TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ገበያ

በድሮ ጊዜ ገበያ መሄድና እቃ መግዛት በጣም አድካሚ ሥራ ነበር። የሚፈልጉትን እቃ ለማግኘት ረዥም መንገድ መጓዝ፣ ዋጋና ጥራትን ለማወዳደር ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ፣ የሚፈልጉትን እቃ አለማግኘትና እቃውን ማጓጓዝ ከብዙዎቹ የግብይት ችግሮች ጥቂቶቹ ነበሩ።

ምስጋና ለTechnology ይግባና የKorojo መተግበሪያ ይህን ሁሉ ልፋት አስቀርቶ ካሉበት ቦታ ሆነው የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ በስልክዎ ብቻ መገብየት አስችሏል።

የKorojo መተግበሪያን አውርደው በአቅራቢያዎ ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎችን ይመልከቱ፣ ይሸምቱ። https://korojo.app/download
" የጦርነት ያክትም " እናታዊ ተማፅኖ

በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነትና በየቦታው የሚነሱ የብሔር ግጭቶች በሴቶች፣ በወጣቶችና በሕፃናት ላይ ስቃይና ሰቆቃን አስከትለዋል፡፡

እናቶች እንባቸውን የሚያብስላቸው አጥተዋል፡፡ ሕፃናት ተሳቀዋል፡፡ ወጣቶች የጦርነት ሰለባ ሆነዋል፡፡

በየአካባቢው በሚነሱ ግጭቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሞተዋል፡፡ ሕፃናት ያለ ወላጅ ቀርተዋል፡፡ በተለይ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከዓመት በፊት የተነሳው ጦርነት ዛሬም አልሻረም፡፡

የብዙዎችን ሕይወት ነጥቆ፣ አካል ጉዳተኛ አድርጎ፣ ሥነ ልቦና ሰልቦ በተለይም የአካባቢውን ነዋሪዎች ለሰቆቃና ሰቀቀን ዳርጓል፡፡

ዛሬም የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመ ነው፡፡ ይፋዊ ጦርነት ዳግም ይጀመር ይሆን? የሚለው የበርካቶች ሥጋት ሆኗል፡፡ በተለይ የእናቶችን ልብ አርዷል፡፡ በእንባ እንዲታጠቡ ምክንያት ሆኗል፡፡

በጦርነትና ግጭት ምክንያት ለዓመታት ያፈሩት ንብረቶች የወደመባቸው፣ ልጆቻቸውንና ባሎቻቸውን በጦርነት ያጡና ግራ የተጋቡ እናቶች በአግባቡ እንኳን እግዚአብሔር ያፅናችሁ ሳይባሉ፣ የሚገርፋቸው ረሃብና ጉስቁልና ከትከሻቸው ሳይወርድ ሌላ የጦርነት ፍዳ ከፊታቸው ተደቅኗል፡፡

ሆኖም የእናቶችን እንባ የሚያብስ ጠፍቷል፡፡ የታሰረ አንጀታቸውን የሚፈታም ናፍቋቸዋል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ የተከሰተው አሰቃቂና አሳዛኝ ምዕራፍ እንዲዘጋ ምኞታቸውና ፍላጎታቸው ነው፡፡

ይህ እንዲሳካ ደግሞ በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ሁሉ ጆሮ እንዲሰጧቸው፣ ልባቸውን ከፍተው ችግራቸውን እንዲያዳምጧቸው ይማፀናሉ፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-05-22-2

Credit : ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mokeypox ከሰሞኑ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖርቱጋል፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) ተከስቷል። ለመሆኑ የበሽታው መገለጫዎች ምንድናቸው ? የጦጣ ፈንጣጣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ቫይረሱን የሚሸከሙ እንስሳት ባሉበት ሞቃታማ የዝናብ ደኖች አቅራቢያ ይገኛሉ። የጦጣ ፈንጣጣ የሚጀምረው ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ ሕመም ፣የንፍፊት…
#update

በትላንትናው እለት እስራኤል እና ስዊዘርላንድ የመጀመሪያዉን የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሽታ ሪፖርት አድርገዋል።

ባለፉት ሳምንታት በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በቤልጂየም፣ በጣሊያን፣ በፖርቹጋል፣ በስፔን እና በስዊድን እንዲሁም በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በአውስትራሊያ ከ100 በላይ የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ(Monkeypox) መገኘቱን ተከትሎ ቫይረሱ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ቫይረሱ በሌለባቸው አገሮች ውስጥ ያለው ወረርሽኝ ያልተለመደ እንዲሁም የአሁኑ የጦጣ ፈንጣጣ(Monkeypox) ዝርያ የሚለየዉ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ሊሆን እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል።

የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ከተጠቁ ሀገራት እና ከሌሎች ጋር በመሆን የበሽታ ክትትልን በማስፋት የተጠቁ ሰዎችን ለማግኘት እና ለመደገፍ እንዲሁም በሽታውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መመሪያ ለመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

የዝንጀሮ በሽታ ከኮቪድ-19 በተለየ ሁኔታ ይተላለፋል። ሆኖም ግን በንክኪ ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፍ ስለሚችል ጥንቃቄ ይሻል ።

እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ገለፃ በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተለያዩ የአዉሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ ሪፖርት ሊኖር እንደሚችል ገልጿል።

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

@tikvahethiopia
#EthiopianFederalPolice

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የተደራጀ ቡድን ሊቋቋም እንደሆነ አሳውቋል።

የሚቋቋመው ግብረ ሃይል ከህክምና፣ ፎረንሲክ፣ መረጃና ሌሎች ተቋማት የሚውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር ቡድኑን መመስረት የሚያስችሉ አሰራሮችን ለመዘርጋት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል።

በኢትዮጵያ የአውሮፕላን አደጋን ጨምሮ በሚከሰቱ ሌሎች ከባድ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጎጂዎችን የሚለይ “ዲዛስተር ቪክትም አይደንቲፊካሽን ቲም” እስካሁን አልተቋቋመም።

በዚህም ምክንያት ለአደጋ ፈጥኖ ያለመድረስ፣ ተቀናጅቶ አለመስራት፣ የዘረመል ምርመራ አለማድረግ እና ሌሎችም ችግሮች እንደነበሩ ተገልጿል።

የሚቋቋመው ቡድን በቀጣይ አደጋዎች ሲገጥሙ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የነበሩ ችግሮች ይቀርፋል የተባለ ሲሆን ከተለያዩ አገሮች ልምድ ተወስዶ የሚቋቋም በመሆኑም በአደጋ ወቅት ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን እንደሚያስቀር ተገልጿል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WFP #Ethiopia የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል። ኤድሪያብ ቫን ደር…
#Afar

ሰይድ ሞሃመድ (የዓለም አቀፉ ህፃናት አድን ድርጅት የአፋር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ) ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" ማህበረሰቡ ድብርብርብ ሸክም ነው የገጠመው ፤ የመጀመሪያው በርካታ የውሃ አቅርቦት እና ሌሎችም መሰረታዊ አገልግሎት ተቋማትን ስራ ያስተጓጎለው ፤ ያቋረጠው ግጭት በዚህ ላይ ድርቅ ሌላው ፈተና ነው።

ላለፉት በርካታ አመታት አፋር በተከታታይ በድርቅ ሲጠቃ ነው የቆየው ፤ ስለሆነም ድርቁ ለአፋር ማህበረሰብ ሌላ ፈተና ነው ማለት ይቻላል ። "

@tikvahethiopia
Berhan Bank S.C floats a bid for HQ design, Design-Building Service.

The addresses for processing activities regarding the bid are the following:
a) for registration of bidders: 2nd Floor, WOMSADCO Bldg.
b) for delivering of Bids: 9th Floor, TK 2 Bldg.
c) for Bid Opening: 9th Floor, TK 2 Bldg.

TK Building is located opposite Skylight Hotel on Africa Avenue, adjacent to the NOC filling station, and houses Berhan Bank’s current Head Office. WOMSADCO building across the road from Brass Maternity and Childern Medical Center and opposite Celavie Chicken & Burger, approximately 250 meters from TK building, and houses the Facilities Management, HROD and Finance departments.

N.B for further information please see the attachment on our website.
Website; https://berhanbanksc.com/.../bid-for-design-build-services/
Telegram; https://t.iss.one/berhanbanksc
ኢሰመኮ የፌዴራል መንግሥት እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች "በተቀናጀ መንገድ የሕግ በላይነትን ማስከበር" በሚል ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰድ በጀመሩት እርምጃ፣ ጋዜጠኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።

ኢሰመኮ ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ፤ የተወሰኑት ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በቤተሰቦቻቸው የተጎበኙና በተለያየ የጊዜ መጠን ወደ ፍ/ቤት የቀረቡ ቢሆንም በርካታ ታሳሪዎች ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ መታሰራቸውን፣ ፍ/ቤት ያለመቅረባቸውን፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውን አመልክቷል።

 በተለይ በአማራ ክልል በርካታ ታሳሪዎች ከመደበኛ መኖሪያ አካባቢያቸውና ከመደበኛ እስር ቦታዎች ውጭ ጭምር በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን እንኳን ለማወቅ መቸገራቸውን አስረድቷል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር መንግሥት በሕጋዊ መንገድ ሊወስድ የሚችላቸውን እርምጃዎች እገበዘባለሁ ያለው ኮሚሽኑ " የዚህ አይነት የሰብአዊ መብቶች መርሆዎችን ያልተከተለና የተስፋፋ እስር ተገቢ አለመሆኑን " ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገልጸዋል።

" በተለይ የፌደራል ሆነ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን ከወንጀል ምርመራ በፊት ከማሰር፣ ጋዜጠኞችን በስራቸው ምክንያት ከማሰር እና ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ ሰዎችን ከማሰር ሊታቀቡ ይገባል። በማናቸውም አይነት ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች ሁሉ ቤተሰቦቻቸው ወዲያውኑ እንዲያውቁ እንዲደረግና ወደ ፍ/ቤትም ሊቀርቡ ይገባል” ብለዋል፡፡

አክለውም ኮሚሽኑ በማናቸውም ስፍራ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታ በድንገተኛ ጉብኝት ለመከታተል በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት፣ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀው ሁሉም የፌደራልና የክልል መንግሥታት አካላት ለኮሚሽኑ ሥራ የመተባበር ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

@tikvahethiopia
#ኮሮጆ
ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚፈልጉትን እቃ መግዛት እጅግ አድካሚ ሆኗል። በተጨማሪም የሚፈልጉትን እቃ ማግኘት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው። የግዢ ሂደትዎን በማዘመን ቤትዎ ውስጥ ሆነው ወይም ስራ ቦታ ስልክዎን ብቻ በመጠቀም Korojo መተግበሪያ ላይ የፈለጉትን ማማረጥና መሸመት ይችላሉ።

መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፤ የፈለጉትን ይሸምቱ። https://korojo.app/download
#AmharaRegion

የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ፤ በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል።

ቢሮው ዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሰሞኑን መንግሥት ያካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ መሆኑን አመልክቷል።

የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳሳለኝ ጣሰው የአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ከ4 ሺ በላይ ሰዎች መካከል 40 የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ፍርድ የተላለፈባቸው መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን 210 የሚሆኑት ደግሞ በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ ዳሳለኝ ጣሰው በአሁኑ ወቅት መንግሥት ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ከሚደረግ ሥራ ውጭ ክልሉ አስተማማኝ ሰላም ላይ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

" ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት አይታገስም " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
በዲማ ወረዳ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች በተፈፀመ ጥቃት የ6 ዜጎች ህይወት አልፏል።

ከትላትን በስቲያ ፤ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ በሚገኘው ስደተኛ መጠለያ ጣቢያና በመርከስ ቀበሌ ለጊዜው ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ ግለሰቦች የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ፤ " ቅዳሜ ምሽት 3:30 አካባቢ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት የ4 ሰው ህይወት አልፏል " ብሏል።

ግለሰቦቹ ከዲማ ከተማ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኡኩጎ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ከቀኑ 10:30 አካባቢ በመርከስ ቀበሌ " ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ " ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

'አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ-AYuTe Ethiopia Challenge ' የተሰኘና በኢትዮጵያ ግብርናን ለማሻሻል የሚረዳ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ዕድሜያቸው ከ18-29 የሆኑ ኢትዮጵያንን የሚያሳትፍ ውድድር ይፋ ሆኗል።

ውድድሩ፥ በኢትዮጵያ ያሉ አነስተኛ አርሶ አደሮችን ተግዳሮቶች መቅረፍ ምርትን ምርታማነትን፣ ገቢን፣ የፋይናንስ አቅርቦትንና የመቋቋም አቅም ያላቸውን የግብርና ቴክኖሎጂ ሀሳቦችን አወዳድሮ ለመሸለም ያለመ ነው።

የማመልከቻ ጊዜው ከግንቦት 13 ቀን 2014 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አሸናፊዎች 20 ሺ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ለማመልከት : https://ayute-ethiopia.et/apply-here/

@tikvahethmagazine
#አቢሲንያ_ባንክ

ገንዘብ በጣም አስፈለገዎት፣ ክፍት የሆነ ባንክ የለም ? የ ኤ.ቲ.ኤም ካርድዎንም አልያዙም ? አይጨነቁ የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን ተጠቅመው በአቅራቢያዎ ከሚገኙት የ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ያለ ካርድ ገንዘብዎን በቀላሉ ማውጣት ይችላሉ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth