#ሰበር_መረጃ
በነገው ዕለት #በአዲስ_አበባ ከተማ ሊካሄዱ የነበሩት የጠዋቱ የኦሎምፒክ ሳምንት የመክፈቻ ፕሮግራም እና የከሰዓቱ የስጦታ-ለአዲስአበባዬ ፕሮግራሞች ሙሉ በሙሉ #ተሰርዘዋል።
Via Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ሰበር_ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት የጄኔራል ሰዓረ መኮንን ገዳይ ነው የተባለውን ተጠርጣሪ ማንነት ይፋ አደረገ። የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ይፋ እንዳደረገው ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የተገደሉት አስር አለቃ #መሳፍንት_ጥጋቡ_መኮንን በተባለ ተጠርጣሪ ነው። ከ250 በላይ ተጠርጣሪዎች በባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የፍትኅ የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።
Via #DW
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #DW
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት #በሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ተከታታይ #ግድያ የመፈጸም #ዕቅድ እንደነበር አስታውቋል።
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና የቀድሞው የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ጄኔራል ኣብርሃም ወልደማርያም /ኳርተር/ በታይላንድ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ጄኔራል ኣብርሃ ኢትዮጵያ ከነበሯት 4 ባለ ሙሉ ጄኔራሎች አንዱ የነበሩ ሲሆን የሌላውን ጄኔራል ሰዐረ መኮንን ህልፈት ተከትሎ የሙሉ ጄኔራሎች ቁጥር በአንድ ሳምንት ወደ ሁለት ዝቅ ብሏል። በስራ ላይ ያሉ ሙሉ ባለ ሙሉ ጄኔራል ደግሞ አንድ ብቻ ሆነዋል።
ለሟች ነፍስ ይማር ለቤተሰብ መፅናናት ይሁን!
Via #Petros_Ashenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄኔራል ኣብርሃ ኢትዮጵያ ከነበሯት 4 ባለ ሙሉ ጄኔራሎች አንዱ የነበሩ ሲሆን የሌላውን ጄኔራል ሰዐረ መኮንን ህልፈት ተከትሎ የሙሉ ጄኔራሎች ቁጥር በአንድ ሳምንት ወደ ሁለት ዝቅ ብሏል። በስራ ላይ ያሉ ሙሉ ባለ ሙሉ ጄኔራል ደግሞ አንድ ብቻ ሆነዋል።
ለሟች ነፍስ ይማር ለቤተሰብ መፅናናት ይሁን!
Via #Petros_Ashenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ የማእከላዊ ኮሚቴ አቶ ዩሐንስ ቧያለው የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል በተመሳሳይ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አገኘው ተሻገርን ለአዴፓ ስራ አስፈፃሚነት እና ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚነት እንዲያድጉ ተደርጓል። ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደርነት ደግሞ አቶ ተመስገን ጥሩነህን በእጩነት እንዲቀርቡ ወስኗል።

#Breaking #ሰበር_ዜና
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፦
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የሲዳማ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት ውሳኔን መሰረት በማድረግ በህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደ አዲስ የማደራጀት፣ የምርጫ ቦርድ ስልጣንና ተግባር የሚወስነውን ህግ የማርቀቅ እና በተወካዮች ምክር ቤት የማጸደቅ፣ የምርጫ ህጎችን የማሻሻል፣ ተቋማዊ ለውጦችን የማከናወን እንቅስቃቄ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ከነዚህ ተቋማዊ ለውጦች መካከል የቦርዱን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት አድርጎ የተከናወነው የምርጫ ቦርድ አባላት መረጣ ዋነኛው ነው፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ የቦርድ አባለት መረጣ ሰፊ ምክክርና ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጐበት ከተለየ በኋላ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 06 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ተጨማሪ አራት የቦርድ አባላት ሹመት ተከናውኖ ቦርዱ አባላት ተሟልተውለት ስራውን ጀምሯል፡፡
ቦርዱ ተሟልቶ ስራ በጀመረበት ባለፈው አንድ ወር በእንጥልጥል የሚገኙ እና አስቸኳይ ናቸው ያላቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በቦርዱ አለመሟላት ምክንያት በእንጥልጥል ከቆዮት ጉዳዮች አንዱ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለቦርዱ የቀረበው የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ ማደራጀት ነው፡፡
ቦርዱ ስራ ከጀመረ አንስቶ የሲዳማ ዞን ክልልነትን የሚመለከቱ በተለያዩ ጊዚያት የቀረቡትን ጥያቄዎች ከመመልከቱም በላይ ከክልሉና የዞን መስተዳድር አመራሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
እንደሚታወቀው የሲዳማ ዞን የክልልነት ህዝበ ውሳኔ የማደራጀት ጥያቄ ከክልሉ ምክር ቤት ለቦርዱ የደረሰው ህዳር 12/2011 ዓ.ም ሲሆን በህገ መንግስቱ አንቀጽ 47/3/ለ/ ለክልሉ የተሰጠው “ጥያቄው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በአንድ አመት” የሚለው የማደራጀት ጊዜ ገደብ ለቦርዱም ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡
በመሆኑ በህግ መንግስቱ የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ በቀሩት 5 ወራት ውስጥ ህዝበ ውሳኔውን ለማከናወን የመጀመሪያ ደረጃ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
ህዝበ ውሳኔ የሚከናወነው የህዝብን ፍላጐትና ውሳኔ ህጋዊ እና ነፃ በሆነ አግባብ መሰጠቱን ለማረጋገጥ ነው፡፡ በመሆኑም ቦርዱ ተገቢና በቂ ዝግጅት አድርጐ ህዝበ ውሳኔውን ማካሄድ ይችል ዘንድ የሚያደርጋቸው ዝግጅቶች
- የህዝበ ውሳኔ አካሄድ የሚመራበት የስነስርአት መመሪያ ማዘጋጀት
- የህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ጊዜ ሰሌዳና በጀት ማዘጋጀት
- በህዝበ ውሳኔ ዝግጅትና ድምፅ መስጠት ሂደት ስለሚኖረው የፀጥታ አጠባበቅ ሁኔታ ግብረ ሃይል ማደራጀትና ዕቅድ ማፅደቅ
- ገለልተኛ የምርጫ አስፈፃሚዎች መመልመል፣ ማሰልጠንና ማሰማራት
- ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መድረክ ማዘጋጀት፣ የድርጊት መርሃ ግብር ማውጣት
- በህዝበ ውሳኔ አፈፃፄም ሂደቱ ላይ የጋራ ምክክር መርሃ ግብሮችን አውጥቶ መተግበር
- የሰነድና ቁሳቁስ ዝግጅትና ህትመት ስራዎች ማከናወን
- ድምፅ መስጫ ወረቀቶችና ፖስተሮች ማዘጋጀት፣ ማሳተም፣ ማሰራጨት
- ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ማሰጠት
- ቆጠራና ውጤት ማሳወቅ
ሲሆኑ በሌላ በኩል ሂደቱ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህም መሰረት፦
1. የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከክልሉ መንግስትና ከዞኑ መስተዳደር ጋር በመመካከር በአሁኑ ወቅት የክልሉም የዞኑም አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና የምታገለግለው የሀዋሳ ከተማ የህዝበ ውሳኔው ውጤት የሲዳማን ክልል መሆን የሚያረጋግጥ ቢሆን በከተማዋ ላይ ሁለቱ አካላት የሚኖራቸውን መብትና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የሃብት ክፍፍል ጥያቄዎችን የሚያስተናግዱበትን አሰራር አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዲያሳውቁ
2. በአዋጅ 532/1999 አንቀጽ 107 በተጠቀሰው የትብብር ድንጋጌ መሰረት የህዝበ ውሳኔው ጸጥታና ደህንነትን ( electoral security) ማስጠበቅን አስመልክቶ የፌደራል ፓሊስ፣ የክልሉ ፓሊስና የዞኑ ፓሊስ በትብብር የሚሰሩበትን ዝርዝር እቅድ እንዲያወጡና ከቦርድ ጋር ተባብረው እንዲሰሩ
3. የደቡብ ክልል ምክር ቤት በሲዳማ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ የሌሎች ብሄር ብሔረሰብ አባላት ከህዝበ ውሳኔው በኋላ የሚኖራቸውን ህጋዊ የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ ግልጽ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፍ እንዲያዘጋጅና ለቦርዱ እንዲያሳውቅ ምርጫ ቦርድ የወሰነ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የሚመለከታቸው አካላት ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ምላሽ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በጽሁፍ እንዲያሳውቁ ወስኗል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህገ መንግስቱና በምርጫ አዋጁ የተሰጠውን ሃላፊነት አለም አቀፍ የምርጫ መሰረታዊ መርሆዎች ጋር በማጣመር ሃላፊነቱን ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ለመግለጽ ይወዳል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሐምሌ 10/2011 ዓ.ም

#ሰበር_ዜና በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በሚገኙ #ሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ልዩ ወረዳዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ #ታውጇል። #ETHIOPIA
#State_of_emergency
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#State_of_emergency
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሲዳማ እና የሀድያ ዞን ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከኃላፊነት #ማገዱን አስታወቀ።
#ደኢህዴን ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ዞን አመራሮች የታገዱት ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማና እና በሲዳማ ዞን የገጠር አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የራሳቸው ሚና ነበራቸው በሚል ነው። የሃድያ ዞን አመራሮች በዞኑ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ላይ ከሚጥሉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ የማገድ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።
ድርጅቱ ከስልጣን አግጃቸዋለሁ ያላቸውን የሲዳማና የሀድያ ዞን ባለስልጣናት ''የፊት አመራሮች '' ከማለት ውጪ ቁጥራቸውንም ሆነ ማንነታቸውን አልጠቀሰም። በደቡብ ክልል በከፋ እና በወላይታ ዞኖች የተስተዋሉት ተመሳሳይ ድርጊቶችም የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ናቸው ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ጠቁሟል።
ምንጭ: የጀርመን ራድዮ

የ12ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ከአንድ ሰዓት በኋላ ይለቀቃል ተባለ። የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ከፍል ውጤትን አስመለክቶ ከአንድ ሰዓት በኋላ መግለጫ ለመስጠት መገናኛ ብዙሃነን ጠርቷል። መግለጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ተፈታኞች ከ11 ዐሰት ጀምሮ በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ ገብተው ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።
Via ETHIO FM

የዳዉሮ ዞን ም/ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ የሥራ ዘመን 8ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በዛሬዉ ቀን ረቡዕ 15/12/2011 ዓ.ም የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል። በተከበሩ አቶ አባስ መሐመድ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ለምክር ቤቱ አባላት የቀረቡት:-
1. የተከበሩ ወ/ሮ ፀሐይ ገሉ ዋና አፌ ጉባኤ
2. አቶ ተክሌ በዛብህ በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሲሆኑ
3. አቶ ግዛቸዉ ታደሰ የዞኑ ዓቃቤ ህግ መምሪያ ኃላፊ እንዲሆኑ የዞኑ ምክር ቤት አባላት ያለምንንም ልዩነት በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።
©የዳዉሮ ዞኑ ህዝብ ግኑኝነት ጽ/ቤት

አትሌት ደምስ ፀጋው አረፈ!
ባለፉት በርካታ አመታት ሀገሩ ኢትዮጵያን ወክሎ በተለያዩ ውድድሮች ሲወዳደር የነበረው አትሌት ደምስ ፀጋው ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ አትሌቱ ኢትዮጵያን በመወከል በሀገር አቋራጭ እና የአስፓልት ላይ ውድድሮችን በርካታ ጊዜ ያደረገ ሲሆን በአደረበት ህመም ምክንያት ህይወቱ አልፏል፡፡
አትሌት ደምስ #በግሉ እና #ሀገር በመወከል በርካታ ውድድሮችን አድርጎ ጥሩ ውጤት ያመጣ እንደነበርም ታውቋል፡፡ አትሌቱ ህይወቱ ያለፈው በአሜሪካ ሀገር ሲሆን በቅርብ ቀናት አስከሬኑ ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ይገባል ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ አውሎ ሚዲያ/Bekal Alamirew/

አቡበክር አል ባግዳዲ መገደሉ ተረጋገጠ!
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአይኤስ-አይኤስ (ISIS) መሪው አቡበክር አልባግዳዲ አሜሪካ በወሰደችው የጥቃት መገደሉን አረጋግጠዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፥ የሀገሪቱ ወታደሮች በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ባካሄዱት የፀረ ሽብር ዘመቻ የአይ ኤስ መሪ አቡ ባከር አል ባግዳዲ መገደሉን አስታውቀዋል።

ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ፦
"ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው።
ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ። የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታት እና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።
መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል።
ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም።
የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል።
ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል ፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በንቃት እንዲቃኝ እና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።"
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በetv እየሰጡ በሚገኙት መግለጫ ዛሬ ምሽት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች ጥቃት እንደተፈፀመበት አስታውቀዋል።
ጥቃቱን የፈፅሙት "ካሃዲ ኃይሎች እና ያደራጁት ኃይል" ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ "ጥቃቱ በሀገራችን እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች እጅግ አስነዋሪ ነው፤ ሰላም ለማስከበር በተለያየ ሀገር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት እንኳን በውጭ ኃይሎች ያልደረሰበት ጥቃት በገዛ ወገኖቹ ከጀርባው እንዲመታ ተደርጓል" ብለዋል።
በተፈፀመው ጥቃት ብዙዎች የሰራዊቱ አባላት ተሰውተዋል ፤ ቆስለዋል ፤ ንብረቶች እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል።
በትግራይ ክልል መቐለ እና ሌሎች አባባቢዎች ከተፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ በአማራ ክልል በዳንሻ በኩል ጥቃት ተፈጽሟል ፤ በአማራ ክልል የነበረው ኃይል ጥቃቱን መክቷል ብለዋል።

በሁመራ፣ በዳንሻ እና በቅራቅር አካባቢ በነበሩ ውጊያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ያደረጉት ተጋድሎ በታሪክ የሚዘከር ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ተናገሩ።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ በመከላከያ ሰራዊት ተግባር 'ህውሓት' ያሻውን ሳያደርግ የሞከራቸው ሙከራዎች ከሽፈው ውለዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

የታንዛኒያው ፕሬዜዳንት ጆን ማጉፉሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ፕሬዜዳንቱ በ61 ዓመታቸው ነው ዳሬሰላም በሚገኝ ሆስፒታል ህይወታቸው ያለፈው።
የፕሬዜዳንት ማጉፉሊን ህልፈት ያሳወቁት ምክትል ፕሬዜዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሲሆኑ ህልፈታቸው ከልብ ህመም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልፀዋል።
ከሰሞኑን ፕሬዜዳንት ማጉፉሊ ለሳምንታት ያህል ያለመታየታቸው መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል ፤ አንዳንዶችም በኮቪድ-19 ተይዘው በውጭ ሀገራት (ኬንያ እና ህንድ) ህክምና ላይ ናቸው ሲሉ ነበር።
ለመጨረሻ ጊዜ በህዝብ ፊት የታዩት የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ/ም ነው።
ፕሬዜዳንቱ በተለይ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በሽታውን ሲያናንቁት፣ ለበሽታው ፀሎትና እንፋሎት መታጠን በቂ ነው የሚልና ሌሎችም አነጋጋሪ አስተያየቶችን በመስጠት ይታወቃሉ።
አንዳንዶች ህልፈታቸውን ከኮቪድ-19 ጋር ቢያገናኙትም ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ የህልፈታቸው ምክንያት "የልብ ህመም" ነው ሲሉ ገልፀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻው ዙር የድምፅ አሰጣጥ ተጠናቋል። በቀጣይ የድምፅ ቆጠራው ይካሄዳል። በመጨረሻው ዙር ምርጫ ፈርማጆ አልያም ደግሞ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፉክክሩን በድል ያጠናቅቃሉ። ፈርማጆ ካሸነፉ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሆነው ዳግም ይመረጣሉ ፤ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ካሸነፉ ከፈርማጆ በፊት የነበሩበትን የፕሬዜዳንትነት መንበር በመረከብ ሀገራቸውን ዳግም የመምራት እድልን ያገኛሉ።…
#ሰበር_ዜና
የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ በድጋሚ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሆነው ተመረጡ።
ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የአሁኑን የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብድላሂ ፈርማጆን እጅግ ፉክክር በተሞላበት ሶስት ዙር የምርጫ ሂደት አሸንፈዋቸዋል።
የመጨረሻ ውጤት ፦
👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 214 ድምፅ
👉 ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 110 ድምፅ
3 ድምፅ ዋጋ ቢስ ሆኗል።
@tikvahethiopia