TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በእሳት አደጋው 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ውድሟል "

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ገልጿል።

ኮሚሽኑ አደጋው ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ መድረሱን አመልክቷል።

በገበያ ማዕከሉ ከሚገኙ 1 ሺ 600 ሱቆች ውስጥ 84 የሚሆኑት ላይ የእሳት አደጋው የደረሰ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት 1 ሺህ 516 የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ማትረፍ (500 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት) መቻሉን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በሰጠው መረጃ ፦

- አደጋውን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች እና 95 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተው ነበር።

- አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 4 ሰዓት 28 ደቂቃ ወስዷል።

- በአደጋው እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

- የአደጋ መንስኤ እየተጣራ ነው።

- የሾላ የገበያ ማዕከል በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ የገበያ ማዕከላት ውስጥ አንዱ ነው።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#ድሬድዋ

የኮንቴይነር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠጥ ላይ የሚገኘው የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ በድሬዳዋ ተጨማሪ የጭነት አገልግሎት የሚሰጥበት ጣቢያ መከፈቱን አሳውቋል።

ጣቢያው ፤ ደንበኞች ያላቸውን ጭነት በፈለጉት ቦታና ሰዓት ለማድረስ የሚስችል ተጨማሪ አማራጭ በመሆን  ያገለግላል ብሏል።

የኢትዮ - ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ ፤ የባቡር ኮንቴይነሮች የጭነት አገልግሎት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ ዋና ዋና ከተሞች መካከል በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ የተጀመረው የጭነት አገልግሎት አሁን ካሉት ዋና ዋና የእቃ ማጓጓዣ ጣቢያዎች ማለትም፦
- እንዶዴ፣
- ሞጆ፣
- አዳማ
- ናጋድ ጣቢያ በተጨማሪ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ " በድሬዳዋ ባቡር ጣቢያ የተጀመረው የጭነት አገልግሎት የጅምላ ጭነት ማጓጓዝ ለሚፈልጉ ደንበኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ወደሚፈልጉት የሀገሪቱ ክፍል ለማጓጓዝ የሚያስችል ነው " ያለ ሲሆን ዋጋ በማረጋጋት ረገድ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ብሏል።

#EDR

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ጉምሩክ ኮሚሽን በኮምፒውተር " ሲስተም ዩኒት "  ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፀ።

ኮሚሽኑ ፤ በሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር " ሲስተም ዩኒት " ውስጥ ተደብቀው የገቡ ፦

👉 100 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ፣
👉 ሀርዲስኮች
👉 ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ፦

- የኤክትሮኒክስ እቃዎቹ (ላፕቶፕ፣ ሀርድዲስክ፣...) የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን ሲስተም ዩኒት ውስጡን ባዶ በማድረግ የገቡ ናቸው።

-  በተገኘ የፍተሻ ውጤት ሰነድ ላይ ያልተገለፀው ዕቃ የቀረጥና ታክስ መጠን ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ነው።

- የተፈፀመዉ #የንግድ_ማጭበርበር ተግባር  በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፤ ምርመራም እየተጣራበት ነው።

- በተያዘው እቃ ላይም የውርስ ውሳኔ ተሰጥቷል።

መረጃው ከጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለታት ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረውን የሽረ የመንገደኞች በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል።

Photo Credit : ENA

@tikvahethiopia
🤔

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃደኛ አለመሆን የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት እያደረግኩት ባለው ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስነብቧል።

የቢሮ ኃላፊ አቶ አሥራት አዳሮ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፦

" በክልሉ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ #ባለሙያዎችንና #ኃላፊዎችን የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ትምህርታቸውን ባጠናቀቁበት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ በመሄድ ማስረጃዎቹ ሐሰተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ለማጣራት ሙከራ ብናደርግም የግል ትምህርት ተቋማት ፈቃደኞች አይደሉም፡፡

ከ5 እና 6 ወር በኋላ ተመልሳችሁ ኑ የሚል ምላሽ ስለሚሰጡን ወደ ትምህርት ተቋማቱ የምንልካቸው ባለሙያዎች ለእንግልት እየተዳረጉ ነው።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የትምህርት ጥራትን ከመጉዳትም ባሻገር የተማረ የሰው ኃይል በተፈለገው ቦታ ላይ እንዳይሠራና ጥራት ያለው አገልግሎት ለኅብረተሰቡ እንዳይሰጥ የሚያደርግ ነው።

በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው በሥራ ላይ በሚገኙ #አመራርና #ባለሙያዎች ሕዝቡ ትክክለኛ አገልግሎት እንዳያገኝ ሲያደርጉ ነበር ፤ ክልሉ የሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የትምህርት መረጃን አጣርቶ በሚያገኘው ውጤት መሠረት ከሥራ እና ከደመወዝ ከማገድ ባሻገር በሕግ እንዲጠየቁ ይደረጋል።

የማጣራቱን ውጤት ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ6ቱም ዞኖች የተጠቃለሉ መረጃዎችን በማደራጀት ምን ያህል አመራርና ባለሙያ በሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥሮ ሲሠራ እንደነበር ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል።  "

#EPA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ፦

#ከመገናኛ ወደ #ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

የአዲስ አበባ መገዶች ባለስልጣን ፤ የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍልና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

Credit : AARA

@tikvahethiopia