የሚያያዙ የካንሰር አይነቶች መበራከት

- በወቅቱ ሕክምና ሳያገኙ የኖሩ ሰዎች አሁን አሁን ወደ ሕክምና እየመጡ በመሆኑና ሌሎች መሰል ምክንያቶች ናቸው።

ወደ ሕክምና የሚመጡት 70 በመቶ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን የህመሙ ደረጃ ከፍ ካለ እና ስር ከሰደደ በኃላ ነው።

ዶ/ር ናትናኤል ፤ " ከካንሠር ሕመም መዳን ይቻላል " ያሉ ሲሆን ይህም ተገቢዉን ምርመራ እና ህክምና በተገቢዉ ጊዜ ማድረግ ሲቻል ፣ ስር ሳይሰድ ህክምና ካገኘ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ለህሙማን ሁለንተናዊ የሆነ እንክብካቤ እና ድጋፍ ሁሉም ካለዉ ቀንሶ እንዲያደርግ ፣ ማህበረሰቡ በካንሰር ላለመያዝ አጋላጮቹን መከላከል እና ቅድመ ምርመራ ላይ እንዲያተኩር አሳስበዋል።

@tikvahethiopia