TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ "የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት ጀመረ" የሚሉ በርካታ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

መንግስት በዚህ ጉዳይ በይፋ ያሳወቀው ነገር ባይኖርም ከዚህ ቀደም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት መቃረቡ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጩ ለነበሩት የግድቡ መረጃዎች ምንጫቸውን ለማወቅ ብናስስም ልንደርስበት አልቻልንም።

በይፋ በመንግስት ይሁን በግል ሚዲያ ላይ ቀርቦ ይህንን ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ለህዝብ ያሳወቀ አካል የለም፤ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ተቋማት በኩልም በፅሁፍ የወጣም ነገር የለም።

የግድቡ ሂደት በኃይል ማመንጨቱ በኩል አሁን ስላለበት ሁኔታ የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

ነገር ግን በዚህ ሂደት ማህበራዊ ሚዲያውን ስንዳስስ የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ላይ ፦

" የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ኤሌክትሪክ ለማመንጨት እየተሞከረ ነው።

ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨትም በላይ ነው።

ከNoMore ጉዟችን ብዙ እንደሚመጣ ግልፅ ነው። " የሚል ፅሁፍ ከላይ ከምትመለከቱት ፎቶ ጋር አስፍረው ተመልክተናል።

የህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት በቅርብ ጊዜ እውን እንደሚሆን በመንግስት በኩል ከሳምንታት በፊት መገለፁ መላው ሀገር ወዳድ ህዝብ ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተለው ሆኗል።

ከዛሬ ነገ የላቡን ውጤት ለማየት ፣ ታሪካዊውን ሂደትም ለመመዝገብ በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል፤ በሚመለከታቸው ተቋማት በኩል መረጃ ባለመኖሩ ግን ለማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ላልሆኑ መረጃዎች ተጋላጭ ሆኗል።

@tikvahethiopia
#AU2021

ኢትዮጵያ እንግዶቿን መቀበል ጀመረች።

የዝምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስት ፍሬድሪክ ሻቫ እና የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና በ40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት የህብረቱ የስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ ጥር 25 እና ጥር 26 ቀን 2014 ዓ/ም ይካሄዳል።

ፎቶ : ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#CHINA

ቻይና በኢትዮጵያ 🇪🇹 እየተሻሻለ መጥቷል ያለችውን የሀገር ውስጥ ሁኔታና መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀነ ገደብ ከመድረሱ በፊት እንዲያበቃ ያሳለፈው ውሳኔ ደስ እንዳሰኛት ገልፃለች።

የኢትዮጵያ ህዝብ የውስጥ ጉዳዩን በአግባቡ የመቆጣጠር ጥበብና ብቃት እንዳለውም አምናለሁ ስትል አስታውቃለች።

@tikvahethiopia
ዩኤኢ የሚሳኤል ጥቃት ተሰነዘረባት።

የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግ ' ታሪካዊ ' ለተባለው ጉብኝታቸው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) በገቡበት በትላንትናው ዕለት የተባባሩት አረብ ኤሜሬትስ 2 የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት በአቡ ዳቢ ተሰንዝሮባታል።

የሀገሪቱ ጦር የተፈፀመውን ጥቃት ማክሸፉንና የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ገልጿል።

የሚሳኤል ጥቃት ፈፃሚው የየመን ሀውቲ እንደሆነም ጦሩ አሳውቋል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬት የአየር ኃይል በየመን ህጋዊነትን ለመመለስ ከተመሰረተው ጥምረት ጋር በመሆን በየመን አል-ጃውፍ ግዛት የሚገኘውን የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ቦታ ማውደሙን ገልጿል።

የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ፤ ማንኛውም አይነት ስጋት ለመመከት እንዲሁም ሀገሪቱን ከማንኛውም አይነት ጥቃት ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑ አረጋግጧል።

የእስራኤል ፕሬዜዳንት ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፕሬዜዳንቱ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የስራ ጉብኝታቸውን አቋርጠው እንደማይመለሱና በጉብኝታቸው እንደሚቀጥሉ አሳውቋል።

ሀውቲዎች ስለትላንቱ ጥቃት እስካሁን ያሉት ነገር ባይኖርም በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ላይ እያካሄድን ነው ስላሉት ኦፕሬሽን በቀጣይ ሰዓት መግለጫ እንደሚያወጡ ገልጸዋል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ከሀውቲ ኃይሎች የትላንቱ መሰል ጥቃት ሲፈፀምባት በዚህ ወር ለ3ኛ ጊዜ ነው።

ከጥቂት ቀናቶች በፊት የ ሀውቲ ኃይሎች በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ላይ በፈፀሙት ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ እና ጉዳት መድረሱ ይህንንም ጥቃት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራትና ተቋማት ማውገዛቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ - የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ አየር ኃይል ከጥምር ጦሩ ጋር በመሆን በየመን " አል-ጃውፍ " ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ቦታ በተሳካ ሁኔታ ማውደሙን በመግለፅ ከላይ የተያያዘውን ቪድዮ አጋርቷል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ የሀውቲን ጥቃት አወገዘች።

አሜሪካ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ አቡ ዳቢ የተፈፀመውን የሃውቲ ሚሳኤል ጥቃት እንደምታወግዝ አሳውቃለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቅባይ የሆኑት ኔድ ፕራስ ፥ " የእስራኤል ፕሬዝዳንት በአካባቢው መረጋጋትን ለማስፈን እና ድልድይ ለመገንባት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ባሉበት በአሁን ወቅት ሀውቲዎች ሰላማዊ ሰዎችን የሚያሰጉ ጥቃቶችን መሰንዘር ቀጥለዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

በነገራችን ላይ አሜሪካ ከሁለት ቀናት በፊት ለዜጎቿ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያስቡበት ማሳሰቢያ ሰጥታ ነበር።

አሜሪካ ከኮቪድ19 ምክንያት በተጨማሪ በሚሳኤል ወይም የድሮን ጥቃቶች ስጋት የተነሳ እና ሁኔታው አሳሳቢ በመሆኑ ዜጎቿ ወደ ሀገሪቱ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያስቡበት ነበር ያሳሰበችው።

አሜሪካ ለዜጎቿ ባሰራጨችው የጥንቃቄ መልዕክት የቅርብ ጊዜ ጥቃቶች ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እና በሲቪል መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠሩ እንደነበረ አሳውቃ ነበር።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ከሆኑት መካከል አንዷ እንደሆነች ይታወቃል።

@tikvahethiopia
" ጽኑ ሀገር " - በአቶ እስክንድር ነጋ

አቶ እስክንድር ነጋ የፃፉት መፅሀፍ ዛሬ ሰኞ ለገበያ ይቀርባል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ሆነው የፃፉት 'ጽኑ ሀገር' የተሰኘው አዲስ መፅሐፍ ዛሬ ገበያ ላይ እንደሚውል የመፅሐፉ አሳታሚ ሞረሽ መፅሐፍት መደብር አስታውቋል።

መፅሐፉ ጥልቅ ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን የያዘ እና በ256 ገፆች የተቀነበበ ነው ተብሏል።

በአራት ክፍሎች የተከፋፈለው ይህ መፅሐፍ የሰሜኑን ጦርነት እንዲሁም ምርጫ 2013ን በስፋትና በጥልቀት እንደሚተነትን ነው የተገለፀው።

ከዚህ በተጨማሪም የ1997 ዓ.ም. እና የ2002 ዓ.ም. አገራዊ ምርጫዎች፣ የአረብ ፀደይ አብዮት በመባል የሚታወቀው ፖለቲካዊ ክስተት እና ሌሎች ተዛማጅ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በመፅሐፉ መተንተናቸው ተነግሯል።

አቶ እስክንድር ነጋ ከዚህ ቀደም ድል ለዴሞክራሲ ፣ ምርጫ 97 የተባሉ መፅሐፍትን ለንባብ አብቅተው ነበር።

የመረጃ ምንጭ፦ የባልደራስ ፓርቲ የሚዲያ ክፍል ነው።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የአፍሪካ ህብረት ቡርኪናፋሶን አገደ።

በቡርኪና ፋሶ ከተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ጋር በተያያዘ የአፍሪካ ህብረት ሀገሪቱን ከማንኛውም የህብረቱ እንቅስቃሴ ማገዱን ዛሬ አሳውቋል።

እግዱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ወደነበረበት እስኪመለስ ይቀጥላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray , #Mekelle 📍

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በመቐለ ከተማ ለሚገኙ ሆስፒታሎች ወሳኝ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ማከፋፈል መጀመሩን ትላንት አሳውቋል።

ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያዎቹን አምስት በረራዎች ማጠናቀቁን ገልፆ በነበሩት በረራዎች ኢንሱሊንን ጨምሮ እጅግ አስቸኳይና አስፈላጊ መድሃኒቶችን ማጓጓዙን ገልጿል።

ይኸው ተግባር በዚህ ሳምንትም እንደሚቀጥል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#UAE

ጠ/ሚ መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ዩኤኢ ይገኛሉ።

የሶማሊያ ጠ/ሚር መሀመድ ሁሴን ሮበል በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የስራ ጉብኝት ላይ እንደሚገኙ አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ጠ/ሚ ሮብሌ በትናንትናው ዕለት ወደ አቡዳቢ ያቀኑ ሲሆን ከአገሪቱ አመራሮች ጋር በመወያየት ላይ መሆናቸውን ዘገባው ይገልፃል።

ባለፉት ቀናት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን እንዲሁም ትላንት የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብላ አስተናግዳለች።

ከየሀገራቱ መሪዎች ጋርም በተለያዩ ጉዳዮች መክራለች።

ፎቶ : #SomaliPM

@tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም ሪፖርት ፦

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የኩባንያውን የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ዛሬ ሪፖርት አድርገዋል።

በዚህ መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም ፦

• በ6 ወር አመርቂ ትርፍ እንዳገኘ ተገልጿል።

• በ6 ወር 28 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝቷል። ይህም ከእቅዱ 86.4 በመቶ አሳክቷል፤ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ6.7 በመቶ እድገት አሳይቷል።

• በውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 74.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝቷል፤ የእቅዱ 89.3 በመቶ አሳክቷል።

• ጦርነት ፣ በግጭት፣ ምክንያት በ3,473 የሞባይል ጣቢያዎች፣ ታውሮች ላይ የአገልግሎት መስተጓጎል እና አደጋ እንዳጋጠመ አሳውቋል። በዚህም በ6 ወር ውስጥ 3.67 ቢሊዮን ብር ገቢ አጥቷል።

• በጦርነቱ የተጎዱ እና እስካሁን መድረስ በተቻለባቸው አካባቢዎች የወደሙ ንብረቶችን ለመተካት እንዲሁም ደግሞ አግልግሎት ለማስጀመር 328.9 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።

አሁን ላይ በፀጥታ ችግር ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት ያልተቻለባቸው ወረዳዎች እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

በአካባቢዎቹ ላይ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ያሉበትን ሁኔታ ምንም ማወቅ እንዳልተቻለ ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት መቋረጥ ላጋጠማቸው ደንበኞች በሙሉ ይቅርታ ጠይቋል።

መረጃ ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
ፎቶ : የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@tikvahethiopia
#Share #ሼር

ለጠቅላላ ሀኪሞች የወጣ የኮንትራት ቅጥር ፦

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በዞን ጤና መምሪያ እና በልዩ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ክፍት የስራ መደብ ላይ ተፈላጊውን ችሎታ የሚያሟሉ ሀኪሞችን በኮንትራት ቅጥር አወዳድሮ መመደብ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

👉 የስራው መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 የሙያ መስመር /ተፈላጊ ችሎታ - በጠቅላላ ህክምና በዲግሪ የተመረቀ/ች
👉 የስራ ልምድ- #ዜሮ_ዓመት
👉 ብዛት - 379 (#ሶስት_መቶ_ሰባ_ዘጠኝ )
👉 ደመወዝ - 9,056
👉 የስራ ቦታ - በእጣ ነው የሚለየው

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በሚመደብበት በማንኛውም ዞን / ልዩ ወረዳ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ /የሆነች።

2ኛ. በዕጣ ከጤና ቢሮ ለዞን/ልዩ ወረዳ ሲመደቡ ዞን/ልዩ ወረዳ በሚሰጠው በማንኛውም ጤና ተቋማ /ምደባ / ቦታ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች።

3ኛ. በማንኛውም የመንግስት ተቋም ውስጥ ያልተቀጠረ /ያልተቀጠረች

የመመዝግቢያ ጊዜ ፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት። (ከተሰጠው ቀን ውጭ የሚመጣ አይስተናገድም)

የመመዝገቢያ ቦታ ፡ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ሲሆን ኦርጂናል የትምህርት እና የሙያ ፍቃድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር መያዝ እንዳትዘነጉ።

የፈተናው ቀን : በቀጣይ ይገለፃል።

@tikvahethiopia
#GoodayOn Mobile App

የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ!

አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም

ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።

GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ ፤ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
#ችሎት

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ታስረው እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጠ።

ከህዳር 4 ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ በስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሜቴክ ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ጋር ተያይዞ በዓቃቢህግ በቀረበባቸውባቸው የሙስና ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መጀመራቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት በሀምሌ 11ቀን 2013 ዓ/ም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፍርድ ቤት ቀርበው እ.ኤ. አ በ2014 ዓ/ም በተደረገ በዝቅተኛ ወለድ ስምምነት ኢትዮጲያ ከፖላንድ መንግስት ባገኘችው 50 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እዛው ፖላንድ ሀገር ለሚገኙ የዕርሻ መሳሪያ መለዋወጪያ ኩባንያዎች መከፈሉን እና ገንዘቡ ወደ ሀገር ውስጥ አለመምጣቱን በማብራራት የመከላከያ የምስክርነት ቃላቸው ተሰምቶ ነበር።

በዚሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ተሰቶባቸው የነበሩት የቀድሞ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።

ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መጥሪያ እንዲያደርስ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኩል አፈላልጌ ላገኛቸው አልቻልኩም ሲል መልስ ሰቶ ነበር።

 የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው የሮማን ፉውንድሽን እንደሚሰሩና በመንግስ ፖሊስ እጀባ እየተደረገላቸው እንደሚቀሳቀሱ ጠቅሰው ይህ በሆነበት ሁኔታ ፖሊስ ላገኛቸው አልቻልኩም በማለት የሰጠው ምላሽ  አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ በድጋሚ ትዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፖሊስ አቶ ሀይለማርያምን ደሳለኝን ካሉበት አፈላልጎ አስሮ እንዲያቀርባቸው ትዛዝ ሰቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tarik-Adugna-01-31

#TarikAdugna