TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች " ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ፤ ድምፄን አሰማለሁ " በሚል በተለይም የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰልፍ ተደርጓል።

ሰልፉን የሞያ ማህበራት፣ የሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደጠሩት ነው የተገለፀው።

በዚሁ ሰልፍ ላይ የሰልፉ ተሳታፊዎች፣ ህወሓት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና የትግራይ ህዝብ አሁን ላለበት ችግር ምንጭ ነው ያሉ ሲሆን ለቀጠናው ዘለቂ ሰላም ህወሓት #ትጥቅ_መፍታት አለበት ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሰልፈኞቹ " በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የጦር ሰራዊት አይኖርም ፣ በሉዓላዊነታችን አንደራደርም ፣ በሰብዓዊ እርዳታ ስም ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሰልፉ ተካፋዮች ፤ " የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አሳፋሪ ድርጊት መፈፀሙን ተከትሎ ነው " ያሉ ሲሆን " ከዛ በኃላም ለሰላም የተሰጠውን ዕድል አልተጠቀመም አሁንም ቢሆን ለ4ኛ ዙር ጥቃት እንዲከፍት ዕድል መስጠት አይገባም። " ብለዋል።

ምዕራባውያንና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በእርዳታ ስም ሆነ በሌላ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ምንጭ የሆነውን " ህወሓት " ን መደገፍ ሊያቆሙ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#Malawi

ባለፈው ሳምንት " 25 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች " አስክሬን ያለበት የጅምላ መቃብር ምዚምባ በተባለ ግዛት ደን ውስጥ መገኘቱን የማላዊ ፖሊስ ገልጿል።

የአካባቢው ወጣቶች ደኑ ውስጥ የሚያውክ ሽታ እንዳለ መጠቆማቸውን ተከትሎ ነበር አስክሬኖቹ በቁፋሮ የተገኙት።

የጅምላ መቃብሩ ከተገኘ በኋላ በቅርብ ርቀት ሌላ የጅምላ መቃብር ተገኝቶ ተጨማሪ 4 አስክሬኖችን ፖሊስ አውጥቷል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ፤ የማላዊ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የማላዊ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር ጃን ሴንዴዝ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ የተናገሩት፦

- በጣም የሚያሳዝን ነው። አስከፍቶናል። መንግሥታችን እንዲህ ያለ ድርጊት በጽኑ ያወግዛል። ትክክል አይደለም።

- ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ይውላሉ።

- ኢትዮጵያውያኑ በምን ምክንያት እንደሞቱ ለማወቅ የአስክሬን ምርመራ ይደረጋል።

- የጅምላ መቃብሩ ከተገኘበት ጥበቅ ደን ርቆ በሚገኝ ሌላ ደን ውስጥ 72 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተገኝተው በፖሊስ ተይዘዋል።

- ድንበር አቅራቢያና በአውራ ጎዳናዎች ላይ የሚያደርገው ቁጥጥር ጠብቋል። በሰሜናዊ የማላዊ ግዛት ሰው አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ እየተሞከረ ይገኛል።

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በማዘዋወር የተጠረጠሩ 10 የማላዊ ዜጎች መታሰራቸው የተነገረ ሲሆን እስከሁን ግን ፍ/ቤት አልቀረቡም ተብሏል።

አብዛኞቹ ማላዊ የሚገቡ ስደተኞች ከምሥራቅ አፍሪካ የሚነሱ ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ፤ኢትዮጵያ ከማላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር ስለ ክስተቱ ምርመራ እያደረገች ነው ብለዋል። በክስተቱ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልፀው የምርመራው ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ቤተሰቦች ስለ አንፋጋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ምን አሉ ? ፍርድዮስ ዩሱፍ ለኤፍ ኤም 97.1 ሬድዮ የተናገሩት ፦ " ... አሊ በራ ሞተ ምናምን እያሉ በየጊዜ ያወጣሉ። ነገር ግን የትላንትናው በጣም እኛንም የጎዳ ያሳዘነን ነው። ከትላንት ወዲያ ነው ከሆስፒታል የወጣው ፤ በጤንነት ጥዋት ላይ ደግሞ የሚገርመው በእግሩ እኔ ሄዳለሁ አብራችሁኝ ሂዱ ብሎ በመኪና ይዘነው…
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ #በህይወት አለ።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንጋፋው የሀገራችን አርቲስት ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ " አረፈ / ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል የተነሳ በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል ለላፉት ቀናት #የሕክምና_ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።

የ75 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ፤ ከዚህ ቀደምም የጤና እክል አጋጥሞት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የውስጥ ደዌ ህክምና ተደርጎለት ነበር።

ከዚህ ቀደም ህክምና ላይ እያለ ህይወቱ እንዳለፈ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሰተኛ መረጃዎች ተሰራጭተው የነበረ ሲሆን በዚህ ሀሰተኛ መረጃ ቤተሰቦቹ እጅግ #መጎድታቸው እና #ማዘናቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።

ሳናረጋግጥ የምናወራው ወሬ ምን ያህል የሰዎችን ህይወት እንደሚበጠብጥ እናውቀው ይሆን ?  ሁሉ ነገር ስርዓት አለው ፤ የሰውን ሀዘን ለማርዳት ይሄን ያህል መቸኮል ምንድነው ? ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ወዳጅ ይደነግጣል አይባልም ? በችኮላ እና መረጃ አደረስኩ ለማለትና ለዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰቢያ ሲባል ያልተረጋገጠ መረጃ ማሰራጨት ፍፁም ስርዓት የጎደለው ተግባር ነው።

#ውድ_ቤተሰቦቻችን ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የምትመለከቱትን ሀሰተኛ መረጃ ከማጋራት ተቆጠቡ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #KENYA ትላንት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በስልክ ከጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን " ሲትዝን ቲቪ ኬንያ " ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ፤ ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሲሆን የተወያዩባቸው #ዝርዝር_ጉዳዮች በይፋ አልተገለፀም። አሜሪካ ከሰሜን…
#Update

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ።

ውይይቱ ፤ በኢትዮጵያ እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ኬንያ ስላላት ወሳኝ ሚና ላይ ያተኮረ እንደነበር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስትሩ ፤ በታህሳስ ወር ለማካሄድ ከታቀደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዕቅዶች ዙሪያም ውይይት ማድረጋቸው ተመላክቷል።

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ለሚገኘው ጦርነት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ማሳወቋ ይታወቃል።

ነገ ሰኞ / ጥቅምት 14 በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ህብረት መሪነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሰላም ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ መያዙ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካፒታሉን ወደ 300 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ማቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

አየር መንገዱ አሁን ያለውን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማሳደግ ያቀረበው ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ ሲሆን ቦርዱ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን ያለንን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማሳደግ የፈለግንበት ምክንያት፣ ወሮታችን ከፍ እያለ በመምጣቱ ሲሆን፣ በቅርቡ ያፀድቁልናል ብለን እናስባለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የአየር መንገዱ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ እንደሚገኝ ጋዜጣው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ማረጋገጡን አመልክቷል።

አቶ መስፍን የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄውን ምክንያት በተመለከተ፤ " የምናንቀሳቅሰው ገንዘብ እያደገ በመምጣቱና የካፒታል ማሻሻያ ከሌለ ትክክለኛ የፋይናንስ አያያዝ ለመፍጠር ስለሚያስቸግር " ነው ብለዋል።

" በተጨማሪም አሁንም አዳዲስ አውሮፕላኖች እያስመጣን ነው፡፡ በምናስመጣበት ወቅት የዕዳና ካፒታል ምጣኔ መመጣጠን አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአውሮፕላን የሚገዛው በብድር ስለሆነ አበዳሪዎቹ ጋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍ ያለ የሀብት መጠን መድረስ አለበት። ብለዋል፡፡

የዕዳ እና ካፒታል ምጣኔ ተቋሙ ካለው ካፒታል አንፃር ሲታይ ምክንያታዊ ካልሆነ አበዳሪዎቹ ለማመን እንደሚቸገሩ አቶ መስፍን መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከሰሞኑን - ሰሜን ኢትዮጵያ ! ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ከኢፌድሪ መንግስት ፣ ከአሜሪካ መንግስት ፣ ከተመድ ፣ ከአውሮፓ ህብረት እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት የተሰጡ መግለጫዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች ፦ ➦ አሜሪካ ባወጣችው መግለጫ ፤ በባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር አጋማሽ ላይ " ህወሓት / TPLF " በአማራ ክልል በ " ቆቦ " አካባቢ ዘመቻ ማካሄዱንና በዚህም…
#Update

" በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል " - የኢትዮጵያ መንግስት

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

" ይህንን ሲያደርግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትን ወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል " ብሏል።

በዚሁ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ የርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ እየሠራ እንደሚግኝ አመልክቷል።

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ መሆኑንም አሳውቋል።

ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ እንደሚገኝ አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር የሚሳተፍ መሆኑንም ገልጿል።

መንግስት አጋጣሚውንም የሰላም ንግግሩን ግጭቱን በሰላም ለመፍታት የሚቻልበት ዕድል አድርጎ ይመለከተዋል ብሏል።

" በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት እየተስተካከለ የመጣውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር አድርጎ ይወስደዋል " ሲል አክሏል።

" በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል " ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ። ውይይቱ ፤ በኢትዮጵያ እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ኬንያ ስላላት ወሳኝ ሚና ላይ ያተኮረ እንደነበር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። ሚኒስትሩ ፤ በታህሳስ ወር ለማካሄድ ከታቀደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዕቅዶች ዙሪያም ውይይት…
#Update

አፍሪካ ህብረት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ይጀምራል ተብሎ ጥበቃል።

ለዚሁ የሰላም ንግግር የህወሓት ልዑክ ስፍራው መድረሱ ተነግሯል። ከዚህ በፊት ህወሓት የሰላም ድርድር የሚያደርጉት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ እንደሆኑ መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል፤ የሰላም ንግግሩ ተካፋዮችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ማቅናታቸውን አመልክቷል።

ከወራት በፊት የፌዴራል መንግሥት የሰላም ተደራዳሪ ቡድን አባላቱ አቶ ደመቀ መኮንን (ሰብሳቢ)፣  ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (አባል)፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ (አባል) ፣ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር (አባል)፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (አባል) ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ (አባል)፣ ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር (አባል) መሆናቸውን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#የመከላከያ_ሠራዊት_ቀን

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከለካያ ሚኒስቴር ከዚህ ዓመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በየዓመቱ " ጥቅምት 15 " ቀን እንዲከበር ወስኗል። ቀኑ " የሠራዊት ቀን " ተብሎ እንዲሰየም ሚኒስቴሩ የተለያዩ ታሪካዊ ኩነቶችን መቃኘቱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ የሠራዊት ቀን ሲከበር የመጀመሪያው ነውን ?

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ1950 ዓ.ም ግንቦት 20 የተካሄደው የስፖርት ውድድር በሠራዊታቸው ውስጥ የፈጠረው መነቃቃት አስደስቷቸው ዕለቱ የጦር ኃይሎች ቀን ሆኖ በየ 3 ዓመቱ እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፈዋል።

ከ1966 ዓ/ም በኋላ የጦር ኃይሎች ቀን አንዴ ሲከበር አንዴ ሲቋረጥ ቆይቷል።

ከ1987 ዓ/ም ጀምሮም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት በአዋጅ የተቋቋመበትን ቀን ለማሰብ የካቲት 7 ቀን የሠራዊት ቀን ሆኖ ሲከበር ቆይቷል።

ጥቅምት 15 ለምን ተመረጠ ?

ይኽ ቀን " የሠራዊት ቀን " ሆኖ ሲመረጥ የተለያዩ ታሪካዊ ኩነቶች ከግምት ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።

በዚህም የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደ አንድ የሀገሪቱ ተቋም ሆኖ በሚኒስቴር መስሪያ ቤትነት ደረጃ የተቋቋመበት ጥቅምት 15 ቀን 1900 የሠራዊት ቀን እንዲሆን ውሰኔ ላይ ተደርሷል።

አጼ ምኒሊክ 1900 ካቋቋሟቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አንዱ የጦር ሚኒስቴር ሲሆን ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ በሚኒስትርነት ተሾመውም ነበር።

ንጉሱም ይህንን ዜና በይፋ ለዓለም ሀገራት ማሳወቃቸውን ተከትሎ በአሜሪካና በእንግሊዝ ጋዜጦች ጭምር ታትሞ ወጥቷል።

ዘንድሮ ቀኑ በፖናል ውይይት እንዲሁም በመጽሐፍ ምረቃ ብቻ የሚከበር ሲሆን በቀጣይ "ለማይታወቁ ጀግኖች" እንዲሁም ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት የቀብር ሥፍራ ለማዘጋጀት ሥራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia