TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013 አጫጭር መረጃዎች ፦

- ምርጫ ቦርድ የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት በዚህ ሳምንት አሳውቃለሁ ብሏል። ከዚህ ቀደም ለቦርዱ ያልደረሱ 30 የምርጫ ውጤቶች አሁን ላይ ተጠቃለው ገብተዋል።

- የቁጫ ምርጫ ክልል የድምጽ ቆጠራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉበት በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው።

- ኦሮሚያ ክልል ነገሌ የምርጫ ክልል ድምፅ ባልተሰጠባቸው 30 የምርጫ ጣቢያዎች በቀጣይ ሀሙስ ድምጽ ይሰጣል።

- የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ምርጫ በተወዳደሩበት ኦሮሚያ ክልል ጎማ ቁጥር 2 በሰፊ ድምፅ አሸንፈዋል።

- ዛሬ ይፋ በተደረጉ የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች የአብኑ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተወዳደሩበት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ምርጫ ክልል ማሸነፋቸው ተገልጿል።

- ከምርጫው ቀን አንስቶ ከቆጠራ እና ድመራ ጋር በተያያዘ በ153 የምርጫ ክልሎች 31 ፓርቲዎች፣ 7 የግል ተወዳዳሪዎች በጽሁፍ፣ ስልክና በSMS አቤቱታ አቅርበዋል። ምርጫ በተካሄደባቸው በሁሉም ክልሎች ቅሬታ ቀርቧል።
• በአማራ ክልል 49 ምርጫ ክልሎች፣
• በደቡብ ክልል 40 ምርጫ ክልሎች
• በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ምርጫ ክልሎች
• በአፋር ክልል በ21 ምርጫ ክልሎች በርካታ ቅሬታ የቀረቡባቸው ናቸው።

#SolainaShimeles #NEBE

@tikvahethiopia
#NEBE

በመላው ሀገሪቱ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ማቋረጡን (suspend) አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ ያጠናቀቀ መሆኑ ይታወቃል። በቢኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ በታህሳስ ወር ምርጫውን ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ተግባራትን ማከናወን ጀምሮ ነበር።

የኢ.ፌዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀውን አገር አቀፍ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትላንትና ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ማጽደቁን ተቀትሎ ቦርዱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ያቋረጠ (suspend) መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#NEBE

ትላንትና ህ/ተ/ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አሳስቧል።

ማሳሰቢያው ከተሰጣቸው ፓርቲዎች መካከል ፦ ብልፅግና፣ ኦፌኮ፣ አብን ፣ ኦነግ ፣ ነእፓ፣ ኦብነግ፣ መኢአድ ይገኙበታል።

(አጠቃላይ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የቤት ውስጥ የመታሰር ጉዳይን አስመልክቶ ለፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤቶች ደብዳቤ ፅፏል።

የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቤቱታ የሚያጣሩ ቡድኖች ወደ አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም በመሄድ አቶ ዳውድ ያሉበትን ሁኔታ አጣርተዋል።

አጣሪዎቹ በሪፖርታቸው እንዳቀረቡት የቡድኑ አባላት የሊቀመንበሩ መኖሪያ ቤት ሲደርሱ አንኳክተው የከፈቱላቸው ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሰራተኞች መሆናቸውን ማንም ሰው መግባት እንደማይፈቀድለት ገልፀው ገብተው ለማየት መጀመሪያ ፍቃድ መጠየቅ ያለበት መሆኑን ከየት እንደመጡና ለምን እንደመጡ መጠየቃቸውን፣ በመጨረሻ እንዲጎበኟቸው መፈቀዱን ገልፀዋል።

የቡድኑ አባላት ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት የያዙት ቦርሳ መፈተሹን እንዲሁም ስልካቸውን ይዘው መግባት እንደማይችሉ እንደተገለፀላቸው በመጨረሻም ይህን ፈፅመው ከአቶ ዳውድ ጋር እንደተገናኙ ለቦርዱ ሪፖርት አቅርበዋል።

የአጣሪ ቡድኑ አባላት ከአቶ ዳውድ ጋር ባደረጉት ውይይት የተረዱት ከመጋቢት 24 /2013 ዓ /ም ጀምሮ ከቤት እንዳይወጡ የታጠቁ ሰዎች ግቢያቸው ውስጥ ተመድበው የከለከሏቸው መሆኑን ነው።

ምርጫ ቦርድም አቶ ዳውድ ኢብሳ የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገደበ ተገንዝቧል።

በመሆኑም ቦርዱ እኚህ የፓርቲ አመራር በየትኛውም የህግ አግባብ ተቀባይነት በሌለው ሁኔታ የሚገኙበትን የቤት ውስጥ እስር በአፋጣኝ መቆም እንዳለበት አስገንዝቧል።

ተቋማቱ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ግቢ የመደቡትን ጥበቃ እንዲያነሱና የሊቀመንበሩን የመንቀሳቀስ መብት አስከብረው በአስቸኳይ ለቦርዱ እንዲገለፁም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ትላንትና ህ/ተ/ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አሳስቧል። ማሳሰቢያው ከተሰጣቸው ፓርቲዎች መካከል ፦ ብልፅግና፣ ኦፌኮ፣ አብን ፣ ኦነግ ፣ ነእፓ፣ ኦብነግ፣ መኢአድ ይገኙበታል።…
#NEBE

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚህም እስካሁን ጠቅላላ ጉባኤ ያካሄዱ ፓርቲዎች ብልጽግና ፣ ህዳሴ ፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ፣ ጋህነን መሆናቸውን አመልክቷል።

እንደ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ በጊዜ ገደቡ መሰረት ቀን ያሳወቁ 3 ፓርቲዎች አሉ።

ቦርድ 12 ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ ጠይቀው ምላሽ የሰጣቸው መሆኑንም አሳውቋል።

ከእነዚህ መካከል ፦ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ አንዱ ሲሆን ለጉባኤው አስፈላጊ የሆኑ የፋይናንስና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች አስቻይ ባለመሆናቸው ገልጾ መጋቢት 18 ቀን 2014 እንዲያካሂድ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፓርቲው አባላቶች በእስር ላይ ስለሚገኙ፣ የፓርቲው የክልል ጽህፈት ቤቶች ተዘግተው ስለሚገኙ፣ በግጭቶች ምክንያት በበርካታ የኦሮምያ ዞኖች እና ሌሎ ች ክልሎች ውስጥ ያለው ሁኔታ ያልተረጋጋ ስለሆነ በሚል አቤቱታ አቅርቦ መጋቢት 17 እና 18/2014 ዓ/ም እንዲያካሂድ ቦርዱ ፈቅዶለታል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ/ም እንዲያካሂድ ጠይቆ ቦርዱ ፈቅዶለታል።

4 ፓርቲዎች ደግሞ በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ባለው ከፍተኛ የጸጥታ ችግር የተነሳ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እንደማይችሉ ጠቅሰው ቦርዱ ፈቅዶላቸዋል ከእነዚህም መካከል ዓረና ፓርቲ ይገኝበታል።

3 ፓርቲዎች ደግሞ ለቦርዱ የማራዘም ጥያቄ አቅርበው ውሳኔ ያልተሰጠባቸው እና ምክንያታቸው እየታየ ያለ ሲሆን ፓርቲዎቹ ፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ናቸው።

ሙሉውን ያንብቡ telegra.ph/NEBE-03-16

@tikvahethiopia
#NEBE

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል።

በዚህም ምክክር ወቅት ይፋ ያደረገው ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ መጠን ከላይ ተቀምጧል።

የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ ቀደም በፀደቀው መመሪያ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል።

ምርጫ ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ ፦ ፓርቲው ከሚያዚያ 18 /2014 ዓ/ም ጅምሮ በ2 ወራት ጊዜ እስከ ሰኔ 18 /2014 ዓ/ም ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ ብሏል።

በተጨማሪም ፤ ፓርቲው በደንቡ መሰረት የሚቀርፃቸውን አጀንዳዎች ጨምሮ በጉባኤው የመነጋገር መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ቀደም እልባት ያላገኘው " የአመራር ሪፎርም ወይም ለውጥ ማድረግ " የሚለው ለጉባኤው በአጀንዳነት ቀርቦ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥበት እና አግባብነት ያለው ምርጫ እንዲደረግ ብሏል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ነጻነት ፓርቲ (ኢንፓ) ሚያዝያ 02 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በተመለከተ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት ፦

" ... የጉባኤው ምልዓተ ጉባኤ በቁጥር ደረጃ የተሟላ ቢሆንም የቦርዱ ተወካዮች ከታዘቡት እና የጉባኤው ማገባደጃ አካባቢ ከተፈጠረው ግርግር መረዳት እንደቻሉት አብዛኛው የጉባኤ ተሳታፊዎች የፓርቲ አባል ስለሆኑ የተገኙ ሳይሆን በልመና ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና #በአበል የተገኙ ናቸው "

📎 ምርጫ ቦርድ ኢነፓ ያደረገውን ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ ፓርቲው ያቀረባቸውን ሠነዶችና ሪፖርቶች እንዲሁም የቦርዱ ታዛቢዎችን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ፓርቲውን የማገድ ውሳኔ አሳልፏል። ሙሉ የቦርዱ የውሳኔ ሀሳብ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደቡብ_ኢትዮጵያ_ክልል " በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ " የፌዴሬሽን ምክር ቤት ፦ - የወላይታ፣ - የጋሞ፣ - የጎፋ፣ - የደቡብ ኦሞ፣ - የጌዴኦ፣ - የኮንሶ ዞኖች እንዲሁም - የደራሼ፣ - የአማሮ፣ - የቡርጂ፣ - የአሌ፣ - የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " ለመመስረት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጿል። ም/ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት…
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ለቦርዱ ያቀረበው የሕዝበ ውሣኔ ማደራጀት ጥያቄ ላይ ውሣኔ አሳለፈ !

ነሐሴ 12/2014 የፌዴሬሽን ም/ ቤት ፤ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6 ዞኖችን እና 5 ልዩ ወረዳዎችን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በ3 ወር ህዝበ ውሳኔ በማድረጃት ውጤቱን ለምክር/ቤቱ እንዲያሳውቅ ብሎ ነበር።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለምክር ቤቱ ምላሹን ሰጥቷል። ምላሹ የህግ አግባብን ተከትሎ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ለህዝበ ወሳኔ የሚወስደውን ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ የመወሰን ፣ የመርሀ ግብር ሰሌዳ የማዘጋጀት የማፅደቅ እንደ አስፈላጊነቱ የማሻሻል እና የማስፈፀም ስርልጣን የተቋሙ ብቻ መሆኑን ምርጫ ቦርድ አስገንዝቧል።

ከቦርዱ ምላሽ ፦

" ... ቦርዱ ለዚህ ጉዳይ አፈፃፀም የሎጂስቲክስ ዝግጅት ለማድረግ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ምደባ ለመተግበር፣ የምርጫ ፀጥታ ጉዳይን ለመገምገም፣ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት፣ የምርጫ ጣቢያዎች ለማደራጀት፣ ለታዛቢ ሲቪል ማህበራት ፈቃድ ለመስጠት እና በጉዳዩ ላይ የሚያገባቸውን ባለድርሻ አካላት ለማወያየት የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ለምክር ቤቱ እንደሚገልፅ ከአክብሮት ጋር እናሳውቃለን። "

(ቦርዱ ያሳለፈው ውሳኔ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፦
- በጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ወላይታ፣
- ጌዴኦ፣
- ደቡብ አሞ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ደግሞ ፦
- በአሌ፣
- ቡርጂ፣
- አማሮ፣
- ባስኬቶ እና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች በምርጫ አስፈጻሚነት የነበሩ በቀጣይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ለሚካሄደው #ሕዝበ_ውሣኔ በምርጫ አስፈጻሚነት በድጋሚ ለመሣተፍ ፍቃደኛ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡለት ጠይቋል።

ፍቃደኛነታቸውን ለመግለፅም ከላይ የተጻፈው መልዕክት (text message) በእጅ ስልካቸው ሲደርሳቸው አንድን ተጭነው እንዲመልሱ መልዕክት ተላልፏል።

መልዕክቱ ከታች ከተያያዘው ማስፈንጠሪያ (Link) ጋር ከደረሳቸው የሚጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ፍቃደኝነታቸውን ማሳየት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

https://nebecertificate.org.et/recruitment 

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፦ - በጋሞ፣ - ጎፋ፣ - ወላይታ፣ - ጌዴኦ፣ - ደቡብ አሞ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ደግሞ ፦ - በአሌ፣ - ቡርጂ፣ - አማሮ፣ - ባስኬቶ እና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች በምርጫ አስፈጻሚነት የነበሩ በቀጣይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ለሚካሄደው #ሕዝበ_ውሣኔ በምርጫ አስፈጻሚነት በድጋሚ ለመሣተፍ ፍቃደኛ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡለት…
#NEBE

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ለሚያካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የጠየቀው በጀት 👉 541,270,104 ብር !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል መንግሥት ውስጥ በ6 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ማለትም ፦
- ጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ወላይታ፣
- ጌዲዮ፣ 
- ኮንሶና፣
- ደቡብ ኦሞ ዞኖች
- ቡርጂ፣
- አማሮ፣
- ደራሼ፣
- ባስኬቶ፣
- ኧሌ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ማስፈጸሚያ ያስፈልገኛል ያለውን አምስት መቶ አርባ አንድ ሚልዮን ሁለት መቶ ሰባ ሺህ አንድ መቶ አራት ብር ከሰማንያ ሁለት ሳንቲም (የ541,270,104.82) ተገማች በጀት ለኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NEBE

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን ገልጿል።

ቦርዱ የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ለህዝብ ይፋ ተደርጓል ብሏል።

@tikvahethiopia