TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በወጣላቸው የጉዞ መርሃ - ግብር መሰረት ለፈተና ወደየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች እየተሸኙ ይገኛሉ።

ከዚህ ባለፈም ፤ ሰኞ መስከረም 30 ለሚጀምረው ፈተና ተማሪዎች ወደፈተና ማዕከሎቻቸው እየገቡ ሲሆን በሚገቡበት ተቋም እንዲሁም ከመነሻቸው የፀጥታ አካላት ፍተሻ እያደረጉ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቀ እንዲሁም የተማሪዎች ደህንነት እና የተቋማት ሰላም እንዲረጋገጥ 8,000 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይሳተፋሉ።

NB. የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29 እሁድ ጠዋት ላይ መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል።

ፎቶ፦ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ፣ የደ/ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን ፣ በሺንሺዳ ከተማ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጋምቤላ ክልል የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበለው እና እንደሚያወግዝ በገለፀበት መግለጫ ምን አለ ? - ሚዛናዊነት የጎደለው በመሆኑ ምርመራውን አልቀበለውም፤ በጥብቅም አወግዛለሁ። - ሪፖርቱ የአንድ ክልል የፀጥታ ተቋምን ከተራ የአሸባሪ ቡድን ተላላኪ ጋር በአንድነት ያየ፤ በክልልና በአገር ላይ ይደርስ የነበረ ከፍተኛ ጥቃት በመቀልበስ ሂደት የህይወት መስዋዕትነት የከፈለውን የፀጥታ ተቋሙን በጅምላ የፈረጀ፤…
* ከኢሰመኮ የተለከ መግለጫ !

" በጋምቤላ ከተማ በብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋም እና ሠራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በክልሉ የስብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ምልከታ የሚጥል በመሆኑ የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ሊያስቆሙ ይገባል " - ኢሰመኮ

ከኢሰመኮ መግለጫ የተወሰደ ...

" ... የሪፖርቱን (https://t.iss.one/tikvahethiopia/73948) ይፋ መደረግ ተከትሎ በማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾች እና መገናኛ ብዙኃን የተሳሳተ፤ አነሳሽ እና ዛቻ ያዘሉ መረጃዎች ሲሰራጩ  እንዲሁም በኢሰመኮ ባልደረቦች ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ መልእክቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል።

ኮሚሽኑ ጉዳዩን ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍታት እንደሚቻል በማመን ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ ቆይቷል።

ሆኖም መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ/ም በቡድን ሆነው የመጡ ሰዎች ወደ ኢሰመኮ ጋምቤላ ጽሕፈት ቤት በመሄድ የተለያዩ የጥፋት ድርጊቶችን የፈጸሙ ሲሆን፣ በኢሰመኮ ባልደረቦች ላይ #ዛቻ እና #ማስፈራሪያ አድርሰዋል።

እንዲሁም በከተማዋ የተለያዩ የስብአዊ መብቶች ሥራዎችን በሚያከናውኑ ሌሎች ድርጅቶች ላይ ተመሳሳይ ጥፋት አድርሰው ድርጅቶቹ ከከተማው ለቅቀው እንዲወጡ አስፈራርተዋል። "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዜዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተቀብለዋቸዋል። ሩቶ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የቴሌኮም ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል። ዶ/ር…
#HappeningNow

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱን በአዲስ አበባ " ወዳጅነት አደባባይ " በአሁን ሰዓት እያካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ስነስርዓት ላይ ቀደም ብሎ እንደተገለፀው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ተገኝተዋል።

Photo Credit : Safaricom Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱን በአዲስ አበባ " ወዳጅነት አደባባይ " በአሁን ሰዓት እያካሄደ ይገኛል። በዚሁ ስነስርዓት ላይ ቀደም ብሎ እንደተገለፀው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ተገኝተዋል። Photo Credit : Safaricom Ethiopia @tikvahethiopia
#BREAKING

ለሳፋሪኮም ሞባይል መኒ ተፈቀደ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ " ሞባይል መኒ " መፈቀዱን አስታውቀዋል።

ይህን ያሳወቁት በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ነው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ተጨማሪ መረጃዎችን እንልክላችኃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ለሳፋሪኮም ሞባይል መኒ ተፈቀደ። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ " ሞባይል መኒ " መፈቀዱን አስታውቀዋል። ይህን ያሳወቁት በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ተጨማሪ መረጃዎችን እንልክላችኃለን። @tikvahethiopia
#MobileMoney

ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ምስጋና አቀረቡ።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊልያም ሩቶ የኢትዮጵያ መንግስት ለሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር እንዲያደርግ በመፍቀዱ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

ፕሬዜዳንት ሩቶ " የኬንያ ህዝብ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ  ይህን እንዳስፈጽም የቤት ስራ ሰጥቶኝ ነበር፤ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አገልግሎት በመፍቀዱ አመሰግናለሁ " ብለዋል።

ሳፋሪኮም በኬንያ በ " ኤም ፔሳ " የገንዘብ አገልግሎት ያገኘውን ስኬት በኢትዮጵያ ለመድገም እንደሚሰራም ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia