TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከወዳጅ ዘመድዎ የሚላክልዎትን ገንዘብ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ቅርንጫፎች በኩል ይቀበሉ!
ሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተንቲባ ተሹሞላታል።

የከተማው አስተዳደር ምክር ቤት ፤ በግምገማ ከስልጣናቸው በተነሱት ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ምትክ ዛሬ አዲስ ከንቲባ ሾሟል።

አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ሲሆኑ ከተማይቱን በምክትል ከንቲባ ማእረግ እንዲያስተዳድሩ ተሹመዋል።

አቶ መኩሪያ የዛሬው ሹመት እስከተሰጣቸው ጊዜ ድረስ የሲዳማ ክልል ከተማ ልማትና ካንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ ተብሏል።

ከንቲባው በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሐላ ከፈፀሙ በኃላ ካቢኔያቸው አፀድቀዋል።

ላለፉት ዓመታት ሀዋሳን ሲያስተዳድሩ የነበሩት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቅርቡ በተደረገ የአመራሮች ግምገማ በ " ብልሹ አሰራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " በሚል ከስልጣን ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሲዳማ የሲዳማ ክልል መንግሥት ፤ " የተሰጣቸውን የመንግስትና የህዝብ አደራ ወደ ጎን በመተው በሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ ተሳትፈዋል " ባላቸው አመራሮች ላይ የፖለቲካ ውሳኔ መተለለፉን አሳወቀ። ክልሉ እኚሁ አመራሮች እንደየሥራቸው ከህግ ተጠያቂነት አያመልጡም ብሏል። የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት  አቶ ደስታ ሌዳሞ በሰጡት መግለጫ ፤ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡና በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ…
" ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም " - ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ

በከንቲባነት ዘመኔ ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም አሉ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሬፌሰር ፀጋዬ ቱኬ።

የቀድሞ ከንቲባ ይህ ያሉት ዛሬ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባወጡት ፅሁፍ ነው።

በቅርቡ በተደረገ ግምገማ በ" ብልሹ አመራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " ከስልጣናቸው የተነሱት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ በእሳቸው ምክት አዲስ ከንቲባ በተሾመበት ዕለት ባሰራጩት መልዕክት በስልጣን ዘመናቸው ቅንጣት ታክል ጥፋት እንዳልሰሩ ገልጸዋል።

የቀድሞው ከንቲባ ፤ " እኔ በፈጣሪ ፊት የምመሰክረዉ እዉነት በከንቲባነት ዘመኔ ህዝቤን የሚጎዳና የማይጠቅም የተቀመጥኩለትን አላማ የሚያጎድፍ ቅንጣት ጥፋት አልሰራሁም ብዬ አምናለሁ " ብለዋል።

" ምናልባትም የግለሰቦችን የጥቅም ፍላጎት ካለማርካት በቀር፤ እኔን ማሳደዱ የስልጣን ፍላጎትና የእዉቅና ሽሚያ ካልሆነ በስተቀር ፣ በክልሉ ይፋ ያልወጡ በህዝብ እንባና ላብ የከበሩ እንኳን ህግ ፈጣሪም ይቅር የማይለዉ  ወንጀል/ጥፋት የፈጸሙ የህዝብን ሀብት በሽፋን የሚዘርፉ አካላት አሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም እነዚህ አካላት " የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በቅርብ  ይፋ ይወጣሉ። " ብለዋል።

የቀድሞው ከንቲባ " በህዝብ እምባ እና ላብ የከበሩ " ስላሏቸው አካላት ስም አልገለፁም።

በሲዳማ ክልል ያለዉ ነባራዊ ሁኔታ በብልፅግና ፓርቲ መርህ  ሕዝብን ማገልገል የሚያስቸግር ነው ያሉት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ፤ " ቡድንተኝነትና በሴራ ፓለቲካ የተተበተበ፤ በመሆኑ እኔም ሆንኩ በተሻለ አፈጻጸም ላይ የነበሩ አመራሮች የፓርቲን መርህ ባልተከተለ መልኩ ከኃላፈነት ተነሰተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እድል ያገኘን ቀን እዉነቱን በቅርቡ በፈጣሪ እና  በህዝባችን ፊት ቆመን በመረጃና በማስረጃ እንታገላለን " ብለዋል።

አሁን ያለዉ የክልሉ የፖለቲካ ጉዞ ሁኔታ ይህንን ማድረግ የሚያስችል እንዳልሆነ የገለፁት ረ/ፕ ፀጋዬ ፤ በቤተሰባቸው  ላይ ለሚደርሰዉ አንዳች እንግልትና ጉዳት ተጠያቂዉ የክልሉ መንግስት እንደሆነ ገልጸዋል።

ወደፊት ሀገራቸው በምትፈልጋቸው ቦታና ግዜ ህዝብን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ሀዋን ለ3 ዓመታት የመሩት የቀድሞው ከንቲባ ባሰራጩት ፅሁፍ ለአዲስ ተሿሚ አካላት መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተዋል።

ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ በአመራሮች ግምገማ ወቅት ከስልጣን እንደተነሱ እና በህግ እንደሚጠየቁ ይፋ ከተደረገ በኃላ አንድ የክልሉ ባለሥልጣን ረ/ፕ ፀጋዬ " የት እንዳሉ " እንደማያውቁ መናገራቸው ይታወሳል።

በበኃላም የቀድሞው ከንቲባ የት ሀገር እንደሚገኙ በግልፅ ሳይናገሩ በህክምና ክትትል ላይ እንዳሉና በቅርቡ በህዝብ መኃል ተገኝተው እውነታውን እንደሚያጋልጡ መግለፃቸው አይዘነጋም።

በሲዳማ ክልል ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በተለይም ወጣቶች ክልሉ በብልሹ አሰራር ፣ እንዲሁም በሙስናና በትውውቅ በሚሰሩ ስራዎች ነዋሪዎችን እያማረረ መሆኑን እና ከላይ እስከ ታች ያሉት አመራሮች እያንዳንዳቸው እንዲገመገሙና አመራራቸውም እንዲፈተሽ መጠየቃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
The Jasiri Talent Investor, equips aspiring entrepreneurs with a toolkit to help them start high-impact ventures! 🛠 From discovering your 'why,' team formation, opportunity identification, systems thinking, responsible entrepreneurship, to venture creation.

Apply now for Cohort 5 and propel your entrepreneurial journey, https://jasiri.org/application

Join our telegram Channel https://t.iss.one/jasiri4ethiopia
#itel_Mobile

ከፍተኛ ሜሞሪ አቅም ያለው ስልክ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ይሄው አዲሱ አይቴል S23+!

16ጂቢ ራም ከ 256ጂቢ የሜሞሪ የተገጠመለት አዲሱ አይቴል ኤስ23+ እንከን የለሽ አገልግሎት እንዲስጥ ታስቦ እና በአንድ ጊዜ ብዙ ስራዎችን መስራት እንዲችል ተደርጎ የተመረተ የሞባይል ስልክ ነው።  አይቴል ኤስ23+ ስልክ ከፍ ያሉ ግራፊክስ ያላችውን ጌሞች ብሎም ማንኛውንም መተግበሪያዎች በአስተማማኝ ፍጥነት ማስተናገድ የሚያስችለው ፕሮሰሰር ተመራጭ ያደርገዋል።

አይቴል ሞባይል
#ItelMobile #ItelEthiopia #S23+
Follow Us :  Facebook Instagram
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ !

የአዲስ አበባ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማህበር (አአፎባማ) ከግራር የጠቢባን መነሃሪያ እንዲሁም ከUSAID ጋር በመተባበር የዘወትሯ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተጓዥ የፎቶግራፍ አውደርዕይ አዘጋጅቷል።

ይህ አውደርዕይ በሚካኤል ጸጋዬ ዋና አዘጋጅነት የቀረበ ነው።

የመጀመርያ ዙር ቆይታውን በባህርዳር ያደረገው የዘወትሯ ኢትዮጵያ ተጓዥ የፎቶግራፍ አውደርዕይ አሁን ወደ #ድሬዳዋ አቅንቷል።

ከነሃሴ 30 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ለአምስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ላይ 15 የሚሆኑ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች በአጠቃላይ ከ90 በላይ በስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። በቀጣይ ሐዋሳ ላይ ከመስከረም 3 - 7/2016 መዳረሻውን ያደርጋል።

በተዘረሩት ቀናት ላይ በፎቶ አውደርዕዩ ላይ በመገኘት የዘወትሯን ኢትዮጵያ አብረውን ይቃኙ! ኑ! የአንድነታችንን ውበት በጋራ እናድንቅ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ወጥቷል።

4 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0140621904 ሆኖ ወጥቷል።

👉 4 ,000,000 ብር - 0140621904
👉 2,000,000 ብር - 0140163695
👉 1,000,000 ብር - 0140946766
👉 700,000 ብር - 0141151136
👉 350,000 ብር - 0140607557
👉 250,000 ብር - 0140928442
👉 175,000 ብር - 0140869502
👉 100,000 ብር - 0141124088

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

@tikvahethiopia
#ሽንኩርት

በቤንች ሸኮ ዞን የደቡብ ቤንች ወረዳ ገበሬዎች ለሚያመርቱት የሽንኩርት ምርት የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።

በተለያየ ጊዜ ሽንኩርት በሀገሪቱ ያሉ ገበያዎች ላይ ከዋጋዉ መናር ባለፈ የአቅርቦት ችግሩም ጎልቶ ሲነሳ ይታያል።

በቤንች ሸኮ ዞን የተመረተው የሽንኩርት ምርት ግን የሚያነሳዉ አጥቶ ሊበላሽ መሆኑ ገበሬዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተናግረዋል።

ዞኑ በኩታ ገጠም አሰተራረስ ስልት ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ዉጤታማ ከሆኑ ወረዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን የደቡብ ቤንች ወረዳ ደግሞ ግንባር ቀደም ነው።

ይሁንና የገበያ ትስስር አለመኖሩ ሽንኩርቱ ከማሳ ሳይነሳ ይቆይ ዘንድ ምክንያት ሆኗል።

በመሆኑም የወረዳዉ ገበሬዎች ሽንኩርቱ ከመበላሸቱ በፊት የሚመለከተዉ አካል ለኛም ሆነ በሀገር ደረጃ ፋይዳ ያለውን ሸንኩርት እንዲነሳ እንዲያደግ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህ አመት በሰሩት ጠንካራ ስራ በሄክታር 1200 ኩንታል ሽንኩርት መገኘቱንና ባጠቃላይ 1622 ሄክታር መሬት በምርት መሸፈናቸዉን ገልጸዋል።

የገበያ ትስስሩን በተመለከተ በተደጋጋሚ መጠየቃቸዉን የሚገልጹት ገበሬዎቹ በዚህ ምክኒያት ችግር ላይ መዉደቃቸዉን ያነሳሉ።

የደቡብ ቤንች ወረዳ አስተዳደር  በበኩሉ የዞንና የክልል የንግድ ማህበራት እንዲሁም  በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነጋዴዎች ፣ በተማሪ ምገባ ፕሮግራም የሚሳተፉ ትምህርትቤቶችና የከተማ መስተዳድሮች  የሰንደይ ማርኬቶች ሽንኩርቱን በማንሳት ገበሬዉን በማገዝ ራሳቸዉም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጥሪዉን ያስተላለፉት የወረዳዉ ም/ አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ተስፋዬ እንደገለጹት ባካባቢዉ ካሁን በፊት ባልነበረ መልኩ ከፍተኛ የሽንኩርት ምርት መመረቱን ጠቅሰዉ ለገበሬዉ የንግድ ትሰስር ለመፍጠር አየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ቤተሰብ ሀዋሳ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ዜጎች በኑሮ ውድነት / በዋጋ ንረት ምክንያት ክፉኛ እየተማረሩ፤ እየተቸገሩ ይገኛል።

በተለይም የምግብ ነክ ምርቶች ላይ በየጊዜው የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ዜጎች ኑሯቸውን ከባድ ካደረገው ቆይቷል።

ከምንም በላይ በዚህ ወቅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ተስኗቸዋል።

ልጆች ወልደው ለማሳደግ ፣ ለማስተማር፣ ፣ በልቶ ለማደር፣ ህልማቸውንና ሀሳባቸውን ለማሳካት በየጊዜው አየናረ ያለው የኑሮ ውድነት ለዜጎች እንቅፋት ሆኗል።

የዋጋ ንረትን በተመለከተ አሀዱ ሬድዮ ዛሬ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን ጠቅሶ ባሰራጨው አንድ ዘገባ ላይ ፤ ሚኒስቴሩ " የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠንና የፀጥታ ችግር ለንግድ ስርአቱ እንከን ሆኖበታል " ብሏል።

ህዝቡን እያማረረ ላለው የኑሮ ውድነት ምክንያት " በክልሎች የሚፈጠረዉ የሰላም መደፍረስ እንዲሁም የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን " እንደሆነ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በልሁ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

" መንግስት የኑሮ ዉድነት እንዳለ ያምናል " ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዉ " ፍላጎትን የሚያሟላ አቅርቦትን ለማከናወን ከዉጭም ከዉስጥም ያለዉ ችግር እንከን ሆኗል " ብለዋል።

ሆኖም እነዚህ ተግዳሮቶች እንዳሉ ሆነዉ፤ ህብረት ስራ ማህበራት በቀጥታ ከቦታዉ ምርት አምጥተዉ እንዲያሰራጩ ስምምነት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
መላው የኦርቶዶክስ ልጆች አዲሱን ዓመት በዘፈንና ዳንኪራ ሳይሆን በቤተክርስቲያናቸው በጸሎት ፣ በምህላ፣ የቻለም ደግሞ በመጾም፣ እግዚአብሔርን በመመለመን እንዲቀበሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አስተላለፈች።

ቤተክርስቲያን ይህን ጥሪ ያስተላለፈችው የአዲሱን ዓመት አቀባበል በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ ነው።

በዚህም የጷጉሜን ወር ፮ ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ ታውጇል።

ቤተክርስቲያን ፤ ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾምና በጸሎት እንዲያሳልፉ ስትል ጥሪዋን አቅርባለች።

ምዕመናን በዚህ ወቅት ከዘፈን እና ከዳንኪራ እንዲርቁ አሳስባለች።

ብፁህ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ ፤ " አንዳንድ የዘፈን ግብዣዎችን እየሰማን ነው ፤ ሀገር በሚያልቀስበት፣ የንፁሃን ደም በሚፈስበት ሰቆቃ በበዛበት ረሃብ ችግር በሰፈነበት የዳንኪራ ግብዣ እየሰማን ነው " ብለዋል።

" ለምንም የማይጠቅሙ ብዙ ነገሮች እየተስተጋቡ ነው " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይህን እየሰማን ያለነው መደፋፈሩ በዝቶ ፣ ከመጠን በላይ ኑሮ፣ ንቀቱ በዝቶ፣ ማንአለብኝነቱ እንደልብ ተናጋሪው ፣ ፀብ አጫሪው ሃይ የሚለው ጠፍቶ ብዙ ነገሮች እየተደረጉ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው አለኝ ባሉት መረጃ " ቤተክርስቲያን ዘቅዝቆ እሳት ያያያዘ ፣ መስቀል ዘቅዝቆ አንገቱ ላይ ያጠለቀ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊዘፍን ተዘጋጅቷል፤ ግብዣም ተደርጓል። " ብለዋል።

" የሰዎችን መብት መንካት ስለማንችል እንደ ኢትዮጵያውያን እገሌ እገሌ ሳይል ከእንዲህ አይነቱ ማንም ተካፋይ ሳይሆን እንደ ኦርቶዶክሳዊያን ዳግሞ የኦርቶዶክስ ልጆች ለፀሎት ታውጇል ፣ ለጾም ለጸሎት እራስን ከማዘጋጀት ውጭ ምንም ትርፍ የሌለው ከሳንቲም ውጭ ትርፍ ለሌለው የሀገርን ገፅታ የሚንድ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ከመሆን #እንድትቆጠቡ " ብለዋል።

" አባቶቻችን ቅድሚያ የሚሰጡት ለጾም ፣ለጸሎት ለፍቅር፣ ለሰላም ነው ፤ ውሃ ሙላት እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚሉት አባቶች በዘፈን እና በዳንኪራ እያሳሳቀ ወደ ሞት፣ ወደ ማዕበሉ የሚገፋ ነገር ላይ ተሳታፊ እንድንሆን ቤተክርስቲያን አትፈቅድም ፣ የሃይማኖት ሰዎችም ድርሻ አይደለም " ሲሉ አስግዝበዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ " እኔ ምን አገባኝ በሚል በዘመናዊ ስሜት እንደልብ ተካፋይ መሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ነውር ነው ፤ ወንጀልም ነው " ያሉ ሲሆን " ፀብ አጫሪ መሆንም አስፈላጊ ስላልሆነ የኦርቶዶክስ ልጆች በቤታችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ተቀመጡ፤ የሚመለከተው እንደፈለገ ይሁን ፤ ኦርቶዶክሳውያን ከቤተክርስቲያናችሁ ተገኝታችሁ ጸልዩ፣ እግዚአብሔርን ለምኑ አብረን ተያይዘን እንዳንጠፋ " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በጳጉሜን 6 ቀናት ሁሉም ምዕመናን እግዚአብሔር መጪውን ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ የአንድነት፣ ብሶተኛ የማይኖርበት ተራብኩ ተጠማሁ ተፈናቀልኩ ተሰቃየሁ ተንገላታሁ የሚል የማይኖርበት ፣ ኢትዮጵያውያን በፍቅር በአንድነት የምንኖርበት ዘመን እንዲሰጠን ጸሎት በማድረግ እናሳልፍ ስትል አደራ ብላለች።

ጸሎት ለሁሉም የታወጀ ሲሆን ፤ ጾምን በተመለከተ የወደደ ይጹም ፤ ያልወደደም / ፕሮግራሞች ቀደሞ የያዘም እንዲጾም አይገደደም በነፃነቱ መጠቀም ይችላል ተብሏል።

@tikvahethiopia