TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
"በምዕራብ ወለጋ 10 ባንኮች ተዘርፈዋል"- የዞኑ አስተዳዳሪ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን 10 ባንኮች በታጣቂዎች መዘረፋቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ለDW ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ በዞኑ የአራት ወረዳዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን እና በሌሎቹ ወረዳዎች #ዝርፊያ መፈጸማቸውን ገልጸዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ተመስገን ለDW እንደተናገሩት በመንግስት እና የግል ባንኮች ላይ ዝርፊያው የተፈጸመው ትላንት 10 ሰዓት ገደማ ነው። አስተዳዳሪው የታጠቁ ባሏቸው ኃይሎች ተፈጸመ ያሉት ዝርፊያ የተከናወነው በተመሳሳይ ሰዓት መሆኑንም ገልጸዋል።

“የታጠቀው ኃይል እዚህ አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እና በደረሰን መረጃ መሰረት 10 የሚሆኑ የመንግስት እና የግል ባንኮች ተዘርፈዋል” ብለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ። ከተዘረፉት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ሕብረት ባንክ እንዲሁም የኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ ባንክ እንደሚገኙበት አስረድተዋል። በባንኮቹ ዝርፊያ የተወሰደው ገንዘብ መጠኑ ግን እስካሁን አለመታወቁን ጨምረው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia