TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BirbirCity📍

የገዛ ልጁን በሽጉጥ በማስፈራራት የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ።

በደቡብ ክልል በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ " መንደር ሰባት " ነዋሪ የሆኑት ኢኒስፔክተር ግርማ ጌታቸው የገዛ ልጁን መንግሥት ባስታጠቀው ሽጉጥ በማስፈራራት በመድፈሩ 9 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ።

የልጅቷ ዕድሜዋ 20 ሲሆን የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ናት።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው በቀን 6 ቀን 6/2014 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ተበዳይ ጩኸት ማሰማቷን ተከትሎ የደረሰው ጎረቤት ለፖሊስ ጥቆማ አድርጓል።

ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ ካቀረበ በኋላ የጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ፍ/ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ተከሳሹ በ9 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት ፍርድ እንዲቀጣ መወሰኑን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

More : @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#AtoTewoldeGebremariam የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀዋል። አቶ ተወልደ ይህንን የገለፁት ለ ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብለው ጡረታ መውጣታቸውን ገልፀው ፤ ለመንግስት ያስገቡት…
#Update

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ከጤናቸው ጋር በተያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አረጋግጧል።

በሌላ በኩል ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል።

አቶ ግርማ ፤ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የካበተ ልምድ ያላቸው ሲሆኑ አየር መንገዱን ዛሬ ለደረሰበት ስኬት መሰረት በጣለ መልኩ ለ7 ዓመታት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው አገልግለዋል።

ቦርዱ በቅርቡ አዲሱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የአቶ ተወልደ ገ/ማርያምን ተተኪ ያሳውቃል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፤ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ግንኙነት በሌሎች ኃይሎች በጎ ፈቃድ እንዲንጠለጠልና ራሷን የማትከላከል ሽባ አገር ያደርጋታል ያሉትን ረቂቅ ህጎች [ HR.6600 እና S.3199 ] እንዳይፀድቁ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ይፋዊ ጥሪ አቀረቡ።…
#Update

ዛሬ የአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ኢትዮጵያን በሚመለከተዉ S.3199 በተባለዉ ረቂቅ ሕግ ላይ ይነጋገራል።

በ2021 ላይ የተረቀቀዉ ሕግ የኢትዮጵያን ሠላም እና ዴሞክራሲን ለመደገፍ (ለማበረታት) ያለመ እንደሆነ አርቃቂዎቹ አስታዉቀዋል።

ይህ S.3199 ረቂቅ ሕግ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት ከቀረበዉና H.R.6600 በሚል መለያ ከሚታወቀዉ ጋር ተመሳሳይ ግን ተጨማሪ ነዉ።

ውድ ቤተሰቦቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ መረጃ እንዲኖራችሁ የጀርመን ሬድዮ ያሰራጨውን መረጃ በዚህ 👉https://telegra.ph/DW-03-23 አንብቡ።

በሌላ በኩል ዛሬ የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን እዚህ ኢትዮጵያ የሚገኙትን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተር ፊልድ በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፤ ተወያይተዋል።

በዚህ ውይይት ወቅት የH.R. 6600 እና S3199 ጉዳይ የተነሳ ሲሆን አቶ ደመቀ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ እና ታሪካዊ ግንኙነት ከግምት ያላስገባ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ሰላም እና ዴሞክራሲን ከማስፈን ይልቅ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚጎዳውን ረቂቅ ታጸድቀዋለች የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።

ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቀናት በፊት ረቂቅ ህጎቹ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የጸጥታ፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነት በሌሎች ኃይሎች በጎ ፈቃድ እንዲንጠለጠል እና ራሷን የማትከላከል ሽባ አገር ያደርጋታል ሲሉ ተናግረው ረቂቅ ህጎቹ እንዳይፀድቁ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ይፋዊ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
" ዶላር የሚታመን መገበያያ አይደለም " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ጋዝ የምትሸጠው በራሷ የመገበያያ ገንዘብ “ሩብል” እንዲሆን መወሰናቸውን RTን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የጋዝ ሽያጭ በሩሲያ ገንዘብ እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፋቸው ታውቋል።

የዚህ ውሳኔ ተግባራዊነትም በፍጥነት እንደሚከናወን ሩስያ አስታውቃለች።

RT እንደዘገበው ሞስኮ ከዚህ በኋላ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር " በዩሮም ሆነ በዶላር የመገበያየት ስሜት የላትም "ብሏል።

ቭላድሚር ፑቲን ዶላር የሚታመን የመገበያያ ገንዘብ እንዳልሆነ መናገራቸውን RT ዘግቧል።

የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ እና የካቢኔ አባላት ከአውሮፓ ጋር በሩብል የሚካሄደውን ግብይት በተመለከተ በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሳኔ እንዲያስቀምጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን ምንም እንኳን የተለያዩ ሀገራት የሩሲያን ሀብት ቢያግዱም ሀገራቸው ግን በገባችው ውል መሰረት ነዳጅ ማቅረቧን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

ምንጭ፦ RT/አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የማመልከቻ ቀኑ ተራዘመ። የትምህርት ሚኒስቴር ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እንዲያስተካክሉ የሰጠው ጊዜ ትላንት መጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ ይፋ ባደረገው ማስታወቂያ ለተጨማሪ ቀናት አራዝሟል። በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም…
#AmharaEB

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀንን በድጋሚ እንዲያጤነው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጠየቀ።

ቢሮው ፤ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜ ከመወሰኑ በፊት በፈተና ሂደቱና በመቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ የቀረቡ ቅሬታዎችን እንዲያጣራ በተቋቋመው ኮሚቴ በሚቀርቡ ግኝቶች ላይ ተነጋግሮ መተማመን እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ የቀረበው ቅሬታ አሳስቦኛል ያለው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ችግሩን ለመፍታት የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን መጠየቁን አስታውሷል።

በተጨማሪም ቅሬታውን የሚያጣራ ቡድን ወደ ፈተናዎች አገልግሎት መላኩን ገልጿል።

የተላከው ኮሚቴም በትምህርት ሚኒስትሩም ሆነ አገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሃላፊዎች ይሁንታን አግኝቶ የማጣራት ስራ እየሰራ እንደሆነ አሳውቋል።

ሆኖም ግን የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ ለመግባት የሚያስችላቸውን ፎርም እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ ሞልተው እንዲያጠናቅቁ አሳስቧል፡፡

የወጣውን መረጃ ተመልክቼዋለሁ ያለው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርቱን አቅርቦ ውይይት ባልተደረገበት ሁኔታና የኮሚቴው ግኝት ይዘት ባልታወቀበት ሁኔታ የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ በቅርቡ እንደሚደረግ መገለፁ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በቀረበው ቅሬታ ላይ አስፈላጊ መተማመን እስኪፈጠር ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር (በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜውን እንደገና እንዲያጤነው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጠይቋል፡፡

@tikvahethiopia
😢

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መሪዎች ተጎድተውም ቢሆን ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርጉ በእንባ ተማፀነች።

ኮማንደር ደራርቱ ተማፅኖዋን ያሰማችው በቤልግሬድ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ላይ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የአትሌቶች እና አሰልጣኞች ቡድን በተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው።

" የሀገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያመናል " ያለችው ደራርቱ " የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆማለች " ስትል ተናግራለች።

ኮማንደር ደራርቱ ፤ ከትግራይ ክልል የተገኙ ድንቅ አትሌቶችን ክብር ይገባችኃል ያለች ሲሆን " በብዙ ፈተናዎች አልፈው በብዙ ተፅእኖ አልፈው የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ስላደረጉ ምስጋና አቅርባለች።

" በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ " ያለችው ደራርቱ " ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች " ስትል ተናግራለች።

ኮማንደር ደራርቱ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት መሪዎች ተጎድታችሁም ቢሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ ብላችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት ስትል በእንባ የተማፀነች ሲሆን " ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች። " ብላለች።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ አሜሪካ ፤ በ " H.R. 6600 " ኢትዮጵያንም ሆነ ትግራይን ለመጥቀም ሳይሆን ለመበተን እንደሆነ ተናግራ መሪዎች ከተስማሙ የሚፀድቅበት ምክንያት ስለሌለ ለወደፊት ኢትዮጵያ ሲሉ እዲስማሙ ተማፅናለች።

ህዝቡም በመተባበር #ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርባለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
😢 ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መሪዎች ተጎድተውም ቢሆን ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርጉ በእንባ ተማፀነች። ኮማንደር ደራርቱ ተማፅኖዋን ያሰማችው በቤልግሬድ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ላይ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የአትሌቶች እና አሰልጣኞች ቡድን በተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው። " የሀገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያመናል " ያለችው ደራርቱ " የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን…
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በእንባ ተሞልታ ያቀረበችው ተማፅኖ ፦

" ... የሀገራችን ጉዳይ ያመናል ሁላችንንም። ... ሁላችንንም የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው ። በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆምና የኢትዮጵያን ባንዲራ ታውለበልባለች።

ስለዚህ አይክፋችሁ ክብር ይገባችኃል። በብዙ ፈተናዎች አልፋችሁ በብዙ ተፅእኖ አልፋችሁ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ስላደረጋችሁ በጣም እናመሰግናለን።

ትግራይ ትላንትም ብትሆን ኢትዮጵያ ናት ፤ ዛሬም ኢትዮጵያ ናት ፤ ነገም ኢትዮጵያ ነች ስለዚህ እባካችሁ መሪዎቻችን እባካችሁ...እባካችሁ ... እባካችሁ ተጠቅማችሁ አይደለም ፤ ተጎድታችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት እባካችሁ !!! ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። ስለዚህ መሪዎቻችን ተጎድታችሁ ለኢትዮጵያ ብላችሁ ፣ ለህዝብ ብላችሁ እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች።

... ስፖርት ወንድማማችነት ፣ ፍቅር ፣ ሰላም ነው!! ለሰላም ፣ ለፍቅር ቆመው እነዚህ ልጆች ምንም ሳይበግራቸው ለዚህ ውጤት በቅተዋልና አሁንም ቢሆን ክብር ይገባቸዋል። እናከብራችኃለን። በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች።

አሜሪካ ትግራይን ለመጥቀም አይደለም፤ ኢትዮጵያንም ለመጥቀም አይደለም ለመበተን ነውና H.R. 6600 የሚባልው አሁን ሊፀድቅ በመንገድ ላይ ያለው መሪዎቻችን ስለህዝባችን አይተው ፤ ስለወደፊት ኢትዮጵያ አይተው ከተስማሙ H.R. 6600 የሚፀድቅበት ምክንያት የለውም።

ህዝባችን ከመንግስቶቻችን ጎን ቆሞ ሁላችንም የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ እኔ የትግራይ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ስል ምቾት አይሰማኝም እንደኢትዮጵያ ነው ሁላችንም የምናየው ፤ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦቻችን ኢትዮጵያ ናቸው ፤ ትላንትናም ተባብረውና ኢትዮጵያውያን እዚህ ያበቁትና ነገም ዛሬም እንተባበር ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት።

እኛ ልጆቻችሁ ከኦሮሞ የመጣ፣ ከአማራ የመጣ፣ ከትግሬ የመጣ፣ ከጉራጌ ከየትም የመጣው ለዚህ ነው አንዷን ባንዲራ ከፍ ያደረግነው ስለሆነም ብሄር ሳንለን፣ ሃይማኖት ሳንለይ፣ ፆታ ሳንለን፤ ባንዲራችንን ያነሳነው ስለተባበርን ነው፤ በፅናት ስለቆምን ነው። ለእናተም አያቅትም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም የኢትዮጵያ መንግስትም እባካችሁ ...ስለስለነገዋ ኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለብልፅግናዋ ፣ ስለእድገቷ፣ ስለሰላሟ፣ እባካችሁ አያቅታችሁም እኛም ከጎናችሁ አለን ስፖርት ሰላም ነው ፤ ስፖርት ፍቅር ነው ብለናል ተያይዘን ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት። እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ያድርግልን። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ከጤናቸው ጋር በተያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አረጋግጧል። በሌላ በኩል ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል። አቶ ግርማ ፤ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የካበተ ልምድ ያላቸው ሲሆኑ አየር…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ38 ዓመታት ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ትላንት አዲሱን የአቶ ተወልደ ገ/ማርያም ተተኪ እንደሚያሳውቅ መግለፁ እይታወሴ።

አዲስ እንደተቋቋመ የተነገረለት የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ አቶ ተወልደ ገ/ማርያምን ተክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን አሳውቀዋል።

አቶ መስፍን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን እኤአ ከ2019 ጀምሮም የአየር መንገዱ ስራ አመራር ቦርድ ውስጥ ሲያገለግሉ ነበር።

ከዚያ ቀጥለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ 40 በመቶ ድርሻ ያለበትን አስኪ አየር መንገድን ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን በመምራት ላይ ነበሩ።

በሌላ በኩል አዲስ የተዋቀረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ፦
👉አቶ ግርማ ዋቄ የቦርድ - ሰብሳቢ፣
👉 አቶ ተክለወልድ አጥናፉ - አባል
👉 አቶ ተመስገን ጥሩነህ - አባል
👉 ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ - አባል
👉 አቶ ታደሰ ጥላሁን - አባል
👉 አቶ ረታ መላኩ - አባል
👉 አቶ አለማየሁ አሰፋ - አባል ሆነዋል።

@tikvahethiopia
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ!

ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

አሁን ላይ 4ተኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት በምዝገባ ላይ እንገኛለን።

የሥልጠናው ፕሮግራም የሚያካትተው ፦

• የተከታታይ 9 ቀን የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሥልጠና

• 3 ወር የንግድ ማበልጸግ እና ማማከር አገልግሎት (Business Development and Consultation, including coaching and pitching)

• 8 ወር የተለያየ የማማከር ድጋፍ, ክትትል እና ሜንቶርሺፕ

• ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

👉 የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

👉 የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

👉 ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን፤

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ 👇
https://forms.office.com/r/TtnFJdedji

#StemPower #VISA #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Kereyu Incident Investigation Report.pdf
" የእርቅ ሂደቱ የወንጀል ተጠያቂነትን መተካት ወይም ማስተጓጎል የለበትም " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ለተፈጸመው ግድያ የወንጀል ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ስራ በተመለከተ መግለጫ ልኮልናል።

ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ፤ በጅላ አባላቱ ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ አባላት ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ያሉበትን ደረጃ መገምገሙን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ፤ የተፈጸመውን ግድያ ለመመርመር ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ መሆኑና እስከ መጋቢት 4/2014 ዓ.ም ድረስም 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው የሚገኝ መሆኑን አሳውቋል።

ኢሰመኮ የክልሉ መንግስት ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች ቢሆንም በሂደቱ ላይ ክፍተቶች የታዩ መሆኑን አመልክቷል።

ከተያዩት ክፍተቶች መካከል ፤ በአካባቢው ማህበረሰብ በግድያው ተሳፍቶ ያላቸው መሆኑ የተጠቆሙ / በድርጊቱ ዋነኛ ፈፃሚ ናቸው የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር አልዋሉም / ምርመራም እየተደረገባቸው አይደለም።

ከዚህ ባለፈ ተጠርጣሪዎቹ በመንግስት ስራ ኃላፊነት ቦታዎች የሚገኙ ጭምር ስለሆነ በምርመራ ሂደቱ ጫና እያደረሱ ፤ ለሂደቱ አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ የሚገባቸው የፀጥታ እና የአስተዳዳር አካላትም ሥራው በሚፈለገው ፍጥነት እንዲጠናቀቅ በቂ ትብብር እያደረጉ እንዳልሆነ ተገልጿል።

በተጨማሪም ፤ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎችም በህግ በተቀመጠው ጊዜ ወደ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/EHRC-03-24

@tikvahethiopia