TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ

ክረምቱ እየተጠናከረ ነውና #ከፍተኛ_ጥንቃቄ አድርጉ።

በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየጣለ ካለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር በተያያዘ በጎርፍ ምክንያት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ፣ ንብረትም ላይም ጉዳት እየደረሰ ነው።

ትላንት ከክረምቱ ጋር በተያያዘ አደጋ ደርሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፤ ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

- በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ በአንድ መጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ግለሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ በዚህም የ2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ሌሎች ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ በ8 ቤቶች የሚኖሩ 30 ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ደርሷል።

🌊 የትላንቱ አደጋ የደረሰው የፍሳሽ ቦዮች በግንባታ ተረፈ ምርት በመደፈናቸውና ከዚህም ጋር ተያይዞ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ገንፍሎ የወጣ ጎርፍ በመጋዘን ቤት ውስጥ ተጠራቅሞ የመጋዘኑን አንዱን የግንብ ግድግዳ በመናዱ ነው። ቦታው ከዚህ ቀደም በስጋት ቀጠና ከተለዩት አንዱ ነው።

- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9፣ ልዩ ቦታው ፋና ወጊ በተባለ ቦታ ትላንት 9:00 ሰዓት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው ነዋሪዎች የንብረት ጎዳትና መሠረት ልማቶች ላይ፤ የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ ፣ የወንዝ ድጋፍ ግንባታ ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 እና ወረዳ 07 ነዋሪዎችን የሚያገናኝ ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በሌሎችም አከባቢዎች ለጎርፍ አደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎች ላይ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው የተሰባሰበው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው።

@tikvahethiopia