TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነዳጅ

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ  ሥራ መጀመሩን አሳውቋል።

ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ተብሏል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን እና የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር እንደሚያደርግ ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።

የነዳጅ ግብይቱ በ #ቴሌብር አማራጭ የሚከናወን ነው የተባለ ሲሆን በዚህ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ሁሉም የመንግስት እና የግል ተሽከርካሪዎች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

ሚኒስቴሩ በቅርቡ የትራንስፖርት ትኬት በዲጂታል እንደሚጀመር አሳውቋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በማደያዎች የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የማካሄድ የሙከራ ትግበራ  ሥራ መጀመሩን አሳውቋል። ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት ይጀመራል ተብሏል። ዛሬ በአዲስ አበባ ለሙከራ የተጀመረው የዲጂታል ግብይት በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። ግብይቱ በዲጂታል መሆኑ ምርት እንዳይባክን…
#ነዳጅ

" ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈፀማል " - የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ #በኤሌክትሮኒክስ_የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ገልጾ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም አሳውቋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ #ከሐምሌ_አንድ ጀምሮ #በአስገዳጅነት እንደሚተገበር ተጠቁሟል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በ " ቴሌ ብር " ውጤታማ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በ " ቴሌ ብር " ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አመልክቷል።

የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መገንባቱንም አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር ደግሞ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ያለ ሲሆን በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን ይፈታል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ሲል አሳውቋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በ " ቴሌብር " ብቻ ተግባራዊ ይደረጋል ሲል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። በ " ቴሌብር " ነዳጅ ስለ መቅዳት አሸከርካሪዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች ምንድናቸው ? ☞ በቅድሚያ የ " ቴሌብር "ተጠቃሚ መሆን፤ ☞ በቂ ክፍያ የቴሌብር አካውንት ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ፤ ☞ የ " ቴሌብር " የሚስጥር…
#ነዳጅ #አዲስአበባ

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል አማራጭ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ከቴሌ ብር በተጨማሪ ሌሎችም የክፍያ ሥርዓቶችን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ክፍያ በ " ቴሌ ብር " ብቻ እንደሚፈፀም እያሳወቀ ይገኛል።

ባለፉት ተከታታይ ቀናትም ቢሮው የመኪና ባለቤቶች በቀሩት ጥቂት ቀናት የነዳጅ ክፍያ በ" ቴሌ ብር ብቻ " እንደሚከፈል በመገንዘብ ከእንግልት ለመዳን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ እያሳወቀ ነው።

ቢሮው መሰል መልዕክቶችን በተረጋገጠ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ ነው ለህዝብ እያሰራጨ የሚገኘው።

ለመሆኑን የነዳጅ ክፍያ ከ " ቴሌ ብር " ውጭ መፈፀም አይቻልም ?

ኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ለዚሁ አገልግሎት የሚውል " #ነዳጅ " የተባለ የሞባይል መተግበሪያ ማቅረባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

መተግበሪያው ተገልጋዮች የነዳጅ ክፍያቸውን ከንግድ ባንክ አካውንታቸው የተርጋ ቁጥራቸውን ብቻ በመጠቀም መክፈል ያስችላል ያለ ሲሆን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የነዳጅ ክፍያው " በቴሌ ብር ብቻ " ነው የሚፈፀመው እያለ ለህዝብ እያሰራጨ ያለው መልዕክት ትክክል እንዳልሆነ አስረድቷል።

" ነዳጅ " የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ከክፍያ አማራጭነት በተጨማሪ አሽከርካሪዎች አቅራቢያቸው የሚገኙትን ማደያዎች ከአቅርቦታቸው ጋር ማግኘት የሚችሉበት አማራጭም እንዳለው ድርጅቱ ገልጾልናል።

የክፍያ አማራጩ በሀገሪቱ ከሚገኙ ማደያዎች 60 በመቶ ማዳረስ መቻሉንም ጠቁሟል።

መተግበሪያው የት ይገኛል ? https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር መተግበሪያ አማካኝነት ነዳጅ ለመቅዳት የሚያስችል አዲስ የዲጅታል አሠራር መዘርጋቱን ገልጿል።

ክፍያውም በማንኛውም ስልክ በሲቢኢ ብር አጭር ቁጥር ወይም በሞባይል መተግበሪያው መፈጸም ይቻላል ተብሏል። አሰራሩ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተጠቆመው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ከነገ ሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጮች ብቻ ይደረጋል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያቀረበውን #ነዳጅ የተባለ መተግበርያ በመጠቀም ከ900 በላይ የሚሆኑ ማደያዎች ላይ የነዳጅ ግብይት መፈፀም የሚያስችል አሰራራር አስተዋውቋል።

የነዳጅ መተግበሪያን በመጠቀም እንዴት መገበያየት ይቻላል ?

- በመጀመሪያ የነዳጅ መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር ያውርዱ፤

- ሙሉ መረጃዎን በማስገባት መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ ወዲያውኑ የነዳጅ መለያ ቁጥር በ አጭር የጽሁፍ   መልዕክት ይደርስዎታል።

- በመቀጠል መተግበርያው ላይ የተሽከርካሪዎን የሰሌዳ ቁጥር በማስገባት ተሽከርካሪዎን ይመዝግቡ።

- የነዳጅ መለያ ቁጥርዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ Utility ውስጥ በመግባት Utility payment በመምረጥ በመልእክት የደረሰንን የነዳጅ ID አስገብተን Link ማድረግ ወይንም በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ።

ከዚህ በኋላ ቀጥታ ከሂሳብ አካውንትዎ ግብይት መፈጸም ብቻ !

- ነዳጅ ለመቅዳት ማደያ በሚሄዱበት ወቅት የነዳጅ ቀጂ ባለሙያው የሰሌዳ ቁጥርዎን ፣  የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን በ(ነዳጅ ቀጂው) መተግበሪያ ላይ በማስገባት ግብይቱን ያስጀምራል።

- ወዲያውኑ በሚደርስዎት የአጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ የሚስጥር ቁጥሩን(OTP) ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው በመንገር ግብይቱን ያጠናቅቁ።

ነዳጅን ለየት የሚያደርገው ፦

አንድ ጊዜ ብቻ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር በማስተሳሰር ቀጥታ ከአካውንትዎ የነዳጅ ግብይት የሚፈጽሙበት መሆኑ!

በአቅራቢያዎ ያሉ ነዳጅ ማደያዎችን እንዲሁም ነዳጅ መኖሩን እና አለመኖሩን አረጋግጠው መሄድ የሚያስችሎትን አማራጭ ይዞ መምጣቱ!

አንዴ በመተግበሪያው ላይ ከተመዘገቡ በኋላ የስማርት ስልክ አለማስፈለጉ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ?

ፕላይ ስቶር:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

አፕስቶር : https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

አሰራሩ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ማከናወን ይቻላል።

#ነዳጅ #CBE #ኤግልላየን