TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ለሰላሙ ብቸኛው መፍትሄ ተኩስ አቁም እና ፖለቲካዊ ንግግር ነው " - ሙሳ ፋኪ መሀመት

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ በተረጋገጠ ይፋዊ በትዊተር ገፃቸው ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት ብቸኛው መፍትሄ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ማድረግ እና ፖለቲካዊ ንግግር መጀመር ነው ብለዋል።

ሙሳ ፋኪ ፥ " ግጭቱ በሚያሳዝን ሁኔታ ቀጥሏል " ያሉ ሲሆን በአፍሪቃ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ሁለቱን ወገኖች ለማሸማገል የጀመሩትን እንቅስቃሴ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አንድ_ሚሊዮን_ዳያስፖራ ወደ ሀገር እንዲገባ በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ሰሜን አሜሪካና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በራሱ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚፈለገውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትኬት ቅናሽ እንዲሁም ተጨማሪ የሻንጣ የኪሎ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና አየር መንገዱ የማይበርበትም ሥፍራ ቢኖር፣ ገበያውን ለማምጣት እንደሚሰራ ከአየር መንገዱ መስማቱል ሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚ ቀደምም ሆነ ወደፊትም ለልዩ ልዩ በዓልና ተመሳሳይ ወቅቶች የተለየ ቅናሽ እንዲሁም አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በሌላ አጭር መረጃ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ''ቢዝነስ ትራቭለርስ '' መጽሄት የሚያዘጋጀውን “የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች የአፍሪካ ምርጥ” አሸናፊ ሆኗል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ሊያገኝ የቻለው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያያዘ እየወሰዳቸው ያሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች ፣ ከጉዞ ትኬት ጋር በተገናኘ የሚሰጠው ፈጣን ምላሽ እንዲሁም በወረርሽኙ ወቅት ለተከሰቱ የጉዞ መስተጓጐሎች ለሰጠው የተቀላጠፈ የጉዞ ማስተካከያ አገልግሎት እና ተያያዥ መስፈርቶች በቢዝነስ መንገደኞች በመመረጡ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ነው።

አካል ጉዳተኞችን እንደተረጂ ማየት ትክክል አይደለም!

አካል ጉዳተኞችን በህክምና እንዴት ማስተካከል ወይም ማከም እንደሚቻል ብቻ ማሰብ ትክከለኛ አመለካከት አይደለም!

#ዓለም_አቀፍ_የአካል_ጉዳተኞች_ቀን ዘንድሮ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ29ኛ ጊዜ እና በዓለም ለ30ኛ ጊዜ “የአካል ጉዳተኞችን መሪነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ አካታች፣ ተደራሽ እና ዘላቂ ድህረ ኮቪድ-19 ዓለምን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ እየተከበረ ይገኛል።

#ጤናማቃላት #ኢሰመኮ #ሁሉንምያካተተ

@tikvahethiopia
#Sudan | የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የተባበሩት መንግሥታት (UN) የሽግግር መንግሥቱን እንዲደግፍ ጥሪ አቀረቡ።

ሌ/ጀነራል አል-ቡርሃን ጥያቄውን ያቀረቡት የተመድ የሱዳን ተወካይ የሆኑትን ቮልከር ፔርዝስ አግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ቮልከር ፔርዝስ ከአል-ቡርሃን ጋር መገናኘታቸውን በተረጋገጠ የትዊተር ገጻቸው የገለጹ ሲሆን፤ ምንም አንኳ ሱዳን ሕገ መንግሥታዊው ሥርዓት እንዲመለስ ብትስማም፤ ሌሎች ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮች መከናወን አለባቸው ብለዋል።

ጀነራል አል-ቡርሃን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት የሲቪል መንግሥት መሪ ጠ/ሚ አብደላ ሐምዶክ ጋር አብሮ ለመሥራት እና ምርጫ እስኪከናወን ድረስ አብደላ ሐምዶክ ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት በ18 ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲያካሂድ ጫና እየተደረገበት መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#SituationReport | #Amhara #Tigray #Afar

#UN_OCHA በአፋር ፣ ትግራይ እና አማራ ክልል ስላለው ሁኔታ እና እየተደረገ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴ ሪፖርት አውጥቷል።

ዋና ዋና ነጥቦች ፦

- በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት 9.4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

- እኤአ ከህዳር 20 ጀምሮ ከትግራይ ምዕራብ ዞን ወደ ማይ-ፀብሪ፣ ሸራሮ እና ደደቢት ወረዳዎች በርካቶች ተፈናቅለው የገቡ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሽሬ በስተ ምዕራብ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደደቢት ብዙ ሺህ ሰዎች ደርሰዋል፤ አዲስ ተፈናቃዮች ፍሰት የቀጠለ በመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል።

- በትግራይ ክልል 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 400,000 ያህሉ በርሃብ መሰል ሁኔታ ላይ ያሉ ናቸው።

- በአፋር ክልል በዚህ ዙር በተደረገ ድጋፍ ከ86,000 በላይ ሰዎች ምግብ አግኝተዋል።

- በአማራ ክልል 3.7 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

- በአማራ ክልል በሰ/ወሎ፣ ዋግ ኽምራና ከፊል ደቡብ ወሎ እንዲሁም በአፋር ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ በተለይ በአኗኗር ፣ በገበያ መቋረጥ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ ባለመቻሉ አሳሳቢ ነው።

- በአማራ ክልል አዲስ ተፈናቃዮች አሁንም አሉ። በደብረ ብርሃን ከተማ ተፈናቃዮችን የሚያስተናግዱ የጋራ ቦታዎች ቁጥር ከስድስት ወደ 10 ከፍ ብሏል፣በተመሳሳይ በኮምቦልቻ ከ2 ወደ 17 ከፍ ብሏል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

@tikvahethiopoa
" 19 ሰዎች ሕክምና አጥተው ሕይወታቸው አልፏል " - ዶ/ር ብርሃኑ ዓለሙ

የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሽብርተኛው ህወሓት ባደረሰው ውድመት ምክንያት 19 ሰዎች ህክምና በማጣት ህይወታቸው ማለፉን ሪፖርት አደረገ።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ዓለሙ ለአሚኮ በሰጡት ቃል ሆስፒታሉ ከተመሰረተ ጀምሮ ያከማቻቸው የሕክምና መሳሪያዎች፣ መድኃኒቶች እና ሌሎች ግብዓቶች ወድመዋል።

በሆስፒታሉ ክትትል ላይ የነበሩ 19 ሰዎች ሕክምና አጥተው ሕይወታቸው አልፏል።

በህክምና እጦት ህይወታቸው ያለፈው 7 ነፍሰጡር፣ 5 ሕጻናት እና 7 ተመላላሽ ታካሚዎች መሆናቸውን ዶ/ር ብርሃኑ አሳውቀዋል።

ህወሓት በሆስፒታሉ ንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑንን ዶ/ር ብርሃኑ ጨምረው ተናግረዋል።

አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ150,000 በላይ ሕዝብ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሆስፒታል መሆኑን ከአሚኮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፦

ከሐምሌ 5/2013 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጠው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል የብድር ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ብቻ ከነገ ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መሰጠት ይጀምራል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ታርጋዎችን ይመለከታል ፦

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አጠቃላይ ለልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች እና ክልሎች አገልግሎት የሚውል 18,027 ታርጋዎችን አምርቶ ለስርጭት ዝግጁ አድርጓል።

ከዚህ መካከል ለአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት የሚውል 4,225 ታርጋዎች ያካትታል።

ይህን አገልግሎት የሚሰጡ ክልሎችና ከተማ አሰተዳደሮች ለስርጭት የተዘጋጁትን ታርጋዎች በመውሰድ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ እንዲያደርሱ ተጠይቋል።

ተገልጋዮች ጥያቄያቸውን በማቅረብ እንዲገለገሉ ተብሏል።

(የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ነው ያለው አውድን ያላገናዘበ ፣ አሳሳች የዲፕሎማሲ፣ የሚዲያና የወትዋቾች ዘመቻ በቃ ሊባል ይገባል ሲል አሳውቋል።

ጉባኤው በመግለጫው ፥ ወቅታዊ ሀገራዊ ችግርን መነሻ በማድረግ አንዳንድ የምዕራቡ ሀገራት መንግስታት የያዙትን አቋም ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ አውግዟል።

ድርጊታቸው የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ታሳቢ ያላደረገ መሆኑንም አንስቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገራዊ የውስጥ ጉዳዮች የሚታዩትን ግልፅ ተፅእኖ እና ጣልቃ ገብነትን እንዲያቆሙና የኢትዮጵያ እውነት ድምፅ እንዲሰማ ጥሪ አቅርቧል።

የምዕራቡ መንግስታት ከተሳሳተ አቋማቸው እንዲመለሱም ጉባኤው ጠይቋል።

ጉባኤው የኢትዮጵያ ጉዳይ አስጨንቋቸው ብሄራዊ ጥቅሟ ሳይሸራረፍ ሀገራዊ ሉኣላዊነት እና ክብሯ እንዲጠበቅ ከጎኗ ለቆሙ ሁሉ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
" አዲስ አበባ #ሰላማዊ የአፍሪካ ከተማ ናት " - አውሪሊያ ካላብሮ

በኢትዮጵያ የተመድ (UN) የኢንዱስትሪ ልማት ቀጠናዊ ቢሮ ዳይሬክተሯ ሚስ አውሪሊያ ካላብሮ አዲስ አበባ እጅግ ሰላማዊዋ የአፍሪካ ከተማ ናት ብለዋል።

ዳይሬክተሯ ይህንን የተናገሩት በአፍሪካ ሌዘር ፣ ጨርቃ ጨርቅ ፣ ፋሽን እና የዘርፉ ቴክኖሎጂዎች ኤግዚቢሽን መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

አውሪሊያ ካላብሮ ፥ " አዲስ አበባ ከተማ ከሚወራው እጅግ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ በአፍሪካ እጅግ ሰላማዊ ከሆኑ ከተሞች አንዷ ናት " ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም ዓለም አቀፍ የቆዳና የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪና የዘርፉ ነጋዴዎች እዚህ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ መገኘታቸውን ገልፀዋል።

ኤግዚቢሽኑ ባለፉት 3 ዓመታት የኮቪድ 19 ካደረሰው ጫና በኋላ አዲስ የንግድ ስልቶችን በመማር የተዘጋጀ ነውም ብለዋል።

ምንጭ፦ አሻም ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
#Update

ባለፉት 2 ተከታታይ ቀናት በተደረገው ኦፐሬሽን በሸዋ ግንባር የቀወት ወረዳ፣ ለምለም አምባ፣ ጀውሐ፣ ሰንበቴ፣ አጣየ እና ካራ ቆሬ ከተሞችና አካባቢዎች ከህወሓት እጅ ነፃ መውጣታቸውን በጋሸና ግንባር ደግሞ ኮን እና ዳውንት ሙሉ በሙሉ ከአሸባሪው መፅዳታቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ አስታወቀ።

ዕዙ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በወረኢሉ ግንባር ልጓማ ከተማ ነጻ መውጣቷን የገለፀ ሲሆን " በተወረሩት አካባቢዎች የጸጥታ ኃይሎች የጋራ ጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ሕወሐት ጀሌዎች እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ " ብሏል።

ዕዙ " አሸባሪው ሕወሐት እየተሸነፈ በመሆኑ በግንባር ያጣውን ድል በሐሰት መረጃ ለመሸፈን እየጣረ ነው " ያለ ሲሆን " አሸባሪው ሕወሐት የኢትዮጵያ ልጆችን ብርቱ ክንድ መቋቋም አቅቶት ሲፍረከረክ፣ የአሸባሪው አመራሮች መሸነፋቸውን ላለማመንና ወጣቶችን ውጤት በሌለው ጦርነት አሁንም ለመማገድ በማሰብ፣ ስልታዊ ማፈግፈግ አድርገናል በማለት ራሱንና ተስፈኛ ጋላቢዎቹን በማጽናናት ላይ ይገኛል " ሲል ገልጿል።

አክሎም፥ " አሸባሪው ሕወሓት ከዚህ በኋላ ለወረራ የገቡ ጀሌዎቹን የሚያድንበት ዐቅም የለውም፡፡ ወደተወረሩ አካባቢዎች የገባው የአሸባሪው ሕወሐት ጀሌ ሁሉም የመውጫ በሮች ተዘግተውበታል። " ሲል አሳውቋል።

" ወራሪው ኃይል በከንቱ ያሰለፋችሁ ወጣቶች ከዚህ በኋላ ማምለጫ እንደሌላችሁ ተገንዝባችሁ፣ እጃችሁን ለጸጥታ አካላት በመስጠት፣ ራሳችሁን እንድታድኑ መንግሥት ያሳስባል " ብሏል ዕዙ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ያልወጡ አካባቢዎችን በተሟላ መልኩ ነጻ ለማውጣት በተጋድሎ ላይ እንደገሚገኙም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#GONDAR

ዛሬ ከሁመራ አድርጎ ወደ ጎንደር ከተማ በመግባት ላይ ያለ ተሳቢ መኪና ተገልብጦ ሹፌሩን ጨምሮ የ5 ሰዎች ህይወት ጠፋ።

አደጋው በጎንደር ከተማ በፋሲል ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኩረበረብ ተብሎ እሚጠራው አካባቢ ቀን 8:30 ገደማ የደረሰ ሲሆን 2 ወንድ እና 3 ሴቶች ህይወታቸው ሲያልፍ 3 ሰዎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።

የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የማህበሰረብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ም/ ኢንስፔክተር ስማቸው ፈንቴ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia