TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በነበረው ውይይት ስለተደረሰበት ስምምነት አሳውቋል። በዚህም ከመንግስት ጋር፦ - የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱ መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲያደርግ፤ - አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤ እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት…
#መግለጫ
ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ስምምነቱን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ስምምነቱን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ስምምነቱን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia
#EOTC
ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
Credit : EOTC TV
@tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
Credit : EOTC TV
@tikvahethiopia
#EOTC
በእሥር ላይ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያንን በተመለከተ #በጥቂት_ቀናት ጉዳያቸው ታይቶ እንደሚፈቱ ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ብፁዕ አቡነ አብርሃም ማሳወቃቸውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙሀን አገልግሎት ዘግቧል።

Photo
" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል " - ቅዱስ ሲኖዶስ
ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጥ የተወሰደ ፦
" ... በዛሬው ዕለት የቤተ ክርስቲያን ጸሎቷ፣ ሐዘኗና ጩኸቷ ተሰምቶ ወደ ነበረችበት ልዕልናዋና አንድነቷ ተመልሳለች፡፡ ይህ አንድነቷና ልዕልናዋ እስከ ዓለም ፍጻሜ ተጠብቆ ይኖራል፡፡
በቅርቡ በቤተ ክርስቲያናችን ተከስቶ የነበረው ችግርም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ተፈትቷል፡፡
... በችግሩ አፈታት ወቅት መንግሥት በተለይም ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፖለቲካዊ ችግሩን በፖለቲካዊ መንገድ ከመፍታታቸውም ባሻገር የቤተ ክርስቲያን ችግር በቀኖናና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንዲፈታ ታላቁን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡
ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀደም ሲል ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ በማድረግ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አሁንም የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተጠብቆ እንዲኖር ላደረጉት መልካም ተግባር ቤተ ክርስቲያን ከልብ ታመሰግናለች፡፡
... ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል፡፡ ካህናት፣ ምእመናን በሀዘናችን ተካፋይ የነበራችሁ በሙሉ የዚህ ደስታ ተካፋዮች በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ቅድስት ቤ ክርስቲያን ደስታዋን ትገልጻለች፡፡ "

#ስምምነት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያጋጠመውን ፈተና ለመፍታት የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ፦
1. በኦሮሚያ ክልል በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት፤ ቅዳሴ እና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲሰጡ የተጀመረው ሥራ የሕዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልኩ እንዲጠናከር። ለዚህም ከዚህ በፊት ከተደረገው በተጨማሪ አስፈላጊው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።
2. በኦሮሚያና በሌሎች አካባቢዎች የተዳከሙ አብያተ ክርስቲያናት ቋንቋውን በሚያውቁ አገልጋዮችና በአገልግሎት እንዲጠናከሩ አስፈላጊው ዕቅድ ተዘጋጅቶ ከበፊቱ በበለጠ ተገቢው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።
3. በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚያገለግሉ ቋንቋውን የሚያውቁ አገልጋዮችን የሚያሠለጥኑ ተጨማሪ ኮሌጆች እና ማሠልጠኛዎች እንዲከፈቱ፣ የተከፈቱትም እንዲጠናከሩ እንዲደረግ።
4. ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት በቂ የሆነ የኦሮምኛ ቋንቋን የሚያውቁና በቋንቋው የሚያገለግሉ ኤጲስቆጶሳት በቀጣይ የግንቦት ርክበ ካህናት ተወስኖ እንዲሾሙ፡፡
5. ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብጹዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ ሀገረ ስብክታቸውና የክነት ማዕረጋቸው እንዲመለሱ።
6. በሦስቱ አባቶች የተሾሙት አባቶች ቀድሞ ወደነበሩበት የክነት ማዕረግ ይመለሳሉ፡፡ ከእነርሱ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ተመዝነው የሚያሟሉት እንደገና በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሾሙ ይደረጋል።
7. በአስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ በፋይናንስ ፣ በምደባ፣ በቅጥር የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት የወንጌል አገልግሎትን በሚያጠናክር መልኩ እናሻሽላለን።
8. የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከርና ለትውልድ አርአያ የሚሆን ቤተ ክህነት እንዲኖረን ለማድረግ አሠራራችንን በጥናት አሻሽለን ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ እናሻግራለን፡፡
9. ጥላቻን የሚያባብሱ ጉዳዮችን ከማድረግ መቆጠብ ይገባል። ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራን እና አባቶች ፍቅርን ከሚያጠፋ፣ ጥላቻን ከሚያበዛና መለያየትን ከሚያሰፋ ነገር ሁሉ እንዲቆጠቡ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ይሄንን ተግባር ሆን ብለው የሚያደርጉትንም እናወግዛለን።
10. የገጠመን ፈተና ይበልጥ ውስጣችንን ለመፈተሽ፤ አንድነታችንን ለማጠናከር፤ ወንጌልን የበለጠ ለመስበክና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስፋፋት ለበጎ እንጠቀምበታለን።
በመጨረሻም #ፍቅር ፣ #ይቅርታ እና #አንድነት እንዲመጣ የደከማችሁትን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም እናመስግናለን። ዋጋችሁንም እግዚአብሔር እንዲከፍላችሁ እንጸልያለን።

በወልቂጤ ምን ሆነ ?
ዛሬ ረቡዕ በወልቂጤ ከተማ ውስጥ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ 2 ሰዎች ሲገደሉ 7 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል።
በከተማው ነዋሪዎችን ካማረረ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን ለማቅረብ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ ወስደዋል።
በዚህ የፀጥታ ኃይሎች እርምጃም 2 ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች እና የጤና ምንጮችን ዋቢ በማድረግ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።
የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የሟቾቹን እና የቁስለኞቹን ብዛት ማረጋገጡን ዘገባው አክሏል።
ለሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ክስተት መነሻ፤ በአዲስ ክ/ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ላለፉት 3 ወራት መቋረጡ እንደሆነ የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ከመኖሪያቸው 14 ኪ/ሜ ርቀት ከሚገኙ አካባቢዎች ሲያጓጉዙ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
በተመሳሳይ ዛሬ ጠዋት ውሃ ለመቅዳት በተለምዶ " ዱባይ ካፌ አደባባይ " ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ቢጓዙም፤ በስፍራው የውሃ አገልግሎት በመቋረጡ ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ መውጣታቸውን የዓይን እማኞች ገልፀዋል።
ነዋሪዎቹ የጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ የወልቂጤ ከንቲባ ጽ/ቤት እና የወልቂጤ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ወደሚገኙበት ስፍራ በማምራት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ሲገልጹ ቆይተዋል።
በአካባቢው ጸጥታ ለማስከበር የተሰማሩት #የደቡብ_ክልል_ልዩ_ኃይል አባላት የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን #የአስለቃሽ_ጭስ በመተኮሳቸው ሰልፈኞቹ ድንጋይ ወደ መወርወር መግባታቸውን የዓይን እማኞቹ ገልጸዋል።
ይህን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ 2 ሰዎች ሲገደሉ 9 ሰዎች ቆስለዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Photo Credit ፦ ብስራት ዜዶ