TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianFederalPolice

መነሻቸውን ብራዚል ሳኦፖሎ መዳረሻቸውን ደግሞ ዱባይና ናይጄሪያ በማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩ የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ 🇪🇹 ፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ 2 ናይጄሪያዊያንና አንዲት ብራዚላዊት ሲሆኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገባቸው ፍተሻ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ አደገኛ ዕፁን በውስጣዊ የሻንጣ አካል በመደበቅና ውጠው በሆዳቸው በመያዝ ለማሳለፍ ሙከራ ቢያደርጉም የፌደራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት የተጠናከረ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት 3 የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ መካከል በብራዚላዊቷ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከ13 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 666 ጥቅል ፍሬና በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ከ17 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 11 እሽግ ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በሻንጣዋ ይዛ መገኘቷን ተረጋግጧል።

ሁለቱ ናይጄሪያዊያን አደገኛ ዕፁን በሆዳቸው ይዘው ሊያዘዋውሩ እንደሚችሉ በመጠራጠር በፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል በተደረገላቸው የኤክስ ሬይ ምርመራ የተገኘባቸው ሲሆን 1,650 ግራም የሚመዝን 83 ፍሬ ኮኬይን ከሆዳቸው እንዲወጣ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአሁኑ ወቅት ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡

@tikvahethiopia
የቤህነን ታጣቂ ቡድን መሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ የቤህነን ታጣቂ ቡድን መሪ የሆነው ህድር መሐመድ አሊ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ኢፕድ ዘግቧል።

ግለሰቡ በመንጌ ወረዳ፣ ጎልሞሶ ቀበሌ ነው በቁጥጥር ሥር መዋሉ የተገለፀው።

የታጣቂ ቡድኑ መሪ በቁጥጥር ሥር በዋለ ጊዜ ፦
- 1 ክላሽ
- 2 ካርታ
- 60 የክላሽ ጥይት
- 5 የጭስ ቦምብ
- 1 ሞቶሮላ ሬዲዮ መገናኛ
- የሱዳን ወታደራዊ ልብስ አብሮ ተይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በህወሓት ተይዘው የነበሩ ተጨማሪ ቦታዎች ነፃ ማውጣቱ ተገልጿል።

የፀጥታ ኃይሎች ጥምረቱ ፦
- የመሐል ሜዳ፣
- ጨፋ ሮቢት፣
- ሐርቡና መኮይ ከተሞችና አካባቢውን ነጻ እንዳወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።

የኢትዮጵየ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " ጥምር የጸጥታ ኃይሎቹ በጥልቀት ገብተው በየቦታው የተበተነውን የአሸባሪውን ጀሌ በመልቀም ላይ ናቸው " ብሏል።

አክሎም ፥ " በጥምር የጸጥታ ኃይሎቹ የተመታው አሸባሪ ኃይል ዘርፎና አውድሞ፣ መሣሪያውንም ይዞ እንዳይወጣ የየአካባቢው ሕዝብ ተደራጅቶ መንገድ በመዝጋት ፣ የአሸባሪውን ጀሌዎች በመማረክ ፣ እምቢ ባሉትም ላይ ርምጃ በመውሰድ የተለመደ ጀግንነቱን እንዲደግም " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,300 የላብራቶሪ ምርመራ 143 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 217 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር ፦ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ። ዝግ የሚሆኑት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ነው። #ምክንያት ፦ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው። ት/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት…
የቢቢሲ (ወርልድ) ዘገባ ?

ትላንት የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ለአንድ ሳምንት ማለትም ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚዘጉ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

ት/ ቤት የሚዘጋው ያልተሰበሰብ ሰብል ለመሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት ለማካሄድ መሆኑ በግልፅ ተነግሯል።

ይህንን አንዳንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የተለየ ርዕስ ሰጥተውት ሲዘግቡ ታይተዋል።

ከነዚህ ሚዲያዎች ዋነኛው BBC World) /ቢቢሲ - ዋርልድ / ሲሆን በተረጋገጠ 33.7 ሚሊዮን ተከታዮች ባሉት ይፋዊ የትዊተር ገፁ ላይ " ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች " ሲል ዘግቧል።

በተያያዘው ሊንክ ተገብቶ ሙሉ ዜናውን ለተመለከተው ሰው ግን ዝርዝር ዘገባው እና ለዜናው የተሰጠው ርዕስ የሚገናኝ አይደለም።

በተጨማሪ P.M News የተባለ የናይጄሪያ ጋዜጣም የትምህርት ቤቶችን መዘጋት " ኢትዮጵያ ለጦርነት ለማንቀሳቀስ ስትል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ዘጋች " የሚል ርዕስ በመስጠት አቅርቧል።

የዜናውን ዝርዝር ገብቶ ለመለከተው ከተሰጠው ርእስ ጋር የሚገናኝ አይደለም።

@tikvahethiopia
#HappeningNow

በቴፒ ከተማ የእርቀ ሠላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በደ/ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞን በተለይ በየኪ ወረዳ እና ቴፒ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር በእርቀ ሠላም ኮንፈረንስ ለመፍታት ያለመው የእርቅ እና የሰላም መድረክ በቴፒ ከተማ በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#UNICEF

UNICEF በደብረ ብርሃን ከተማ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ለአዳዲስ ተፈናቃዮች ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ህይወት አድን የሆነ የተመጣጠነ ምግብና ውሃ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦቶችን እና አገልግሎቶችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ UNICEF አሳውቋል።

UNICEF የህጻናት ህይወት፣ ጤና፣ ደህንነት እና የወደፊት ህይወት ንፁህ ውሃ እና ንፅህና ሳያገኙ ሲቀሩ አደጋ ላይ ይወድቃል ብሏል።

@tikvahethiopia
#Borana #Dawa

የIOM WASH ቡድን በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ለህብረተሰቡ የውሃ ማጓጓዝ ስራ መስራት መጀመሩን ገልጿል።

IOM በዚህ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በከባድ ድርቅ ለተጎዱ እና አስተማማኝ የውሃ ምንጭ ለሌላቸው ማህበረሰቦች ውሃ የማድረስ ስራ እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

ይህንን ተግባር ለማከናወን የጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ልግስና ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና በሶማሊ ክልል በዳዋ ዞን በከፋ ድርቅ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ሰዎችም በውሃ እጥረት ለከፋ ችግር መጋለጣቸው መገለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አንድ_ሚሊዮን_ዳያስፖራ ወደ ሀገር እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል። አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ሰሜን አሜሪካና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በራሱ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚፈለገውን…
" የትኬት ሽያጭ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቅ ይችላል " - አምባሳደር ፍፁም አረጋ

1 ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደሀገር ቤት በታኅሣሥ 29 ቀን 2014 እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት አገር ወዳድ ወገኖች የአውሮፕላን ትኬት እየገዙ መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አሳውቀዋል።

አምባሳደር ፍፁም ፥ የትኬት ሽያጭ በአጭር ጊዜ ሊጠናቀቅ እንደሚችል በሎስ አንጀለስ ላይ ተገኝተው መረዳት እንደቻሉ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

"አየር መንገዳችን ፣ ሆቴሎችና ሌሎችም የመስተንግዶ ተቋማት ጥሪውን የሚመጥን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ይታየናል" ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በቁጥጥር ስር መዋሏን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " የጋሸናን ግንባር ምሽጎችን በመሰባበር የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ…
" እስካሁን ባደረግነው ማጣራት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስን ጨምሮ ሁሉም አገልጋይ መነኮሳት ጉዳት አልደረሰባቸውም " - ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው

የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጥቃት እንዳልደረሰበት ገልጿል።

ህወሓት ካሳለፍነው ነሀሴ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ላሊበላ ከተማን ተቆጣጥሮ ቆይቶ ነበር፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ፋኖ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በወሰዱት መልሶ ማጥቃት አካባቢውን ከሶስት ከሚልቁ ወራት በኋላ መልሰው ተቆጣጥረዋል።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ቅርሶቹ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ከአል ዓይን ኒውስ የተጠየቁት የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ፥ ላሊበላ ከተማን ጨምሮ አካባቢው ከህወሃት ወረራ ነጻ መሆኑን ተከትሎ የቅርሱ ደህንነትን በተዘዋዋሪ ማጣራታቸውን ተናግረዋል፡፡

" እስካሁን ባደረግነው ማጣራት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስን ጨምሮ ሁሉም አገልጋይ መነኮሳት ጉዳት አልደረሰባቸውም " ብለዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በሚቀጥለው ሳምንት የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች እና አመራሮች ወደ ስፍራው እንደሚጓዙ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ገልጸዋል፡፡

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ ከ43 ዓመት በፊት ነበር በተመድ የሳይንስ ፣ የትምህርት እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) በዓለም የሚዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው፡፡

መረጃው ከአል ዓይን ኒውስ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia