#ትኩረት
በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዚህ ሰዓት የፀጥታ ችግር መኖሩን በወረዳው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።
ያለው ሁኔታ #እጅግ_በጣም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ባለው የፀጥታ ስጋት " ለነፍሳችን ሰግተናል " ያሉ ነዋሪዎች የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ሁኔታው እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።
ዛሬ በወረዳው ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፤ "ሰንበቴ በአሁኑ ሰአት ጭንቅ ውስጥ ገብታለች ፤ ዱኣ ወይም ፀሎት ትፈልጋለች!! የሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካላትን ልዩ ትኩረት ትሻለች። " ሲል አንድ አጭር ፅሁፍ አሰራጭቷል።
ወረዳው ይህንን ከማለት ውጭ ስለጉዳዩ ምንም የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።
በአጣዬ በኩልም ስጋት መኖሩን ቤተሰቦቻችን እየገለፁ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው ካሉት የቤተሰብ አባላቱ ሁኔታውን ለመከታተል ጥረት ያደርጋል።
ይህ የሀገራችን ቀጠና ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግር ሲከሰትበት እና የሰዎች ህይወት ሲቀጠፍበት ፣ ንብረትም ሲወድምበት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አረዳ " #በፍቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው " ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን መርምሮ ሹመታቸውን እንደሚያጸድቅ…
ፎቶ ፦ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ከስልጣናቸው በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁትን የቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ አግኝተው ማናጋገራቸና ምስጋና ማቅረባቸው ተሰምቷል።
ከሰሞኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና አቶ ሰላሞን አረዳ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ በምትካቸው አቶ ቴዎድሮስ ምህረት (ፕሬዜዳንት) እና ወ/ሮ አበባ እምቢአለ (ምክትል ፕሬዜዳንት) ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
Photo Credit : PMOEthiopia

#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና " ላልተገደበ ጊዜ " እንደሚሰጥ አሳውቋል።
የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሚያገኙት ፈተናውን ወስደው ብቁ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው ተብሏል።
ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው መውሰድ የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሀመድ ለኢፕድ ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በየስድስት ወሩ ፈተናውን የሚወስዱበት ዕድል እንዳለ ኃላፊው ጠቁመዋል።
የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ለአንድ ጊዜ ብቻ የፈተና ወጪያቸው እንደሚሸፈንላቸው ገልጸዋል።
በመንግሥትና በግል ተቋማት ላይ የሚሰጡ ከ300 በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዳሉ ያነሱት ኃላፊው፤ በየትምህርት መስኩ እየተደረገ በአስር ዙር ፈተናው ለመስጠት ታቅዷል።
#ኢፕድ
More : @tikvahuniversity

#አስቸኳይ በአሁን ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጨማሪ አሃዶችን የመፍጠር ቴክኖሎጂዎች (Blockchain technologies) ላይ የተመሰረቱ የክሪፕቶ ምርቶችና አገልግሎቶች ሁኔታ በመስፋፋት እና ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የክሪፕቶግራፊ ውጤት/ምርትንና አገልግሎትን በተመለከተ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 808/06 አንቀጽ…
#ETHIOPIA
የምናባዊ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ክሪፕቶከረንሲ) የሚመራበትን መመሪያ እና የቁጥጥር ስርዓት በመቅረፅ ላይ እንደሚገኝ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል።
አስተዳደሩ የክሪፕቶከረንሲ ግብይት አሁን ላይ ህጋዊ መሰረት የሌለው መሆኑን አስረግጦ ተገልጿል።
የክሪፕቶከረንሲ ተጠቃሚዎች በኢንሳ በይነ መረብ ኦንላይን እንዲመዘገቡ መልዕክት ተላልፏል።
የመመዝገቢያው አድራሻ https://crypto.insa.gov.et/register መሆኑ ተመላክቷታ።
አሁን ላይ የሚያንቀሳቅሱ አካላት ለህጋዊነታቸው ከወዲሁ ቢመዘገቡ ይበጃል ያለው አስተዳደሩ ሳይመዘገቡ የሚንቀሳቀሱት ላይ ክትትልና እርምጃ በቀጣይ የሚደረግባቸው እንደሚሆን አስጠንቅቋል።
Credit : FM ADDIS 97.1

ቅዱስ ሲኖዶስ ህገወጥ ነው ያለውና ቤተክርስቲያንን ያሳዘነው ፤ ምዕመኑንም ያስደናገጠው የ " ጳጳሳት " ሹሙት ምንድነበር ? ትላንት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት ተፈፅሞ ጳጳሳትን የመሾም ተግባር መከናወኑን መግለጿ ይታወሳል። ይኸው ሲመተ ጳጳሳት ፤ #ከቅዱስ_ሲኖዶስ እውቅና ውጭ #በሕገወጥ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ነው ቤተክርስቲያን ያሳወቀችው። …
#Update
ዛሬ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት አስቸኳይ ጉባኤ በማካሄድ " ሃይማኖታዊ ክህደት ፣ ቀኖናዊ ጥሰት እናአስተዳደራዊ ግድፈት " ታይቶበታል ያለውን የወሊሶውን " ሹመት " ማወገዙ ተገልጿል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ተገቢውን ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ምዕመናን በጸሎት እንዲቆዩም አሳስቧል።
ጉባኤው፤ በቤተክርስቲያን ላይ የተፈፀመው ሁሉን አቀፍ ክህደት ነው ያለ ሲሆን ክህደቱን የፈጸሙት አካላት ሥልጣን የሰጣቸውን መዋቅር(ተቋም) በመካድ የፈጸሙት ድርጊት እጅጉን አሳዛኝ ነው ብሏል።
የተፈጸመው ጉዳይ ህገ ወጥና ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ወንጀል እንደሆነ ገልጾ በምንም መመዘኛ ይህን ከፈጸሙ አካላት ጋር መደራደር በተዘዋዋሪ የቤተክርርቲያንን ሕግና ሥራዓትን ማፍረስ ነው ሲል አስገንዝቧል።
ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ አካል ሊሆኑ የሚችሉ የውሳኔ ሀሳቦችን ከቀኖና ቤተክርስቲያን እና ከሕግ አንጻር በመነሳት ጠቁሟል።
ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/EOTCPR-01-23
በሌላ በኩል፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና የብፁዕ አቡኑ ኤዎስጣቴዎስን እና የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት ማሸጉ ተሰምቷል።
እርምጃው ትላንት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመናድ እና ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለመከፋፈል በማቀድ " 26 ጳጳሳትን ሾመናል " ማለታቸውን ተከትሎ የተወሰደ ነው ተብሏል።
በተጨማሪ መረጃ፤ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሕገ ወጥ መንገድ ጵጵስና ተሹመዋል ያላቸውን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ኃይል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያንን አስተዳዳሪ ማገዱ ታውቋል።
ፎቶ፦ TMC

Photo
#Update
የህ/ተ/ም/ቤት የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ነገ ይመራል።
ነገ የሚኒስትሮችን ሹመት ማፅደቅ ጨምሮ ሌሎችም አጀንዳዎች የተያዙበት የምክር ቤቱ የ2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።
በዚሁ ስብሰባ ከታይዙት አጀንዳዎች መካከል ፤ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት እና ሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ማጽደቅ ይገኙበታል።
ተጨማሪ አጀንዳዎች ምንድናቸው ? ከላይ ተያይዟል።

#Update ዛሬ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት አስቸኳይ ጉባኤ በማካሄድ " ሃይማኖታዊ ክህደት ፣ ቀኖናዊ ጥሰት እናአስተዳደራዊ ግድፈት " ታይቶበታል ያለውን የወሊሶውን " ሹመት " ማወገዙ ተገልጿል። ቅዱስ ሲኖዶስ ተገቢውን ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ምዕመናን በጸሎት እንዲቆዩም አሳስቧል። ጉባኤው፤ በቤተክርስቲያን…
#Update
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
፤ ለሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የተሰጠ የመኖሪያ ቤት ውል በማቋረጥ ቤቱ እንዲታሸግ መደረጉን አሳወቀች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ፤ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ከጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠ ትዕዛዝ ከድርጅቱ የተሰጣቸውን መኖሪያ ቤት ውል በማቋረጥ ቤቱን መረከቡ ተገልጿል።
ድርጅቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው በህገ ወጥ መንገድ የቤተክርስቲያንን ቀኖና እና ህግጋት በመጣስ በትላንትናው እለት የተሰጠውን ህገ ወጥ ሹመት ተከትሎ ዋነኛ አስተባባሪና ተሿሚ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ መሆኑን ከቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ECSOC & ACSOT (1).pptx
16.3 MB
#Tigray
በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስተባባሪነት ወደ መቐለ ያመራው ልዑክ ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።
በፕላኔት ሆቴል በተዘጋጀው የውይይት መድረክ በትግራይ ክልል ያሉ 50 እንዲሁም ከአዲስ አበባ የመጡ 60 የሚደርሱ የድርጅቱ አባላት ተሳትፈውበታል።
በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ሪፖርቶች የቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
በውይይቱ ምን ሀሳቦች ተነሱ ?
በውይይቱ ጦርነቱ በማህበረሰቡ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን አድርሶ ማለፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የደረሰውን ውድመት በማየት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አሁን የተደረሰውን የሰላም ስምምነት በመጠቀም በሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብና መልሶ ግንባታው ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባው ተነስቷል።
በተጨማሪም ፤ በስነልቦና የተጎዳውን ህዝብ እንዴት ማከም እንደሚቻልና ከዚህም ሁሉ ችግር መሻገር እንደሚቻል ማሳየት የሚቻልበት መንገድ መፈጠር እንደሚኖርበት ተጠቁሟል።
ልዑኩ ከሰዓት ላይ ሰባ ካሬ ባለው የስደተኞች መጠለያ ካምፕ እና ዓይደር ሆስፒታል ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውንና በፌስቱላ የተጠቁ ሴቶችን በመመልከትና ነዋሪዎቹን በመጎብኘት የነበረውን ሁኔታ መረዳት ችሏል።
(ከላይ የተያያዘው ፋይል በውይይቱ በትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት የቀረበ የትግራይ ሁኔታ መግለጫ ሲሆን በርካታ መረጃዎችን ይዟል፤ ያንብቡ)

ዛሬ በመቐለ በነበረው ውይይት ወቅት ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የተወሰኑ መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም ግን መስተካከል ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ በትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት በኩል ሃሳቦች ተነስተዋል።
ይኸውም መሻሻል ያለባቸው ተብሎ የተነሱት ፦
- የገንዘብና የቁስ አጥረት መኖር፤
- የቴሌኮም አገልግሎቱ ቢጀመርም ደካማ መሆን፤
- የደህንነት ችግር፤
- የተሟላ የባንክ አገልግሎት ያለማግኘት
- ለሰራተኞች የሚከፈል ደሞዝ እጥረት እና ተነሳሽነት ማጣት፤
- ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማትና ሌሎች የውጭ ድርጅቶች ጋር ያለው ግንኙነት የተገደበ መሆኑና ሌሎችም ናቸው።