TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከፓኪስታን - መካ በእግር . . .

የፓኪስታኑ ተማሪ ኡስማን አርሻድ ለሃጅ ሃይማኖታዊ ጉዞ ጃንጥላ እና በጀርባ ላይ የሚታዘል ሻንጣ ይዞ 4,000 ኪሎ ሜትር በእግሩ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ደርሷል።

አቅሙ ያለው ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለማሳካት የሚመኘውን የሃጅ ጉዞ ኡስማን አርሻድ በእግሩ በመጓዝ አውን አድርጎታል።

ጉዞውን የጀመረው ፤ ከትውልድ ከተማው የፓኪስታኗ ኦካራ ሲሆን፣ ስድስት (6) ወራትን ተጉዞ ነው መካ የደረሰው።

ቅዱሱን የሃይማኖታዊ ጉዞ በእግሩ የፈጸመው ኡስማን በሺዎ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በእግር በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ለመድረስ የተለያዩ አገራትን ማለትም ኢራን ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን (UAE) አቆራርጧል።

ኡስማን አርሻድ ስለ ጉዞው ምን አለ ?

" ሁሉም ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ #መካ መጥቶ የፈጣሪን ቤት ማየት ይነኛል።

የእኔ ምኞች ደግሞ በእግር ተጉዤ የፈጣሪንና የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)  መስጂድ ማየት ነበር።

ጉዞው ከባድ ነበር የኢራቅ ቪዛን ማግኘት ስላልቻልኩ ከኢራቅ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ለመግባት ጀልባ ነበር የተጠቀምኩት።

አንዳንድ ችግሮች ነበሩ መጥፎ የሆነ የአየር ሁኔታ እና በጉዞው ምክንያት እግር መቁሰል አጋጥሞኛል።

አብዛኛው መንገድ ሰው የማይታይበት እና መንደርም ሆነ ከተማ ያልነበረው ነው።

ጉዞዬን እንድቀጥል ያደረጉኝ መንገድ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎች ናቸው። ረጋ ብዬ ጉዞዬን መጨረስ እንዳለብኝ አበረታተውኛል።

ባገኘሁበት ቦታ ነበር የማድረው፣ በመስጂድ  ፣ በፍተሻ ጣቢያ ፣ በሆቴል፣ ወይም እንዳርፍ ከፈቀዱልኝ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል። አማራጭ ሳጣ ድንኳን ጥሬ በረሃ ላይ ብዙ ጊዜ አድሬያለሁ።

በመጨረሻም ከ6 ወር በኃላ ያሰብኩበት ደርሻለሁ።

ምንም ነገር ማድረግ ብትፈልጉ በራሳችሁ ተማመኑ።  ማንኛውንም ጉዞ እንድትፈፅሙ ፈጣሪ ይረዳችኋል። "

Via BBC - Al Jazeera

@tikvahethiopia
" ዝግጅቱ ተጠናቋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት #መጠናቀቁን አስታወቀ።

ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

በሚኒስቴሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ " የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እውቀትና ብቃት ለመለካት የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቋል " ብለዋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትክክለኛ ተፈታኞችን ቁጥር እንዲያጣራ በማድረግ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 95 ሺህ 755 እንዲሁም ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 74 ሺህ 776 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎቸ ዲግሪ እንደማይሰጣቸው እና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው የፈተና ጊዜ መሰረት ድጋሚ እንደሚፈተኑ አመልክተዋል።

ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ከተማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የሚባሉ ከ12 እስከ 17 የትምህርት ዓይነቶች ፈተና እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የፈተና ንድፍና የብቃት መመዘኛ መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከግንቦት 15 ጀምሮ ለ211 የትምህርት ፕሮግራሞች የፈተና ጥያቄዎች በማውጣት ለፈተናው ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

ፈተናው በኦንላየን የሚሰጥ በመሆኑም አስፈላጊ የቴሌኮም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ካሉ 325 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 161 እና ከመንግስት ደግሞ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስፈትኑ ጠቅሰዋል።

ዶ/ር እዮብ ፤ " ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የመውጫ ፈተናው ከ2015 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት መስኮችና መርሐ ግብሮች መስጠት እንዲቻል ስራዎች ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰሩ ቆይቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለማን ነው አቤት የምንለው ? " በታጣቂዎች የታጋቱ ሹፌሮች እና ረዳቶች ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ። ከቀናት በፊት ሹፌሮች እና ረዳቶች ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር እና በተቃራኒው ጉዞ ላይ የነበሩ አዳራቸውን " አሊዶሮ " ላይ ካደረጉ በኃለ በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦች መግለፃቸው ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድርጊቱ በተፈፀመበት ዕለት መልዕክት ካደረሱት ተጨማሪ…
#Update

በኦሮሚያ ክልል፣ " አሊ ዶሮ " ላይ ከታገቱት ሹፌሮች እና ረዳቶች መካከል በአጋቾች የተጠየቀውን ብር ከፍለው የተለቀቁ ስለመኖራቸው ቪኦኤ ሬድዮ ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ቃላቸውን የሰጡ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን 1 ሚሊዮን ብር ከፍለው ከእገታው እንዳስለቀቁ አመልክተዋል።

ከታገቱት አሽከርካሪዎች ውስጥ ሰባቱ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ዐማኑኤል ከተማ ወጣቶች እንደሆኑ የጠቆሙት እኚህ አባት፣ ከልጃቸው ጋራ አምስቱ እንደተለቀቁ አክለው ገልጸዋል።

ከቀናት በፊት ልጃቸው መታገቱንና 1 ሚሊዮን ብር ቢከፍሉ እንደሚለቁላቸው፣ በስልክ ያነጋገራቸው አካል መኖሩን የተናገሩት እኚኹ አባት በተጠየቁት መሠረት ከተለያየ ቦታ ያሰባሰቡትን ገንዘብ በማዳበሪያ አስረው በማድረስ ልጃቸውን እንዳስለቀቁ አስረድተዋል።

የታጋች ቤተሰቦች የእገታ ድርጊቱን በመፈፀም የከሰሱት መንግሥት " ሸኔ " እያለ የሚጠራውን አካል / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / ነው።

ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን በመንግሥት በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ እንደሆነ የገለፁት ኦዳ ተርቢ ፤ ታጣቂዎቻቸው እንዲህ አይነቱን ድርጊት እንዳልፈጸሙ ገልጸው፣ በተጠቀሰው አካባቢ፣ የተለያዩ ኃይሎች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ለቪኦኤ ሬድዮ ተናግረዋል።

ከሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል " አሊ ዶሮ " ላይ ወደ 30 የሚደርሱ ሹፌሮች እና ረዳቶቻቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ፤ ከእገታው በኃላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተደወለ እስከ 1 ሚሊዮን ብር መጠየቁን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መጠቆማቸው የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ ቤት በመንግሥት ተቋማት በርካታና ሰፋ ያሉ የኦዲት ክፍተቶችን በኦዲት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል።

ባለፈው ፤ ማክሰኞ ለፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ነበር።

ይህ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ 6 ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ 19 ተቋማት ደግሞ የጎላ ችግር ያላባቸው ሆነው በመገኘታቸው " ተቀባይነት የሚያሳጣ " አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡

#ሒሳባቸው_የጎላ_ችግር_ያለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል ፦
- የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣
- የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት አገልግሎት
- የፌዴራል ፖሊስ
- ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣
- ቦሌሆራ ዩኒቨርሲቲና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አስተያየት ለመስጠት አልቻልኩባቸውም ካላቸው ተቋማት መካከል ፦
- የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል፣
- አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣
- ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣
- የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣
- የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሉበት፡፡

ከ1 ዓመት እስከ 6 ዓመት ዕድሜ ያለውና ለመንግሥት ገቢ መደረግ የነበረበት 13.4 ቢሊዮን ብር ውዝፍ የጉምሩክ #ቀረጥ እና #ታክስ ዕዳ መኖሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

• የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 👉 124 ሚሊዮን ብር፣
• የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር 👉 65 ሚሊዮን ብር፣
• የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን 👉 64 ሚሊዮን ብር፣
• የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ 👉 7.9 ሚሊዮን ብር፣
• የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 👉 5.6 ሚሊዮን ብር፣
• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 👉 4.8 ሚሊዮን ብር በድምሩ 307.5 ሚሊዮን ብር የተሟላ ወጪ ሳይቀርብ በወጪ መዝግበው የተገኙ መሥሪያ ቤቶች ናቸው።

በሌላ በኩል ፤ ከደንብ እና ከመመርያ ውጪ ያላግባብ ክፍያ ከፈጸሙ ተቋማት መካከል ፦

- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ 👉 30 ሚሊዮን ብር፣
- የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 👉 22 ሚሊዮን ብር፣
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 👉 11.8 ሚሊዮን ብር፣
- የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን 👉 7.6 ሚሊዮን ብር፣
- የቤተ መንግሥት አስተዳደር 👉 6.5 ሚሊዮን ብር፣
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ 👉 6.1 ሚሊዮን ብር በድምሩ 134.2 ሚሊዮን ብር ተጠቃሽ ሲሆን ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት የግዥ አዋጅ ደንብና መመርያ ያልተከተሉ ግዥዎችን የፈጸሙ 82 ተቋማት በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህ መሥሪያ ቤቶች የተገኘው የግዥን ሕግ የጣሰ ክፍያ 592.4 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

ተቋማቱ ፦
> ጉምሩክ ኮሚሽን፣
> ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
> ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣
> የኢንፎርሜሽን መረብና ደኅንነት አገልግሎት፣
> የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካደሚ
> ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡

" በተከፋይ ሒሳብ " ተመዝግበው የተገኙ ነገር ግን ዝርዝር ማስረጃ ባለማቅረቡ የሒሳቡን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ያልተቻለባቸው ያሉ ሲሆን። ከእነዚህ ተቋማት መካከል ፦
- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 👉 1 ቢሊዮን ብር፣
- የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 👉 583 ሚሊዮን ብር፣
- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 👉 131.8 ሚሊዮን ብርና ጉምሩክ ኮሚሽን 96.5 ሚሊዮን ብር ይገኙበታል፡፡

#ከተደለደለላቸው_በጀት_በላይ_የተጠቀሙ መሥሪያ ቤቶችም በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ፦
• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 👉 358.9 ሚሊዮን ብር፣
• ዲላ ዩኒቨርሲቲ👉 125 ሚሊዮን ብር፣
• ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 👉 139.9 ሚሊዮን ብር፣
• ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ 👉 166.7 ሚሊዮን ብር፣
• አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 👉 113 ሚሊዮን ብር ናቸው፡፡

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በ2014 የተፈቀደላቸውን በጀት መጠቀም ሲገባቸው ባለመጠቀማቸው የተገኘው አጠቃላይ ገንዘብ 35 ቢሊዮን ብር መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በጀት ሥራ ላይ ካላዋሉ መሥሪያ ቤቶች ፦
- የመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር 👉 8.9 ቢሊዮን ብር፣
- የገንዘብ ሚኒስቴር 👉 6.3 ቢሊዮን ብር፣
- የጤና ሚኒስቴር 👉 3 ቢሊዮን ብር፣
- ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 👉 1.2 ቢሊዮን ብር፣
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር 👉 1 ቢሊዮን ብር፣
- የትምህርት ሚኒስቴር 👉 915 ሚሊዮን ብር፣
- የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር 👉 599 ሚሊዮን ብር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-06-29

@tikvahethiopia
እጥፍ ወለድ ያግኙ!
የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ
=================

ደንበኞች ከውጭ ሀገራት የተላከላቸውን ገንዘብ ወይም በባንኩ የሚመነዝሩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ የሚያስቀምጡበት የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡ 

የቁጠባ ሂሳቡ በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡

• ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል፤ 
• ደንበኞች ገንዘብ ከውጭ ሀገራት ሲላክላቸው ወይም በባንኩ ሲመነዝሩ የአየር ሰዓት ስጦታ ያገኛሉ፤
• የሂሳቡ ባለቤቶች ለውጭ ሀገር ጉዞ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎታቸው ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፤
• ደንበኞች ከባንኩ ጋር ከሚሠሩ ድርጅቶች ለሚያገኙት አገልግሎት ወይም ለሚገዙት እቃ በፖስ ሲከፍሉ ቅናሽ ያገኛሉ፤
• ሌሎችንም በርካታ ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡

ሂሳቡን በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይክፈቱ፤ ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ይደውሉ!
 
ይቆጥቡ፤ የበለጠ ያግኙ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ : https://t.iss.one/combankethofficial
#ሳፋሪኮም_ኢትዮጵያ

በሳፋሪኮም ሜጋ የኢንተርኔት ጥቅል በዛ ያለ ዳታ ረዘም ላለ ጊዜ! 3 ወይም 6 ወራት በሚቆዩ የሳፋሪኮም ሜጋ ኢንተርኔት ጥቅሎች አብሮነታችንን እናጠናክር!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገልጿል። #የሁሉም_ነዳጅ_ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በግንቦት ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚሁ መሠረት :- 1. ቤንዚን ----- ብር 69.52 በሊትር …
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሰኔ 23 / 2015 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባለበት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት ፦

1. ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ52 ሳንቲም

2. ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም በሊትር

3. ኬሮሲን 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም

4. የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 65 ብር ከ35 ሳንቲም

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 57 ብር ከ97 ሳንቲም

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 56 ብር ከ63 ሳንቲም የሚሸጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከፍትሕ ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው " ካለፉት 22 ዓመታ ጀምሮ ሽሽት ላይ የነበረውና በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወቅት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተክርስቲያን የተሸሸጉ 2,000 (ሁለት ሺህ) ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የተጠረጠረው ፉልጌንሴ ካይሼማ መያዝ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች #ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው ተብሏል። የተባበሩት…
የዘር ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፈው የፖሊስ መኮንን ከዓመታት በኃላ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።

ፈረንሳይ ሀገር የሚገኝ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል በተከሰሰ አንድ የቀድሞ የሩዋንዳ ፖሊስ መኮንን ላይ የዕድሜ ልክ እሥራት መፍረዱን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ)ን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

ስሙ ፊሊፔ ሄትጌኪማና የተባለው ሩዋንዳዊው የፖሊስ መኮንን ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት በተፈጸመው የጅምላ ፍጅት ወቅት የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙ ተረጋግጧል።

የፖሊስ መኮንኑ ወንጀሉን የፈፀመው በፈረንጆቹ 1994 በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ወቅት ነው።

በወቅቱ የሁቱ ታጣቂዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎችን መግደላቸው ይታወሳል።

የፈረንሳይ ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ግለሰቡ እሱ ራሱ የሰዎችን ነብስ ከማጥፋቱም በላይ #ሌሎች ግድያ እንዲፈፅሙ #ያነሳሳ ነበር።

ፊሊፔ በጅምላ ግድያው ወቅት ኒያንዛ በተሰኘችው የደቡብ ሩዋንዳ አካባቢ የፖሊስ መኮንን ሆኖ ያገለግል ነበር።

ነገር ግን የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ካቆመ በኋላ ወደ #ፈረንሳይ አቅንቶ ለአስርታት ማንነቱ ደብቆ ሲኖር ቆይቷል።

ግለሰቡ ፈረንሳይ ከገባ በኋላ መጀመሪያ የስደተኛ ወረቀት አግኝቶ፤ ቀጥሎ ደግሞ ፊሊፔ ማኒዬ በተሰኘ ስም ዜግነት ተሰጥቶት ኖሯል።

ፈረንሳይ ውስጥ ሳለ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ጥበቃ ሆኖ ሲያገልግል ከቆየ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2017 ወደ #ካሜሩን ያቀናል።

ሰውዬው ይህን ያደረገው አንድ ሰው እሱ ላይ ቅሬታ እንዳለው ድምፁን ካሰማ በኋላ ነው።

ፊሊፔ በቁጥጥር ሥር የዋለው በካሜሩኗ ዋና ከተማ ያውንዴ ውስጥ ሲሆን ከዚያም ወደ ፈረንሳይ እንዲሄድ ተደርግ የፍርድ ሂደቱን ሲከታተል ቆይቷል።

በመጨረሻም የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።

በሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊ ሆነው የተገኙ ግለቦች ፈረንሳይ ውስጥ ፍርድ ሲሰጣቸው ፊሊፔ አምስተኛው ነው።

በሚቀጥለው ዓመት 30ኛ ዓመቱን የሚይዘው እና በ100 ቀናት ውስጥ 800 ሺህ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎች አሁን ድረስ ጉዳያቸው አልተዘጋም።

ከወር በፊት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረ የቀድሞ የፖሊስ አባል (ፉልጌንሴ ካይሼማ) ከ22 ዓመታት ሽሽት በኃላ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙ ይታወሳል።

ግለሰቡ በተያዘበት ወቅት የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፤ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ ፤ ከሩብ ምዕተ አመታት በኃላም ቢሆን እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች ከፍትህና ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

@tikvahethiopia
" የወረዳ አመራሮቹ 50 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ይዤያቸዋለሁ " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ አስፈፃሚ እና ምክትላቸው " ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ያዝኳቸው " ሲል ፖሊስ ገለፀ።

የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አያናው አስራት ፤ ምክትላቸው የስራ ኢንተርፕራዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እዮብ አፈወርቅ በ " መስሪያ ቦታ " አሰጣጥ ተደራድረው የሙስና ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዙን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሳውቀው።

ፖሊስ ፤ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ከስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ብሎክን መሰረት በማድረግ የተፈጠረ የስራ እድል ላይ ከተጠቃሚ ወላጅ ጋር የተሻለ " የመስሪያ ቦታ እናሰጣለን " በማለት የተጠቃሚዋን ወላጅ አባት " ብር ካልሰጠኸን ልጅህን ከስልጠና እናወጣታለን፣ የስራ እድልም አይፈጠርላትም " በማለት ወላጅ አባቷን በማስፈራራት 6 ኪሎ አከባቢ ልዩ አዲስ ሆቴል 50,000 ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ገልጿል።

ግለሰቦቹ እጅ ከፍንጅ የተያዙት ዛሬ ከቀኑ 10:30 ሰዓት ላይ መሆኑን ያሳወቀው ፖሊስ አሁን ላይ ፖሊስ ጣቢያ ገብተው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብሏል።

ፖሊስ የከተማው ነዋሪዎች በየትኛውም የመንግስት ተቋም ሙስና #የሚጠይቁ እና #የሚቀበሉ ማናቸውም አካላትን ለፖሊስ እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Telebirr #CBE ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በአጋርነት በ " ቴሌብር " ተጨማሪ የፋይናንስ አገልግሎት መሰጠት ጀመሩ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎቶችን በቴሌብር አማካኝነት ለማቅረብ የሚያስችል አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል፡፡ አገልግሎቱ ፥ የግለሰብ ደንበኞች እና ተቋማት በቴሌብር የሚያከናውኗቸውን ግብይቶች መሰረት አድርጎ…
" 3,114 ደንበኞቼ 21,592,811 ብር ብድር አግኝተዋል " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 3,114 ደንበኞቹ 21,592,811 ብር ብድር ማግኘታቸውን አሳወቀ።

ኢትዮ ቴሌኮም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በአጋርነት በ " ቴሌብር " አዳዲስ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች መጀመሩ ይታወቃል።

ከእነዚህ ከተጀመሩት አዳዲስ አገልግሎቶች መካከል አንዱ " እንደራስ " የተሰኘው አገልግሎት ነው።

ይህ አገልግሎት ፤ የግለሰብ ደንበኞች በ " ቴሌብር " እንደሚያከናውኑት የግብይት መጠን እስከ ብር 15,000 ድረስ የአነስተኛ ብድር አገልግሎት የሚሰጥበት ነው።

ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ባደረገው መረጃ በዚሁ አገልግሎት ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ 3,114 ደንበኞቹ 21,592,811 ብር ብድር ማግኘታቸውን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ " ስንቅ " በተሰኘው አገልግሎት 2,035 ደንበኞቹ 1,719,754 ብር እንደቆጠቡ ገልጿል።

ይህ " ስንቅ " የተሰኘው አገልግሎት ደንበኞች ከወለድ ነጻ ወይም የተለያየ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብባቸው የተንቀሳቃሽ እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ የቁጠባ አገልግሎት የሚያገኙበት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ ቤት በመንግሥት ተቋማት በርካታና ሰፋ ያሉ የኦዲት ክፍተቶችን በኦዲት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል። ባለፈው ፤ ማክሰኞ ለፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ነበር። ይህ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ 6 ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ 19 ተቋማት ደግሞ…
#ኦዲት

" በ86 የመንግስት መስሪያ ቤቶች 6 ቢሊዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ነው ተመላሽ የሆነው " - የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት

የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ፤ የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ ስለመጣ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰቡ።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ይህ ያሳሰቡት ከቀናት በፊት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለፓርላማው የ2014 ዓ/ም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ክንዋኔ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለት ዓለማ በትክክል እንዲውል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚበረታታ ነው " ያሉት አቶ ክርስቲያን " የክዋኔ ኦዲት ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ የሪፖርቱን ተአማኒነት እና ተቀባይነትን ማረጋገጥ ይገባል " ብለዋል።

ዋና ኦዲተር የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ እና ሪፖርት በወቅቱ በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመጣ በይበልጥ ጥረቱን አጠናክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ " አስፈጻሚው አካል ለኦዲት ግኝቶች ትኩረት ባለመስጠት የገንዝብ የመመለስ ምጣኔው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ፤ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተቋማትን በመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ማስፈን ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ የመጣ በመሆኑ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው " ሲሉም አሳስበዋል።

የፌደራል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ በበኩላቸው ፤  " በ86 የመንግስት መ/ ቤቶች 6 ቢለዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ተመላሽ በመደረጉ የሚፈለገውን ለውጥ እያመጣ አይደለም።  " ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ኦዲተሯ ፤ በተወሰኑ የመንግስት እና የህዝብ ሃብት ባባከኑ የስራ ኃላፊዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ በገንዘብ ሚኒስቴር መወሰዱን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

#HoPR

@tikvahethiopia