TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Turkey : ቱርክ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 አገራት አምባሳደሮች አገሯን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የቱርክ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ባስተላለፉት ውሳኔ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች አንካራን ለቀው እንዲወጡ ተወስኗል።

አምባሳደሮቹ እንዲባረሩ የተወሰነው በፈረንጆቹ 2016 ዓመት ከተካሄደው እና ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጀርባ እጁ አለበት በሚል ተጠርጥሮ ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ ያለ አንድ ግለሰብ ከእስር እንዲፈታ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው።

ኦስማን ካቫላ የተሰኘው ይህ የመፈንቅለ መንግስት ተጠርጣሪ በፈረንጆቹ 2013 ዓመት በቱርክ ረብሻ እንዲከሰት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል እና በ2016ቱ የከሸፈው መፈንቅለ መንግስት እጁ አለበት በሚል በእስር ላይ ይገኛል።

ግለሰቡ ባሳለፍነው ሳምንት የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበረው ሲሆን በአንካራ የሚገኙ የአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ሆላንድ፣ እና ኒውዝላንድ አምባሳደሮች የፕሬዘዳንት ረሲፕ ኤርዶሀን መንግስት ተከሳሹን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ በጋራ ጠይቀዋል።

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አምባሳደሮቹን ጠርቶ ስለጉዳዩ እንዲያብራሩ የጠየቀ ሲሆን ድርጊቱ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው እና በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት መሆኑን ጠቅሶ ውድቅ አድርጎታል።

ፕሬዘዳንት ኤርዶሃን በአምባሳደሮቹ ድርጊት መበሳጨታቸውን ገልጸው በአስቸኳይ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ተናግረዋል።

የአሜሪካ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ በጉዳዩ እስካሁን ያሉት ነገር እንደሌለ ሮይተርስ በዘገባው አክሏል።

ምንጭ፦ አል ዓይን / ሮይተርስ
Photo Credit : AFP

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 14 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,762 የላብራቶሪ ምርመራ 441 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 528 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የ2 ዳኞችን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በወንጀል መጠርጠራቸውን በመጥቀስ ምርመራ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ መጠየቁን ተከትሎ ውሳኔውን ያሳለፈው።

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥቅምት 12 / 2014 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በቀረበው ጥያቄ ላይ በሰፊው ተወያይቶ በአዋጅ ቁጥር 1233/13 አንቀጽ 34(2) መሰረት የሁለቱንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ መወሰኑን ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Bahridar : በባህር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የአባይ ድልድይ የግንባታ ብረት የሰረቁት ግለሰቦች በቁጥጥር ዋሉ።

ከ50 ዓመት በላይ አግልግሎት የሰጠው የባህርዳር ከተማ አባይ ድልድይ በእድሜ ብዛት ወቅቱን የሚመጥን የትራፊክ ፍሰትን ማስተናገድ ተቸግሯል።

ይህንን ለመቅረፍ በከፍተኛ በጀት አዲሱ ድልድይ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ነው።

የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ፥ "ይህንን የህዝብ ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል የፈለጉ ስግብግብ ግለሰቦች የተለያዩ የስርቆት ወንጀል መፈፀማቸውን ተረጋግጧል" ብሏል።

በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩት የሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ባልደረቦች በ12/02/2014 ዓ/ም ምሽት የድልድዩን የግንባታ ብረት ሰርቀው ሊያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርምራ እያጣራ ይገኛል ሲልም አክሏል።

አጠቃላይ በስርቆቱ የተሳተፉ እና በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ግን በፖሊስ መረጃ ላይ አልተገለፀም።

የባህር ዳር ፖሊስ ፥ " ክልሉ የህልውና ትግል ላይ ባለበት በዚህ ወቅት የሀገርንና የህዝብን ሃብት በመዝረፍ ለግል ጥቅም ለማዋል የሚጥሩትን የውስጥ ባንዳዎች ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል" ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#GONDAR : በጎንደር ከተማ ህግ ተላልፈዋል የተባሉ 53 የፀጥታ አካላት እንዲጠየቁ መደረጉን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ገለፀ።

መምሪያው ይህ ያሳወቀው በመምሪያው ኃላፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁ አማካኝነት ለከተማው ነዋሪዎች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመወያያ ፅሁፍ ባቀረበበት ወቅት ነው።

በከተማዋ የእገታ ወንደል ህገ ወጥ የጥይት ተኩስ ተጀራጅቶ ዘረፉ ዋና ወና የከተማዋ ወንጀሎች መሆናቸውን አቶ ፋሲል ገልፀዋል።

በዚህ የእገታ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ 34 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል።

4 በእገታ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑም ጠቅሰዋል።

በከተማዋ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉት 14 በየደረጃው በሚገኙ የፀጥታ አመራሮች 20 የፓሊስ አባላትና 14 የሚኒሻ አባላት ተጠያቂ መሆናቸውም አሳውቀዋል።

የመስቀል በዓልን ምክኒያት በማድረግ ጥይት ተኩሰዋል የተባሉ 115 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

የከተማዋን ፀጥታ በመጠበቅ ረገድም ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዎ የሚበረታታ ነው የተባለ ሲሆን የጀመረውን የሰላም የፀጥታ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠልና በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተብሏል።

መረጃው የጎንደር ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Dessie : በዛሬው ዕለት የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ወቅታዊ ሁኔታን ተንተርሶ ለከተማው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው ባስተላለፉት መልዕክት " የጸጉረ ልውጦችን እንቅስቃሴ ለመግታት ያመች ዘንድ #ከዛሬ ጀምሮ የሞተር እና የባጃጅ እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ እንዲቆም በጸጥታ ምክር ቤት ውስኗል ሲሉ አሳውቀዋል።

በከተማው የተዘጉ የተለያዩ የንግድ ቤቶች በተለይ መድሀኒት ቤቶች በአስቸኳይ ተከፍተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ያሳሰቡ ሲሆን ይህን በማያደርጉት ላይ አስፈላጊውን የህግ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

አቶ አበበ ፥ የከተማው ነዋሪ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ጸጉረ ልውጦችን ለጸጥታ ሀይሉ የማስረከብ ስራ ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ከንቲባው ፥ "ለሰራዊታችን የሚደረገው የምግብና የውሀ አቅርቦት በአደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል" ያሉ ሲሆን " ወጣቱ ፣ አመራሩ፣ የመንግስት ሰራተኛው፣ እና አጠቃላይ ህዝባችን የጀመረውን የግንባር ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥል" ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኬላ እና የውስጥ ከተማውን ጥበቃ በማጠናከር የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ ሁሉም ማህበረሰብ እርብርብ እንዲያደርግ ፤ የከተማዋ ማህበረሰብም በመደራጀት ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን የከተማውን ቁልፋ እና መለስተኛ በሮች በመዝጋት የጥላት ሰርጎ ገበች እንዳይገቡ መከላከል እንደሚገባም በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

አቶ አበበ ፥ " ነዋሪው ከተለመደው የጥላት የሀሰት ወሬ እና ፕሮፖጋንዳ እራሳችንን በማራቅ ከተማችን ላይ ተረጋግተን መቀመጥ አለብን" ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Dessie : በዛሬው ዕለት የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ወቅታዊ ሁኔታን ተንተርሶ ለከተማው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከንቲባው ባስተላለፉት መልዕክት " የጸጉረ ልውጦችን እንቅስቃሴ ለመግታት ያመች ዘንድ #ከዛሬ ጀምሮ የሞተር እና የባጃጅ እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ እንዲቆም በጸጥታ ምክር ቤት ውስኗል ሲሉ አሳውቀዋል። በከተማው የተዘጉ የተለያዩ የንግድ ቤቶች በተለይ…
#DessieCity

የደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ከዛሬ ጀምሮ የሞተር እና የባጃጅ እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ እንዲቆም ውስኗል።

በከተማው የተዘጉ የተለያዩ የንግድ ቤቶች በተለይም ደግሞ የመድሀኒት ቤቶች በአስቸኳይ ተከፍተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ይህንን በማያደርጉት ላይ አስፈላጊውን የህግ እርምጃ እንደሚወሰድ የደሴ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey : ቱርክ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 አገራት አምባሳደሮች አገሯን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የቱርክ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ባስተላለፉት ውሳኔ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች አንካራን ለቀው እንዲወጡ ተወስኗል። አምባሳደሮቹ እንዲባረሩ የተወሰነው በፈረንጆቹ 2016 ዓመት ከተካሄደው እና ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጀርባ እጁ…
#RecepTayyipErdoğan

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ የሰጡባቸው የ10 ሀገራት አምባሳደሮች ፦

🇩🇪 ጀርመን
🇺🇸 አሜሪካ
🇸🇪 ስውዲን
🇳🇴 ኖርዌይ
🇳🇱 ኔዘርላንድስ
🇩🇰 ዴንማርክ
🇳🇿 ኒው ዚላንድ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇨🇦 ካናዳ
🇫🇮 ፊላንድ ናቸው።

ትላንት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ኤስኪሴሃይር በተባለ ስፍራ ለተሰበሰቡ ሰዎች ባደረጉት ንግግር ላይ እንዲህ አሉ ፦

" አምባሳደሮቹ ወደ ቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሄድ ትዕዛዝ ለመስጠት ሊደፍሩ አይገባም። ምን መደረግ እንዳለበት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴራችን አስፈላጊውን ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ።

እነዚህ 10 አምባሳደሮች በአንድ ላይ በአገሪቱ ውስጥ ተቀባይነት የሌላቸው /ፐርሶና ነን ግራታ/ ሊባሉ ይገባል።

በአስቸኳይም መፍትሄ ይደረግለታል"

@tikvahethiopia
#HappeningNow : በቤንች ሸኮ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ የሠላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ ከፍተኛ የክልል፣ የዞን አመራሮች ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች ተገኝተዋል።

በጉራፈርዳ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ከዚህ ቀደም በነበረው የፀጥታ ችግር በርካታ ነዋሪዎች መገደላቸው ፤ እና መፈናቀላቸው አይዘነጋም።

ፎቶ : ከቤንች ሸኮ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#ENDF : የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ በምእራብ ግንባር የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተገለፀ።

ከኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ ዛሬ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በአየር ተመቷል ሲል አሳውቋል።

ፎቶ : ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ENDF : የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ በምእራብ ግንባር የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተገለፀ። ከኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ ዛሬ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በአየር ተመቷል ሲል አሳውቋል። ፎቶ : ፋይል @tikvahethiopia
#ተጨማሪ

የመንግስት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓም፣ ዐድዋ አካባቢ የሚገኝ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ሲል አሳውቋል።

ከዚሁ ከአየር ጥቃት ጋር በተያያዘ በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የትግራይ ነፃ አውጪ ቃል አቃባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የጥቃቱን መፈፀሙን ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

"የመጀመረው ጥቃት በአንድ የገጠር ሆስፒታል አቅራቢያ ተፈጽሟል" ነው ያሉት።

በዐድዋ በተፈጸመው ጥቃት "ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች ውድመት ደርሶበት የነበረው እና ጥቂት ተርፎ የነበረው የአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ መመታቱን" ለሮይተርስ ተናግረዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች የሚገኙባቸው የማይ አኒ እና አዲ ሃሩሽ የመጠለያ ጣብያዎች በማይጠምሪ አቅራቢያ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሚንስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመጠለያ ጣብያዎቹ ለአየር ጥቃቱ ተጋላጭ እንዳልነበሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ እየፈፀመ የሚገኘው የአየር ጥቃት ከንፁሃን በራቀ ሁኔታ በሽብረተኛ ድርጅትነት የተፈረጀውን TPLF ኢላማ ያደረገ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል።

ፎቶ : ፋይል

@tikvahethiopia
የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኗ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ሱዳን ይጓዛሉ።

ኮሚሽነር ጁታ በሶስቱ ሀገራት ቆይታ የሚያደርጉት ከጥምቅት 14 እስከ ጥቅምት 17 ድረስ ነው።

ጉዟቸው የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ #ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም ከአፍሪካ ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ለመግለፅ እና ለማጠናከር ነው ተብሏል።

ነገ ሰኞ ኮሚሽነር ኡርፒላይነን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔት ዌበር ጋር አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ማክሰኞ ከኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ጋር ይገናኛሉ እንደ አውሮፓ ህብረት መረጃ።

በአዲስ አበባ ያላቸው ቆይታ ካጠናቀቁ በኃላ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች ስብሰባን ለመካፍል ኪጋሊ የሚገቡ ሲሆን በመጨረሻም ረቡዕ ዕለት በሱዳን ካርቱም የሽግግሩን አመራሮች የሚያገኙ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት እና ሱዳን የፖለቲካ ውይይትንም እንደሚያስጀምሩ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,377 የላብራቶሪ ምርመራ 247 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 523 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia