TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#IGAD #SUDAN

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የጠሩትን ስብሰባ ሱዳን ተቃወመች።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ኢጋድ በጠራው ስብሰባ ላይ ሀገሪቱ እንደማትሳተፍ እና እንደማይመለከታት አስታውቋል።

ሱደን ስብሰባውን የተቃወመችው ስብሰባው መጠራት ያለበት በወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር በሱዳን እንጅ በዋና ፀሀፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እንዳልሆነ ገልጻለች።

የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ የፕሬዝዳንቶች ጉባዔ ጠርተው የነበረ ቢሆንም፤ ይህንን ስብሰባ ሱዳን እንደማትሳተፍ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አሊ ሳዲቅ ተናግረዋል።

የኢጋድን ስብሰባ ከወቅቱ ሊቀመንበር ከሱዳን ውጭ ማንም መጥራት እደማይችልም ነው ያስታወቀው። ከዚህ በተጨማሪም በተጠራው ጉባዔ ላይ ሱዳን አጀንዳ መሆን እንደሌለባትም ነው የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

የወቅቲ የኢጋድ ሊቀመንበር ሱዳን ስትሆን ይህንንም ሲመሩ የነበሩት የቀድሞው የሀገሪቱ ሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ነበሩ።

አሁን ላይ ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ባይኖራትም የወቅቱ ሊቀመንበር፤ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፈታህ አልቡርሃን እንደሆነ አስታውቃለች።

የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ በሱዳን ከኢጋድ ልዑክ መሪ ጋር ተገናኝተዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Russia የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጸረ ኑክሌር ኃይላቸው በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዙ፡፡ ፑቲን ከገቡበት የዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከምዕራባውያን ሃገራት ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ጦሩ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ እንዲሆን ያዘዙት፡፡ ዛሬ ከከፍተኛ ባለስልጣናቶቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) አባል የሆኑ…
#WW3

" ምዕራባውያን ሩስያን ወደ 3ኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ ነው " - የቤላሩስ ፕሬዜዳንት

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የምዕራባውያን ማዕቀቦችን " ሩሲያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ " ነው ሲሉ ተጠያቂ አድርገዋል።

#NATO ሀገራት ሩስያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሉካሼንኮ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ምዕራባውያን ከማዕቀብ ጋር በተያያዘ እየሄዱበት ያለው መንገድ ከጦርነትም የከፋ ነው ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ ሩሲያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፋ ነው ብለዋል።

ምዕራባውያን ከጽንፈኛ እርምጃዎቻቸው ወደኃላ ማለት ካልጀመሩ መጨረሻው ወደ #ኑክሌር_ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ፕሬዜዳንቱ አስጠንቅቀዋል።

ይህ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ማስጠንቀቂያ የተሰማው የሩስያ አቻቸው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጸረ ኑክሌር ኃይላቸው #በከፍተኛ_ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ካዘዙ በኃላ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በጠላፊዎች ተጠልፎ የቆየው ከ 866,000 በላይ ተከታይ ያለው የዋልታ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ዛሬ ሰኞ ወደ አገልግሎት መመለሱ ተሰምቷል።

ዋልታ ፤ ከዚህ ቀደም ይጠቀምበት የነበረውን የገፁን ስያሜ www.waltainfo.com ወደ #WMCC (Walta Media and Communication Corporate) በመቀየር ወደ አገልግሎት መመለሱን አሳውቋል።

ዋልታ የፌስቡክ ገፁ እንዲመለስ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ አስተዳደር እና በአፍሪካ የፌስቡክ ኩባንያ አስተዋፆ ማድረጋቸውን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION🚨

በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች 225 ሺህ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህፃናት እና 100 ሺህ ነፍሰ ጡር እናቶች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) አሳውቋል።

የUNICEF የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ሞሀመድ ማሊክ ፋል በሁለቱ ክልሎች 225 ሺህ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህፃናት እና 100 ሺህ ነፍሰ ጡር እናቶች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።

ዳይሬክተሩ ፥ " ዩኒሴፍ በድርቅ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ለማከም የተንቀሳቃሽ የጤና እና የስነ ምግብ ቡድኖችን ይደግፋል። ነገር ግን የአየር ንብረት ለውጥን ተፅእኖ ለመቋቋም ተጨማሪ ያስፈልጋል። " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዩክሬን ከሩስያ ጋር ለመነጋጋር ተስማምታለች። የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቢሮ ፤ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ለፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዘሌንስኪ ዛሬ ደውለውላቸው እንደተነጋገሩ ገልጿል። የዩክሬን ልዑካን ከሩሲያ ልዑካን ጋር " ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ " በዩክሬን-ቤላሩስ ድንበር በፕሪፕያት ወንዝ አቅራቢያ ተገናኝተው ለመነጋገር መስማማታቸውን ቢሮው አሳውቋል። አሌክሳንደር ሉካሼንኮ…
#Update

ዩክሬን እና ሩስያ የሰላም ንግግር ጀመሩ።

ጦርነት ላይ የሚገኙት ዩክሬንና ሩስያ በቤላሩስ የሰላም ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል።

ዘ-ጀሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ሩስያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች በሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ንግግሩ ላይ ይገኙበታል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ሩስያዊው ቢሊየነር በዩክሬናውያን የሰላም ንግግሩን እንዲያግዙ ተጠይቀው ነው በሰላም ንግግር መድረኩ ላይ የተገኙት።

5ኛ ቀኑን በያዘው የዩክሬን እና የሩስያ ጦርነት እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች አልቀዋል ፣ በርካታ ንብረት ወድሟል፣ በመቶ ሺዎች ሰላም ፍለጋ ድንበር አቋርጠው ተሰደዋል፣ በሁለቱ ሀገራት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚውና በሌላውም ዘርፍ ከፍተኛ ተፅእኖ ተፈጥሯል።

@tikvahethiopia
#GoodayOn Mobile App

የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ ነው።

አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም።

ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።

GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
#Turkey

" ...በኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት የሚያመጣ ማንኛውንም መንገድ እየደገፍን ነው " - ያፕራክ አልፕ

ቱርክ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የሚያመጣ ማንኛውንም መንገድ እየደገፈች መሆኑን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ገልፀዋል።

አምባሳደሯ ይህን የገለፁት በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ግጭት በቀጠለበት በዚህ ወቅት ነው።

ቱርክ በቅርቡ የተጀመረውን ብሔራዊ የውይይት ሂደት በደስታ እንደምትቀበል አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ተናግረዋል።

ሁለቱ ሀገራት [#ቱርክ እና #ኢትዮጵያ] በአስቸጋሪ ጊዜያት እርስበርስ መደጋገፋቸውን ያነሱት አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ፥ " በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚደረጉትን ሁሉንም እርምጃዎች በደስታ እንቀበላለን። አሁን ይህ እየሆነ በመምጣቱ ደስተኛ ነን ፤ ለሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ግጭቱ በቅርቡ እንደሚቆም ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቱርክ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ እና ወደ ንግግር እንዲገባ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ ስታቀርብ እንደነበር የቱርክ መንግሥት ደጋፊ እንደሆነ የሚነገረው ዴይሊ ሳባህ ፅፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AfCFTA ሁለት ኢትዮጵያውያን ሹመት ተሰጣቸው። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነት ሴክሬታሪያት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ እና አቶ ታፈረ ተስፋቸውን የንግድ እና ኢንዱስትሪያል ልማት አማካሪ ምክር ቤት አባል አድርጎ መሾሙን ሪፖርተር ጋዜጣ [እንግሊዘኛው ክፍል] ዘግቧል። ዶ/ር አርከበ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐብይ አህመድ ልዩ አማካሪ ሆነው በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ባለፉት 30…
14ቱ የAfCFTA የንግድ እና ኢንዲስትሪ ልማት አማካሪ ምክር ቤት አባላት እነ ማን ናቸው ?

ከቀናት በፊት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነት ሴክሬታሪያት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ልዩ አማካሪ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ እና ዓለም አቀፍ የንግድ እና ልማት አማካሪ ዶ/ር ታፈረ ተስፋቸውን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ልማት አማካሪ ምክር ቤት አባል አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።

ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የተሾሙበት የአማካሪ ምክር ቤቱ አጠቃላይ 14 አባላት ናቸው ያሉት።

ለመሆኑ 14ቱ የአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት አነማን ናቸው ?

1ኛ. ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ
2ኛ. ዶ/ር ሮብ ዳቪስ
3ኛ. ዶ/ር ታፈረ ተስፋቸው
4ኛ. ዶ/ር ዲፔሎ
5ኛ. ካርሎስ ሎፔዝ
6ኛ. ጄን ኢዚሪጋዌ
7ኛ. ዶ/ር ሴሌስቲን ሞንጋ
8ኛ. አምባሳደር ማግዳ ሻሂን
9ኛ. ፕሮፌሰር ካሮሊን ንኩቤ
10ኛ. ፕሮፌሰር ፊዮና ትሬጌና
11ኛ. ዶ/ር ስቴፈን ካሪንጊ
12ኛ. ፕሮፌሰር ኦይባንጂ ኦይላራን
13ኛ. ዶ/ር ጌይንሞር ዛናምዌ
14ኛ. ፕሮፌሰር ፋይዘል ኢስማኢል ናቸው።

(ስለሁሉም የአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት ዝርዝር መረጃ ከላይ በምስሉ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN #RUSSIA የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ም/ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ሩስያ ሞስኮ የሚገኙ ሲሆን ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል። ሄሜቲ ከሩስያ ምክትል ጠ/ሚ አሌክስአንደር ኖቫክ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ይኸው ጉዧቸው ሀገራቸውና ወታደራዊ መንግስታቸው ከምዕራብ ሀገራት ያገኝ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ…
" በግልፅ አውግዢ "

ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሩስያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ' ወረራ ' በግልፅ እንድታወግዝ እና ለዩክሬን የግዛት አንድነት ድጋፍ እንድታሳይ ተጠየቀች።

ይህን የጠየቁት ምዕራባውያኑ ሀገራት አሜሪካ፣ ኖርዌይ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም ካናዳ እና ስዊዘርላንድ ናቸው።

ትላንት እሁድ የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሱዳን የሚገኙትን የአውሮፓ፣ ትሮይካ፣ ካናዳ እና ስዊዘርላንድ ዲፕሎማቶችን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚህም ወቅት በሱዳን የአውሮፓ ህብረት ተወካይ ሮበርት ቫን ደን ዶል ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ሱዳን በግልፅ እንድታወግዝ ጠይቀዋል።

" በተለይም በጉዳዩ ዙሪያ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሱዳንን አቋም በከፍተኛ ጉጉት እንጠብቃለን " ሲሉ ቫን ደን ዶል አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይኸው ስብሰባ የተካሄደው የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ጄነራል ሞሀመድ ምዳን ደጋሎ (ሄመቲ) በሞስኮ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ሄሜቲ ሞስኮ ሲደርሱ ፑቲን ተገንጣይ የዩክሬን ክልሎችን እውቅና ለመስጠት ያሳለፉትን ውሳኔ ደግፈዋል ተብሎ የተነገረ ሲሆን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሄሜቲ መግለጫ ከአውድ ውጭ ተወስዷል ሲል በፍጥነት አስተባብሏል።

የአውሮፓ ህብረት ልዑካን የሱዳን ባለስልጣናት " የዩክሬን ግዛት አንድነት " እንዲያረጋግጡ እንዲሁም " በዶኔስክ እና ሉጋንስክ ክልሎች የታወጀውን የሩስያን ህገ-ወጥ ውሳኔ እንዳይከተሉ " አሳስበዋል።

በተጨማሪ ሱዳን በዩክሬን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥያቄን እንድትቀላቀል ጥሪ ማቅረባቸውን ሱዳን ትሪብዩን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WW3 " ምዕራባውያን ሩስያን ወደ 3ኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ ነው " - የቤላሩስ ፕሬዜዳንት የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የምዕራባውያን ማዕቀቦችን " ሩሲያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ " ነው ሲሉ ተጠያቂ አድርገዋል። የ #NATO ሀገራት ሩስያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሉካሼንኮ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። ፕሬዝዳንቱ…
#Belarus #Russia #Ukraine #USA

ቤላሩስ የሩሲያን የኒዩክለር ጦር መሳሪያ በቋሚነት በግዛቷ ውስጥ እንዲተከል መስማማቷን ዛሬ በሰጠችው ህዝብ ውሳኔ በሙሉ ድምጽ ማጽደቋን አስታውቃለች፡፡

በዛሬ እለት ተቀልብሷል የተባለው ነባር ህግ የቤላሩስን ገለልተኝነት የሚሽር ሲሆን ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጠንካራ ወታደራዊ ልምምድ በር ይከፍታል ተብሏል፡፡

ባለፈው ሀሙስ በወታደራዊ ልምምድ ወደ ዩክሬን የሄዱት የሩሲያ ወታደሮችም ከዚሁ ከቤላሩስ የተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተነግሯል።

ለውጡ ቤላሩስ ከሶቭዬት ህብረት ነጻ ከወጣች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዛቷ የኒውክለር መሳሪያ እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተያያዘ መረጃ አሜሪካ በቤላሩስ ያላትን የኤምባሲ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቷን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ማስታወቋን ቪኦኤ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ሩስያ እና ዩክሬን መካከል ዛሬ የመጀመሪያው የሰላም ንግግር በቤላሩስ ተደርጓል፤ ውይይቱ ረጅም ሰዓታት የወሰደ ሲሆን የተገኘ ፍሬ ነገር ስለመኖር አለመኖሩ እስካሁን አልታወቀም። የሁለቱም ሀገራት ልዑካን ወደ የሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማሳሰቢያ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሹ አመልካቾች student.ethernet.edu.et በመግባት ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል። በተመሳሳይም በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ሲል አሳውቋል። ኤጀንሲው ምላሹን በማመልከቻ ቅጹ…
#ማስታወሻ

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ከውጤት ጋር በተያያዘ ከሐሙስ የካቲት 17/2014 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን እና በአካል እየተገኙ ቅሬታ እያቀረቡ ሙሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል።

ኤጀንሲው ቅሬታ የመቀበል ሂደቱ እስከ ዛሬ የካቲት 22/2014 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ መሆኑን አሳውቆ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በጊዜ ገደቡ እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

ከዚህ ጊዜ ገደብ ውጪ የሚመጡ ቅሬታዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል ኤጀንሲው በኦንላይን ቅሬታ ያቀረቡ የብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ያቀረቡት ቅሬታ መልስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- www.neaea.gov.et:8080 በመግባት ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።

ቅሬታቸውን በአካል ያቀረቡ ቅሬታ አቅራቢዎች ምላሹ በስልክ ተደውሎ ይነገራቸዋል ብሏል።

ምላሽ ያልተሰጣቸው ቅሬታ አቅራቢዎች ለአገልግሎቱ የቀረቡት ቅሬታዎች እጅግ በጣም ብዙ ስለሆኑ በትእግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#NATO

NATO ሩስያን ለማስቆም ወደ ዩክሬን የመግባት ሀሳብ እንደሌለው ገለፀ።

የNATO ዋና ፀሀፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ሩሲያን ለማስቆም NATO በምድርም ሆነ በአየር ወደ ዩክሬን የመግባት ሀሳብ እንደሌለው ተናግረዋል።

ስቶልተንበርግ " የNATO ሃላፊነት ግጭቱ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን፣ እንዳይባባስ ወይም በአውሮፓ ከNATO አጋሮች ጋር ወደ ሙሉ ጦርነት እንዳይቀየር ማረጋገጥ ነው " ሲሉ መናገራቸውን ኬዬቭ ኢንዲፔንደንት ፅፏል።

ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ NATO የዩክሬንን ሰማይ ከበረራ ቀጠና ነፃ ሊያደርግ ይችላል የሚለውም ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ተነግሯል።

በሌላ በኩል የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት የዩክሬን አየር ክልልን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታውቋል።

@tikvahethiopia