መንግስት " ለጎዳና ህጻናትና ወጣቶች ተገቢውን ጥበቃ አላደረገም " በሚል ክስ ቀረበበት።
በመዲናዋ በተሰራ ጥናት ፥ ወደ 66ሺህ 575 የሚጠጉ የጎዳና ተዳዳሪዎች እንደሚገኙ፤ 85 በመቶ የሚሆኑትም ከ10 - 40 ዓመት የዕድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ መሆናቸውን ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ትላንት በሰጠው መግለጫ ከ31 ሺህ 4 መቶ 34 ውሎና አዳራቸውን በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ያደረጉ ዜጎች ማንሳቱን ገልጿል።
የችግሩ መንስኤ በርካታ በሆንም መንግስት ችግሩን ለመፍታት ግዴታውን አልተወጣም በሚል ክስ እንደቀረበበት ሰምተናል።
ክሱን ያቀረበውም የህግ ባለሞያዎች ለሰብዓዊ መብቶች የተሰኘው ድርጅት ሲሆን በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ በሚኖሩ ዜጎች በተለይ ህጻናት ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል።
ክሱን አስመልክቶ የህግ ባለሞያው ዶ/ር መሰንበት አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቁጥራቸው ከ60 እስከ 70 ሺ የሚደርሱ የጎዳና ተዳዳሪዎች አዲስ አበባ ውስጥ የሚሉት ዶ/ር መሰንበት "ሰፊ የሆነ ማኅበራዊ ቀውስ ነው ያለው ይህ ለማንም የሚታዘበው ነው። መንግስት በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 36 የተቀመጠውን እንዲሁም በተለያዩ አዎጆች መሰረት ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም " ሲሉ ያነሳሉ።
ስለ ክሱ ጭብጥ ሲያስረዱም፥ "መንግስት ይሄንን ቀውስ ለመፍታት በቂ አደረጃጀትም፤ ፋይናንስም፤ አሰራርም የለውም ነው የእኛ ትልቁ መከራከሪያችን... ጥያቄው በጀት መድቦ እንዲህ ያድርግ ብቻ አይደለም፤ የመንግስት አሰራር፣ ቁመና በአጠቃላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ችግር በሚፈታ መልኩ [ያለ] አይደለም ነው፤ ይህንን ነው ለፍርድ ቤት ለማስረዳት እየሞከርን ያለው" ሲሉ ያስረዳሉ።
ህጻናትን በዚህ ሁኔታ መተው ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መበት ጥሰት መፈጸም ነው የሚሉት ዶ/ር መሰንበት " ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ካልሆነ በስተቀር መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የአደረጃጀትም የአሰራርም የፖሊሲ ማዕቀፍም የለውም። በዚያ ደረጃ ነው ትኩረት እንዲሰጠው የምንፈልገው " ሲሉ ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ፥ " ትልልቅ ስብሰባዎች ሲኖሩ ህጻናትን አንድ ቦታ ማጎር በፍጹም ህገወጥ ነው፤ ፍርድ ቤቱ ይሄንን የመንግስት አሰራር እና እርምጃ በፍጹም ህገ-ወጥ እንደሆነ ውሳኔ እንዲሰጥበትም እንጠይቃለን " ብለዋል።
ይህንን ክስ ለመመስረት ጥናት ተደርጓል ?
ዶ/ር መሰንበትን ስለሂደቱ ጠይቀናቸው ጥናቶች መደረጋቸውን፤ ህጻናቱ ያሉበትን ሁኔታ መመልከታቸውን፤ የመንግስት አካላትንም ማነጋገረቸውንና፣ በዚህ ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማቶች ጋርም መምከራቸውን ጠቅሰው ይህንን ሁሉ ጭብጥ ይዘን ነው ወደ ፍርድ ቤት ክስ የገባነው ብለዋል።
ክሱ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ለሚለው ጥያቄም ክስ የቀረበባቸው የመንግስት ተቋማት መጥሪያ ደርሷቸዋል፤ ምላሽ እየጠበቅንም ነው ብለዋል።
የክስ ሂደቱ ስለሚከተለው ስልት ፦
ማኅበሩ አሁን እየተከተለ ያለው "ስልታዊ የፍርድ ቤት ሙግት" የምንለውን ዘዴ መሆኑን ባለሞያው ገልጸዋል። ይህም የመብት ጥያቄን ለመፍታት ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ቀውሶች ሲኖሩ እነዛን እንዴት በህግ ማዕቀፍ ለመፍታት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
ልምዱ ምን ይመስላል ?
ልምዱ ብዙ አይደለም። ዜጎች መብታችን ተነክቷል ሲሉ የሚከሱት በዋናነት የመንግስት ተቋማትና የመንግስት መስሪያቤቶችን ነው ህገመንግስቱም፤ የህግ ማዕቀፋችንም ይህንን ይፈቅዳሉ። ፍርድ ቤቶች እዚህ ላይ ብዙ ደፍሮ ያለመወሰን አለ፤ ግን ቀስ እያለ የህግ ግንዛቤ እየሰፋ ሲሄድ ይሻሻላል ብለን ነው የምናስበው ሲሉ አስረድተዋል።
@tikvahethiopia

የኢትዮጵያን ስም ያስጣራው የ23 ዓመቱ አባስ ሐዲ ዑመር !
ዱባይ በተካሄደ የቁርኣን ውድድር ኢትዮጵያዊው አባስ ሐዲ ዑመር ከባንግላዴሽ ተወካዩ በመከተል ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል።
አባስ ሐዲ ዐመር #ለ26ኛ ጊዜ በዩናይትድ አረብ ኤምሬት ዱባይ ሲካሄድ በቆየው ዓለም አቀፉ የቁርኣን ወድድር ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ተወዳድሮ 2ኛ አሸናፊ መሆን የቻለ ሲሆን ዛሬ ረቡዕ ወደ ሐገሩ ተመልሷል፡፡
ቃሪዕ አባስ ሐዲ ዑመር ዛሬ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በቅርቡ 24ኛ ዓመቱን የሚደፍነው አባስ በዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር ላይ ሲሳተፍ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተባቧል።
ከዚህ ቀደም በቱርክ በተካሄደ ውድድር ተሳታፊ ነበር።
#ሀሩንሚዲያ

" ኢፍጣራችን ለወገናችን "
ሶስተኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የፊታችን ቅዳሜ ዕለት / ረመዳን 17 ይከናወናል ተብሏል።
የዘንድሮው ኢፍጧል " ኢፍጧራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።
የቅዳሜው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሰዉ ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት ጉዳት ያደረሰባቸዉና የተቸገሩ ወገኖቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በዕለቱ ለተቸገሩ ወገኖች የሚሆን ፦
- እንደ ፉርኖ ዱቄት፣
- ሩዝ ፣
- ፓስታ፣
- መኮረኒ፣
- ዘይት፣
- የበቆሎ እህል፣
- ምስር፣
- የህፃናት የታሸጉ ብትን ወተቶች፣
- የሕፃናት አልሚ ምግቦች
- የንጽህና መጠበቂያ፣
- አልባሳት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ይዞ መምጣት እንደሚችል ተገልጿል።
በረመዷን 17 ዕለት የሚከናወነው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ ዘንድሮ በበላይነት የአዲስ አበባ ከተማ መጅሊስ ከሀላል ፕሮሞሸን እና ከነጃሽ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር እንደሚያዘጋጁት መገለፁን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#ዝርዝር የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል። የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ? #የመንግስት_ግዥ_ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት…
" በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው " - የፍትህ ሚኒስቴር
ትላንት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የፓርላማ አባሉ ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
የቀድሞው የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጫላ ዋታ፤ #ዛሬ_ረቡዕ ረፋድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፍትሕ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትን ዋቢ በማድረግ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ዘግቧል።
ዶ/ር ጫላ በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት #በሙስና_ወንጀል_ተጠርጥረው መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ ለድረገፁ በሰጠው ቃል ገልጿል።
ማስታወሻ ፦ ዶ/ር ጫላ ዋታ የተጠረጠሩባቸው የሙስና ጉዳዮች ምንድናቸው ? እሳቸውስ ትላንት ለህ/ተ/ም/ቤት ምን አሉ ? መለስ ብለው በዚህ ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/77517

#እንድታውቁት
ከአዲስ አበባ - ሙከጡሪ አለም ከተማ - ደጎሎ መስመር ከሙከጡሪ 72.3 ኪ.ሜ. እርቀት ላይ የሚገኘው ሀገር አቋራጩ የጀማ ወንዝ ድልድይ ጉዳት ደርሶበታል / ተሰብሯል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዛሬ ምሽት ባሰራጨው የማሳሰቢያ መልዕክት ድልድዩ ጉዳት የደረሰበት ከተወሰነላቸው የክብደት መጠን በላይ በጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ሳቢያ እንደሆነ ገልጿል።
ድልድዩ በአሁኑ ወቅት ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አመልክቷል።
ይህንን ድልድይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ለማብቃት እንዲያስችል አስፈላጊውን የጥገና ሰራ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚከናወን አሳውቋል።
የዚህ መስመር ተጠቃሚዎች ለድልድዩ አስፈላጊውን የጥገና ስራ ተከናውኖ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ መልዕክት ተላልፏል።
የእንሳሮ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጉዳዩን በተመለከተ ባሰራጨው መልዕክት ፥ " የጀማ ድልድይ ዛሬ ሁለት ሲኖ ትራክ ተከታትለው ሲሆዱ አንዱ ሲኖ ትራክ የውሃ መያዣ ቦቴ የጫነ ሲሆን አደኛ አፈር ጭኖ ሲጓዝ ባልታወቀ ምክንያት ድልድዩ ሊደረመስ ችላል ፤ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " ብሏል።
የፎቶ ባለቤት ፦ የእንሳሮ ወረዳ ኮሚኒኬሽን

#ሊትል
መነሻውን ኬንያ ያደረገው ድርጅታችን ሊትል ሊሚትድ በዋነኝነት በመተግበሪያ የታገዘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ሲሆን ፤ በአሁን ስአት ከ 5ዐዐዐ በላይ ድርጅቶች አለም ላይ አብረውን ይሰራሉ። ከ2016 EC ጀምሮ ላለፉት 7 አመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን ።
ይህን የዳበረ ልምድ ይዘን የሀገራችንን ህዝብ እና ድርጅቶች ለማገልገል ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) መግባታችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል የሆነ መተግበሪያ አዘጋጅተን የአሽከርካሪውንም ሆነ የተሳፋሪውን ደህንነት በተጠበቀበት ሆኔታ አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን።
ሀበሻ ዊክሊ ያዘጋጀውን ባዛር በማስመልከት የኛን መተግበሪያ ተጠቅመው ሲጓዙ 35% ቅናሽ ያገኛሉ።
አጠቃቀም ፤ መተግበሪያችንን (Little Ride) ከ Play store/App store በማውረድ Promo Code የሚለውን አማራጭ በመጫን LITTLE EASTER በማስገባት አሽከርካሪ መጥራትና የ35% ቅናሽ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ለተጨማሪ መረጃ 7933 ይደውሉ።
(ሊትል ሊሚትድ)

Photo
" የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እየተካሄደ ነው " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የመደርመስ አደጋ የደረሰበትን የጀማ ወንዝ የብረት ድልድይ ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገልጿል።
አንድ መቶ ሜትር ርዝማኔ ያለው የብረት ድልድይ ትላንት መደርመሱ ይታወቃል።
የአደጋው ምክንያት ተከታትለው ይጓዙ የነበሩ ሁለት ከባድ የጭነት መኪኖች በአንድ ጊዜ በደልድዩ ላይ በማለፋቸው ነው።
ድልድዩን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የኮከብ መስክ አለም ከተማ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን የሚያካሂደው “CSCEC ፦China state construction engineering company ” የተባለው ተቋራጭ አስፈላጊውን የጥገና ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።
የመንገድ ተጠቃሚው ሕብረተሰብ ድልድዩ በአጭር ጊዜ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ ተላልፏል።
ከዚህ በተጨማሪ ከተፈቀደ የክብደት በላይ መጫን በመንገድ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት መንገዶችን ከብልሽት ለመጠበቅ የመንገድ ተጠቃሚዎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ተብሏል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የፎቶ ባለቤት ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር