TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
#Gembi #Dmbidolo

ዛሬ ከጋምቤላ በተጨማሪ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ከተማ ከማለዳ 12:30 ጀምሮ በጣም የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ነዋሪውም በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ እንደሆነ የጊምቢ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

በሌላ ደምቢዶሎ ከተማ ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ ከባድ የተባለ ተኩስ ልውውጥ እንደነበር የቲክቫህ ደምቢ ዶሎ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

የተኩስ ልውውጡ መንግስት ሽብርተኛ ብሎ በህ/ተ/ም/ቤት የፈረጀው ሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ነው የሚጠራው) እና በመንግስት ሀይል መካከል ነው ብለዋል።

ከደቂቀዎች በፊት 5:00 ላይ ተኩሱ የከባድ መሳራያ ጭምር ተጨምሮበት ከተማዉ አለመረጋጋት ውስጥ መሆኑን የቤተሰብ አባላቶቻችን ገልፀዋል።

ነዋሪዉ በከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ሲሆን ማንም ከቤቱ እየወጣ እንዳልሆነ እና ታጣቂዎቹ እስረኞችን ማስለቀቃቸውን እንደሰሙ ገልፀዋል።

የድምጽ ፋይልም አያይዘዋል (ከደምቢ ዶሎ)

@tikvahethiopia