TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ የመቐለ ከተማ ሙስሊም ማህበረሰብ ዛሬ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነ ስርዓት አካሂዷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተው እንደነበር ድምፂ ወያነ ዘግቧል።

የፎቶ ባለቤቶች ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጎረቤት ሱዳን ያለው ውጊያ ዛሬ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል። ከካርቱም ጨምሮ ከሌሎች ከተሞች በወጡ መረጃዎች ዛሬም በከባባድ መሳሪያ የታገዘ የከተማ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ ነው። በተለይም በካርቱም ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ክፍል የከባድ መሳሪያ ውጊያ እንዳለ ተነግሯል። የሠራዊቱ ጠቅላይ ዋና መሥሪያ ቤት በር ፊት ለፊት ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን አርኤስኤፍ (RSF) ከቅዳሜ ጀምሮ…
#Sudan

በሱዳን የአሜሪካ ኤምባሲ ተሽከርካሪ በጥይት ተደበደበ።

በሱዳን ፣ ካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን አስታወቀ።

ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።

ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን የEU አምባሳደር ጥቃት ተፈፀመባቸው።

በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰማ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ #አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
#DigitalElectronicsPLC

ለሚሰሩዋቸው ፕሮጀክቶች እና የፈጠራ ስራዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ ኤሌክትሪካል እና ሜካኒካል እቃዎች እንዲሁም ማሽነሪዎች እናቀርባለንⵆ
#join ቴሌግራም ቻናል @ethioinvention
website https://digitalelectronicsplc.com/
📌Contact
📱0914-839754
📱0703-839754
📌#ኣድራሻችን4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ፡ 1ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 103ለ
@ethioinvention
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EOMmarket

የልጅዎን ውሎ እና የቤትዎን ደህንነት በየትኛውም ቦታ ሁነው በቀጥታ መከታተል የሚችሉበት ድንቅ የደህንነት ካሜራ!

ህይወትዎን ቀላልና ዘመናዊ የሚያደርጉ ጥራት ያላቸው እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ትልቁ ገበያ 👇https://t.iss.one/EOMMarket

የመረጡትን እቃ ይዘዙን፤ያሉበት ድረስ በነፃ  እናደርሳለን 𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲  ☞ 0929181818 / 0909868788

ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !! አድራሻችን፦
ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ  የሱቅ ቁጥር  G-10 ግራውንድ [ እንደገቡ በስተቀኝ በኩል ]
ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ ቁጥር #338

𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 : @EOMmarket
     
" የኢትዮጵያ መንግስት የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን ይልቀቅ " - አምንስቲ ኢንተርናሽናል

የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዉሞን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብትን እንዲያከብርና የታሰሩ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን እንዲፈታ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ትናንት ባወጣዉ መገለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አማራ ክልል በተፈጠረዉ ሁከት ምክንያት ያሰሯቸዉን 7 የመገናኛ ዘዴ ባልደረቦች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ከእስረኞቹ ባንዷ ላይ ተፈፀመ የተባለዉን አካላዊ ጥቃት እንዲያጣሩ ጠይቋል።

መግለጫዉ እንዳለዉ  ባለስልጣናቱ " ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ሁሉም ወገን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብቱን ማስከበር አለባቸዉ። "

ባለፈዉ ሳምንት በአማራ ክልል የመብት ጥሰትና ሁከት መቀስቀሱ እንዳሳሰበዉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታዉቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቀባይ ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸዉ፣ አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸዉንም ድርጅቱ «አሳሳቢ» ብሎታል።

የመንግስት ኃይላትም ሆኑ #ሌሎች ታጣቂዎች " የሰብአዊ ርዳታ ሰራተኞችን ያለማጥቃት ኃላፊነት አለባቸዉ። " ብሏል አምነስቲ።

የኢትዮጵያ መንግስት " አስቸኳይ፣ ጥልቅ፣ ገለልተኛና ዉጤታማ ምርመራ አድርጎ ተጠያቂዎችን ለፍርድ ማቅረብ አለበት " እንደ መግለጫዉ።

በምስራቅ አፍሪቃ፣ በአፍሪቃ ቀንድና በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ምክትል ተጠሪ ፍላቪያ ምዋንጎቭያ «ዘግናኝ» ያሉት የገነት አስማማዉ፣ ጌትነት አረጋዊ፣ አራጋዉ ሲሳይ፣መስከረም አበራ፣ አባይ ዘዉዱ፣ ዳዊት በጋሻዉና ቴዎድሮስ አስፋዉ መታሰር ሐሳብን በነፃነት በመግለጥ መብትና በመገናኛ ዘዴ ነፃነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነዉ።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት 7 የመገናኛ ዘዴ ሰራተኞች ባስቸኳይ እንዲለቁና የተመሰረተባቸዉን ክስ እንዲነሱም ምዋንጎቭይ ጠይቀዋል።

በሌለ በኩል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።

እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN በሱዳን የEU አምባሳደር ጥቃት ተፈፀመባቸው። በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰማ። አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)። ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል። የዲፕሎማቲክ…
" የሱዳን ጎረቤቶች የእርስ በርስ ጦርነትን አይፈልጉም " - ኦቪግዌ ኢግዌጉ

የጂኦፖለቲካ እና የፀጥታ ጉዳይ ተንታኝ ኦቪግዌ ኢግዌጉ ለአልጀዚራ በሰጡት ቃለ ምልልስ ፤ የሁሉም ቀጠናዊ ሀገራት ዋና ጉዳይ በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ወደ " ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት " እንዳይቀየር ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

" ለዚያ #ቅርብ ነን ነገር ግን በእውነቱ በዚያ ደረጃ ላይ አይደለንም። " ያሉት ተንታኙ ፤ ከሱዳን ጋር ድንበር የሚጋሩ ሀገራት የእርስ በርስ ጦርነት የሚያደርሰውን ውድመት ያውቁታል ሲሉ ተደምጠዋል።

የእርስ በርስ ጦርነት እንደ ህገወጥ ስደትና ቀድሞውኑም ደካማ ወደሆኑት ጎረቤት ሀገራት ስደተኞች እንዲፎርፉ ያደርጋል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ባንካችን አቢሲንያ የ2015 ዓ.ም የሐጅ ጉዞን ቀልጣፋ ፣ ለማድረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ካበለፀገው ሲስተም ጋር የማገናኘት (Integration ) ሥራ ማጠናቀቃችንን እያበሰርን፣ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን በመገኘት ክፍያችሁን መፈጸም የምትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን::

አቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዕሴትዎን ያከበረ!

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #hajj2023
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ኢድም አይደል፤ ታዲያ ባህርማዶ ያለ ወዳጅ ዘመድ የበዓል ስጦታ በአጋሮቻችን #Talkremit #Worldremit #Azimo #MasterRemit #Majority #Moneytrans #Remitly #ria #Taptapsend በኩል ሲልክልዎና ያለ ውጣ ውረድ እና እንግልት ባሉበት ሆነው በቴሌብር ሲቀበሉ፤

እንዲሁም በዌስተርን ዩኒየን ሃዋላ የተላከልዎትን ገንዘብ በአገልግሎት ማዕከሎቻችን ሲቀበሉ እና ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ሲያስተላልፉ፤

የተላከልዎትን ገንዘብ መጠን 5% እንዳሻዎ ለማንኛዉም ክፍያ ሊጠቀሙ የሚችሉበት የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ

ቴሌብር ሃዋላ የሩቁን ያቀርባል!
ኢድ ሙባረክ!