TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#እግድ " የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ጣቢያ " በመንግስት #በጊዜያዊነት ታገደ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ እሁድ በፃፈው ደብዳቤ " ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ " ን በጊዜያዊነት እንዳገደ አሳውቋል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም " ሰበር ዜና " በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን…
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ በላከው መግለጫ ፤ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ህጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው ሲል ገልጿል።

ኢዜማ ፤ " የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ከተልዕኳቸው ውጪ የገዢው ፓርቲ ልሳን ሆነው የህዝብን በደል እና የመንግሥትን ብልሹ አሰራር ጆሯቸውን ደፍነው ዘወትር የውዳሴ ዘገባ ለገዢው ፓርቲ እና መንግሥት በማቅረብ ለተጠመዱት የህዝብ መገናኛ ብዙኋን ምንም አይነት #ተግሳጽ እንኳ ሳያቀርብ ባለፈው እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም ለማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት በፃፈው የእግድ ደብዳቤ ብሮድካስት ባለፍቃዱን በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል " ብሏል።

" ይህ የእግድ ውሳኔ ምክንያቱ ሕጋዊ ሆነም አልሆነ በመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2021 አንቀጽ 73 ፣ 76 እና 81(2) የተጠቀሱትን በቅድሚያ #ማስጠንቀቂያ የመስጠትም ሆነ የሚዲያ ተቋሙ #ራሱን_እንዲከላከል ቀድሞ እድል የመስጠት ሕጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው " ሲል ኢዜማ ገልጿል።

" ተቋማት የሚወስዷቸው እርምጃዎች በእርግጥም ሕግን ከማስከበር መነሻነት ይልቅ በማን አለብኝነት ድርጅታዊ ፍላጎትን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነው " ያለው ኢዜማ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ላይ የወሰደው እርምጃ ይህን በግልፅ ያስረዳል ብሏል።

ተቋማት ከእንደዚህ አይነት ወጥነትና ገለልተኝነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲወጡም አሳስቧል።

ፓርቲው ፦

- የመገናኛ ብዙኀንን ጨምሮ ገለልተኛ ሊሆኑ የሚገባቸው ተቋማት ከገዢው ፓርቲ አባላት ተጽዕኖ ነፃ ማውጣት፤

- የመንግሥት እና የፓርቲ አሠራር የተለያዩ መሆናቸውን በሕግም በተግባርም ማረጋገጥ፤

- የሚወሰዱ እርምጃዎች ሕግ እና ሕግ ላይ ብቻ መሠረት ያደረጉ ብቻ ሊሆኑ ይገባል ብሏል።

ኢዜማ ፤ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን የወሰደው እርምጃ " በአዋጅ ከተሰጠው ሥልጣን ወሰን ተላልፎ የወሰደው " ነው ያለ ሲሆን ፓርቲው ሕገ ወጥ ነው ያለው ውሳኔ እንዲሽር፤ ባለስልጣኑ ይህን ውሳኔ ያሳለፉትን አካላት ተጠያቂ በማድረግ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE #ይፋዊ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ #በይፋ አሳውቋል። ሚኒስቴሩ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ይሰጣል ብሏል። የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን…
#Update #የመውጫ_ፈተና

ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል።

በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በመገኝበት በአሁን ሰዓት ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ በ2015 በመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ብሉ -ኘሪንት የተዘጋጀ መሆኑና የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት አብራርተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናን ለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም የገለፁት ሚኒስትሩ፤ የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም አብራርተዋል፡፡

በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) ተለይተው፤ በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በሁሉም የትምህርት መስኮት የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱንም አስረድተዋል፡፡

መረጃው የህ/ተ/ም/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #የመውጫ_ፈተና ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በመገኝበት…
#MoE

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎችን አፈፃፀምን በተመለከተ ለህ/ተ/ም/ቤት ባቀረቡት ሪፖርት የ2015 የፈተና ዝግጅትን በተመለከተ አብራርተዋል።

ለ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፣ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በየትምህርት አይነቱ እራሱን የቻለ የፈተና ዝግጅት ቢጋር እንዲዘጋጅ ተደርጓል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ " የ12ኛ ክፍል ዋናና የሙከራ ፈተና በፈተና በቢጋሩ መሰረት ከተለኪ ባህሪያት አንፃር ተገቢና አስተማማኝ ጥያቄዎችን በጥንቃቄና #ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በተዘጋጀ የስራ መመሪያ ቼክ ሊስት መሰረት በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከቀናት በፊት ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ቴሌ_ብር

እንዲህ ቢሆን ብለው የተመኙትን ሁሉ በአንድ አድርጎ በቀላል አጠቃቀም ያቀረበልዎን የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ እስካሁን ካላወረዱ ከ https://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ ይጠቀሙ ስጦታዎን ያግኙ!

ሕይወትዎን ያቅልሉ ፤ የወደፊቱን አሁን ይኑሩ!!

ቴሌብር- ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎችን አፈፃፀምን በተመለከተ ለህ/ተ/ም/ቤት ባቀረቡት ሪፖርት የ2015 የፈተና ዝግጅትን በተመለከተ አብራርተዋል። ለ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፣ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በየትምህርት አይነቱ እራሱን የቻለ የፈተና ዝግጅት ቢጋር እንዲዘጋጅ ተደርጓል ብለዋል። ሚኒስትሩ ፤ " የ12ኛ ክፍል…
#MoE

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ሀገሪቱ ካሏት 47 ሽህ ገደማ ትምህርት ቤቶች 99 በመቶዎቹ አመቺ አይደሉም።

በተሰራው ምዘና አራት ትምህርት ቤቶች ብቻ ከፍተኛውን ደረጃ አሟልተዋል።

86 በመቶ የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም 71 በመቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፍፁም ከደረጃ በተታች ናቸው።

በትምህርት ምዘናና ጥናት ውጤት ከ4ተኛ ክፍል 20 በመቶዎቹ ፤ ከ8ተኛ ክፍል ደግሞ 12 በመቶዎቹ ብቻ በትምህርት ፖሊሲው የተቀመጠውን 50 በመቶ ውጤት አስመዝግልዋል።

ችግሩን ለማስተካከል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን ነው ፤ የትምህርት ጥራትን ለማስተካከል ረዘም ያለ ጊዜ ይወስዳል። "

@tikvahethiopia
" በቅርቡ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን እንሾማለን "

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ሌላው ፈተና ነው የተባለው በትግራይ ክልል የሚገኙ ሊቃነጳጳሳት እንቅስቃሴ ጉዳይ አሁንም መቀጠሉ ተነግሯል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ያሉ አባቶች ቤተ ክህነት ማቋቋማቸውን ማሳወቃቸው ይታወቃል።

ሊቃነ ጳጳሳቱ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ " በቅርቡ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን እንሾማለን " ብለዋል።

በቅርቡ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን በአገር ውስጥና በውጭ እንደሚሾም የተናገሩት ሊቃነ ጳጳሳቱ አዲሶቹ ተሿሚዎች በቅርብ ጊዜ ውስጥም ወደ ሥራ ይገባሉ ሲሉ ማሳወቃቸውን ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በትግራይ ክልል የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት መሥርተነዋል ያሉትን ቤተ ክህነት ካቋቋሙበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ጉዳይ ያሉት ነገር ባይኖርም አሁን ላይ ኤጲስ ቆጶሳትን እንደሚሾሙ አሳውቀዋል።

ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ፤ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጠቅላይ ጽ/ቤትም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ሙከራ ማድረጉን ነገር ግን እንዳልተሳካ ዘግቧል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡን ይታወቃል።

በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ክልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ ቢቆዩም ውጤት ግን ሊያመጡ አልቻሉ።

በቅርቡም ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ ሰይሞ የነበረ ሲሆን ግንኙነቱን ለማስቀጥል ያመች ዘንድ አንድ ልዑክ ወደ ትግራይ እንደሚልክ ተነግሮ ነበር፤ ነገር ግን ከዚህ በኃላ የተሰማ አዲስ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
የአሜሪካ ጦር በሶማሊያ የአየር ድብደባ አካሄደ።

ባለፈው ቅዳሜ ዕለት የአሜሪካ ጦር የ " አልሸባብ " ታጣቂዎችን ኢላማ ያደረገ አዲስ የአየር ድብደባ ማፈፀሙ ተረጋግጧል።

የአሜሪካ ጦር በሰጠው ማረጋገጫ ጥቃቱ የተፈፀመው በደቡብ ሶማሊያ መካከለኛው ጁባ ግዛት ፣ ጅሊብ ከተማ ሲሆን ጥቃቱ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር የተፈፀመ ነው ተብሏል።

የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቶች በጥቃቱ የተገደለ / የተጎዳ ሲቪል እንደሌለ አመልክተዋል።

በጥቃቱ ከፍተኛ የ " አልሸባብ " አዛዦች ኢላማ መደረጋቸውን በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም።

ጅሊብ ፤ ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ምዕራብ 385 ኪሎ ሜትር (239 ማይል) ርቃ የምትገኝ በ " አልሸባብ " ይዞታ ስር ያለች ከተማ ናት።

@tikvahethiopia
የስዕል ተስዕጦ ላላቸው የቀረበ ዕድል!

ሪድም ዘጀኔሬሽን USAID ጋር በመተባበር ዕድሜያቸው ከ18 -29 ለሆኑ ወጣቶች በቡድን ሆነው የሚሳተፉበት የስዕል ውድድር አዘጋጅቷል። ውድድሩ በሁሉንም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 80 የሚሆኑ ወጣቶች ክህሎታቸውን ተጠቅመው ስለሰላም በጋራ እንዲሰሩ የሚያግዝና መልዕክት የሚያስተላልፉበት ነው።

ምዝገባው ከዛሬ ግንቦት 14 እስከ18 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ተሳታፊዎች በሥራ ሰዓት በሪድም ቢሮ በአካል ወይም በኦላይን https://forms.gle/rQr7ojZ8jXkCrkA18 ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

አንደኛ ለሚወጣው የሥዕል ሥራ የ60,000 ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፤ ሁለተኛ ለወጣው አሸናፊ ደግሞ የ40,000 ብር ሽልማት ያስገኛል። በማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ላገኘው የሥዕል ሥራ ደግሞ የ10,000 ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ስለውድድሩ ዝርዝር መረጃና ለመሳተፍ ስለሚያስፈልጉ መስፈርቶች በቀጣዩ ሊንክ ይጠቀሙ https://telegra.ph/Call-for-Applicants-05-22

ለተጨማሪ መረጃ  0930098219 / [email protected] ላይ ይጠይቁ።
#EthiomartShopping

ሴኩሪቲ ካሜራ ሽያጭና ነፃ ገጠማ : 0911582926

security camera CCTV (ባለ 4 አና ባ 8 ካሜራ) ለቤትዎ፤ ለድርጅት፤ ለሱቅ፤ ለፋርማሲ፤ ለዳቦ ቤት፤ ለቡቲክ፤ ለህንጻዎ ፤ ለመጋዘንዎ አና ለንብረትዎ የአመታት ልምድ ባለው ድርጅታችን ሴኩሪቲ ካሜራ ያስገጠሙ።

- 4 ካሜራዎች :- 4 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች  35,000 ብር
-8 ካሜራዎች :- 8 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 50,000 ብር

ቦሌ መድሀንያለም ቤዛ ህንጻ 208
#ሱዳን

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ እና ሱዑዲ አረቢያ አደራዳሪነት የተኩስ ማቆ ስምምነት ላይ ማድረሳቸው ቢነገርም እንደ ከዚህ በፊቶቹ ስምምነቶች ሁሉ ተጥሶ ካርቱም ትላትናም በፍንዳታ ስትናጥ መዋሏን ቪኦኤ ዘግቧል።

የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ከሰኞ ምሽት ለአራት ሩብ ጉዳይ ይጀምራል የተባለና ለሰባት ቀናት የሚቆይ ነበር።

ተኩስ ኡቅም ላይ ተደረሰ በተባለ በደቂቃዎች ውስጥ የአየር ድብደባ እና የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል። በሰሜን ካርቱም ውጊያ ሲካሄድ፣ ከካርቱም በሥተ ምስራቅ ደግሞ የአየር ድብደባ እንደነበር ዘገባው ጠቁሟል።

በአንዳንድ የካርቱም ክፍሎች ደግሞ፣ የሚያስጨንቅ ጸጥታ ሰፍኖ እንደነበር እና ነዋሪዎቹም የሰላም ስምምነቱ ውጊያውን ያስቆማል በሚል ተስፋ አድርገው እንደነበር ተነግሯል።

ነዋሪዎች ሕይወት አድን ርዳታ እንዲደርስ እና ወደ ጦር አውድማነት ከተቀየረችው ካርቱም በሕይወት ለመውጣት እንደሚሹም ታውቋል ሲል ቪኦኤ በዘገባው ገልጿል።

እስካሁን ድረስ ከ1,000 በላይ ሰዎች የሞሩ ሲሆን ከሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። 250 ሺሕ የሚሆኑትን ደግሞ #ኢትዮጵያን ጨምሮ የተሻለ ሰላም እናገኛለን ወዳሉባቸው ጎረቤት አገራት ሸሽተዋል።

@tikvahethiopia