TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ያደርገዋል የተባለው ስብሰባ የተቋሙን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው " - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በመጪው አርብ ያደርገዋል የተባለው ስብሰባ የተቋሙን ገለልተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡ በምክር ቤቱ የተወከሉ በርካታ የአፍሪካ አገራት እያሉ በስብሰባው የሚካፈል…
" በዚህ ሳምንት የሚያሸብሩትን ነገር ትተውታል " - አቶ ከበደ ዴሲሳ

መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ዜጎቻቸው ከሀገር ለቀው እንዲወጡ ሲያወጡት የነበረው ማስጠንቀቂያ / ማስፈራሪያ በዚህ ሳምንት መቀነሱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ተናገረዋል

አቶ ከበደ፥ "መቀመጫቸውን በአ/አ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤንባሲዎች ከማስጠንቀቂያ አልፎ ማስፈራሪያ ሲያስተላልፉ ነበር" ብለዋል።

ከነዚህ ሀገራት ኤምባሲዎች መካከል በዋነኝነት የአሜሪካ ኤምባሲ ሲሆን ለ1 ወር ሙሉ በየቀኑ አንዳንዴ በቀን 2 እና 3 ማስጠንቀቂያ ሲያወጣ ነበር።

አቶ ከበደ፤ " አዲስ አበባ ሰላሟ የሚያሰጋ ነው የሚል የተለያዩ ተጨባጭ ያልሆኑ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ነበር ነገር ግን በዚህ ሳምንት ቀንሷል " ብለዋል።

" አሜሪካ በቀን ሁለቴና ሶስቴ ኢትዮጵያ ሰላም የላትም በሚል ዜጎቿ እንዲወጡ ጥሪ ስታቀርብ ነበር፤ ሌሎችም ኤምባሲዎች መስሏቸው / ሆን ብለው ያንን ሲከተሉ ነበር ፤ በተደጋጋሚ ተቋማት ዜጎች አ/አ ለቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር " ያሉት አቶ ከበደ፥ " ህወሓት አዲስ አበባ እገባለሁ ብሎ የገባላቸውን ቃለ ሳይፈፅም ወደኃላ ስለተመለሰ ይመስላል በዚህ ሳምንት የሚያሸብሩትን ነገር ትተውታል " ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ አቋማቸውን ቀይረዋል ለማለት የሚያስችል ነገር ባይኖርም ቢያንስ እውነታውን ተገንዝበው ከድርጊታቸው በመቆጠባቸው እውቅና እንሰጣለን ብለዋል።

ከሁሉም በላይ የአንዳንድ ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ለቃችሁ ውጡ ሲባሉ ኢትዮጵያ ላይ እምነት አሳድረውና ለኢትዮጵያ ባላቸው ፍቅር በእንቢታ ጥሪውን ውድቅ አድርገው ኢትዮጵያ ውስጥ በመቆየታቸው አሁንም ኑሯቸውን ስራቸውን በመቀጠላቸው ሊመሰገኑ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#TechZone

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599  ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrHirutKassaw የሻደይ፤ አሸንድየ እና አሸንዳ በዓላት በማይዳሰሱ ቅርስነት የመመዝገብ ጉዳይ በሚቀጥለው አመት በዩኔስኮ ድምጽ እንደሚሰጥበትና እንደሚመዘገቡ እንደሚጠበቅ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ለአልዓይን ተናግርዋል። የዘንድሮ አሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድየ በዓላት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ እየተከበሩ አይደለም። @tikvahethiopiaBot…
#UNESCO

በትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚገኙ ባህላዊ የሴቶች ጨዋታ የሆኑት አሸንዳ/ ሻደይ/ አሸንድዬ/ አይኒዋሪ/ ማርያ/ ሶለል በሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ምዝገባ ላይ UNESCO ዛሬ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ቢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ታሪካዊ ትውፊቶቹ በቅርስነት እንዲመዘገቡ ለተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከአመታት በፊት ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ ፓሪስ በሚደረገው ዝግጅት እልባት ያገኛል።

* Update

በኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለሥልጣን ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ ግርማ ለምዝገባው የሚያስፈልገውን መስፈርት ለማሟላት በገምጋሚ አካላት በኩል ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ምላሽና ማብራሪያ ቢቀርብም በዚህ ዓመት ለሚሰጠው ውሳኔ ሳይደርስ መቅረቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሀርቡ ከተማ ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመልሶ ተገናኝቷል። በሀርቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተመለሰው ዛሬ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ነው። የጃማ እና ወረኢሉ ከተሞችን ኃይል ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ የጥገና ስራ የተጠናቀቀ መሆኑን ተነግሯል። #EEU @tikvahethiopia
#Update

ጃማ፣ ወረኢሉና ኩታበር ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል አገኝተዋል።

የሀይቅና ቢስቲማ ከተሞች የዝቅተኛና የመካከለኛ መስመር ጥገና እደተጠናቀቀ አገልግሎት እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ከ850 ሺህ በላይ የኩፍኝ መከላከያ ክትባቶች ባለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መግባቱን ዩኒሴፍ ዛሬ አሳውቋል።

ዩኒሴፍ ክትባቱ ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መከተባቸውን ለማረጋገጥ በጣም ወሳኝ እርምጃ ነው ብሏል።

የኩፍኝ በሽታ በጣም ተላላፊ ነገር ግን በክትባት በቀላሉ መከላከል ይቻላል።

#UNICEF

@tikvahethiopia
" ... በድንገት የተላለፈው ውሳኔ ዜጎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከማምጣት በቀር ለሰላሙ ምንም አማራጭ አይሰጥም " - ካረን ባስ

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ካረን ባስ የአፍሪካ ሃገራት በአሜሪካ ገበያ እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያዘውን የአጎዋ ስምምነት የባይደን አስተዳደር እኤአ ከጥር 1 ቀን 2022 ጀምሮ እንዲቋረጥ ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም የሚፈልጉ መሆኑን ባወጡት መግለጫ አስታውቁ፡፡

በተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ካረን ባስ፣ በመግለጫቸው እኤአ ህዳር ሁለት የተላለፈው የአጎዋ እገዳ ውሳኔ የኢትዮጵያ ህዝብና መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሱ አሜሪካውያን ደክመው ያመጡትን የምጣኔ ሀብት እድገት ይቀለብሳል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ለችግር ተጋላጭ የሆኑትን የህብረተሰ ክፍሎች ችግሮች ያባብሳል በማለት አክለዋል፡፡

ስለሆነም የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ወገኖች ይህን ግጭት ለማስቆም ተገቢውን እምርጃ ሁሉ እንዲወስዱ ፣ የሰብአዊ እርዳታን ለሚሹ ሰዎች እርዳታ እንዲለግሱ፣ ሰላምን ለማምጣት የሚያደርጉትን ድርድር ለመቀጠል በቂ ጊዜ እንዲያገኙ፣ የባይደን አስተዳደር በቂ ጊዜ እንዲሰጣቸው አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

ካረን ባስ “እኤአ ጥር 1 2022 ተግባራዊ እንዲደረግ በድንገት የተላለፈው ውሳኔ ዜጎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከማምጣት በቀር ለሰላሙ ምንም አማራጭ አይሰጥም” ሲሉ ማሳሰባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopoa
መኪና የተሸለሙት መምህር...

የነቀምቴ ከተማ የቀድሞ ተማሪዎች የሒሳብ መምህራቸው ለነበሩት ግለሰብ 'ለእኛ ትውልድ ለዋልከው ውለታ' በሚል በ750 ሺ ብር መኪና ገዝተው መሸለማቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ የሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎች ለሒሳብ መምህራቸው ለነበሩት አቤል ቡልቻ መኪና ገዝተው በስጦታ ማበርከት የፈለጉት ያላቸውን ክብርና ፍቅር ከመግለጽ ባለፈ፣ የመምህራቸውን ውለታ በቋሚነት ለመዘከር በመፈለጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።

100 የሚሆኑት የቀድሞ ተማሪዎች የመምህራቸውን ውለታ አስታውሰው፣ ስጦታ በመስጠት ሲያመሰግኑ የሌሎች ተማሪዎች ሞራል በማነሳሳት ረገድ ትልቅ ድርሻ መወጣቱን ሽልማቱን የሰሙ ግለሰቦች ተናግረዋል።

መምህር አቤል በነቀምቴ የተለያዩ ት/ቤቶች አስተምረዋል፤ በአሁኑ ጊዜ በአ/አ በአንድ የግል ት/ቤት ውስጥ እያስተማሩ ነው።

ሽልማቱን ያልጠበቁት መሆኑን የተነጋሩት መምህሩ ፥ "እኔ ከዚህ ልጆቹ ካበረከቱልኝ ስጦታ በላይ፣ ያስተማርኳቸው ገሚሱ ዶ/ር ሆኖ፣ የተወሰኑት ፓይለት እንደዚሁም ኢንጂነር ሆነው ማየቱ ይበልጥ ያስደስተኛል። ትውልድን በትምህርት ማብቃትን የመሰለ ደስ የሚያሰኝ ነገር የለም" ብለዋል።

መምህሩ ከዚህ በፊት መኪና እንዳልነበራቸው ብቻ ሳይሆን ይኖረኛል ብለው አስበው እንደማያውቁ ተናግረዋል።

"በመምህር ደሞዝ መኪና መግዛት የማይታሰብ ስለሆነ መንጃ ፈቃድ ስለማውጣትም አስቤ አላውቅም።"

መምህር አቤል ቡልቻ ተማሪ በነበሩበት ጊዜ የአስተማሪና የተማሪ ግንኙነት ጥሩ እንዳልነበረ በማስታወስ እሳቸው ግን "የማስተምራቸውን ልጆች እንደ እኩያ፣ እንደወንድምና እንደአባት እቀርባቸዋለሁ። ተማሪውን ስለቀረብከው ተገቢውን ክብር አይነፍግህም፤ ያከብርሃል እንጂ" ሲሉ ከተማሪዎችቻው ጋር ስላላቸው ቅርበት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#EACC

የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ትላንት ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ አድርጎ ነበር።

ስብሰባውን ተከትሎ ሴንተር ጂም ኢንሆፍ ለካውንስሉ በላኩት መረጃ መሰረት ኢትዮጵያን በጅኖሳይድ ለመጠየቅ በሴኔት ቢሮ የታሰበው HR 4350 ውስጥ አንቀፅ 6464 ከረቂቅ Determination of potential Genocide or crimes Against Humanity የሚለው ሙሉ በሙሉ ህጉ መሰረዙን ይፋ አድረገዋል።

መረጃውን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሙሉ ፦

የአ/አ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ለማቀላጠፍ እና የደንበኞቹን የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለማዘመን ሁሉንም የቆጣሪ አይነቶች በአዲስ መልኩ ለመመዝገብ የተቋሙ ባለሞያዎች መድቦ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ያከናውናል፡፡

በመሆኑም ደንበኞች መረጃውን ለማሰብሰብ ለሚላኩ የተቋሙ ባለሙያዎች ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉና የቆጣሪያቸው ሙሉ መረጃ በአግባቡ እንዲያስመዘግቡ አገልግሎቱ ጠይቋል፡፡

የሚላኩት ባለሙያዎች የተቋሙን የመታወቂያ ባጅና አንፀባራቂ አርማ ያለው የደንብ ልብስ የሚለብሱ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፌልትማን የግብፅ፣ ቱርክ እና የUAE ጉዞ ፦ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፣ ቱርክ እና ግብፅ እንደሚያማሩ ተሰምቷል። የጉዟቸው ዓላማ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመምከር ነው። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤህ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራስ በሰጡት መግለጫ ፌልትማን ወደ ሦስቱ አገራት ጉዟቸውን የሚያደርጉት ከዛሬ ሐሙስ ህዳር…
#Update

ፌልትማን ታህሳስ 4 እና 5 ቱርክ ነበሩ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ታህሳስ 4 እና 5 ቀን 2014 ዓ/ም ቱርክ፣ አንካራን ነበሩ።

በቆይታቸው ከቱርክ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ፌልትማን የጋራ ግቦቻችን በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ነው ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

ፌልትማን በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ አፅንኦት በመስጠት የመስራት ፍላጎት ያላቸውን ሀገራት በሙሉ ሀገራቸው አሜሪካ በደስታ ትቀበላለች ብለዋል።

ህዳር 29 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ ከህዳር 30 ጀምሮ ፌልትማን ወደ ግብፅ ፣ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ እና ቱርክ እንደሚጓዙ አሳውቆ ነበር፤ ከዚህ የሚኒስቴሩ መግለጫ በኃላ በይፋ የተገኘው መረጃ የቱርክ ጉዞ ሲሆን ፌልትማን ወደ ግብፅ እና ዩኤኢ ስለመሄዳቸው ፣ ሄደውም ከሆነ ስለምን እንደተወያዩ ይፋ የሆነ መረጃ መግኘት አልተቻለም።

@tikvahethiopia
Turkey 🤝 Africa

" ለጋራ እድገት እና ብልጽግና የጎለበተ ወዳጅነት "

3ኛው የቱርክ - አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ነገ በቱርክ ኢስታንቡል ይጀመራል።

ለዚሁ ጉባኤ የተለያዩ ሀገራት ባለስልጣናት ቱርክ እየገቡ ይገኛሉ። በዚህ ጉባኤ የ39 ሃገራት ሚንስትሮች እና 13 ፕሬዚዳንቶች ለመሳተፍ ከወዲሁ ማረጋገጫ ልከዋል።

" ለጋራ እድገት እና ብልጽግና የጎለበተ ወዳጅነት " በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የሁለት ቀን ጉባኤ ቅዳሜ ዕለት የቱርክ ፕሬዜድሬቺፕ ጣይብ ኤርዶሃን ንግግር ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ለዚሁ ጉባኤ ቱርክ ከሚገኙት የኮትዲቯር (ካንዲ ካማራ) ፣ ቡሩንዲ (አምባሳደር አልበርት ሺንጊሮ) እና ዚምባብዌ (ፍሬድሪክ ሻቫ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

@tikvahethiopia