TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሞጆ - ሀዋሳ ፈጣን የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆኑት ፦ 👉 በክፍል ሶስት ባቱ - አርሲ ነጌሌ 57 ኪ.ሜ 👉 በክፍል አራት የአርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ 52 ኪ.ሜ የአስፓልት ኮንክሪት የዲዛይን እና ግንባታ ፕሮጀክቶች በመስክ የስራ ቅኝት መጎብኘታቸው ተገልጿል። ቅኝቱ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ እና በሌሎች የተቋሙ ስራ ሀላፊዎችና በሚመለከታቸው አካላት…
ሞጆ 🛣 ሀዋሳ !

የባቱ - አርሲ ነጌሌ ግንባታ ፦

👉 በእስራኤሉ SBI international holdings A.G /ኤስ ቢ አይ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግስ ኤ.ጂ ነው/ የሚነናወነው።

👉 የማማከርና ቁጥጥር ስራውን ኩንውሀ ኢንጂነሪንግ እና ኮንሰልቲንግ ከኮሪያ ኤክስፕረስ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ እያከናወኑ ነው።

👉 ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚሆነው ሶስት ቢሊየን ሶስት መቶ አምስት ሚሊየን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ብር እየተሸፈነ የሚገኘው ከአለምባንክ በተገኘ ፋይናንስ ነው፡፡

👉 የአፈር ቆረጣ ስራ፣ ሰብ ቤዝ ስራዎች፣ የስትራክቸር ፣የውሀ ማፋሰሻ ፣ የአቃፊ ግንብ፣ ትላልቅ የድልድይ ግንባታ፣ ማሳለጫዎችና ማቋረጫዎች እና የክሬሸር ስራ በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

👉 21 ኪ.ሜ የDBM/ ለመጨረሻ የአስፋልን ንጣፍ ስራ ዝግጁ የማድረግ ስራ ተጠናቋል/ ።

አርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ የሚዘልቀው የመንገድ ክፍል ፦

👉 ሚገነባው የስራ ተቋራጭ cccc ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ነው።

👉 የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ቤጂንግ ኤክስፕረስ ዌይ ሱፐር ቪዥን ካምፓኒ ሊሚትድ ከውሀን ጄአይኦኬ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንሲ ሊሚትድ ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩት ነው ፡፡

👉 መንገዱን ለመገንባት የሚውለውን ወጪ አምስት ቢሊየን አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ብር በቻይናው ኤግዚም ባንክ 85 በመቶ እና 15 በመቶ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡

👉 በአርሲ ነጌሌ - ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት የአፈር ቆረጣ እና ድልዳሎ ስራ፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣የስትራክቸር ስራዎች፣ የሰብ ቤዝ ስራ፣ የውሀ ማፋሰሻ ቱቦዎች ቀበራ ፣ የድልድይ ግንባታ፣ የጠጠር ንጣፍ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡

👉 የ3 ነጥብ 4 ኪ.ሜ ለመጨረሻ የአስፋልት ንጣፍ ስራ ዝግጁ የማድረግ ስራ የDBM ተጀምሯል።

#ERA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ። የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች…
#ETHIOPIA

የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር ተሰጥቶ ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ከሆነ ቀናት ተቆጥሯል።

የፈተናው ውጤት እና የመቁረጫ ነጥቡ በተለያዩ ተማሪዎች/ወላጆች፣የትምህርት ቢሮና መምሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ ትልቅ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል።

መንግስት ለቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥም ግፊት እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምደባ ለማድረግ ተማሪዎች ማስተካከል ያለባቸውን መረጃዎች እንዲያስተካክሉ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ መጋቢት 19 ላይ ተጠናቋል።

ተማሪዎች ግን መቼ ተመድበው ትምህርት እንደሚጀምሩ እስካሁን አይታወቅም።

በውጤት እና መቁረጫ ነጥብ ላይ ከተነሳው ቅሬታ ባለፈ ወደዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይገቡ ሌላው ቀርቶ የት እንደሚማሩ ሳያውቁ ለመቀመጥ ተገደዋል፤ ይህም ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።

መንግስት እየተነሱ ላሉ ቅሬታዎች ያለውን ምላሽ በፍጥነት እንዲሰጥና ሌሎች ውጤት የመጣላቸውና ወደ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል ያለባቸውን ተማሪዎች በፍጥነት ወደ ትምህርት እንዲያስገባ ከወላጆችና ተማሪዎች እየተጠየቀ ይገኛል።

ይህ ዓመት ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት የቀረው ሲሆን እስካሁን ተማሪዎች አልተመደቡም፤ ዩኒቨሲቲዎችም መቼ ጥሪ እንደሚያደርጉ አይታወቅም።

የኮቪድ19 ወረርሽኝ በሀገሪቱ ከተነሳ ጊዜ አንስቶ በኃላም በሰሜን ኢትዮጵያ የተነሳው ጦርነት የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ከባድ ሆኖ ቀጥሏል።

በትግራይ ተማሪዎች የ2012ና የ2013 ፈተናን አልወሰዱም የ2014 ይወስዳሉ ተብሎ አይታሰብም።

በሀገር ደረጃም የትምህርት መርሃግብሩ ቀድሞ ወደነበረበት ሊመለስ አልቻለም። ይህ ትውልዱ ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚያሳድር በመሆኑ መፍትሄ ያሻዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ሊኖር አይችልም " - አቶ ሰዒድ ሙሳ ኢብራሒም (የኤሬብቲ ጎሣ መሪ) አፋር ክልል ውስጥ የቀጠለው ጦርነት " ለሰብዓዊነት ሲባል በታወጀው ግጭት ማቆም ውሳኔ " ላይ አደጋ መደቀኑን ዲፕሎማቶች ተናግረዋል። ሮይተርስ ፤ አፋር ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን 2 የሰብአዊ ርዳታ ሠራተኞች እንዳረጋገጡለት አስነብቧል። በአፋር 6 ወረዳዎች በትግራይ ኃይሎች…
#Update

21 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል " አብኣላ " መንገድ ወደ ትግራይ ክልል መጓዝ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ከሰዓት አስታውቋል።

ተሽከርካሪዎቹ የእህል እርዳታ የጫኑ ሲሆን በዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) አማካኝነት ነው በአፋር አብዓላ በኩል በየብስ ወደ ትግራይ እየሄዱ የሚገኙት።

መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ ቀደም እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል መሄድ ከጀመሩ በኃላ በፀጥታ ችግር ወደ ኃላ መመለሳቸውን መግለፁ አይዘነጋም።

መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ እና በትግራይ ክልል በኩል በጎ ምላሽ ከተገኘ በኃላ በየብስ ወደ ትግራይ ክልል ምንም እርዳታ አልገባም።

ለዚህ ደግሞ መንግስት የ " ህወሓት " ን ኃይል ተጠያቂ አድርጎ ነበር።

እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ ህወሓት ከያዛቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች ለቆ መውጣት እንዳለበት አስገንዝቦም ነበር፤ አሁን እርዳታ መጓጓዝ የጀመረው ህወሓት ከያዛቸው ቦታዎች ለቆ ነው ? ወይስ ሳይለቅ ? ስለሚለው የሚታወቅ ነገር የለም።

ትላንት ሮይተርስ የዜና ወኪል ባወጣው ዘገባ በአፋር ህወሓት ተቆጣጥሯቸው በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ጦርነት መቀጠሉን እና ይህም ሁኔታ ለሰብዓዊነት ሲባል የታወጀውን ግጭት የማቆም ውሳኔ አደጋ እንደደቀነበት ዲፕሎማዮቶች ተናግረው ነበር።

ዛሬ እንደተሰማው ፤ 21 ተሽከርካሪዎች በየብስ በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ ጀምረዋል።

ትግራይ ክልል ውስጥ የተረጂዎችን ፍላጎት ለማሟላት በየዕለቱ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 100 ተሽከርካሪዎች ሊገቡ እንደሚገባ የረድኤት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም መግለፃቸው ይታወሳል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #KENYA ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ጋር በሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ለመተባበር ተስማምታለች። ዛሬ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ ተወያይተዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኬንያ አቻቸው ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ባደረጉት ምክክር ሁለቱ አገሮች…
#Ethiopia #SouthSudan

በጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ ቡድን በደቡብ ሱዳን የሥራ ጉብኝት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው የሚመሩት ልዑክ በደቡብ ሱዳን ጁባ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

በዚህ የስራ ጉብኝት ጀነራል አበባው ታደሰ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ሉ/ጄኔራል ቶይ ቻኒይ ሬይት ጋር ውይይት አድርገዋል።

በሎጂስቲክስ እና በአቅም ግንባታ ጉዳዮች ለደቡብ ሱዳን ድጋፍ ለማድረግና ተሞክሮ ለማጋራት እንዲሁም የሁለቱ አገራት #የድንበር_አካባቢ ፀጥታና ደህንነትን ለማረጋገጥ በትብብር ለመሥራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

ትላንትና የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ በናይሮቢ ከኬንያ አቻቸው ከጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ ሁለቱ ሀገራት በሰላም እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ስምምነት ማድረጋቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion የጠቅላላ ሀኪም የቋሚ ቅጥር ፦ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ባሉ ጤና ተቋማት ጠቅላላ ሀኪሞችን መድቦ ማሰራት ይፈልጋል። 👉 የስራ መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም 👉 ደመወዝ - 9,056 ብር (ዘጠኝ ሺ ሃምሳ ስድስት ብር) 👉 ብዛት - 631 (#ስድስት_መቶ_ሰላሳ_አንድ) 👉 የስራ ቦታ - በክልሉ ባሉ የጤና ተቋማት ክፍት ቦታዎች 👉 ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት - በጠቅላላ…
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ከዚህ ቀደም ለ631 ጠቅላላ ሃኪሞች የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ ቢሮው ለ84 ሆስፒታሎች 409 ጠቅላላ ሃኪሞችን መቅጠሩ ታውቋል።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር እና የክልሉ ጤና ቢሮ (በማችንግ ፈንድ) በመተባበር ለ631 ጠቅላላ ሃኪሞች የቅጥር ማስታወቂያ ቢወጣም ቢሮው አወዳድሮ ሊቀጥር ያቻለው 409 ጠቅላላ ሀኪሞችን ነው።

የአብክመ ጤና ቢሮ የሰዉ ሃብትና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸዉ ደሬ ፤ " የማችንግ ፈንድ ለ631 ጠቅላላ ሃኪሞች በጀት ቢለቅም በገባያ ላይ 409 ጠቅላላ ሃኪሞች ብቻ ነው የተገኙት " ሲሉ ገልፀዋል

የክልሉ ጤና ቢሮ በቀጣይ ጊዜ ለቀሩት 222 ጠቅላላ ሃኪሞች የቅጥር ማስታወቂያ እንደሚወጣ አሳውቋል።

ያልተቀጠሩ በተለያየ ሙያ ያሉ የጤና ዘርፍ ባለሙያዎች በነበረዉ ሃገራዊ ችግር ምክንያት ቢሮዉ " በሙሉ በጀቱን ለህልዉና ዘመቻ በማዋሉ " እደሆነ ገልፆ በቀጣይ ጊዜያት ከጤና ሚንስቴር እና ከአጋር አካላት ጋር በመነጋገር የቅጥር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ተሰናብተዋል። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሰላም ከወረዳና ግንኙነታቸው ከተሻሻለ ከ20 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራ በኢትዮጵያ አምባሳደር አድርጋ የሾመቻቸው አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የስራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ተሰናብተዋል። ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶምን ማሰናበታቸውን ከፕሬዜዳንት ፅ/ቤት…
ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ አስፈፃሚ ሾመች።

አቶ ቢንያም በርሄ በኢትዮጵያ የኤርትራ ጉዳይ ፈፃሚ (Chargé d'affaire) ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ቢንያም የሹመት ደብዳቤያቸውን ትላንት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ደመቀ አጥናፉ ማስረከባቸውን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሹመቱ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከተሻሻለ በኃላ በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ለሶስት ዓመት ካገለገሉና የስራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ከተሰናበቱ በኃላ የመጣ ነው።

ኤርትራ ከአምባሳደር ይልቅ ለምን የጉዳይ አስፈፃሚ (Chargé d'affaire) እንደመደበች ወይም ወደፊት አምባሳደር እንደምትልክ ግልፅ አለመደረጉን ኢትዮ ኒውስፍላሽ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#UN #ETHIOPIA

ኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈፅመዋል ለተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲያጣራ ባቋቋመው ገለልተኛ ዓለማቀፍ መርማሪ ኮሚሽን ዙሪያ የውሳኔ ሃሳብ አቅርባ ድምጽ እንዲሰጥ አድርጋለች።

ኢትዮጵያ ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ላቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን ጠቅላላ ጉባዔው የስራ ማስኬጃ በጀት #እንዳይፈቅድ የሚጠይቅ ነው።

በዚህም ዛሬ ምሽት በ193 አባል ሀገራት ባሉት የጠቅላላ ጉባኤው በጀት ኮሚቴ ድምፅ የተሰጠ ሲሆን ፦

👉 27 ሀገራት ደግፈዋል።

👉 66 ሀገራት ተቃውመዋል።

👉 39 ሀገራት ድምፅ ከመስጠት ታቅበዋል።

በአብላጫ ድምፅ የውሳኔ ሃሳቡ [ ኢትዮጵያ የጠየቀችው የስራ ማስኬጃ በጀት እንዳይፈቀድ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ] #ውድቅ ሊሆን ችሏል።

የኢትዮጵያን የውሳኔ ሀሳብ ደግፈው ከቆሙ ሀገራት መካከል ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ ፣ኩባ ፣ ቻይና ፣ ሌሴቶ፣ ማሊ፣ ጋቦን፣ አንጎላ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኡጋንዳ ፣ ብሩንዲ፣ ሩስያ ፣ ኢራን ይገኙበታል።

ተቃውሞ ካደረጉት መካከል ደግሞ አሜሪካ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ኖርዌይ፣ ኒውዝላንድ ፣ ፖላንድ ፣ ሮማኒያ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ፊንለንድ ፣ ቤልጂየም፣ ጀርመን፣ ጃፓን ፣ ጣልያን፣ ሞናኮ፣ ሜክሲኮ ፣ ካናዳ ይገኙበታል።

ድምፀ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ቦትስዋና ፣ ግብፅ ፣ ኮትዲቯር ፣ ኩዌት ፣ ሌባኖስ ፣ማሌዥያ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ ፣ ሞሮኮ ፣ ሳዑዲ አረቢያ ፣ ሴኔጋል ፣ ደ/አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ቶጎ፣ ሲንጋፖር፣ ዩናትድ አረብ ኤሜሬትስ ይገኙበታል።

ቱርክ ፣ ሱማሊያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሩዋንዳ ፣ ጋምቢያ ... ሌሎችም በርካታ ሀገራት ሙሉ በሙሉ በድምፅ አሰጣጡ አልተሳተፉም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

ከጂዳ እና አካባቢ ባሉ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሃገር ቤት መመለስ ዛሬ ይጀመራል።

ዛሬ 1831 በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ከታቀደው 102 ሺህ ዜጎቻችን መካከል ከ80,000 የማያንሱት የሚገኙት በጄዳ አካባቢ በሚገኙ እስር ቤቶች እና የማቆያ ማዕከላት መሆኑ ተገልጿል።

ዛሬ በሚደረጉ አራት በረራዎች ከጅዳ 1438 በሳኡዲ አረቢያ በእስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ኢትዮጵያ ይገባሉ።

ከትላንት በስቲያ በጀመረው በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ በአንድ ቀን ከሪያድ 936 ኢትዮጵያዊን ማምጣት የተቻለ ሲሆን ዛሬ ማለዳም 393 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " የብሔራዊ ምክክሩ " ን በተመለከተ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው፤ አካታች ብሔራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው ሆኖ መከናወን አለበት ብለዋል።

" ይኽም የሚሆነው ሁላችንም የምክክር ሂደቱን በበላይነት የሚመራውን የምክክር ኮምሽን በተለያዩ መንገዶች መደገፍ፣ ማትጋትና ማጽናት ስንችል ነው። " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በዚህ ጉዳይ ዳር ቆሞ መገኘት በታሪክ ፊት የሚያስወቅስ ተግባር ነው። " ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ሁሉም አካል በባለቤትነት ስሜት ለምክክር ሂደቱ አስተዋጽዖ በማድረግ ተሳትፎውን ያረጋግጣል እንጂ አንዱ ጋባዥ ሌላው ተጋባዥ እንደሆነ አድርጎ መቁጠር ከታሪክ ተጠያቂነት ነጻ አያደርግም ሲሉም አስገንዝበዋል።

በመንግሥት በኩል እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ድረስ የተቋቋመው የምክክር ኮሚሽን በቅልጥፍና መሥራት እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይልም ገልፀዋል።

የክልል መስተዳደሮች ቀናነት፣ ባለቤትነትና ታሪካዊ ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ለኮሚሽኑ ሥራ አስፈላጊ የሆነውን ግብአት በማቅረብ ለሥራው ምቹ ሁኔታ ሊፈጥሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በውይይቱ እንደሚሳተፍ ብቻ ሳይሆን እንደ ሂደቱ ባለቤት ለሂደቱ ቅልጥፍናና ስኬት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችም ሀገር ስምምነትን በምትፈልግበት በዚህ ወቅት አማካይ ሆነው ሁሉን የማስማማት አደራ ስላለባቸው የመቀራረቢያውን መድረክ በማገዝ ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ከሩስያ ወደ ሀገራቸው በሚገባ ነዳጅ እና ጋዝ ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቀዋል። አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ የመጣል ውሳኔ ካሳለፈች ሩሲያ ለአውሮጳ የምታቀብለውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን እንደምታቋርጥ መዛቷ ይታወቃል። ሩስያ የነዳጅ ማዕቀብ ውጤቱ እጅግ የከፋ እንደሚሆን እና ዳፋውም ለዓለም እንደሚተርፍ ማስጠንቀቋ አይዘነጋም። የምዕራባውያን…
#USA

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሜሪካ " ለችግር ጊዜ " በሚል ካከመቻችው ነዳጅ በገፍ እንዲቀዳ አዘዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህን ትዕዛዝ ያስተላለፉት እየናረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለመዋጋት መሆኑ ተገልጿል።

ባይደን እንዲወጣ ያዘዙት 180 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በማከማቻው ታሪክ ትልቁ ነው።

ዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት ጣራ እየነካ የነበረው የነዳጅ ዋጋ ከባይደን ትዕዛዝ በኋላ ትንሽ ረገብ ማለቱ ተነግሯል።

በዘርፉ ላይ ያሉ ሰዎች ግን አሜሪካ በየቀኑ ለመከራ ጊዜ ካስቀመጠችው ነዳጅ አንድ ሚሊዮን በርሜል ብትቀዳም ችግሩን ሙሉ በሙሉ አይቀርፈውም ብለዋል።

ጆ ባይደን፤ ከማከማቻው እንዲቀዳ የታዘዘው ነዳጅ አሜሪካ "የራሷን የነዳጅ ምርት እስክታሳልጥ ድረስ" እንዲያግዝ በሚል ነው ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ ኩባንያዎች ነዳጅን ከመንግሥት መውሰድ የመጨረሻ አማራጭ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የአረንጓዴ የኃይል ምንጭ የሚከተሉ ኩባንያዎችንም እንዲበረታቱ መክረዋል።

የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ባመጣው መዘዘ አሜሪካን ጨምሮ የዓለም ሃገራት የኑሮ መወደድ እያማረራቸው ነው።

ባይደን፤ " ስትራቴጂክ ፔትሮሊዬም ሪዘርቭ " ከተሰኘው የችግር ቀን ገንዳ ነዳጅ ለመቅዳት የወሰንነው " ያለዕቅዳችን " ነው ብለዋል።

አሜሪካ ከሳዐዲ አረቢያ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ግዙፍ የነዳጅ አምራች ከሆነችው ሩሲያ ነዳጅ አልገዛም ካለች ወዲህ የነዳጅ እጥረት እያንገላታት ይመስላል ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia