TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ : የከተራ በዓል በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ጎንደር ❤️ ከተማ ፤ ጥር 10 ቀን 2014 ዓ/ም ።

የፎቶ ባለቤት 👉 ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው

@tikvahethiopia
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ - ኢትዮጵያ አባላት የጥምቀት በዓልን ስናከብር ከአጠገባችን በችግር ላይ ያሉ የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ ፣ አቅም የሌለንም ስለእነሱ በማሰብ እና ፈጣሪን በመለመን ፣ ለሀገር ሰላም እና ለሰው ልጆች ሁሉ ደህንነት በመፀለይ እንዲሆን አደራ እንላለን።

ዛሬም በሀገራችን የተለያዩ አቅጣጫዎች በችግር እና ስቃይ ያሉ ወገኖች በርካቶች መሆናቸውን በመገንዘብ ፣ እንደኛ ይህን በዓል በሰላም እና በደስታ ማክበር የማይችሉ ወገኖቻችን መኖራቸውን በማወቅ ፈጣሪ ለሁላችን ሰላም እና ፍቅር ፣ መተሳሰብና አንድነት አድሎ በጋራ በሰላም በመሰባሰብ እንድናከብር እንዲረዳን እንለምናለን።

ያዘኑ ወገኖችን ምናፅናናበት፣ የተጣላን የምንታረቅበት፣ የተኳረፍን የምንነጋገርበት ፣ ያስቀየምን ይቅርታ የምንጠይቅበት፣ የበደልን የምንክስበት፣ ያስከፋን የምናስደስትበት ፣ የታመሙ የተጎዱ የሚፈወሱበት ፣ የተጨነቁ ከጭንቀት ነፃ የሚሆኑበት የሰላም ፣ የደስታ፣ የአንድነት፣ የፍቅር በዓል ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
አርቲስት ኑሆ ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አርቲስት ኑሆ ጎበና ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት ኑሆ ጎበና በአፋን ኦሮሞና በተለያዩ ቋንቋዎች በርካታ ዜማዎችን ለአድማጭ አበርክቷል፡፡

አርቲስት ኑሆ ፤ ከአባቱ አቶ መሃመድ ጎበና እና ከእናቱ ወይዘሮ ፋጡማ አደም በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡

#ኤፍቢሲ/#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
#Photo

የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉን ገፅታ የሚያሳዩ ፎቶች ከአ/አ፣ ደሴ፣ ጎንደር፣ ሀይቅ ፣ ኮምቦልቻ፣ ቡሌ ሆራ ፣ ነቀምቴ፣ ቦንጋ፣ አርባ ምንጭ ፣ ሀዋሳ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ ፣ ግልገል በለስ ፣ ድሬዳዋ ፣ሀዋሳ እንዲሁም ከሌሎች ከተሞች በማሰባሰብ ወደ ስልካችሁ ልከናል።

የፎቶ ስብስቦቹ ይመልከቱ 👉 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-19

ሁሉም ፎቶዎች ምንጫቸው የተገለፀበት ነው።
TIKVAH-ETHIOPIA
#AliBira አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ ይገኛሉ። የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው የጉሙሩክ ኮሚሽን አሳውቋል። ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከህመማቸው ተፈውሰው የሚወዱትን ሙያ…
#AliBira

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤ ክቡር ዶክተር አሊ ቢራን ህክምና በሚከታተሉበት ሆስፒታል ተገኝተው ጠይቀዋቸዋል።

ከዚህ ቀደም አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወሳል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

እስር ላይ ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት ኢያስፔድ ተስፋዬ ዛሬ ከእስር ተፈቷል።

ኡቡንቱ የተባለው ሚዲያ መስራችና ጋዜጠኛ እያስፔድ ተስፋዬ ዛሬ ከቀትር በኋላ ነው ከእስር እንደተፈታ ሚዲያው የገለፀው።

ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እያስፔድ 43 ቀናት በእስር ሲቆይ ፖሊስ አንድም ጊዜ ፍርድ ቤት እንዳላቀረበው እና ክስም እንዳልመሠረተበት ሚዲያው ገልጿል።

በትላንትናው ዕለት ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ከእስር መፈታቷ ይታወቃል።

ሌሎች በእስር ላይ ከሚገኙ ጋዜጠኞች መካከል ተራራ ኔትዎርክ የተባለው ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የአሐዱ ሬዲዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ስለመፈታታቸው የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somaliland በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ማቅናቱ ተነግሯል። ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተደረገላቸው ይፋዊ ግብዣ መሰረት ነው ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ የተገለፀው። በሌላ በኩል ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢሳ ካይድ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከፕሬዜዳንቱ ሙሴ ቢሂ አብዲ ቀደም…
የፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ ቆይታ ፦

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ የተነገረላቸው የሶማሊላንድ ፕሬዤዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈው ነበር።

@tikvahethiopia