TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.7K photos
1.56K videos
216 files
4.28K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጋዜጠኞች ግድያ ... #በ2021

የጎርጎሮሳውያኑ 2021 ተጠናቆ ከትላንት ጀምሮ አዲሱ ዓመት 2022 ገብቷል።

በተሰናበተው 2021 በመላው ዓለም 45 ጋዜጠኞች ተገድለዋል።

የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በ2021 የተመዘገበው የጋዜጠኞች ግድያ ከየትኛውም አመት ከተመዘገበው ዝቅተኛ ቁጥር አንዱ ነው ብሏል።

በአንድ ሀገር ከፍተኛ የተመዘገበው አፍጋኒስታን ውስጥ ሲሆን 9 ጋዜጠኞች ተገድለዋል እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ግድያ የተመዘገበባቸው በሜክሲኮ 8 ፣ በህንድ 4 ፣ በፓኪስታን 3 እንደሆነ ተገልጿል።

አፍጋኒስታንን የሚያጠቃልለው ኤዥያ-ፓሲፊክ አካባቢ 20 ግድያዎች የተመዘገቡበትና ከፍተኛው ሲሆን አሜሪካ 10 ፣ አፍሪካ 8 ፣ አውሮፓ 6 እና መካከለኛው ምስራቅ እና አረብ ሀገራት 1 ተመዝግቧል።

በኢራን በደረሰ “አሰቃቂ አደጋ” የ2 ጋዜጠኞች ሞትም ጠቅሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው ? የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ሊለቁ መሆኑን ዘግቧል። የዜና ወኪሉ መረጃውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ዛሬ መስማቱን ገልጿል። ለሚዲያ ማብራሪያ መስጠት ያልተፈቀደላቸው አንድ ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላ ሀምዶክ የቢሮ ሰራተኞቻቸውን አደራ እንዲያስረክቡ ማዘዛቸውን ፤ ሰራተኞቹም ይህን ከእሁድ ማታ ጀምሮ መተግበር…
#BREAKING

ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ለቀቁ።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋ አሳውቀዋል።

አብደላ ሀምዶክ ከጦር ኃይሉ ጋር በተደረገው የፖለቲካ ስምምነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ከተመለሱ ከ6 ሳምንታት በኋላ ነው ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት።

ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ሊለቁ መሆኑን የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ምንጭ መስማቱን መዘገቡ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#UPDATE😷

የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦

🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ በ5 ወር ውስጥ ከፍተኛውን የኮቪድ-19 ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,024 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ይህም በ5 ወር የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው። ባለፈው ወር ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የኦሚክሮን ዝርያ ሪፖርት አድርጋለች።

🇮🇱 እስራኤል ካለፈው መስከረም ወር ወዲህ ከፍተኛውን የኮቪድ-19 ኬዝ ሪፖርት አደርጋለች። ባለፉት 24 ሰዓት 4,197 ሰዎች በቫይረሱ መያዘቸው ተረጋግጧል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት በኦሚክሮን ዝርያ ስርጭት ሳቢያ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ሊጨምሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

🇮🇳 ህንድ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ለ5ኛ ተከታታይ ቀን በእጅጉ መጨመር ያሳየ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

🇵🇸 በፍልስጤም ፤ ጋዛ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር 4ኛው ማዕበል እየመጣ መሆኑን አስጠንቅቋል።

🇶🇦 ኳታር በሶስተኛው የኮሮና ቫይረስ ማዕበል ላይ እንደምትገኝ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ነዋሪዎች የማጠናከሪያ/ተጨማሪ ክትባቱን እንዲወስዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

🇪🇹 በሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 3 ቀናት ብቻ 11,213 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 32 ሰዎች ህይወታቸው አልፋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#LALIBELA ከፊታችን ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ታሪካዊቷ ከተማ ላሊበላ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ አሳውቋል። @tikvahethiopia
#UPDATE

ወደ ላሊባላ ከተማ በረራ ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ ዕለታዊ በረራውን ዛሬ ጀምሯል።

አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ መጓዝ የሚፈልጉ መንገደኞች በአየር መንገዱ መተግበሪያ በመጠቀም ቀጠሮ ማስያዝ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።

በአዲሱ የተቋማት አደረጃጀት መሰረት ቀደም ሲል በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሲሰራ የነበረው ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት ለአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ በውክልና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ቢሮው ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑ በመግለፅ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።

አሽከርካሪዎች አዲስ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት በሚሄዱበት ወቅት ምን ያስፈልጋቸዋል ?

- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም የታደሰ ፓስፖርት፣
- ሲኦሲ ዋናውን፣
- የ8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውን፣
- የ10 ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ሆኖ ትክክለኛነቱ በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተረጋገጠ ሰነድ በመያዝ በአካል በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ለቀቁ። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋ አሳውቀዋል። አብደላ ሀምዶክ ከጦር ኃይሉ ጋር በተደረገው የፖለቲካ ስምምነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ከተመለሱ ከ6 ሳምንታት በኋላ ነው ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት። ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ሊለቁ መሆኑን የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው…
#Update

አሜሪካ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቅ በኋላ፣ የሱዳን መሪዎች ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው መግባባትን መፍጠር እና ቀጣይነት ያለው የሲቪል አስተዳደርን ማረጋገጥ አለባቸው ብላለች።

ሀገሪቱን ይህን ያለችው የጠ/ሚር አብደላ ሀምዶክ ስልጣን መልቀቅን ተከትሎ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣችው አጠር ያለ መግለጫ ነው።

አሜሪካ ቀጣዩ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ካቢኔ የህዝብን የነጻነት፣ የሰላም እና የፍትህ ግቦች ለማሳካት በህገ-መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት መሾም አለበት ብላለች።

አሜሪካ በመግለጫዋ ላይ የሱዳን ሕዝብ ዴሞክራሲን ለማስፈን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከጎናቸው መቆሟን እንደቀጠለች ገልፃ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት መቆም አለበት ስትል አስታውቃለች።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

የጤና ባለሙያዎች ህብረተሰቡ ለኮቪድ -19 የሳል ማስታገሻ በሚል ከሚወሰዱ መድኃኒቶች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

ከኮቪድ - 19 መስፋፋትን ተከትሎ በየፋርማሲዎች የሳል ማስታገሻ መድኃኒቶች ፍላጎት መጨመሩን ባለሙያዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

የአለርት ሆስፒታል የፋርማሲ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አሸብር ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ ከኮቪድና ጉንፋን ወረርሽኞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ በርካቶች ያለሐኪም ምክር ከየፋርማሲው የሳል ማስታገሻ መድኃኒቶችን እየወሰዱ ነው ብለዋል።

ይህ ልምድ ለተጓዳኝ በሽታዎች መባባስ የሚዳርግ በመሆኑ መጠንቀቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በተለይ በከተሞች ላይ የጉንፋን በሽታ ይዞኛል የሚሉ በርካታ ሰዎች “ፍሉ ስቶፕ” የተሰኘውን ማስታገሻ መድኃኒት በመግዛት ያለሐኪም ምክር እየወሰዱ ይገኛሉ ያሉት አቶ ዮናስ፤ ተመሳሳይ መድኃኒቶችን ያለባለሙያ ምክር መውሰድ በተለይ የደምግፊት፣ ስኳር፣ አስምና ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ላለባቸው ሰዎች አደገኛ ነው ብለዋል።

ተመሳሳይ መድኃኒቶች በመንግሥት ሆስፒታሎች በሚገኙ ፋርማሲዎች ውስጥ ያለሐኪም ትዕዛዝ እንደማይሸጡ የጠቆሙት አቶ ዮናስ፣ በግል ፋርማሲዎች ግን መድኃኒቱን ለጠየቀ ሁሉ የመሸጥ ልምድ እንዳለ አስረድተዋል።

ሰዎችም የጉንፋን ምልክት ስላሳዩ ብቻ ያለሐኪም ምክር ማስታገሻዎችን መውሰዳቸው ለከፋ የጤና ችግር እንደሚያጋልጥ በማወቅ በቅድሚያ መመርመር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ያለበለዚያ ግን ለውስብስብ የጤና ችግር የመዳረግ እድላቸው ይሰፋል ሲሉ አሳስበዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-01-03

ምንጭ፦ ኢፕድ

@tikvahethiopia
#INTERPOL

ጆን ሀብቴ ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ለኔዘርላንዳስ ተላልፎ ተሰጥቷል።

በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለዓመታት ሲፈለግ የቆየው ትውልደ ኤርትራዊው የኔዘርላንድ ዜጋ ናይሮቢ ውስጥ ተይዞ ለኔዘርላንድስ ተላልፎ መሰጠቱን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ።

ዓለም አቀፍ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ቡድንን ሲያንቀሳቅስ ነበር የተባለው የ53 ዓመቱ ጆን ሐብቴ ከ2 ሳምንት በፊት ነው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው።

ጆን ሐብቶን ለመያዝ ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም የሆነው ኢንተርፖል አስቸኳይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ተከትሎ የኬንያ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን አባላት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ዳርቻ ላይ በሚገኝ ስፍራ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት ገልፀዋል።

ተጠርጣሪው ናይሮቢ ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ተደብቆ እንደቆየ ባይታወቅም ከ2 ሳምንት በፊት ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

ግለሰቡ ወዲያውኑ ለኔዘርላንድስ ተላልፎ የተሰጠ በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ እዚያው በእስር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ኢንተርፖል ፥ ጆን ሐብቴ በድብቅ የሚንቀሳቀስ ዓለም አቀፍ በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያዘዋውር ቡድን መሪ እንደሆነ እንደሚታመን አመልክቶ ፤ በርካታ ሰዎችን ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር ወንጀል ተጠያቂ ነው ብሏል።

ግለሰቡ በተለይ በርካታ ኤርትራውያንን በእስያ በኩል ወደ አውሮፓ እንዲገቡ አድርገዋል ከተባሉ፣ ቢያንስ አራት የተለያዩ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎች ጋር ስሙ ተያይዞ ይነሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ / https://www.interpol.int/News-and-Events/News/2021/People-smuggling-sting-operation-Kenya-Netherlands-cooperation-lands-renowned-fugitive-in-jail

@tikvahethiopia
#NDRMC

በጦርነቱ በተፈናቁሉ እና እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ዜጎች ስም ከሚሰበሰብ እርዳታ ውስጥ የለሽያጭ የሚቀረበና ለማይገባቸው ሰዎችም የሚደርስ እንዳለ የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

ይህን ያሳወቀው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጠው ቃል ነው።

የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ፥ አንዳንድ አካላት ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ማህበራት እንዲሁም አብዛኛው ተቋማት እያመጡ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ጠቁመው እርዳታውን በራሳቸው መንገድ ለማድረስ የሚሄዱበት አካሄድ ግን እርዳታው ለሚገባቸው ዜጎች በትክክል እንዳይደርስ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ደበበ ፥ "አንዳንድ ጊዜ እንደውም እዚህ ቦታ ይሂድ ይላሉ ድጋፍ ሰጪው ድጋፍ የሚሰጥበትን ቦታ እሱ መምረጥ ተገቢ አይደለም። የት ቦታ ምን እንደጎደለ እኛ ነን የምናውቀው። ህፃናት ለብቻ ናቸው፣ አጥቢ እናቶች፣ ነፍሠጡሮች ለብቻ ናቸው፣ አቅመ ደካሞች ለብቻ ናቸው። እዚህ ደሴ ያገኘሁትን ነው የምናገረው እርዳታው ለጎረምሳ ቀለብ እየሆነና ለገበያ እየዋለ ነው" ብለዋል።

አክለው፥ "ከዛ የሚላከው እዚህ ሲደርስ ተቀንሶ፣ ተቀሽቦ ነው እየደረሰ ያለው ይሄ አግባብ አይደለም። በየመንገዱም የተለያየ ስራ የሚሰራ ከሆነ ትንሽ ኢትዮጵያ እና ህዝቧ እየተደገፈ አይደለም ማለት ችላል" ሲሉ ገልፀዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በትክክል ድጋፍ እንዲያገኙ ከተፈለገ በጋራ እና በትብብር መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ደበበ ለጋሾች ትክክለኛ መረጃ ኖሯቸው ለሚገባቸው ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርሱ ከኮሚሽኑ ጋር አብረው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደብረ ብርሃን ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው በመመለሳቸው መጠለያዎቹ ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውን ኮሚሽኑ ለሬድዮ ጣቢያው አስታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ያለንበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው " - በሳዑዲ የታሰሩ ዜጎች በሳዑዲ እስር ቤት እየተሰቃዩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግፋቸውን ህዝብ እንዲሰማላቸውና የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተማፀኑ። ለበርካታ ወራት በአሰቃቂ ሁኔታ በእስር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውኑ ያሉበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን ገልፀዋል። በእስር ቤቱ በርካታ ቁጥር ያለው እስረኛ እንደሚገኝ የገለፁት ታሳሪዎቹ ከነዚህ ታሳሪዎች…
#Update

በሳዑዲ አረቢያ በስቃይ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ጉዳይ በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ ሰጥቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል ፥ ሚኒስቴሩ ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር በእስር ላይ ያሉ ዜጎችን ወደ አገራቸው ሲመልስ መቆየቱን አስታውቋል፡፡

አምባሳደር ዲና ፥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው የመመለሱ ሂደት አለመቆሙን ጠቁመው የተወሰነ መቀዛቀዝ ግን ነበር ብለዋል፡፡

ይሁንና እንደከዚህ በፊቱ በአስቸጋሪ ህይወት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በቅርቡ በሳዑዲ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው የመመለሱ ዘመቻ ይጀመራል ሲሉ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ እየተሰቃዩ ያሉ ዜጎች ያሉበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን በመግለፅ በእስር ቤት የሚደርስባቸውን ግፍ ህዝብ እንዲሰማላቸው እና የሚመለከተው አካልም መፍትሄ እንዲሰጣቸው መማፀናቸው አይዘነጋም https://t.iss.one/tikvahethiopia/66047?single

@tikvahethiopia