TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ከ850 ሺህ በላይ የኩፍኝ መከላከያ ክትባቶች ባለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መግባቱን ዩኒሴፍ ዛሬ አሳውቋል። ዩኒሴፍ ክትባቱ ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መከተባቸውን ለማረጋገጥ በጣም ወሳኝ እርምጃ ነው ብሏል። የኩፍኝ በሽታ በጣም ተላላፊ ነገር ግን በክትባት በቀላሉ መከላከል ይቻላል። #UNICEF @tikvahethiopia
#Tigray

ዩኒሴፍ፣ የዓለም ጤና ድርጅትና አጋሮቻቸው በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ጀምረዋል።

ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን ከዚህ በጣም ተላላፊ ነገር ግን በቀላሉ መከላከል ከሚቻል በሽታ ለመጠበቅ ከ850,000 በላይ ክትባቶች ወደ ክልሉ መግባታቸው አይዘነጋም።

Credit : UNICEF ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ጥሏል፡፡

ቢሮው በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን መከላከል የሚያስችል የሞተር ብስክሌት ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ በማውጣት ወደስራ መገባቱ አስታውሷል።

በአሁኑ ወቅት ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በርካታ የዲያስፖራ አባላት ወደሀገራቸው እየገቡ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ወቅቱ የበዓል ሰሞን እንደመሆኑ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ በብዛት እንቅስቃሴ እያደረጉ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎ በከተማዋ የትራፊክ መጨናነቅ እና የዝርፊያ ምልክቶች እየታዩ ነው ሲል አሳውቋል።

ስለሆነ ከታህሳስ 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እና እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ምንጭ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

@tikvahethiopia
#Kombolcha

ከነገ ታህሳስ 27 ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኮምቦልቻ እለታዊ የበረራ አገልግሎቱን እንደሚጀምር አስታውቋል።

ተጓዦች የጉዞ ምዝገባ ለመያዝ 👉 https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app መጠመቀም እንደሚችሉ አየር መንገዱ ገልጿል።

@tikvahethiopia
የአሜሪካ ወታደሮች ባሉባቸው የጦር ሰፈሮች የድሮን ጥቃት ተሰንዝሮ መክሸፉ ተነገረ።

ኢራቅ ውስጥ ISISን የሚዋጋው በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ጦር የአሜሪካ ወታደሮች ባሉበት የጦር ሰፈር የተሰነዘሩ የድሮን ጥቃቶችን ማክሸፉን ገለፀ።

በ24 ሰዓት ሁለት ጊዜ የድሮን ጥቃቶች መፈፀማቸው የተነገረ ሲሆን በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ኃይሉ ሁለቱም ጥቃት ማክሸፉን አሳውቋል።

የዓለም አቀፉ ወታደራዊ ጥምረት ባለስልጣን ዛሬ ማክሰኞ እንደተናገሩት ፥ 2 የታጠቁ ድሮኖች በምእራብ አንባር ግዛት ወደሚገኘው ጦር ሰፈር ሲቃረቡ ተመተው ተጥለዋል።

የጥቃቱ ሙከራ አለመሳካቱንም ተናግረዋል።

ጥምረቱ ትላንት ሰኞ በባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ወደሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ሲቃረቡ የነበሩ ሁለት የታጠቁ ድሮኖች ተመተው መጣላቸውን አሳውቋል።

እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ነግሷል... በትናንትናው እለት የኢራን ብሔራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጄነራል ቃሲም ሱለይማኒ ኢራቅ ውስጥ በአሜሪካ ዘመቻ መገደላቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ነግሷል፡፡ ድርጊቱን ተከትሎ ቴህራን ልትወስደው የምትችለውን አፀፋዊ እርምጃ ለመከላከል አሜሪካ ተጨማሪ 3,000 ወታደሮቿን ወደ ቀጠናው መላኳን NBC NEWS ዘግቧል። #AlAin @tikvahethiopiaBot…
#GeneralQasemSoleimani

ጄነራል ቃሲም ሱሌይማኒ የተገደሉበት 2ኛ ዓመት በኢራን እየታሰበ ነው።

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቃሴም ሱሌይማኒ ግድያ ክስ ካልቀረበባቸው እና ተጠያቂ ካልተደረጉ የበቀል እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል እንደገቡ ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ፕሬዜዳንቱ ፥ " አጥቂው እና ዋናው ገዳይ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት (ዶናልድ ትራምፕ) ፍትህ እና ቅጣት ሊጠብቃቸው ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ አክለው ትራምፕ፣ (የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር) ማይክ ፖምፒዮ እና ሌሎች ወንጀለኞች ተይዘው የፍርድ ሂደታቸው ፍትሃዊ በሆነ ፍርድ ቤት ለአሰቃቂ ወንጀሎቻቸው እና ለድርጊታቸው ተጠያቂ ከሆኑና ፍትህ የሚያገኝ ከሆነ ምንም ችግር የለውም ብለዋል።

"አለበለዚያ ግን ለመላው የአሜሪካ መሪዎች የምነግራቸዉ ያለጥርጥር የበቀል ክንዳችን እንደሚያርፍባቸው ነው " ሲሉ ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል።

ጄነራል ቃሲም ሱሌይማኒ ፤ ከኢራቃዊው ሌተናንት አቡ ማህዲ አል ሙሃንዲስ ጋር እኤአ ጥር 3 ቀን 2020 በአሜሪካ ድሮን ኢራቅ፣ ባግዳድ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ መገደላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Dessie #Hayq

ትምህርት ሚኒስቴር በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች በህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ ምክንያት ከ2 ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ እንደጀመረ አሳውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው)

@tikvahethiopia
#DStv

የMyDStv መተግበሪያን በመጠቀም የዲኤስቲቪ አካውንትዎን በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ይቆጣጠሩ።

ሂሳብዎን ይክፈሉ፣ የE-16 እና ሌሎች የቴክኒክ ችግሮችን በቀላሉ ያስተካክሉ!!!

የ MyDStv መተግበሪያን ለማውረድ ይህን ሊንክ ይጫኑ👇
https://bit.ly/theMyDStvApp

#DStvSelfServiceET #DStvየራሳችን
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ለቀቁ። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋ አሳውቀዋል። አብደላ ሀምዶክ ከጦር ኃይሉ ጋር በተደረገው የፖለቲካ ስምምነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ከተመለሱ ከ6 ሳምንታት በኋላ ነው ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት። ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ሊለቁ መሆኑን የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው…
#SUDAN

በሱዳን የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም ቀጥሏል።

ዛሬ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ወታደራዊውን አስተዳደር በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች በሀገሪቱ የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም በካርቱም ከተማ በፕሬዝደንቱ መኖሪያ አካባቢ የተሰባሰቡ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸውን እማኞች መገልፃቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

ዛሬ ከካርቱም በተጨማሪ በኦምዱርማን ከተማ ሱዳናውያን አደባባይ ወጥተው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱን አውግዘዋል።

በሌሎች ከተሞችም ፖርት ሱዳንን ጨምሮ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፎች መኖራቸውን አሶሴትድ ፕረስ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከሥልጣናቸው መልቀቃቸውን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ካሳወቁ በኋላ የሱዳን የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል።

መረጃው የዶቼቨለ እና አሶሼትድ ፕሬስ ነው።

@tikvahethiopia
#ለኢትዮጵያ

የፊታችን ጥር 1 ከቀኑ 9:00 ላይ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ " ለኢትዮጵያ " በሚል የምልጃና የአምልኮ ጊዜ መዘጋጀቱ ተገለፀ።

ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በዘጸአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን ሲሆን ስለኢትዮጵያ የጸሎት እና አምልኮ ጊዜ እንደሚሆን ቤተክርስትያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቃለች።

በዕለቱ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን የገቢ ማሰባሰቢያ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከደህንነት አንፃር ከመንግስት ጋር አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅት መጠናቀቁና ምንም አይነት የሚያሰጋ ነገር ባለመኖሩ ከአዲስ አበባ ሆነ ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ እንዲታደሙ ጥሪ ቀርቧል።

ዝግጅቱ የኮቪድ-19 ጥንቃቄ በሚተገበርበት መልኩ እንደሚሆንም ተነግሯል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የስያሜ ለውጥ አድርጓል ?

ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ስያሜ ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል። በጉዳዩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት መኩሪያ ንጋቱ ለ @tikvahuniversity ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመቋቋሚያ አዋጁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ደረጃና ስያሜ የመስጠት መብት ነበረው።

በዚህም የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረውን የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ወደ ዩኒቨርሲቲ የማደግ ጥያቄ ምላሽ ሰጧል። በየካቲት 2013 ዓ.ም ለኢንስቲትዩቱ "የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ" የሚል ስያሜም ሰጥቷል።

ይሁን እንጂ የስያሜ ለውጡ ኢንስቲትዩቱ ሲቋቋም የተሰጠው ተልዕኮ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ተሻሽሎ፣ በነጋሪት ጋዜጣ መታወጅ እንደነበረበት ኃላፊው ገልጸዋል።

ይህ ሕጋዊ ሂደት ሳይጠናቀቅ በመስከረም 2014 ዓ.ም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ሚኒስቴር ስር መጠቃለሉን አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲም አዲስ በተደራጀው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ስር የተካተተ ሲሆን ''የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት" የሚል ስያሜ እንዲሰጠውም ተወስኗል።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት ''የስያሜ ለውጥ ውሳኔው በድጋሜ ሊታይ እንደሚገባ ለመንግስት ጥያቄ ማቅረባቸውን'' ኃላፊው ገልጸዋል።

"ጥያቄው በተለያዩ ደረጃዎች እየታየና የመንግስት ምላሽ እየተጠበቀ እንደሆነ" ኃላፊው አስረድተዋል።

ከመንግስት ምስረታው በኋላ በአዋጅ ለተቋቋሙ እና የደንብ ክለሳ ለሚያስፈልጋቸው ከ50 ያላነሱ ተቋማት የሚኒስትሮች ም/ቤት በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

More : @tikvahuniversity