TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ተጀመረ ! በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ10,000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል። ሀገራችን ፦ - በአትሌት በሪሁ አረጋዊ - በአትሌት ሰለሞን ባረጋ - በአትሌት ይስማው ድሉ ተወክላለች። ውድድሩን በብሔራዊ ቴሌቪዥን መዝናኛ ቻናል እንዲሁም በDSTV 226 ላይ መመልከት ይቻላል። ድል ለሀገራችን ! ድል ለአትሌቶቻችን ! @tikvahethiopia
#Update

ውድድሩ ከጀመረ አንስቶ የኬንያ እና የዩጋንዳ አትሌቶች ከፊት መስመር ሆነው ዙሩን እያከረሩት ነበር።

ለተወሰነ ዙር በሪሁ አራጋዊ ወደፊት መጥቶ ዙሩን ሲመራ የነበረ ሲሆን አሁን መሪነቱን ኬንያውን ተረክበዋል።

ሌላኛው የሀገራችን ልጅ ይስማው ድሉ ከመሪዎቹ በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

ሰለሞን ባረጋ መጨረሻ ላይ የነበረ ሊሆንም አሁን ላይ #ወደፊት እየመጣ ነው።

አንድ ዩጋንዳዊ አትሌት አቋርጦ ወጥቷል።

አሁን 10 ዙር ይቀራል።

ድል ለሀገራችን !!

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ነሃስ ፤ በሰለሞን ባረጋ።

በሪሁ አረጋዊ አራተኛ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ነሃስ ፤ በሰለሞን ባረጋ። በሪሁ አረጋዊ አራተኛ። @tikvahethiopia
በ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነሃስ አገኝታለች።

ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘው አትሌታችን ነው።

ኡጋንዳ ውድድሩን በአንደኝነት ስትጨርስ ፤ ኬንያ ሁለተኛ ሆናለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነሃስ አገኝታለች። ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘው አትሌታችን ነው። ኡጋንዳ ውድድሩን በአንደኝነት ስትጨርስ ፤ ኬንያ ሁለተኛ ሆናለች። @tikvahethiopia
#Update

በአሁኑም የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ወርቅ ሊገኝ አልቻለም።

ዛሬ በተካሄደው ውድድር ሶስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ ነሃስ አገኝቷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በወንዶች 10000ሜ ወርቅ ያመጣችው እኤአ በ2011 በዴጉ የዓለም ሻምፒዮና በአትሌት ኢብራሂም ጄይላን አማካኝነት ነበር።

ከዛ በኃላ በወንዶች ዘርፍ ወርቅ ተገኝቶ አያውቅም።

ከኢብራሂም ጄይላን በፊት ተከታታይ 4 የዓለም ሻምፒዮናዎችን ወርቅ ያመጣው አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ነበር።

ዛሬ ውድድሩን ያሸነፈው ዩጋንዳዊው ጆሽዋ ቺፕቲጌ ለ3 ተከታይ ሻምፒዮናዎች ወርቁን ወስዷል።

ፎቶ፦ @tikvahethsport (ከሀንጋሪ ፣ ቡዳፔሽት)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአሁኑም የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ወርቅ ሊገኝ አልቻለም። ዛሬ በተካሄደው ውድድር ሶስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ ነሃስ አገኝቷል። ሀገራችን ኢትዮጵያ በወንዶች 10000ሜ ወርቅ ያመጣችው እኤአ በ2011 በዴጉ የዓለም ሻምፒዮና በአትሌት ኢብራሂም ጄይላን አማካኝነት ነበር። ከዛ በኃላ በወንዶች ዘርፍ ወርቅ ተገኝቶ አያውቅም። ከኢብራሂም ጄይላን…
" ህዝቡን ይቅርታ ነው የምንለው " - አትሌት ሰለሞን ባረጋ

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለቪኦኤ በሰጠው ቃል በውድድሩ ውጤት ብዙም ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጾ ፤ ስለተገኘው ውጤት " ይቅርታ " ጠይቋል።

" ብዙም ደስተኛ አይደለንም ፤ ወርቅ ነበር አስበን የመጣነው ፤ የአየሩ ሁኔታ ተፅእኖ አድርጎብናል ብዬ አስባለሁ፤ በአጠቃላይ ደስተኛ አይደለንም " ሲል ገልጿል።

የቡድን ስራ እና ታክቲክን በተመለከተም ፤ " የተሰጠን ሁለት ሁለት ዙር እንድንሄድ ነበር ከ15 ዙር በኃላ ያንን ልናደርግ ነበር ያሰብነው በሪሁ ትንሽ ቀደም ብሎ ወጣ ሩጫው ስለተያዘ ይመስለኛል ፤ ያን ከ15 ዙር በኃላ ብናደርግ በሪሁም የተሻለ ውጤት ያመጣ ነበር ፤ በሰራነው ልክ አይደለም ያገኘነው " ብሏል።

መጨረሻው ላይ ብር ሜዳሊያ ተገኘ ተብሎ ሲጠበቅ እንዴት ሶስተኛ ደረጃ ይዞ እንዳጠናቀቀ የተጠየቀው ሰለሞን " እኔ የጨረስኩ መስሎኝ ነበር ልጁን እያየሁት ነበር ስክሪን ላይ ጨርሼ የቆምኩ ነው የመሰለኝ እኔም በጣም ነው ያዘንኩት፤ ወርቁን ባጣ እንኳን ሁለተኛ የመሆን እድል ነበረኝ ፤ መጨረሻ ላይም የመደናቀፍ ነገርም በተጨማሪ ድካምም ነበር " ሲል አስረድቷል።

ሰለሞን ባረጋ ፤ " ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ነው የምለው ፤ የተሻለ ሰርተን ፊትለፊታችን ኦሎምፒክ አለ ለዛ ጥሩ እንዘጋጃለን " ብሏል።

የቡድን መሪ አትሌት ገዛኸኝ አበራ በበኩሉ ፤ አትሌቶች ከሚገባው በላይ የተዘጋጁበት እንደነበር ገልጿል።

" በእርግጠኝነት ወርቅም ብርም እናመጣለን ብለን አስበን ነበር የገባነው ፤ ነገር ግን ትልቁ ነገር እኛ ጋር ክረምት ነው እዚህ ደግሞ ኃይለኛ በጋ ነው ዛሬ ደግሞ በተለየ መልኩ ሙቀቱ 34 ዲግሪ የደረሰበት ነበር በዚህም በጠበቅነው ልክ ውጤት አልመጣም " ብሏል።

በውድድሩ ነሃስ እና ዲፕሎማ አግኝተናል ያለው ገዛኸኝ ፤ " ይሄ ውጤት ህዝቡም እንደተከታተለው በጣም መስዕዋትነት የተከፈለበት ፣ ስትራቴጂ የተነደፈበት አንዱን ውስጥ አስገብቶ እየተቀባበሉ ይሂዱ ባልነው መሰረት አድርገዋል ፤ እውነት ለመናገር ከአቅም በላይ ነበር፤ አትሌቶቻችን የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል ደስ የሚል ውጤት ተመዝግቧል " ሲል አስረድቷል።

" የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ወርቅ እንጂ የለመደው ብር እና ነሃስ ቅር ይለዋል። የተወዳደሩበትን የአየር ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባልን ፤ በአየር ሁኔታው ምክንያት ወርቅም ብርም አጥተናል፤ በቀረው ውድድር ጥሩ ውጤት እናመጣለን " ሲል ገልጿል።

አሰልጣኝ ም/ኮሚሽነር ሁሴን ሽቦ ደግሞ ለውድድሩ በቂ ዝግጅት ተደርጎ እንደነበር ነገር ግን በአየር ሁኔታው ምክንያት የሚፈለገው ውጤት እንዳልመጣ ገልጸዋል።

" አጋጣሚ የቀን ጉዳይ ሆኖ ወርቅ እና ብር ማምጣት አልቻልንም " ያሉት አሰልጣኝ ም/ኮሚሽነር ሁሴን ፤ ይሄ የሆነበት ምክንያት ውድድሩ የተደረገው በጠራራ ፀሀይ መሆኑና ሙቀቱም 34 ዲግሪ ስለነበር እንደሆነ ገልጸዋል።

የትላንቱ የሴቶች ውድድር ሙቀቱ 23 ዲግሪ እንዲሁም ምሽት 4 ሰዓት ገደማ በመደረጉ ትልቅ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።

" ልጆቼ (የ10 ሺህ ሜትር ወንድ አትሌቶች) ማድረግ የሚገባቸውን አድርገዋል፤ ለኔ ጀግኖች ናቸው ፤ ነገም ሌላ ቀን ነው መልሰን የኢትዮጵያን ህዝብ እንደምንክስ እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

ቃለመጠይቅ በቪኦኤ - ፅሁፍ በቲክቫህ ቤተሰብ የተዘጋጀ።

ፎቶ ፡ @tikvahethsport & VOA

@tikvahethiopia