TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቢሲንያ_ባንክ

አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ስነ ስርዓትን እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ጋር እሁድ ጥር 1 ቀን የሚያደርጉትን ፍልሚያ በጊዮን ግሩቭ ጋርደን በግዙፍ እስክሪን አብረን እንመልከት ይሎታል።

ምግቡ መጠጡ ሙዚቃው ሁሉም ተሰናድቶል። ከምሽቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ክፍት ይሆናሉ።

#መግቢያ_በነፃ

ቪዛ ካርድ የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ ኦፊሻል ስፖንሰር።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ https://t.iss.one/BoAEth

#አቢሲንያ #የሁሉም_ምርጫ #visa
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀው ህውሃት ጋር ባላቸው ልዩ ልዩ ግንኙነት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲጣራባቸው ከነበሩ ግለሰቦች መካከል በድርጊታቸው ተፀፅተው ይቅርታ የጠየቁትን፣ ከፍተኛ ወንጀል ያልፈፀሙ እና ከእሥር ቢወጡም ለከተማዉ ስጋት የማይሆኑት በዋስ ከእስር እየተለቀቁ ነው ብሏል።

የተቀሩትንም እንደ ድርጊታቸው ክብደትና ቅለት እየታየ ወደፊት እንደሚለቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዋስ የተለቀቁ ግለሰቦች ወደፊት እንደ ጥፋታቸው በህግ እንደሚጠየቁ እና በህግ አካላት ጥሪ ሲደደረግላቸው የመቅረብ ግዴታ አለባቸው ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በሽብርተኛ ከተፈረጀው ቡድን ጋር ግንኙነት ማድረግ ሆነ የሽብር ቡድኑን ዓለማ ማራመድ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተረድቶ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት እና የመንግስት ምላሽ !

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ትላንት ረቡዕ ባወጣው ሪፖርት፤ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ የመብት ጥሰት መፈጸሙን ገልጿል።

ተቋሙ በሪፖርቱ፤ ከስደት ተመላሾቹ ላይ “የዘፈቀደ እስር እና እንግልት ደርሶባቸዋል፤ ደብዛቸውም ጠፍቷል” ብሏል።

የሂዩማን ራይትስ ዎች የስደተኞች እና የስደተኛ መብት ተመራማሪ ናዲያ ሃርድማን “በሳዑዲ እስር ቤት አሰቃቂ በደል የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች፤ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በማቆያ እስር ቤቶች እየተቆለፉ ይገኛሉ” ብለዋል።

ሙሉ ሪፖርቱ : https://www.hrw.org/news/2022/01/05/ethiopia-returned-tigrayans-detained-abused

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ሂዩማን ራይትስ ዎች በትላንትናው ዕለት ያወጣው ሪፖርት “ድርሰት ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የተቋሙ ሪፖርት “በኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጫናዎች አካል ነው” ብለዋል።

“በሰፈር፣ በማንነት የተለየ እና የተጎዳ ሰው አልነበረም። እንደዚያ አይነት አሰራርም አልነበረም” ያሉት አምባሳደር ዲና ፥ “ሂዩማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያን በሚመለከት መዓት ድርሰቶች አሉት፤ ይሄም ከድርሰቶቹ አንዱ ነው” ብለውታል።

በጉዳዩ ላይ ከዚህ በላይ ማብራሪያ የሚሰጠበት እንዳልሆነም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵየ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
#Amhara

የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የገና በዓል እና የጥምቀት በዓል በሰላምና ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የፌዴራል እና የክልል የጸጥታ እና የደህንነት አካላት ጋር በጥምረት በመሆን በዓሉ በሰላም ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ እና የፀጥታ ኃይሉ ስነምግባርን ተላብሶ ተግባራትን እንዲከዉን ዝርዝር ዕቅድ ታቅዶ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና አባላት በቂ ኦረንቴሽን በመስጠት ዝግጅት ተደርጓል።

በተለይ ደግሞ በዓሉ በከፍተኛ ሁኔታ በሚከበርባቸው አካባቢዎች ተንቀሳቃሽ እና ቋሚ ጥበቃ ተመድቧል። በዚህም ህዝቡ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ስጋት ሊያከብር ይገባል ተብሏል።

ህዝቡ ከፀጥታ ኀይሎች ጎን በመሆን በዓላቱ በሰላም እንዲከበር የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል።

ነዋሪዎች በአማራ ክልል ማንኛውም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥም በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የፀጥታ ኀይል እንዲጠቁሙ መልዕክት ተለልፏል።

(የዞኖች ፣ የብሄረሰብ አስተዳደሮች እና ከተሞች የፖሊስ ስልክ ከላይ ተያይዟል - በምትኖሩበት አካባቢ ሁሌም የፀጥታ ኃይሎችን ስልክ ቁጥር መመዝገብ እንዳትዘነጉ)

እባክዎትን ስልክ ቁጥሮቹን #Share #ሼር ያድርጉ !

#AmharaPoliceCommission

@tikvahethiopia
የገና ሥጦታ ሎተሪ !

የገና ሥጦታ ሎተሪ ሀሙስ ታህሳስ 28/ 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል።

1ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 1977732

2ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0341880

3ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0929042

4ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 1357756

5ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1288620

6ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 0614488

7ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 20,000 ብር የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 18052

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 05609

9ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 4599

10ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 6941

11ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 883

12ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 250 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 904

13ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 22

14ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 50 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 4 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tikvahethiopia
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

ታህሳስ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ (የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ) በጥር ወር ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች ፣ አረጋውያን ፣ የጤና ችግር ያለባቸው ይገኙበታል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በእስር ላይ የነበሩ በርካታ ሰዎች ታኅሣሥ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ጨምሮ ባለፉት ቀናት ከእስር መለቀቃቸው አበረታች እርምጃ መሆኑን ገልጿል።

ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ሌሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ በቀላል ዋስትና የተለቀቁ ሰዎች ይገኙበታል ብሏል።

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ተመሳሳይ እርምጃዎች እንዲቀጥሉ፣ እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ከግምት በማስገባት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተደነገገው መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ አስፈላጊነቱና የተፈጻሚነቱ አካባቢያዊ ስፋት እየተገመገመ ተገቢው ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም ኢሰመኮ ጋዜጠኞችን ጨምሮ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች የተያዙበት ጉዳይ የማጣራት ሂደቱ የተፋጠነ እንዲሆን፣ የእስር አያያዝ እንዲሻሻል፣ የታሰሩበት ስፍራ ለቤተሰቦች ያልተገለጸ ሰዎች እንዲገለፅ ፤ እንዲሁም በአጠቃላይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የሰብአዊ መብቶችን መርሆች ባከበረ መልኩ መተግበሩ እንዲረጋገጥ በድጋሚ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !

መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በዓሉን በጦርነት እና ግጭት ምክንያት ከቀያቸው ተሰደው፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በመደገፍ፣ አብሮ በመብላት ፣ በማፅናናት ፣ ተስፋን በመስጠት እንድታከብሩ እንማፀናለን።

በተጨማሪ ሁላችንም በያለንበት በጦርነት እና ግጭት ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ ወገኖችን በማሰብ ፤ ስለሀገራችን ዘላቂ ሰላም እና ፍቅር በመፀለይ በዓሉን ልናሳልፍ ይገባል።

ፈጣሪ የሁላችን መጠለያ ፣ መሰብሰቢያ ፣ መሸሸጊያ የሆነችውን ሀገራችን ኢትዮጵያን ጠብቆ ፤ ህዝቦቿን አፋቅሮና አዋዶ ያኖርልን ዘንድ እንለምናለን።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት ፣ ያጠፋን የበደልን ያስከፋን ይቅር የምንባባልበት፣ ብሩህ ተስፋ (ቲክቫህ) የምናይበት ይሆን ዘንድ ተመኘን።

#TikvahFamily
#ETHIOPIA

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አከባበር በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላልይበላ - #Lalibela

Credit : ሙልጌታ አንበርብር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ : የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል አከባበር በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላልይበላ - #Lalibela Credit : ሙልጌታ አንበርብር @tikvahethiopia
በሰላም ተጠናቋል !

በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላልይበላ የተከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እጅግ በታላቅ ድምቀት በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል መንግስት ሪፖርት አድርጓል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ላደረጉ ሁሉ ምስጋና ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ጋር ትናንት ሃሙስ መነጋገራቸው ተገልጿል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና አምባሳደር ፌልትማን መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ትናንት ሃሙስ እንደተነጋገሩ ከመግለጽ ውጪ በምን ዐይነት መንገድ ተነጋገሩ በስልክ ወይስ በአካል ስለሚለው የገለጸው ነገር የለም፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ሆነ ጽህፈት ቤታቸው ስለጉዳዩ ያሉት ነገር የለም፡፡

ንግግሩን ተከትሎ በተለይ ዓመት ያስቆጠረውን ጦርነት በተመለከተ የሚገኙ አዎንታዊ ነገሮች ይኖራሉ በሚል አሜሪካ ተስፋ ማድረጓን ሮይተርስ ሚኒስቴሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ይለቃሉ።

ምንጭ፦ አል ዓይን / ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ “ ጀግና ሕዝብ - በቀኝ እጁ ድልን የሚጨብጥ፣ በግራ እጁ ይቅርታና ምህረትን የሚቸር ነው! ” በሚል መልዕክት አስታላልፈዋል።

በዚህ መልዕክታቸው ከድላችን ማግስት 4 ነገሮችን መርሖቻችን አድርገን እንድሄድባቸዋለን ብለዋል።

እነዚህም ፦

1ኛ. ድላችንን እንዳይቀለበስ አድርገን በሁለንተናዊ መስክ እናጠብቀዋለን።

2ኛ. ድላችን ዘላቂ እንዲሆን በፖለቲካዊና ሰላማዊ መንገዶች እንዲቋጭ እናደርገዋለን።

3ኛ. ድላችንን ለመጠበቅና ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምሕረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን።

4ኛ. ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትህ በሽግርር እና በተሀድሶ ፍትህ እይታ ፣ ሀገራዊ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን ፤ ሲሉ ገልፀዋል።

እነዚህ 4ቱ መርሖች አንዱ ሌላውን ሳይተካ ሁላችንንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ እንደ አስፈላጊነታቸው ሁሉ እንተገብራለን ሲሉም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመልዕክታቸው በድል ፣ በምህረትና ትህትና ኢትዮጵያን ዘላቂና የፀናች አሸናፊ እንደርጋታለንም ብለዋል።

* ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

@tikvahethiopia