TIKVAH-ETHIOPIA
#ሳፋሪኮም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት ነው። በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች…
#DireDawa #SafaricomEthiopia
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች አገልግሎት በ " 700 " ላይ በመደወል ማግኝት ይቻላል።
ዛሬ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ ጀምሯል።
ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎቶች በጥሪ ማዕከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም ፦
- በአማርኛ
- በአፋን ኦሮሞ
- በሱማሊኛ
- በትግርኛ እንዲሁም እንግሊዝኛ የማግኘት አማራጭ የሚኖራቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን " 700 " ላይ በመደወል ማናገር ይችላሉ።
* ማስታወሻ
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት ናቸው። የሽያጭ ማዕከሎቹ የሚገኙት ፦
- #ከዚራ፣
- #መስቀለኛ
- #ኮርኔል ነው።
#SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa
@tikvahethiopia

Photo
#ወልድያ
ወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
የተለያዩ ሚዲያዎች እና የፖለቲካ ተንታኝ ነን የሚሉ የውጭ አካላት በማህበራዊ ሚዲያው ወልድያን በተመለከተ ሀሰተኛ ዜና እያሰራጩ ይገኛሉ።
" ከወልድያ አመራሩ ወጥቷል፣ ወልድያንም ህወሓት ይዟል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ሁሉም ሀሰት መሆኑና ህዝቡን ለማሸበር የሚሰራ ስራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።
ከዚህ ቀደም በነበረው ግጭት በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ አይነት በሀሰት ህዝብን የማሸበር ስራ ሲሰራ፣ ህዝብን ለማስደንገጥ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉና በዚህ ሳቢያ ብዙ መመሰቃቀል ሲፈጠር እንደነበር አይዘነጋም።
እስካሁን ድረስ በወልድያና በቀጠናው ባለው ሁኔታ ከወልድያ ከተማም ይሁን ከጅቡቲ ወደብ የሚነሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን ከተለመደው የዕለት ተዕለት ጉዟቸው ያስተጓጎላቸው ሁኔታ እንዳልተከሰተ ከወልድያ ከተማ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከሚማሩ ተማሪዎች ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው የወጡ፤ የትራንስፖርት አጥተውም በእግር የተጓዙ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።
አንዳንድ መልዕክት የላኩ የግቢው ተማሪዎች ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ " ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግ ፤ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ እነሱም ቤተሰብም ጭምር ጭንቀት ላይ በመሆኑና በዚህ ሁኔታ ትምህርትን በንቃት መከታተል ስለሚያስቸግር ተቋማቸው መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል።
በተማሪዎቹ ስጋት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።

#DireDawa #SafaricomEthiopia የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች አገልግሎት በ " 700 " ላይ በመደወል ማግኝት ይቻላል። ዛሬ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ ጀምሯል። ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎቶች በጥሪ ማዕከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም ፦ - በአማርኛ - በአፋን ኦሮሞ - በሱማሊኛ - በትግርኛ እንዲሁም እንግሊዝኛ የማግኘት…
#SafaricomEthiopia #DireDawa
ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ ፣ ለአየር ሰዓት እና ልዩ ልዩ የደንበኞች አገልግሎት ከ3ቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከላት (ከዚራ፣ መስቀለኛ፣ ኮኔል ከሚገኙት) በተጨማሪ ብራንድድ በሆኑ በሁሉም የከተማው ሱቆች #ሲም_ካርድ እና #አየር_ሰዓት ማግኘት እንደሚቻል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።
#SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa
@tikvahethiopia
ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ ፣ ለአየር ሰዓት እና ልዩ ልዩ የደንበኞች አገልግሎት ከ3ቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከላት (ከዚራ፣ መስቀለኛ፣ ኮኔል ከሚገኙት) በተጨማሪ ብራንድድ በሆኑ በሁሉም የከተማው ሱቆች #ሲም_ካርድ እና #አየር_ሰዓት ማግኘት እንደሚቻል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።
#SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa
@tikvahethiopia
" በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት የአካልጉዳተኞችን መብቶች ያከብሩ " - የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር
ወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ነዋሪ የሆነው እያሱ ዴላባሌ የተባለ አካልጉዳተኛ ግለሰብ፣ በስራ ቅጥር ወቅት የደረሰበት የአንድ አመት ውጣውረድ በሚዲያ ለሕዝብ ይፋ መሆኑን ተከትሎ መረጃውን ለሚዲያ ተቋማት ያደረሰው ግለሰብ ከፍርድቤት ትእዛዝ ውጭ ለእስር መዳረጉን እና በሗላም በፍርድ ቤት ውሳኔ በዋስ መፈታቱን የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማጣራት ችሏል፡፡
ማህበሩ በአቶ እያሱ ላይ የተፈጸመውን የመብት ጥሰት አስመልክቶ ለሚዲያ ተቋማት መረጃ በሰጠው ግለሰብ ላይ የተፈጸመው የመብት ጥሰትም ሆነ ያላግባብ በእያሱ ላይ የተፈጸመው የተንዛዛ የስራ ቅጥር ሂደት፣ ህገወጥ እና ተቀባይነት የሌላቸው በበቂ ሁኔታ ሊወገዙ የሚገባቸው የመብት ጥሰቶች መሖናቸውን እገነዘባለሁ ብሏል።
በዚህ ተጨባጭ ጉዳይም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ከህገወጥ እስር የመጠበቅ፣ በአርባስምንት ሰአት ውስጥ ፍርድቤት የመቅረብ መብት እንዲሁም ሌሎች ሰባዊ መብቶች የተጣሱ መሆናቸውን፤ በሌላ በኩልም የእያሱ ዴላባሌ የስራ ቅጥር መብት የተጣሰ መሆኑን ማህበሩ ማረጋገጡን ገልጿል
በመሆኑም የወላይታ ዞን አስተዳደር በህገወጥ እስር እንዲፈጸም ያደረጉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ , የአቶ እያሱ ዴሌባሌ የስራ ቅጥር ሂደት በአስቸኳይ ተጠናቆ የስራ ቅጥር እንዲፈጸምለት እንዲደረግ, የአቶ እያሱ ዴላባሌን ጉዳይ እንደመነሻ በመውሰድ የወላይታ ዞንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት የአካልጉዳተኛ የስራ ቅጥር አመልካቾችን እና ሰራተኞችን መብቶች እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርቧል።
(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

#Haile_Hotels_and_Resorts
ሃይሌ ሪዞርት በአዲስ አበባ ያስገነባውን ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በቅርቡ ያስመርቃል።
ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ያስገነባውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በቅርቡ እንደሚያስመርቅ ተገልጿል።
ባለ ዘጠኝ ወለል ዘመናዊ ሕንጻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንደሆነ የተነገረለት የሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴል 8ኛ ሆቴል "ሃይሌ ግራንድ ሆቴል" ተብሎ እንደተሰየመ ተሰምቷል፡፡
ሆቴሉ 160 ምቹ የመኝታ ክፍሎች ፤ ስታንዳርድ እና ፕሬዝደንሺያል ተብለው የተለዩ ልዩ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ፤ የመዋኛ ገንዳ ፤ ጂምናዝየም ፤ ቅርጫት ኳስ ፤ የቤት ውስጥ እግር ኳስ ፤የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻዎች እና የምሽት ክበብ አካቶ የያዘ ነው ፡፡
በተጨማሪም 300 መኪኖች የሚይዝ ፓርኪንግ በሕንጻው ምድር ክፍል ተገንብቶለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሰራተኞች ቅጥር እና ስልጠና በመካሔድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 በሃዋሳ አንድ ብሎ የመጀመሪያውን ሆቴል የከፈተው ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በቅርቡ በወላይታ ሶዶ ፤ ደ/ብርሃን እና ኮንሶ ተጨማሪ ሶስት ሆቴሎች እንደሚከፍት ታውቋል፡፡
በቀጣይ በጎርጎራ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ልዩ የመዝናኛ ሆቴል እንደሚገነባ እና ሃይሌ ሪዞርት ዓለም አቀፍ ብራንድ በማድረግ በምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሆቴሎች እና ሪዞርቶች የመገንባት እቅድ እንዳለው ታውቋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

#Update
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባደረባቸው ስጋት ምክንያት ግቢያቸውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በሚመለከት ውሳኔ አሳለፈ።
ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በ22/12/2014 ዓ.ም ባደረባቸው ስጋት ምክንያት የተነሳ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።
በዚህ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1ኛ. የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ #በቀጣይ_ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ይሆናል።
2ኛ. የክረምት መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

* የቀጠለው የግጭት ይቁም ጥሪ !
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ካገረሸ ቀናት ያለፈ ሲሆን ግጭቱ ከቀን ወደ ቀን እየተባበሰ የሚደርሰው ጉዳትም እየጨመረ መጥቷል።
እስካሁን የቀረቡ የሰላም ጥሪዎችም ሰሚ ያገኙ አይመስልም።
በአሁን ሰዓት የአማራ እና የአፋር ክልሎች ዳግም ጦርነት እያስተናገዱ ዜጎችም ክፉኛ እየተሰቃዩባቸው ይገኛሉ።
እስካሁን ድረስ ዳግም ባገረሸው ጦርነት ንፁሃን ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል ፣ በርካቶች በጦርነትና ስጋት ጭንቀት ላይ ወድቀዋል ፤ ዜጎች ተዘርፈዋል ፣ አቅም ያላቸው ሰላምን ፍለጋ በእግር ሊሸሹ ተገደዋል።
ያንን ከወራት በፊት የነበረን የጦርነት ወቅት ፈፅሞ ማስታወስ የማይፈልጉ #እናቶች ልጆቻቸውን ሰላም ወዳሉባቸው ቦታዎች ለማምጣት ዋጋ እየከፈሉ ነው።
ይህ ሁሉ በሚሆንበት በዚህ ወቅት ሰላም እንዲሰፍን እና ግጭት እንዲቆም በሀገር ውስጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎች መቅረባቸውን ቀጥለዋል።
ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱ እንደሚያሳስበው ገልጿል።
ኮሚሽኑ የግጭት ሰለባ በሆኑ አካባቢዎች ያለው ሲቪል ህዝብ ቀድሞ ከደረሰበት ስቃይ ያላገገመ ፣ የሚወዷቸው ያጣ፣ መሰረታዊ አገልግሎት ማግኘት ያልቻለ ማገገምን እና ፍትህን የሚጠብቅ ነው ብሏል።
ኢሰመኮ ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊዎች ግጭት በማቆም ለሰላማዊ መፍትሄ የቆመውን ንግግር እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል ፤ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር በተመድ የተቋቋመው ኮሚሽን ዳግም ግጭት መቀስቀሱ እንዳሳሰበው እና እንዳስቆጣው ገልጿል።
ግጭቱ ሰላማዊ ሰዎች ያለባቸው ችግር ይበልጥ ያባብሳል ብሏል። ሁሉም ወገኖች ውጊያ አቁመው ወደ ውይይት ይመለሱ ሲልም ጠይቋል።
(ተጨማሪ ከላይ ተይያዟል)

#ATTENTION ደሴ ! ከደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማው ሰላም እና ደህንነት ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም ፦ - የምግብ ቤቶች ፣ የምሽት መጠጥ ቤቶች/ግሮሰሪዎች/ ከምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም ምክንያት አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ተከልክሏል። - ማንኛውም ምርት ላይ የዋጋ ጭማሬ የሚያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል። - በመፈናቀል…
#ATTENTION
ሐይቅ !
የሐይቅ ከተማ አስተዳደርና የተሁለደሬ ወረዳ የጸጥታ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም ፦
- የባለ 3 እግር ተሽከርካሪና አነስተኛና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።
- የመጠጥ ግሮሰሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።
- ህግ ከሚያስከብሩ የጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- በየጫት ቤቱና መቃሚያ ቤቶች በማንኛውም ሰዓት መሰባሰብ፤ በነዚህ አካባቢዎች መቃምና መገኘት ተከልክሏል።
- ከጸጥታ ኃይሉ ውጭ በዘመቻ ሰበብ ከመንግስት እውቅና ውጭ ማንኛውንም ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጥ አልባሳት፣ ትጥቅ፣ የጦር መሳሪያና የመሳሰሉትን በማንኛውም ሰዓት በከተማው ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።
- ተፈናቅይም ሆነ ሌሎች ወደከተማው የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት በሚያገኙበት ተቋም ራሳቸውን የመግለፅ እንዲሁም ተቋማቱም መጠየቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
- በከተማው አሉባልታ መንዛት፣ ህዝቡን በማሸበር አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ፣ የግል ንብረት እና እቃ እንዲሰብሰብ ማነሳሳት በጥብቅ ተከልክሏል።
ነዋሪዎች ማንኛውም ጥቆማ ካላቸው በ 033 222 0481 ፣ 033 222 0955 ፣ 0333 222 0006 በመደወል መጠቆም ይችላሉ ተብሏል።

#Korojo
ለዘመን መለወጫ የሚያስፈልጎትን ሁሉ Korojo app ላይ በተመጣጣኝ ዋጋና በብዙ አማራጭ ያገኙታል።
ኤሌክትሮኒክስ፣ አልባሳት፣ ኮስሜቲክስ፣ የቤት እቃዎች እና ሌሎችም ሳይለፉና ሳይደክሙ ካሉበት ቦታ ሆነው በስልክዎ ብቻ ይሸምቱ!
መተግበሪያውን ያውርዱ: https://korojo.app/download

" ኢቫንጀሊካል ቲቪ "
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ኢቫንጀሊካል ቲቪ ነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም የሙከራ ስርጭት እንደሚጀምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት አሳውቋል።
የቴሌቪዥን ጣቢያው በቄስ ዶክተር ገመቺስ ደሰታ ባለቤትነት ስር የነበረ ሲሆን በቅርቡ ለኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብተክርስቲያናት ካውንስል ተበርክቷል።
ለ4 አመታት ያህል የስርጭት ላይ ቆይቶ የነበረው ጣቢያው ለ1 አመት ያህል ስርጭቱ ተቋርጦ ከቆየ በኃላ ወደ አየር ተመልሶ ነሃሴ 26/2014 ዓ.ም የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀምር ተገልጿል።
መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ መደበኛ ስርጭቱን ይጀምራልም ተብሏል።
ኢቫንጀሊካል ቲቪ መደበኛ ስርጭቱን ሲጀምር ልዩ ልዩ ትምህርቶች፥ ስብከቶች፥ ወቅታዊ ዝግጀቶች፥ ቶክ ሾዎች፥ እለታዊ ዜናዎችን ጨምሮ የተለያዩ አስተማሪና ገንቢ ዝግጅቶችን ለተመልካቾቹ እንደሚያቀርብ ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ገልጿል።
የጣቢያው ስርጭት በኢትዮ ሳት- Frequency 11105 - Symbol rate 45000 - Polarization Horizontal እንደሚተላለፍም ተጠቁሟል።