TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፦ • አንቶኒ ብሊንከን የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸምን አድንቀዋል። • የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ አቅርቦትን ለማሻሻል እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት ለመመለስ የወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል። • ብሊንከን የስምምነቱ ተፈፃሚነት የተፋጠነ እንዲሆን አሳስበው ፤ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሰብአዊ መብቶች ተቆጣጣሪዎች ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ…
#Ethiopia

በአሜሪካን ዋሽንግቶን ዲሲ የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ተገናኝተው ተውያይተዋል። የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ IMF ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ፣ በዕዳ ማቅለያ አስፈላጊነትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል። " ያለፉትን ስኬቶቻችንን ለማስጠበቅ እና የጀመርናቸውን ለውጦች የበለጠ ለማጎልበት ቁርጠኝነታችንን እገልጻለሁ " ሲሉ አክለዋል።

- ጠ/ሚሩ ከዓለም ባንክ ቡድን ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ጋር ተወያይተዋል። " የሠላም መስፈን ምርታማነትን እና የስራ ዕድል ፈጠራን የሚያጎለብት የኢኮኖሚ ሽግግር አጀንዳን ለማፋጠን እድል ይሰጣል " ብለዋል። ውይይቱ ባንኩ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፥ የዓለም ባንክ በድረገፁ ባሰራጨው መረጃ ፕሬዝዳንት ማልፓስ ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የውስጥ ግጭቶችን ማስቆም እና ዘላቂ ሰላም ማስፈን አስፈላጊነትን አስገንዝበዋል። በቅርቡ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል።

https://www.worldbank.org/en/news/statement/2022/12/14/readout-from-world-bank-group-president-david-malpass-s-meeting-with-prime-minister-abiy-ahmed-of-ethiopia

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ተቋሙ ፤ " መንግሥት በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ የጀመረውን ጥረት ለማገዝ እየሰራሁ ነው " ብሏል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ሲሆን እነዚህ ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ወጪ በማስቀረት በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላላቸው ለተሸከርካሪዎቹ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦቱን ለማቅረብ የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቷል ሲል ተቋሙ አሳውቋል።

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆናቸውን ተከትሎ ተጨማሪ የኃይል ፍላጎት ጥያቄ ይኖራል ተብሎ እንደሚታሰብ ተጠቁሟል።

ተቋሙ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነና ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት አድርጉ " - የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በተለያየ ምክንያት የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በታህሳስ ወር መጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርይ መምሪያ አሳውቋል። ትምህርት መምሪያው ፦ - በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመሸጋገሪያ…
" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና (የ2ኛ ዙር) ከታህሳስ 18 - ታህሳስ 21 ይሰጣል " - የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ

ከዚህ ቀደም በነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወቅት ፈተናቸውን መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች ፈተና ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል።

ዛሬ ከሲደማ ክልል የትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ሳይፈተኑ የቀሩ ተማሪዎችን በ2ኛ ዙር ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ድረስ ለማስፈተን ዝግጅት ተደርጓል።

@tikvahethiopia
የአምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የስራ ጊዜ አበቃ።

በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ፖርቹጋል ፣ ሞናኮ እንዲሁም UNSECO #የኢትዮጵያ 🇪🇹 አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የስራ ጊዜያቸውን እንዳጠናቀቁ አሳውቀዋል።

አምባሳደር ሄኖክ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ፤ በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣  ሞናኮ እና UNSECO በአምባሳደርነት ሀገራቸውን ያገለገሉበት የስራ ጊዜ ማብቃቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን በውጪ ሀገር ከወከል የበለጠ ትልቅ ነገር እንደሌለ የገለፁት አምባሳደር ሄኖክ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀገራቸውን የማገልገል እድል ስላመቻቹላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ፓሪስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ማህበረሰቡን አመስግነዋል ፤ ሰላምና ብልፅግናን ለኢትዮጵያ ተመኝተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከዚህ ቀደም ታስራ ከእስር የተፈታችው መስከረም አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ባለቤቷ መናገሩን ቢቢሲ ዘግቧል። የመስከረም አበራ ባለቤት አቶ ፍጹም ገ/ሚካኤል እንደተናግረው ፤ ከሰዓት 10፡30 አካባቢ " ሃያ ሁለት / 22 " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አብረው ሳሉ ሲቪል እና የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች መጥተው መስከረምን ይዘው ሄደዋል።…
መምህርት እና ፀሀፊ መስከረም አበራ ፍ/ቤት ቀረበች ።

መምህርትና ፀሀፊ መስከረም አበራ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረበች ሲሆን ፖሊስ " ህገ-መንግስቱን በሀይል ለመናድ በማሰብ በአዲስ አበባ እና በደቡብ ክልል ፤ ጉራጌ ዞን ንቃት በተባለ የበይነ መረብ ሚዲያና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም መንገድ እንዲዘጋ በማድረግና የመከላከያ ሰራዊት እንዳይታዘዝ በመቀስቀስ ወንጀል ተጠርጥራለች " ሲል ለፍ/ ቤቱ አስረድቷል።

ክስ ለመመስረት በቂ የሰነድ ማስረጃ ቢኖሩም የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብ ከጉራጌ ዞን ምስክሮች ማምጣት ስለሚጠይቅ 14 የምርመራ ቀናት ጠይቋል።

በመስከረም ጠበቆች በኩል የተጠረጠረችበት ወንጀል አለመፈፀሟን በማስረዳት የቀረበባት አቤቱታ የዋስትና መብት የማያስከለክላት ስለሆነ ዛሬውኑ በዋስ ተፈታ ጉዳይዋን በውጭ እንድትከታተል ተጠይቋል።

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ የጠበቆቹን መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ ፓሊስ የጠየቀውን 14 የምርመራ ቀናት ፈቅዶ ለ ታህሳስ 20/ 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መረጃውን 👉 የሮሃ ሚዲያ ነው።

@tikvahethiopia
#NationalExam

2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

በሁለተኛው ዙር ለፈተና የሚቀመጡ የሁሉም ክልል ተማሪዎች መለየታቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ፦

• የመጀመሪያውን ዙር ፈተና በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት መፈተን ያልቻሉ፣

• በሕግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው ለመፈተን ያልቻሉ፣

• የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ፣

• በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ፈተና ያልወሰዱ፣

• ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ፣

• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው፣

• ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት ፈተና እንዲወስዱ የተወሰነላቸው።

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአሜሪካን ዋሽንግቶን ዲሲ የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። - ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ተገናኝተው ተውያይተዋል። የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል። - ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ IMF…
#USA #AFRICA

ለ3 ቀናት የተካሄደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ሐሙስ ተጠናቋል።

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በጉባኤው ምን አሉ ?

- ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች በቅርቡ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች የሚያደርግት ጉብኝት እንደ ፕሬዝደንት የመጀመሪያው ነው። ቀኑን እና የትኞቹ ሀገራትን እንደሚጎበኙ ግን አላሳውቁም።

- አፍሪካ እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልፀው አሜሪካ ትኩረቷን እንደምትጨምርም ጠቁመዋል።

- ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ወደ አፍሪካ እንደሚልኩ ገልፀዋል። ወደ አፍሪካ ከሚላኩት ውስጥ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን፣ የገንዘብ ሚኒስትሯ ጃነት የሊን እና የንግድ ሚኒስትሯ ጂና ሬይሞንዶ ይገኙበታል።

- በሚቀጥለው ዓመት ለሚደረጉ ምርጫዎች 165 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመደብ ቃል ገብተዋል።

ፕሬዚደንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን የአፍሪካ አገራት መሪዎችንና ቀዳማዊ እመቤቶቻቸውን በዋይት ሃውስ የእራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአሜሪካ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ሊሳተፍ ወደ አሜሪካ አቅንቶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ሀገር መመለሱን የጠ/ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ አመሻሹን አሳውቀዋል።

#ቪኦኤ #አምባሳደር_ሬድዋን_ሁሴን

@tikvahethiopia
😢

ሀገራችን እኛም እንደ ህዝብ በብዙ መከራና ችግር ውስጥ አልፈናል፤ አጠገባችን የነበሩ ብዙዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ግፍ ታፈፅሞባቸዋል፤ እንደወጡም ቀርተዋል።

በርስ በርስ ግጭት፣ ጦርነት ታገዳድለናል፣ ተጨካክነናል፤ አሁን አሁን ግን የሚታየው ድርጊት ሁሉ አንዳንዶች ምን ያህል ትንሽ እንኳን ርህራሬ የሚባል ነገር ውስጣቸው እንዳሌለ የሚያሳይ ነው።

ከዚህ ቀደም በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ እጅግ ለማየት የሚዘገንን ግፍ ሲፈፀም፣ ሰው በቁሙ ሲቃጠል፣ ተወግሮ ሲገደል፣ ሰዎች ከጀርባቸው በጥይት ሲደበደቡና ወደ ገደል ሲከተቱ፤ ከምን በላይ ደግሞ ልክ በጎና ለትውልዱ ፍቅርና ጅግንነት ያስተላለፉ ይመስል በቪድዮ እየቀረፁ ፍፁም ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ሲፈፅሙ የነበሩ ሰዎች አይተናል።

በየወቅቱ ካየነው ተነስተን "ምናልባት በሀገራችን ያላየነው የተደበቀ፤ ከዚህ የከፋ ይኖር ይሆን?" ብለን ስንጠይቅ ነበር፤ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወረው ይኸው ይሁን ?

የሰሞኑን ቪድዮዎች ምንም ይሁን ምን ይኼን ያህል የሰው ልጅ ይጨክናል ወይ? ትንሽ ርህራኔ የሚባል ነገር አልፈጠረበትም ወይ? የሚያስብል ነው።

ከምንም የከፋው መጥፎ ድርጊት ተፈፅሞ ሲገኝ አድርጊዎቹን ለመከላከልና ለነሱ ጥብቅና ለመቆም የሚደረገው ጥረት እንዲሁም ጉዳዩን ለማብራራት የሚኬድበት ርቀት ነው።

ድርጊቱን ከማውገዝና ፍትህ ከመጠየቅ ይልቅ ካለፈው ጋር እያነፃፀሩ አንዱን ግፍ በሌላ ለማካካስ/ቀለል ብሎ እንዲታይ ለማድረግ የሚሞከረው ሙከራ ምን ያህል ሰብዐዊ መሰረታችን ከቀን ወደ ቀን እየጠፋ መሄዱን አመላካች ነው።

አንድ ድርጊት ሲፈፀም ድጋመኛ እንዳይፈፀም አድራጊዎቹ ምን ተደረጉ? የሚለው መሰረታዊ ጉዳይ ሲሆን ሁሉም ዜጋ ግፍን እኩል ማውገዝ ካልቻለና ፍትህ ካልጠየቀ ከዚህ የከፋ አዙሪት መውጣት አዳጋች ነው።

@tikvahethiopia
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሳዑዲ አረቢያ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ምን አለ ?

አምነስቲ ኢንትርናሽናል ከሰሞኑን በሳዑዲ አረቢያ ፤ ኢትዮጵያውያን ስላሉበት ሁኔታ አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

በዚህ ሪፖርቱ የገለፃቸው ፦

- " ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ናቸው " የተባሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ (ከ30 ሺህ ይበልጣሉ) ኢትዮጵያውን ስደተኞች በተጨናነቁ እስር ቤቶች #በሰቆቃ ውስጥ ይገኛሉ።

- ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች የሚገኙባቸው ስደተኞች በዘፈቀደ ተይዘው በእጅጉ በተጨናነቁት አል-ኻራጅ እና አል-ሹማይሲ በተባሉ እስር ቤቶች ይገኛሉ።

- የሳዑዲ ባለሥልጣናት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን #ኢሰብአዊ እና #ጭካኔ በተሞላበት አያያዝ ላልተገደበ ጊዜ በእስር ካቆዩ በኋላ በግድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ይደርጋሉ።

- ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ ውስጥ ለስቃይ የሚዳረጉት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የላቸውም በሚል ሲሆን ይህም ሁኔታ በ"ካፋላ" የሠራተኞች ቅጥር ሥርዓት ምክንያት የተባባሰ ነው።

- ባለፉት 5 ዓመታት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ በማለፋቸው በርካቶች ለከባድ እና ለዘላቂ አካላዊ እና አእምሯዊ ችግሮች ተዳርገዋል። በአሁኑ ወቅት ከ30,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ሁኔታ ተይዘው ተመሳሳይ ዕጣ እየተጋፈጡ ነው።

- የሳዑዲ ባለሥልጣናት ባለፉት 2 ዓመታት በእስር ቤቶች በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ማሰቃየቶችን እንዲሁም ቢያንስ 10 ሞቶች ላይ ምርመራ ሊያካሂዱ ይገባል።

https://www.amnesty.org/en/latest/news/2022/12/saudi-arabia-ethiopian-migrants-forcibly-returned-after-detention-in-abhorrent-conditions/

#BBC

@tikvahethiopia