ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ አርፈዋል።
ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በውጪ ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው በተወለዱ 66 ዓመታቸው በታህሳስ 28/ 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3.56 ደቂቃ ከዚህ አለም ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ከአባታቸው አቶ ዘለቀ ሸንቁጥ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አሰለፈች አስፋው በሰኔ 21, 1948 ዓ.ም ነበር የተወለዱት።
ክብር ሰውነታቸው በታህሳስ 29, 2015 ዓ.ም ከውጪ በአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ጠዋት አቀባበል ከተደረገለት በኋላ ወደ ቄያቸው መኖሪያ ቤታቸው ጉዞ ይደረጋል ተብሏል።
የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም እሁድ ታህሳስ 30, 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9.00 ሰዓት በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሀዋሳ ከተማ ህዝብ የሀይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት ወደ ዘልዓለም መኖሪያቸው ይሸኛሉ።
ወ/ሮ አማረች ዘለቀ በተለይ በሀዋሳ ከተማ በሆቴል ዘርፍ (ሴንትራል ሆቴል) ከፍተኛ ስራን መስራት የቻሉ ለበርካታ ወጣቶችም የስራ እድል መፍጠር የቻሉ ነበሩ።
(ዶክተር ፍትህ ወልደሰንበት)
@tikvahethiopia

የገና ሎተሪ ዕጣ ወጣ።
የገና ሎተሪ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በህዝብ ፊት በይፋ የወጣ ሲሆን አሸናፊ የሚያደርጉ የወጡ የዕድል ቁጥሮችም ፡-
የ1ኛ ዕጣ የ10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0470132
2ኛ ዕጣ የ5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0914609
3ኛ ዕጣ የ 2.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0059544
4ኛዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0600123
5ኛዕጣ የ1 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0430545
6ኛ ዕጣ የ500 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0057083 እና በርካታ ዕጣዎቸ የወጡ ሲሆን የማስተዛዘኛ ዕጣ ቁጥር 5 በመሆን ወጥተዋል።
ምንጭ፦ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከሰሞኑን የፌዴራሉ መንግስት የ #ሰላም_ስምምነቱን በተመለከተ ከ50 በላይ ለማሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር። ማብራሪያውን ከሰጡት መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ነበሩ። በወቅቱ ፤ የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን አቅርበው ነበር። ምን ተጠየቀ ? ምንስ…
የወልቃይት ጉዳይ ...
" ለወልቃይት የአማራ ማንነት " መከበር የሚታገለው የልሳነ ግፉአን ድርጅት የወልቃይት ችግር በፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅጣጫ፣ በሪፈረንደምም ሆነ በድርድር ሳይሆን በፖለቲካ ውሳኔ ነው የሚፈታው ብሏል።
ከሰሞነኛው የወልቃይት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የድርጅቱ ፕሬዜዳንት አቶ ዓብዩ በለው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህ ወቅት ጋዜጣው የወልቃይት ጉዳይ የፌዴሬሽን ም/ቤት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ እንደሚፈታ መንግሥት በቅርቡ ግልጽ ማድረጉን አስታውሶ ለምን ድርጅታቸው ምክር ቤቱ መፍትሄ አይሆንም እንደሚል ተጠይቀው አብራርተዋል።
(የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በቅርቡ የተናገሩትን በዚህ ያንብቡ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/75534 )
የድርጅቱ ፕሬዜዳንት አቶ ዓብዩ በለው ፦
" በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) የተናገሩትን ማንሳት ይኖርብናል፡፡ ሕወሓት በጉልበት ወልቃይትን መውሰዱን ሬድዋን (አምባሳደር) በግልጽ አውስተዋል፡፡
ሕወሓት በጉልበት መሬቱን ሲወስድ ደግሞ ዝም ብሎ ሳይሆን ብዙ ግፍ ፈጽሞ መውሰዱን እኛ እናውቃለን፡፡ እኛ የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዚያ አካባቢ ተፈጽሟል ነው የምንለው፡፡
ሕወሓት የወሰደውን መሬት፣ እንዲሁም የጨፈለቀውን ማንነት ሕጋዊ ለማድረግ ይጠቅመኛል ብሎ የራሱን ሕገ መንግሥት አውጥቷል፡፡
ሕወሓት ለራሱ ብሎ ባወጣው ሕገ መንግሥት ደግሞ የወልቃይት ችግርን ለመፍታት አይቻልም፡፡ ይህ ምናልባትም አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ እንደሚባለው ነው የሚሆነው፡፡
ሕወሓት ጉዳዩን ለማወሳሰብ ብሎ በፈጠረው አካሄድ ችግሩን መፍታት አይቻልም፡፡ የወልቃይት ጉዳይ ቅሚያ ነው፡፡ በጉልበት መወሰዱን የመንግሥት ኃላፊዎች አምነውታል፡፡ ስለዚህ #በጉልበት የተወሰደውን ወደ ነበረበት መመለስ ነው መፍትሔው፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ችግሩን ይፍታው ማለት ችግሩን ያወሳስባል፡፡ አንደኛ ጉዳዩ የተፈጠረው የፌዴሬሽን ም/ቤት በሌለበት ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ ሆነ ፌዴሬሽን ምክር ከመቋቋማቸው በፊት ነው በጉልበት የተወሰደው፡፡
ሕግ ደግሞ ወደኋላ ተመልሶ ባልነበረበት ቦታ የሆነ ችግርን አይፈታም፡፡ የፌዴሬሽን ም/ቤት ችግሩን ያወሳስበዋል እንጂ ይፈታዋል ብለን አናምንም፡፡
ምናልባትም እነሱ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና አሠራሩን እንዲሻሻል አድርገው ችግሩን ለመፍታት የተሻለ መፍትሔ ይዘው ከቀረቡ እኛ አናውቅም፡፡
በእኛ እምነት ግን ወልቃይት በወረራና በጉልበት ነው የተወሰደው፡፡ ችግሩ መፈታት ያለበትም #በፖለቲካ ውሳኔ ወደ ነበረበት በመመለስ ነው፡፡
የተቀማን ማንነት ፣ የተጨፈለቀን ማንነት ዕውቅና ሰጥቶ መመለስ ነው፡፡
የወልቃይት ጉዳይ የፍትሕ ጉዳይ ነው፡፡ ይህን የፍትሕ ጥያቄ አሳንሶ የድንበር ጉዳይ ማድረግ፣ የ2 ክልሎች ግጭት ማድረግ ተገቢነት አይኖረውም፡፡
ብዙ ጭፍጨፋ እና ዕልቂት የተፈጠረበትን #የፍትሕ ጉዳይ የሁለት ክልሎች ወሰን ወይም መሬት ግጭት አድርጎ ማየት ችግሩን ማቅለል ነው፡፡
ችግሩን አሳንሶ ወይም በተዛባ መንገድ መመልከት ደግሞ የችግሩን አፈታትም ያወሳስበዋል፣ እንዲሁም ያከብደዋል ብለን እናምናለን፡፡ "
ሙሉ ቃለምልልስ ፦ https://telegra.ph/Ethiopian-Reporter-01-08-2
Credit : www.ethiopianreporter.com

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) እንደሚመጡ ተሰምቷል።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ በቅርቡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እንደሆነ ተሰምቷል።
ኪንግ ጋንግ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩን ጉብኝት በማስመልከት የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ ኪን ጋንግ የፊታችን ረቡዕ ጥር 3/2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሐመት ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ።
ከዚህ በተጨማሪ ኪን ጋንግ እና ሙሳ ፋኪ መሐመት በተገኙበት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እና የቻይና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣናት ስትራቴጂካዊ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።
የቀድሞ በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር እና የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ስለመገናኘታቸው እስካሁን የተባለ ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

20/80 እና 40/60 ውል ፦ የቤት እድለኞች #ውል_ለመዋዋል_ሲመጡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው ? - እጣው የደረሰው ግለሰብ ውል ለመፈፀም በአካል መቅረብ፤ - በውጭ የሚኖሩ ጉዳያቸውን በውክልና ለማስጨረስ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ (አውታንቲኬት) ሆኖ የመጣ ውክልና ማቅረብ፤ - የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤ - የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና…
#ማስታወሻ
ከነገ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ውል ማዋዋል ስራ ይጀመራል።
የውል መዋዋያው " #መገናኛ " በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ነው።
በሁለቱም የቤት ልማት መርሀ-ግብር ባለድለኞች #በአካል እየተገኙ ውል እንዲዋዋሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የውል ማዋዋሉ ፕሮግራም ለ60 የስራ ቀናት ወይም ለሁለት ወር ብቻ የሚቆይ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ተዋዋዬች ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በአንድ ማእከል የአገልግሎቱ መስጫ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
በተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎቹን በቢሮና በኮርፖሬሽኑ ዌብሳይት እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ያልተዋዋለ እድለኛ #በመመሪያ_ቁጥር 3.3/2011 መሰረት ቤቱን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የቤት ባለ እድለኞች #ውል_ለመዋዋል_ሲሄዱ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በዚህ መመልከት ይቻላል 👇
https://t.iss.one/tikvahethiopia/75662

ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ አርፈዋል። ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በውጪ ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው በተወለዱ 66 ዓመታቸው በታህሳስ 28/ 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3.56 ደቂቃ ከዚህ አለም ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ከአባታቸው አቶ ዘለቀ ሸንቁጥ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አሰለፈች አስፋው በሰኔ 21, 1948 ዓ.ም ነበር የተወለዱት።…
ፎቶ፦ የሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል ባለቤት ወይዘሮ አማረች ዘለቀ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።
Photo Credit : Hawassa City Communication