TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ?

ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል።

ምክር ቤቱ በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ረቀቂ የውሣኔ ሀሳብ ቀርቦለታል።

ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጋር በጥምረት ያደረጉት ምርመራ ውጤትም መነሻ አድርጎ ተጨማሪ ምርመራ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን እንዲሰማራ ይጠይቃል።

ዓለም አቀፍ መርማሪ ቡድኑ የ1 ዓመት ቆይታ እንዲኖረው የሚጠይቅ ሲሆን የሚላከው ቡድን ከሚያደርገው ምርመራ በተጨማሪ የሽግግር ፍትህ ተግባራዊ የሚያደርግበትን፣ ዕርቅና ተጠያቂነት የሚሰፍንበትን እንዲሁም ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸው ማገገም እንዲችሉ ምክረ ሃሳብ እና የቴክኒክ ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት እንዲኖረው ይጠይቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ? ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል። ምክር ቤቱ በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ረቀቂ የውሣኔ ሀሳብ…
" ኢትዮጵያ 🇪🇹 አትቀበለውም "

በነገው የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ኢትዮጵያ እንደማትቀበልና ተፈፃሚ እንደማይሆን አሳውቃለች።

ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ እንዲካሄድ የተጠራው ልዩ ስብሰባ የሚካሄድበትን ሥነ ሥርዓት አስመልክቶ የም/ ቤቱ ቢሮ ትላንት ውይይት አካሂዶ ነበር።

በውይይቱ ወቅት በተመድ የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ አምባሳደር ማሕሌት ኃይሉ ተገኝተው የኢትዮጵያ መንግሥትን አቋም በግልጽ አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ላይ የተጠራው ልዩ ስብሰባ የምክር ቤቱን የአሠራር ደንብ ያልተከተለና የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትን ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ለፖለቲካዊ ፍላጎቶች መጠቀሚያ የሚያደርግ እንዲሁም፣ ምክር ቤቱ አባል አገሮች ላይ መድሎ እንዲፈጽምና በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያዩ አሠራሮችን እንዲከተል በማድረግ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚያረክስ እንደሆነ ተናግረዋል።

አባል አገሮቹ ይህን ያልተገባ አሠራር እና አንዳንድ አገሮች የሰብዓዊ መብትን ሽፋን በማድረግ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን በምክር ቤቱ በኩል ለማስፈጸም የሚያደርጉትን ጥረት በማውገዝ የምክር ቤቱ ተቋማዊ መርህዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

" በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያን አስመልክቶ የተጠራውን አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እና የዚህን ስብሰባ ውጤቶችን አይቀበልም " ብለዋል።

" በመሆኑም የተጠራቅ ልዩ ስብሰባ እና ምክር ቤቱ በዚህ ስብሰባ ውሳኔ እንዲሰጥበት ተብሎ የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ጋር በቀጥታ የሚጣረስ በመሆኑ ስብሰባውም ሆነ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡ እንዲሰረዙ እንጠይቃል " ሲሉ አምባሳደር ማህሌት ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ? ከትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል። ምክር ቤቱ በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ረቀቂ የውሣኔ ሀሳብ…
" በጥምረት የተካሄደውን ምርመራ እውቅና መንፈግ ነው " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ፕሬዚዳንት ናዛት ካን፣ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት ግልጽ ደብዳቤ ፅፏል።

ኢሰመኮ በጻፈው ደብዳቤ፥ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል እስከ ፈረንጆቹ ሕዳር 3 ቀን 2021 ድረስ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በሌላ አካል በድጋሚ እንዲጣራ ማድረግ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እና በኢትጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጥምረት የተካሄደውን ምርመራ እውቅና መንፈግ ነው ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ምርመራ ተደርጎ በሪፖርት የቀረበውን ጉዳት በሌላ አካል ከማስደገምና ሂደቱን ከማጓተት፣ ቀደም ብሎ በወጣው የምርመራ ሪፖርት መሰረት ተጎጂዎች እንዲያገግሙ፣ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ እንዲሁም እንዲካሱ ብሎም ወንጀል የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ መሠራት ነበረበት ብሏል።

ኮሚሽኑ ሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እንደገና ይጣራ ከተባለ አጥፊዎቹ አካላት የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመካድና እና ኮሚሽኑ የሰራውን ምርመራ ለማጣጣል ብሎም የኮሚሽኑን ተግባር ዝቅ የሚያደርግ ይሆናል ሲል ስጋቱን ገልጿል።

ሙሉ ደብዳቤው በዚህ ተያይዟል : ehrc.org/the-commission-calls-on-the-human-rights-council-to-support-the-implementation-of-the-joint-investigation-recommendations-and-to-encourage-ongoing-independent-investigations-in-ethiopia/

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 9 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,503 የላብራቶሪ ምርመራ 542 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 148 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Afar

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ እና የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ የተመራ ቡድን በአፋር ክልል ጉብኝት አድርጓል።

ዶ/ር ካትሪን ሶዚ ከአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይታቸው የነበረው በክልሉ ስላለው ሰብአዊ ሁኔታና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አጋሮቹ ላለው የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ነው።

በተጨማሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ የመሩት ቡድን ከአፋር ክልል ህብረተሰቡ መሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ በአፋር ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሰብዓዊ እርዳታ በማስፋት ዙሪያ እና ወደ ትግራይ ክልል ቀጣይነት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ያለመ ነው።

ዶ/ር ካትሪን ሶዚ በአፋር ጉብኝታቸው ከመሩት ቡድን ጋር በመሆን በአፋር የተፈናቀሉ ዜጎችን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አጋሮቹ በግጭት የተጎዱ ሰዎች ሰብአዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

እንዲሁም ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ያለውን ቅንጅትና አጋርነት ለማጠናከር በአፋር ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያ በነገው እለት ይፋ አደርጋለሁ ማለቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ካለንበት የታህሳስ ወር ጀምሮ የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ይታወቃል። @tikvahethiopia
#Update

የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ።

በአዲስ አበባ በሚኒባሶች እና ታክሲዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህ መሰረትም ፦ በሚኒባስ (ቅጥቅጥ ወይም ሃይገር ባስ) የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በሚኒባስ በኪሎሜትር ከ40 ሳንቲም ወደ 45 ሳንቲም ከፍ የተደረገ ሲሆን÷ በታክሲ ደግሞ በኪሎሜትር ከ90 ሳንቲም ወደ 1 ብር ከፍ ብሏል፡፡

በሚኒባሶች የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛው 1 ብር ሲሆን÷ ከፍተኛው ደግሞ 2 ብር ሆኗል፡፡

በታክሲ ላይ የተደረገው ጭማሪ ዝቅተኛ 50 ሳንቲም ሲሆን ÷ከፍተኛው ጭማሪ 3 ብር ከ50 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጭማሪው የኪሎሜትር ርቀትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የታሪፍ ጭማሪው በብዙሃን ትራንስፖርት ላይ እንዳልተደረገ የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በመግለጫው ላይ ማሳወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Dessie

" የህክምና ቁሳቁሶቹን ባለሞያዎች መጥተው ነው የፈቷቸው " - የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

በአማራ ክልል እጅግ ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው ሆስፒታሎች መካከል የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዋነኝነት ይጠቀሳል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ ሆስፒታሉ 80 ዓመቱ ሲሆን የደረሰበት ጉዳት 80 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ከ0 እንዲጀምር እንደሚያደርገው ነው የምንቆጥረው ብለዋል።

ሆስፒታሉ በህወሓት ኃይሎች የመድሃኒት ቤቱ አንድም ሳይተርፍ ተዘርፏል/ወድሟል፣ የላብራቶሪ እቃዎች ተዘርፈዋል፣ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የኦክሲጅን ማምረቻው ተዘርፎ ተወስዷል የተረፈው አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርጎ ወድሟል፤ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የካንሰር ህክምና መስጫ ቁሳቁሶች ተዘርፎ ተወስዷል።

ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ዝርፊያው በተጠና መልኩ እንደተካሄደና ባለሞያዎች መጥተው እንደፈቷቸው አሳውቀዋል።

ሆስፒታሉ አሁን ላይ በተወሰነ መልኩ ወደአገልግሎት የተመለሰ ሲሆን የወሊድ፣ ድንገተኛ አገልግሎት እና የተመላላሽ ታካሚዎችን እያስተናገደ ሲሆን ሆስፒታሉ ታካሚዎችን እያስተናገደ ያለው ቁሳቁስ ስላለው ሳይሆን ባለሞያዎች ባላቸው ሞያ ብቻ አገልግሎት መስጠት ስላለባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር ሃይማኖት ገለፃ በሆስፒታሉ በወር በአማካይ 800 እናቶች በሆስፒታሉ ሲወልዱ እንደነበር አስታውሰው አገልግሎት በመቋረጡ በርካቶች ለጉዳት መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአማራ ክልል ምስራቅ አማራ፣ አፋር ክልል እንዲሁም የትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይገለገሉበት እንደነበር የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ለሬድዮ ጣብያው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#MoH

የጤና ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ ርብርብር እየተደረገ ነው።

በግጭት ምክንያት የወደሙና የተጎዱ ጤና ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስ እና የጤና አገልግሎት ለማስጀመር የአዲስ አበባ ጤና ቢሮና የፌዴራል ሆስፒታሎችን ከወደሙ ሆስፒታሎች ጋር በማስተሳሰር ድጋፍ እንዲያደርጉ ሰፊ ስራ መጀመሩን ከጤና ሚኒስቴር ተሰምቷል።

በቀጣይ ሌሎች ክልሎች እና ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በማስተባበር የድጋፍ ስራው በስፋት እንዲቀጥል ይደረጋል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት:-

• ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌንየም ሜዲካል ኮሌጅ 👉 ደሴ ሆስፒታልን፤
• ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 👉 ከልዋን ሆስፒታልና ቦሩ ሜዳ ሆስፒታልን፤
• አቤት ሆስፒታል 👉 ባቲ ሆስፒታልን፤
• የካቲት 12 ሆስፒታል 👉 ወረ ኢሉ ሆስፒታን፤
• ምኒሊክ ሆስፒታል 👉 መሃል ሜዳ ሆስፒታልን፤
• ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 👉 ከሚሴ ሆስፒታልን፤
• ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል 👉 ሀይቅ ሆስፒታልን፤
• ራስ ደስታ ሆስፒታል 👉 ደብረ ሲና ሆስፒታልን፤
• አለርት ሆስፒታል 👉 ኮምቦልቻ ሆስፒታልን፤
• ዘውዲቱ ሆስፒታል 👉 ደጎሎ ሆስፒታልን፤
• ጋንዲ ሆስፒታል 👉 ሞላሌ ሆስፒታልን፤
• አማኑኤል ሆስፒታል የአእምሮ ጤናና የስነልቦና ማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ 👉 ለሁሉም ሆስፒታሎች ድጋፍ ለመስጠት ትስስር በመፍጠር ወደ ስራ ገብተዋል።

ጤና ሚኒስቴር የአዲስ አበባ እና ፌዴራል ሆስፒታሎች እያደረጉ ስላሉት ርብርብ ምስጋና አቅርቧል።

ሆስፒታሎቹ በአፋጣኝ ስራ ለማስጀመር ከክልሉ እና ከጤና ሚንስቴር ጋር እየሰሩ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት ለመመለስ አሁንም ከፍተኛ መዋለ ነዋይና ድጋፍ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የሚመለከተው አካል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
" ለ11 ቀናት መሳቅ አይቻልም ፤ ወደ መጠጥ ቤት መሄድ እና መጠጥ መጠጣትም አይቻልም " - ሰሜን ኮሪያ

የቀድሞውን የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኢልን 10ኛ የሙት ዓመት በማስመልከት በሀገሪቱ ለ11 ቀናት መሳቅ ተከለከለ፡፡

ኪም ጆንግ ኢል ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በአውሮፓውያኑ 2011 ሲሆን ዘንድሮ 10 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡

የቀድሞውን መሪ 10ኛ የሙት ዓመት አስመልክቶም በሀገሪቱ መሳቅና መጠጥ መጠጣት መከልከሉን ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ሰሜን ኮሪያውያን ወደ ግሮሰሪ መሄድ እንደማይችሉ የተነገራቸውም ሲሆን በመታሰቢያ የዚህ የሀዘን ቀናቱ ውስጥ ቤተሰቡ የሞተበት ሰው ጮክ ብሎ ማልቀስ እንደማይችል ሰሜን ኮሪያ አስጠንቅቃለች፡፡

የልደት በዓላቸው በ11ዱ የሀዘን ቀናት ውስጥ የሆነባቸው ግለሰቦች ይህንን ማድረግ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።

ዛሬ አርብ ከደቂቃዎች በፊት በፒዮንግያንግ የነበረው የቢዝነስና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ለ5 ያል ደቂቃዎች ቆሞ የኢል 10ኛ ሙት ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በ69 ዓመታቸው በፈረንጆቹ ታህሳስ 17 ቀን 2011 በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ መሪ ሀገራቸውን ለ17 ዓመታት መርተዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ዴይሊ ሜይል

@tikvahethiopia